Telegram Web Link
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!


@gGetem
@gGetem
@gGetem
የመኖሬን ቅንጣት
በጥርሶችሽ ንጣት
ቀናውን እድሌን
በአይኖችሽ ብሌን
የነገዬን ድምቀት
በውበትሽ ስምረት
አየሁኝ ተስሎ
ነገ አንቺን መስሎ።
                

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ላይድን ቁስል፤
ጨዉ መነስነስ፤
ከድንጋይ ላይ፤
ዉሃ ማፍሰስ ፤
ለሟች ዘመድ ፤
ዳግም ማልቀስ፤
መኖር ካሉት፤
እንደዚህ ነው፤
ሳቅን ትቶ፤
መንሰቅሰቅ ነው


@gGetem
@gGetem
መባቻ ነው ይህ ኑሯችን የኖህ ሆኗል ዝማሚያችን
ግማድ ሆኗል ይህ ፍቅራችን
በዚች  አለም የታሰረ ቅን ልባችን
ስማችን ነው እጣን ከርቤ ሙዳያችን
ከመረጥሽው አንቺ ካልሽው ካህን
ወጣንም ወረድን በደብተራ ምርኩዝ የተነከረብን
እኔ አንቺ ወይ ድውያችን
ታስሮ ኖሯል በደብተራ በመባቻ ፅኑ ኪዳናችን
እኔ እና  አንቺ ወይ ድውያችን መሞቻ ቀናችን
በዘመን በታሪክ ስማችን ተመርጦ መደገሚያ ሆነ ለደብተራ ሸቶን
  
  By አለምሰገድ ወልዴ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ነጋሪት በጆሮ

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @Joyefull
( የወጉት )
=============

ያኔ ....
አይሁድ በጭካኔ
ክንድህን ወጥረው
ለፍቅርህ ብድራት ለውለታህ ዋጋ
አምስት ችንካር ቆጥረው
ያለ ርህራሄ
በመስቀሉ አግድም
እጅህን ሲዘረጉት
አላወቁት እንጂ ...
ባንተ መዳፍ በኩል
እልፍ ልቦችን ነው በምስማር የወጉት !!


@gGetem
@gGetem
@gGetem
ሰላም ውድ የሆናችሁ የሆሄያት ህብር ቤተሰቦች እንደምን ከረማቹ ????
በህይወት ስንክሳር የተነሳ ለረጅም ወራት ከሚዲያው የራቅንም ቢሆን እናንተ ግን በትዕግስት እና በተስፋ ስለጠባቃችሁን ምስጋናችን ከልብ ነው።
እናም ከዚህ በኃላ ባለን ጊዜ ከቀደመው ጊዜ በተሻለ ወደእናንተ ለመድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል።
እስካሁን ስላረጋችሁት ቤተሰባዊ ተሳትፎ ስጦታ አዘጋጅተናል በቀጣይ....
ዮሲ ማን & ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
አልገባኝም
(ሊዮ ማ.)
አውቃለሁ ለመኖር ሰው ሲኖር ይለፋል
ቀናት ሳይገድበው ከቀን ይታገላል።
የእድሜው ምህዋር የእርሱነቱ ጀምበር
እንዳይቀና ሆኖ ድንገት ሲደናገር
ጭብጡ ምን ይሆናል ከመልፋት ባሻገር?
የእንባ ፅንስን ሊወልድ ስቃይ የሚያማምጥ
ከቀኑ ሚሟገት ተስፋው እስኪሟጠጥ
ይህን መሳይ ምስኪን...
ይህን መሳይ ምንዱብ
በምን ታምር ይሆን የሚድን ከዚህ ሰርጥ?
አልገባኝም !!!
@gGetem
@leoyri
መኖር
በፍላጭ ሰከንዶች፤
በሽራፊ ሰዓት፤
በደቂቃ ቅንጣት፤
እለት እየገፉ፤
ወራት እያለፉ፤
እየጣሉ አመታት፤
በዘመን ምትሀት፤
በአንዲት የጊዜ ጋት፤
መኖር መሳብ አይደል፤
ወደሞት መጠጋት ?
          

@gGetem
@gGetem
ቅጽርህ የእናት እቅፍ
ሸክምን የሚያራግፍ
አልተነፍስ ጸሎት አይወጣ ቃል ከአፌ
ይተናል ጭንቀቴ ስመለስ አርፌ

እመጣለሁ ደጅህ ሀሳብ አንጠልጥዬ
እገባለሁ ቅጽርህ አንገቴን ደፍቼ
መች ታዝንብኛለህ
መች ትወቅሰኛለህ በሽቅጬ ከርፍቼ

አይነድህ ድፍረቴ
አይቆጨኝ ስንፈቴ
አይበሽቅህ ስህተቴ
አይገደኝ ዝለቴ
በኦና ተግባሬ
ውድቀት አንከርፍፌ ስቆም ከነእድፌ
ምን አድርጌልህ ነው?
አክመህ ምትልከኝ በምህረት መርፌ

ከመቀመጥ በቀር
ኢምንት ታህል ድርጊት ፈጽሜ የማላውቅ
አንዲት ዘለላ እንባ
በጉንጬ ሳልሰድ እንዴት ደመቅኩ በሳቅ?
እንዴት ቻልኩ መፍገግ?
እንዴት ቻልኩ ማማር?
እሬት ህይወት ይዤ
አጣፍጥልኝ ሳልል ሳልጠይቅ የሀሴት ማር

ትዕቢት አይሉት ጥጋብ
ፍርሃት አይሉት ስጋት
ስም ያላገኘሁለት
አንዳች አሳሪ ኃይል ወርሮኝ እንደ ውጋት
አላልኩኝ እግዚኦታ አልቆምኩኝ ሰዓታት
ፈውስ አሰኝቶኝ አላደረስኩ ኪዳን
ስለረገጥኩ ብቻ
ስላረፍኩ በቤትህ ይገባኝ ነበር መዳን?
እንጃ!

ብቻ እመጣለሁ ሀሳብ አንጠልጥዬ
ደጅህ እገኛለሁ ማረኝ ቃልን ጥዬ
አርፋለሁ ካንዱ ጥግ አንገቴን ደፍቼ
መች ትቆጣኛለህ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ከነእድፌ ተኝቼ

ቆይቼ
ቆይቼ
.
.
.
ቆይቼ ስነሳ
ተጋድሞ አየዋለሁ ሸክሜ እንደ ሬሳ

አልጸለየም ሳትል
አልለመነም ሳትል
አላነባም ሳትል
ይገርመኛል እኮ
ጊዮርጊስ አባቴ ጭንቀቴን ስትጥል

ይገርመኛል ቅጽርህ...
ልክ እንደ እናት እቅፍ
ደስታን 'ሚያሳቅፍ!
አባብሎ 'ሚያሳርፍ!
ሸክምን 'ሚያራግፍ!
.
.
.
እርፍ!

#ኤልዳን

@gGetem
@gGetem
@gGetem
▨▨▨▨▨▨▨▨▨▨▨



#እንስተ_ፀሎት
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ ©
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tg-me.com/leoyri
www.tg-me.com/gGetem
Mole Enter_🍁
Plc share&Join
🎤🎬 #ሳሮን_ተክለ_ወልድ©
ተፃፈ፦04-09-2015ዓ.ም
የሳምንቱ_ ለ
▦▦▦▦▦▦▦▦▦▦▥▦▦▦
በትዕግስት ለጠበቃችሁን ከልብ እናመሰግናለን ።❤️🙏
ባያቸውስ ኖሮ ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)

እርግት ያለች ወተት
ስክን ያለች ቡና …
ይሄን ችኩል ዘመን
አልዋጀችምና …
ተንገበገብኩላት
ተሳተብኝ አቅሌ
ሆንኩላት ባተሌ ።

ጥልል እንደ ጠላ
ኩልል እንደ ጠበል
ከአንገቷ ስር ገነት
ገድ ጥሎኝ ብጠለል
አ..ን..ሰ…ፈ…ሰ…ፈ…ች….ኝ
አ…ር..ገ…ፈ...ገ…ፈ…ች…ኝ
ቃላት ሳ’ተነፍስ
ጥርሶቿን ሳትገልጥ
ቅቤ ሆነ ልቤ..
ገጽዋ ላይ ሲቀልጥ ፤

ያን ጊዜ ተቃናች !
ብታጣብኝ ኩራት
ስስ ጎኔ ቢገርማት
(ዓይኖቿ ፍም እሳት)
አንገቴን ሰበርኩኝ
ፈርቼው ይሄን ፍም
ቢሆንም …
ቢሆንም …
ለዓይኖቿ አፀፋ
መስጠት ሳልፈልግም
ለንቋሳው
……………………….. ተንጋለልሁ
ለዚ’ች ሞቃት ግርግም
:
ደረቷ ላይ ፍግም !

@gGetem
@gGetem
ከባይተዋር ሌሊቶች መጽሐፍ ላይ የተወሰደ...
#ርዕስ#ሁለት_አንድ_ምስል
#አንባቢ_ሊዮ_ማክ
Editor-ገላዬ🙊
@leoyri
@gGetem
@gGetem
ሙቅ ነገር
(ሊዮ ማክ)
አካል ገላ ገላ ገላ
እኔ እና አንቺ ሆነን
ተንጋለን ካንድ አልጋ
በዕምነት ያወጋሺኝ
ሌሊቱ እስኪነጋ
እኔን ይታየኛል
ደግሞም ትዝ ይለኛል፤
ይህኔ ግዜ አንቺ ዘረስቶሽ ይሆናል!!
አካል ገላ ገላ ገላ
በዕለተ በዓሉ
የተጋፍነው ጠላ
ካናታችን ዘልቆ
አዋዝቶን በመላ
ድንገት ቢያዋውለን
ከመዋደድ ጥላ
ያለ አንዳች ከልካይ
ያለ ጊዜ ብትር
ስንቃመስ አደርን
የሚጣፍጥ ነገር።
(ሞቅታ)
#ብድር_አለ_?
@leoyri
www.tg-me.com/gGetem
💌🤔🧎‍♀
.....ያልታደልን...
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tg-me.com/leoyri
www.tg-me.com/leoyri
www.tg-me.com/gGetem
www.tg-me.com/gGetem
👁💚💛❤️
💯 quality 👉👌
Plc share&Join
🎤🎬 #Hermonã_Håbetom (HH)
Audio
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
ምርጥ ግጥም
🎙🎙🎙ናትናኤል
ለሃሳብ እና አስተያየት
Rip የኔ ጀግና ወንድም ስራህ በልቤ ከፍ ብሎ ይደመጣል።🎙🎙🎙ናትናኤል
@gGetem
@gGetem
ካሱ ጠገራው
📙 የ መጽሐፍ ትረካ 🎙
ካሱ ጠገራው
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➮ ከ ሸገር ሼልፍ  ከ ተስፋዬ ማሞ

➮ ተራኪ ግሩም ተበጀ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @gGetem
            ⇨ @gGetem
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ  ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ  በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።

መናፈቅ ማለት …

(ሚካኤል አ )
#አደለ


@gGetem
@gGetem
@gGetem
2025/07/07 12:35:59
Back to Top
HTML Embed Code: