Telegram Web Link
ዘመንም እንደሰው...
.
.
.
.
የጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል
መጤ ከደጅ ቆሞ ቤተ'ኛ ነኝ ይላል.
.
.
ልቀቁ እያለ...
.
.
ፍርድ የለሽ ንግስና ሲሰፋ ባ'ገሩ
የሰውነት ልኬት ሲገፋ ድንበሩ
ለሚነጋ ለሊት...
በግብር አንሰው ወርደው ካ'ውሬ ዘንድ አደሩ።

እረፍ ባይ ሲታጣ በተስፋ መጠውለግ
የኡኡታ ሲቃ እንዲውጥ ሲደረግ
ያኔ ነው መሰደድ ቢሻ መፈናቀል
ጎራ እየመረጠ...
ዘመንም እንደ ሰው ጠብቆ ሲበቀል።
#እግዚኦ 😥

ሊዮሪ©
14/09/2014ዓ.ም
@www.tg-me.com/gGetem
@www.tg-me.com/gGetem
👧እንደ ፀሐይ🌞
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
ሙዚክ፦ማህደር እንዳለ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

👉 #የመድረክ ስራ
#LIVE ...
@gGetem
@gGetem
@sirak6

👉በመድረክ ላይ እንደቀረበ_
የለሙላ ትግል
(ሊዮ ማ.)
ሲፈስ ሳለ የደም ወዝ
ካለመውደቅ የመሸሽ ጥርዝ
ቢታገሉ ለመንፋቀቅ
ሲታገሉ ለመጠንቀቅ
መልስ አልባ ነው
የሚደበቅ።
ነገን በመፍራት ጦስ
ህሊና ሲቃወስ
መቅናት ባለመቅናት
መሆን ባለመሆን
ተስፋ መቁረጥ ሲነግስ
እንደዚህ ሲሆን ነው
እንባ የሚታፈስ።
www.tg-me.com/gGetem
comments. .. @leoyri
ብዙ ሳይጣጣር
        እምብዛም ሳይለፋ
  ከዓይን የራቀ
                ከምናብ የሰፋ
                ይህን ዓለም ሠራ
                        ያለ ጭንቀት ጥበት
                ሆነለት “ሁን” ሲለው
                                እንዲሁ በዘበት
                      …
ሕዋውን በሙሉ
               ግዑዙን ተፈጥሮ
         በቃሉ ትዕዛዝ
                 እንዲህ አሳምሮ
                     ለድንጋዩ ራርቶ
                    የንብ መንጋ መርቶ
                     አበባን አፍክቶ
                           ወፊቱን አብልቶ
                  …
እኔ ትንሽ ነገር
          ከሕይወት ቢጨንቀኝ
            አደራህን ብለው
               “እሺ ቆይ” እያለ
             ይህን ሁሉ ዓመት
                            የሚያጠባብቀኝ
         እንዴት ብከብደው ነው
                  ወይ እንዴት ቢንቀኝ ?
              ….

@gGetem
@gGetem
አይተሻል አንዳንዴ!
(አስቱ)
ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
ሞኝ የሚመስለውም ከብልህ ይልቃል

የወደቀ ዛፍነው ምሳር የሚያበዛው
እቃ ብቻ አደለም ገንዘብ የሚገዛው
አይተሻል አንዳንዴ

ሴጣን ስላለ ነው እግዜር የሚነግሰው
ህመም ሲጠፋ ነው መዳኒት ሚረክሰው
ያው አምላኩ ብሎት
የሙሴ በትር ነው በሀር የገመሰ
በዳዊት ፌት አደል ጎልያድ ያነሰ!

ቢሆንም በትሩ
ባህር ምን ቢገምስም አይበልጥም ከ ሙሴ
ጎልያዶች ሁሉ በምነታችን እንጂ
በድንጋይ አይወድቁም ትልሻለች ነፍሴ።

(አይተሻል አንዳንዴ)

እውር ያለ በትሩ ወዴትም አይሄድም
የሙዋች ስጋ ሁሉ መቃብር አይወርድም
,
የገደለም ሁሉ ወንጀለኛ አደለሞ
ነፍስን ስለማዳን ነፍስ ይጠፋ የለም!?
ይህውልሽ አንዳንዴ

ያፈቀረ ሁሉ ፍቅሩን አያገኝም
ሽበት ያለው ሁሉ ሽምግልና አይዳኝም
,
የሚሮጠው ሁሉ አይሆንም አንደኛ
አይተሻል አንዳንዴ እንደዚህ ነን እኛ።

@gGetem
@gGetem
@leoyri
ረስቼሻለው!!!
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#ለጁማችን_
የሳምንቱ ገፅ🕤
Audio
ሰላም ውድ የሆሄያት ህብር ቤተሰቦች
ከዚህ ቀደም በከሚላ1.2፣በንጋት ላይ ጤዛ እና በሌሎች ስራዎቹ
የምናውቀው
ሊዮ_ማክ አሁን ደግሞ #የራስ_ጥላ የሚልአዲስ ስራ ስለ እናት የሚያትት ከእንባ ጋር የተሰራ ድንቅ ስራ #በቅርብ_ቀን ይጠብቁን።
#Coming_Soon
@gGetem
@leoyri
ለውብ ቀን!
💚


ልብ ታሞቃለች ይቺ ዘፈን አጣጥሟትማ!❤️


ያሰብከው ባይሞላም
ያልከው ባይሳካም
ያለምከው ቢጠፋም


ወዳጅ ፊቱን ቢያዞር
በውሎህ ባትረካ
አትዘን እንግዲህ
ከቶ አትቁረጥ ተስፋ


ጊዜ ሰው ሲፈትን እምነትም ሲከዳ
እውነትም በተራ እውነትነትን ሲያጣ
ህሊና ካልከዳ ወዝህን ብታጣ


ከማገገም በቀር ድካም አይበጅህም
የለቱን የጠሉትስ በዝምታ አይመጣም
ያዘመን ኩርንችት በለስ አያወጣም

ድርሻህን ተወጣ ተስፋን ላበደረ
ንፉግ አይባልም ያለውን የቸረ


እረ እንዲያው ዝምታ ምን ሊሆን
ልብ እየተረታ ሆድ እያመነታ
አንደበትህ ታስሮ በግዜ አትረታ
ጉም ጉሙን ትተህ ተናገር ላንዳፍታ


ልብም እንደ ባዳ ከክዳት ተማክሮ
እውነት በሆድ ይዞ እውነት ተቸግሮ
የነገርን ሳያይ ጎዳ በተስፋ ውሎ አድሮ
ድካም ይጫነዋል እድሜ ብዙ ቆጥሮ
አዬ ጉድ አዬ ጉድ ይላል ያገሬ ሰው
ትዝብቱ ታምቆ ሆዱን ሲያላውሰው
ቀኑም ቢጨላልም ሌሊቱጅም ቢነጋ
ላያልፍ አያለፋም . . . አትጠጋ


ያሰብከው ባይሞላም
ያልከው ባይሳካም
ያለምከው ቢጠፋም
ወዳጅ ፊቱን ቢያዞር
በውሎህ ባትረካ
አትዘን እንግዲህ
ከቶ አትቁረጥ ተስፋ


ጌታም አይጣላህ ሳይደግስ ሳይዘክር
እውነት ከቤት ይዘህ በብድር አትመስክር


ሆድ ከሃገር አይበልጥም ግን ከሃገር ይሰፋል
የወለዱት እንጂ ቃል እንዴት ይጠፋል


ቅጥፈትን ጸጋ አድርጎ ለምኖ ያደረ
አትሁን እንግዲህ ነገ ነው ያማረ


ጎዳናህ ሐቅ ይሁን ውልህን አትርሳ
ዳግም አይጎዳም ወድቆ የተነሳ


ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው


ምንድነው ዝምታዬ


ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው


ምን ይሆን ሚስጥሩ
የዛሬው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ


ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ሃሳብ ያደረው


ምንድነው ቅሬታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ


ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ምን ይሆን ሚስጥሩ
የዛሬው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው


ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ገላዬን ሳይከዳው
ሃሳብ ያደረው


ምንድነው ቅሬታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው
ምንድነው ዝምታዬ
ኧረ እንዲያው ኧረ እንዲያው

ያማረ ቀን!💚

@gGetem
@gGetem
@Leoyri
🇪🇹እሮብ ሚያዝያ ፳፰ ፳፻፲፪ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ሰው_ብቻ
───────
አሁንማ ጀንበር ገባች
አይናችን ስር ተስፋ ሞተ
የመጀገን ቀን አበቃ
የስንፋናህ ዘመን ባተ
አልልህም ምን ብደክም
ርቃን እውነት አስገርፎኝ
በበደልህ ብታሸንፍ
ሀቄ በቁም ህይወት ገፎኝ
መኖርና መሞት መሀል
ያለን ጣዕም አስክረሳ
ባሳልፍም ብዙ ዘመን
እርጥብ ቁስል እልፍ አበሳ

ሙት አለሜ ደስ ብሎኛል!
ዋንዛ ልብህ እንደሙጃ
ሲልፈሰፈስ ተሸንፎ
ጥቅጥቅ ነፍስ ሲገላለጥ
ወና ሲሆን እንደቀፎ
ኧረ አሜን ነው
አሜን አሜን
ደግሞ አሜን አሜን ብዙ
"ይቅርታ" ሲል ይገለጣል
ትሁት ሲሆን የሰው ወዙ
ኧረ አሜን ነው የምን እንቢ
ቀን ጣለልኝ ብሎ ጉራ
ሰው መሆኑ ከስጋ ያልፋል
ለወደቀ ሰው ሲራራ

ልመናዬ እዬ ዬ ዬ
አልነበረም ከንፈሮቼ
ከንፈርህን እንዲስሙ
አልነበረም ወይም ጥዬህ
ድል ማድረጌን እንዲሰሙ
ባንተ አዝኜ እንዳይጠፋኝ
ነበር ያልኩት የሰው መልኩ
ተመስገን ዛሬ አሳየህ
አላነሰም አልወረደም
ከሰውነት የሰው ልኩ ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨ #ዛሬን_ያነበበ ፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨ #ነገን_ይማራል❗️፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተማፅኖ
ሴትና ወንድ ልጅ ከመቅደሱ ገብተዉ
ወደፈጣሪያቸዉ ሲፀልዩ ተግተዉ
በፊቱ የለመኑት የተማፅኗቸው ቃል
መላዕክት ሲያደርሱት እንደዚህ ተፅፏል።
ወንድ
የሥጋዬ እመቤት ገዢ ያደረኳትን
በፍቅሯ ተይዤ የማቀቅሁላትን
ደርሶ ልመናዬ አምላኬ በፊትህ
የኔ አድርጋትና ነፍሴ ታመስግንህ።
ሴት
አምላኬ እንደሰዉ እንዳልሆንክ አዉቃለሁ
ከመቅደስህ ቆሜ እለምንሃለሁ
ከእጅህ ጥበብ ሥራ ባይኖርም የረታኝ
የማገባዉን ሰዉ እንዳፈቅረዉ እርዳኝ።
🤔🙉
ለሀሳብ አስተያየት @Leoyri
@gGetem
የሆሄያት ህብር📝📝
Photo
Now 👇👇👇👇
ተለቀቀ
ተለቀቀ
ተለቀቀ
ዛሬ ምሽት በሆሄያት ህብር ተለቀቀ
ተጋበዙ።🙉😘😘😘
Audio
🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱
’ይህ ስራ ስላንቺ ከመከተቡ አስቀድሞ
በእንባ ጉልበት የስቃይሽን ቅንጣት ያማጥኩባቸው
እኛ ሌቶች ክፍያ ይሁኑሽ’’

‘’የራስ ጥላ’’
ከታቢ እና ምስክረ_ልሳን፦ #ሊዮ_ማክ
ውህደ ሙዚክ፦ቃልኪዳን ማህተም🎧
ፖስተር ዲዛይን፦ማርሲላስ ሐይሉ🩻🪪
ኤዲተር&ፕሮሞሽን፦ሄለን ዋለልኝ🎨🎭
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
``መታሰቢያነቱ ባለመኖር ጭላንጭል ውስጥ እድሜዋን ለገበረችው እናቴ የሪ ይሁን``🤱
‘’ከራስ ጥላ መጽሃፍ ላይ የተወሰደ’’
#The_New_Album
🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱🤱
@gGetem
@gGetem
@leoyri
@leoyri
..... #እንደሀገር ...
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
#አንባቢ_ስመ_ሔዋን
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tg-me.com/leoyri
www.tg-me.com/gGetem
Plc share&Join
🎤🎬 Editor
😘 #Saron_Tariku (SariT)
Comment or feedback
type...
#ግራጫ
🔻🔺ከጥላዬ የፊልም መግቢያ ላይ የተወሰደ።
➢የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
@leoyri
@gGetem
@gGetem
ያንድ ምሽት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ልማድ ሆኖበት፥ ሌቱ ቢገፋ
ምን ሊጠቅመኝ፥ ነው የማንቀላፋ
ህልም ሸክም ነው፥ ፈቺው ከጠፋ፤

ሳይጎድለኝ ለዛ
ሳያንሰኝ ውበት
የቀን ጨረቃ፥ ላይንሽ ሆኘበት፥
ቀልብን የማይስብ፥ የሳር ቀለበት
መወደዴ ብላሽ
ምኞቴ  ዘበት፤

የአሻንጉሊት ላም፥ ጡት እንደማለብ
የፈረስ ሀውልት፥ እንደመጋለብ
ሲሳይሽ ፈልቆ፥ ጣት አያርስም
የትም ብትኖሪ፥ የትም አልደርስም፥

የሚፈሰውን አልፎ ገደቤን
-እንባየን ልሼ
ደረቴን ሰብሮ ፥ የሸሸ ልቤን
ቦታው መልሼ
በፍቅር ፈንታ ፥እረፍት ሸመትሁኝ
ቁርጤን አወቅሁኝ ፤

ለካ ሰው ቢማር፥   
ከሊቅ፥ ከመጻፍ፥ ከኑሮ ከእድሜ
ቁርጥን ማወቅ ነው የእውቀት ፍጻሜ;:
🙄

@gGetem
@gGetem
@leoyri
2025/07/05 12:34:16
Back to Top
HTML Embed Code: