Telegram Web Link
ክፍል ሁለት(፪)

ከባለፈው የቀጠለ....
👉🏾 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
:
👉🏾👉🏾 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
👉🏾👉🏾 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
:
👉🏾👉🏾 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።

👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
👉🏾👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
👉🏾👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
:
👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
:
👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

‼️ለጓደኛዎ #share ማድረጎን አይርሱ።

🔘 የተመቻችሁ 👍
Join us;👉🏼 @gGetem
👍31
የእውነት ትንሳኤ 🚩
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ©

የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
አዘጋጅ እና ማጀቢያ ሙዚቃ፦ሔመን👧
-ከአዲስ አቀራረብ ጋር
>>በየቀኑ አዳዲስ ግጥም ይደርሳቹ ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@gGetem
>>Comment  @leoyri
💆"ለእውነት እንቁም"
1
#ትወደዋለች...

(ሚካኤል አስጨናቂ)

እወደዋለሁ ብላኛለች

ፍቅሯን ነግራኛለች።

አምናታለሁ !

ደግሞም አላምናትም

ብትወደውማ

ከሌላ ወንድ ጋር አብራ አትወድቅም!

እሷ እንደምትለው

ውልደትና እድገቷ ጠባሳው ብዙ ነው

የማጣት ቀንበሩ ሸክሙ ከባድ ነው ...

ያምራታል መታየት

አምሮባት መገኘት

እኩል ለመሆን ነው ከጓደኞቿ ጋር 

ነፍሷን የምታነደው በቁስ ጥቅም ስካር

ለአንድ አልቦ ለአንድ አንባር

አንድ አዳር ግድ ነው ከአንዱ ወንድ ጋር።

እሷ እንደምትለው.. .

ልቧ ታምኖለታል ገላዋ ቢክድም 

እንደዛም ሆኖ ግን

በሱ ስፍር ልኬት ወንዱን አትመዝንም።

ይሄንን አውቃለሁ !

አዎን አምናታለሁ

አፍቃሪው ናት ብዬ

ከእውነታው ኮብልዬ

እሷ እንዳለችው.. .

ትውልድና እድገቷ ጠባሳው ብዙ ነው

የማጣት ቀንበሩ ሸክሙ ከባድ ነው

ገንዘብ ላጣ ድሀ

አምሮበት እንዲታይ መፍትሄው ምንድነው?

ከወንድ ጋር ማደር ከአንገት በላይ መሳቅ

በማስመሰል ስላቅ

መጫወት መደነስ 

መብነሽነሽ መኩነስነስ

ሀጥያት ነው ብዬ ሳልደርስ ለወቀሳ

የማዝን መሰለኝ

ከጓደኞቿ ዘንድ ብትታይ ተናንሳ ። 

አይ አይ አትወደውም !

እላለሁ ለጥቄ

ከእውነት ተናንቄ ...

የላትም ብትባል ቢንቋት ቢተዋት 

ገላዋን ከማርከስ የለም የሚከብዳት ።

አይ .. አይ.. አትወደውም !

ብትወደውማ ...

ከእምነቱ ሰርቃ

ለሌላ ወንድ ወድቃ ...

ከሌላ ወንድ ጉያ ውስጡ ተወሽቃ

አንድ አዳር አይደለም

ለሰከንድ አትቆይም ...

እንዲህ ያለ ክህደት ፍቅር አይባልም።

ብዬ ከማለቴ ... 

ስለሱ ሳወራ ከአንዴም ሁለቴ 

የእንባ ውርጅብኝ ጉንጮቿ ላይ ዘርታ

ነጉዳ በትዝታ ...

በአፍቃሪ ሰው ሲቃ ጠርታዋለች ስሙን

አትወደውም ብዬ

ይሄን ቃል ባወጣ ... ይሆናል ወይ እሙን ?

አይሆንም!

አይሆንም !

መውደድማ ትወደዋለች

ለፍቅሩ ወድቃለች.. .

ሽንፈቱን ደብቃ

ሽንፈቷን ደብቃ ...

እሷ ጓደኞች ዘንድ 

አልቦ ገዝቶልኛል ብላ አውርታለች

ሽቶ ገዝቶልኛል ብላ ተናግራለች ።

እላለሁ በልቤ

በሰው ቁስል እንጨት እንዳልሰድ አስቤ

አይ አይ አትወደውም ደግሞ ይለኛል ቀልቤ

እንደዚህ ሆኜ ነው እሷን የምሰማት 

እንደዚህ ሆኜ ነው እሷን የምቀርባት 

ለዚህ መንታ ሀሳቤ 

ቁስ ንዋዩ ኖራት 

ምናለ ባየኋት ?!... ምናል በመዘንኳት?

ብዬም ደግሞ አውቃለው

ማጣት ያሸነፈው ፍቅር ግን ምንድነው?

አይ አይ... አትወደውም 

አይ አይ ...ትወደዋለች

ብቻ እንጃ.. .

ብቻ እንጃ.. .

ይህች ሴት ቅኔ ነች !

@gGetem
@gGetem
@gGetem
2🥰2
🐺 ቀበሮ ለዶሮ «የአባትህ ድምፅ በጣም ደስ ይለኝ ነበር» አለው።
🐓 ዶሮም «የኔም ድምፅ እኮ እንደ አባቴ ነው» በማለት መለሰ።
🐺 ቀበሮውም «እንደዛ ከሆነማ እባክህ ልታሰማኝ ትችላለህ ??» በማለት ተማጸነው።
🐓 ዶሮው «ምን ችግር አለው !» በማለት ጩኸቱን ለማሰማት ዓይኑን ሲጨፍን ቀበሮው ይዞት አፈተለከ።

ውሾች ሁሉ ዶሮውን ከቀበሮው አፍ ለማስጣል እየጮኹ እግር በእግር ተከታተሉት።

🐓 ዶሮው ለቀበሮው «ከውሾቹ ለመዳን ከፈለግክ ዶሮው የእናንተ ሰፈር አይደለም !!» በላቸው አለው። ቀበሮውም የተባለውን ለመናገር ሲሞክር ዶሮው ከአፉ አመለጠው።
🐺 ቀበሮውም በፀፀት ተውጦ «ዝም ማለት ሲገባው የተናገረ አፉ ይረገም ፤ ይኮነን» አለ።
🐓 ዶሮም በበኩሉ «መንቃት ሲገባው የተጨፈነ አይን ፤ ይኮነን» አለ። ይባላል
የምንነቃበት ቀን ይሁንልን!
@gGetem
@leoyri
👍3🥰1
የህይወት ስሌት
በYorta🤛
በትናንት ሀሣብ ባለፈ ታሪክ
የኋሊት ማለም ግዜን መተረክ
በዛሬ ኑሮ በአሁን ላይ አለም
ግዜን መለካት ህይወትን ማለም
በይሆናል ብሂል በተስፋ ትራስ
ምንም ሳያውቁ ነገን መንተራስ
የህይወትን ስንቅ ቋጥሮ መጠበቅ
በትናንት ትርክት በዛሬ ኑሮ ነገን መታጠቅ
ይህ ነው የህይወት ስሌት
ዛሬ ነገ እና ትናንት
@Yort
@gGetem
👏1🤔1
ዘመን ተወጥሯል
በዜናና ስላቅ
ቀን መሽቶ ይነጋል
ስራችንን ሳና'ቅ።
ወትሮ ድሮ ፣ ድሮ
ሰውን አሳርሮ...
ተናጥቆ ና ሰርቆ...
ከሴት ገላ ወድቆ...
ውሎውን ያበቃ !
እንደ ሰብል ክምር
አዳሩን ሲወቃ…
ሲኮነን ሲረገም
በህሊናው ክሶች
ውሎው ሲገመገም
አድሮ ያነጋጋል
ነገን ለመታረም።
አሁን ይሄ ድሮ
ዛሬ ተቀይሮ
አንዴ በጦር ዜና
አንደዜ በነዋይ
ስጋውን ወጥሮ
ሰውን አሳርሮ
ተናጥቆ ና ሰርቆ
በሴስ ገላ ወድቆ
ነፍሱን የበደለ …
(ራሱን ሳይጠይቅ
እንዴት እንደዋለ)
አቀርቅሮ ይስቃል
በስልኩ ድራማ...
:
ለመጸጸት እንኳን
አያደርሰውማ!

(ሚካኤል አ)
@gGetem
@leoyri
1👍1
Audio
🌚🌘ምሽት በረንዳ ላይ
ገጣሚ፦በእውቀቱ ስዩም
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ስክነት፦አቢ ላላ  🧏
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
🧎‍♂👨‍🦯🚶‍♂🏃‍♂
😢1👌1
ልከኛ ስንኞች!!!
(ቅኔያተኞች)
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#የሳምንቱ ገፅ🕤
👍1🥰1🙏1
.....አንድም ነገር....
😘ሊዮ ማክ©
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

-ከአዲስ አቀራረብ ጋር🙆

>>በየቀኑ አዳዲስ ግጥም ይደርሳቹ ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@gGetem
@gGetem
>>Comment  @leoyri
💆💃🙇


የሳምንቱ
1🤔1🤩1
የሰው አፈጣጠር ግብዝ ነው ፤ ብዙ ይጠይቃል ፣ በጥቂት ይረካል። የማያስፈልገውን ሲያሳድድ ፣ የሚያስፈልገው ይከተለዋል። ወደ አሳዳጁ በዞረ ጊዜ በተሳዳጅ ደክሟልና አቅም ያጣል።

የሰው ልጅ እንዲሁ ግብዝ ነው። የሚያውቃት ፣ በእጁ ያለችውን ዛሬ የማያውቃትን ነገን ለማስደሰት ይሰዋታል።

አለማየሁ ገላጋይ
📚የተጠላው እንዳልተጠላ

inbox
                   @leoyri


@gGetem
👍1🥰1
Forwarded from ዳማት 💚💛
ነባቢት
ሀገሬ ሰንደቅሽ እያደር
ዝቅ
ዝቅ
ዝቅ
እንደምሽት ጀምበር ጥልቅ፤
እን'ዳፍረት ልብስ ድብቅ
ደርሶ ጅረት መስሎ ጭምልቅ_ልቅ
#አይልም
ሊዮሪ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
🥰1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
🤭አይ_ባንዳሽ🤫
ገጣሚ፦ ሊዮ ማክ
#አንባቢ_ቤተል
#ከባሌ_ጎባ
@leoyri
@gGetem
25/03/2014ዓ.ም
ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👏1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
🙆‍♀🙆‍♀🙆‍♀🙆‍♀ ኡ.....ኡ ትበል...😭😭😭😭
ገጣሚ። ረቢና
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
@gGetem
@gGetem
👏1
.....ፈጠራ....
😘ሊዮ ማክ©
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

-ከአዲስ አቀራረብ ጋር🙆

>>በየቀኑ አዳዲስ ግጥም ይደርሳቹ ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@gGetem
@gGetem
>>Comment  @leoyri
💆💃🙇
❤‍🔥21
30😘🤜😷🙄👊
#School_life
@gGetem
@leoyri
🏆2😁1
--ብታዉቂ--

(በእዉቀቱ ስዩም)

ስትሥቂ
ጠፈርንእንደምታደምቂ
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ
ስትስሚ
አጥንት እንደምታለመልሚ ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታዉቂ
ስታወሪ
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኪሴዉን ከሱባኤ
ፈላስፋውን ከጉባኤ እንደምትጠሪ
ብታዉቂ
እንኯንስ በኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋራ ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበረ ስትማቅቂ

By bewuketu seyoum

@gGetem
@gGetem
@leoyri
👍2👏1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀና ሀይሉ ግጥም
- #ደረስንልሽ_ሀገሬ
አንቺን ማቃጠሉ ስለሚቀል እንጂ
ጭስ በጭስ የሆነው
እሳቱን ለማጥፋት ስላንቺ ሚማገድ
ከአመዱ መሀል ብዙ ሰው ነው ያለው
@gGetem
@gGetem
@hanahailu
ለአስተያየት @Leoyri
1
የውጊያ ስልት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሙሴ በበትሩ
ፈርኦን በጦሩ
ኤርትራ ባሕር ላይ ፣ ጦርነት ጀመሩ፡፡
።።።።
ሙሴ በበትሩ…
ግዙፍ ባህር ከፍሎ ፣ ህዝቡን አሻገረ
ፈርኦን በጦሩ
ከነ ወታደሩ
ባሕር ሰጥሞ ቀረ፡፡
።።፣፣
ውጊያ የማይችል ሕዝብ
ግዙፍ ባሕር ከፍሎ ፣ በተዓምር ሲሻገር
ሌላ የውጊያ ስልት
ቀይሮ ይመጣል ፣ ቢሰምጥም ወታደር፡፡






የተሻገረ ህዝብ
ለቀሪ መንገዱ
አሳ እያጠመደ ፣ ከባህር ሲያወጣ
የፈርኦን ወታደር
ሞቶ ለመዋጋት
በአሳ ገላ ላይ ፣ እሾህ ሆኖ መጣ!!!
።።።።
።።።፣
"አሳን መብላት
እንዳይወጋህ ፣ በብልሃት!"
@gGetem
@leoyri
1👏1
ገብረክርስቶስ ደስታ
የፍቅር ፍልስፍና
-----------------*
ጅረቶች ከወንዞች ጋር
የሙጥን ብለው….. ተጣምረው
ወንዞችም ውቅያኖሶችን አቅፈው
የሰማየ ሰማያት ንፋስ
ጣፋጭ ስሜት ሲዋሃደው….
ተመልከችው
ከቶ አንድም ነገር
በአለም ላይ ያላቻ ጓደኛ
ሆኖ አይገኝም ብቸኛ
በውስጠ ሚስጥር ህላዌው
ይጣመራል ሁሉም በውል
በአንድ መንፈስ በአንድ ቃና
ስጋና ደሙን ሲያዋውል፡፡
እኔና አንቺስ ምን አለበት
አንድ ብንሆን ብናውቅበት
እንደመሶብ ከግጣሙ
ሰማያት ምድርን ሲስሙ…..
እይው ጣእሙ፡፡
ማዕበሎችን እያቸው
ባህር ላይ ሲሽኮረመሙ
ሲላላሱ አንዱ ባንዱ ውስጥ ሲሟሙ
አንዱ ማእበል አንደኛውን
አቅፎት ሲሄድ አቻውን….
እይው በሞቴ ጣእሙን፡፡
ደሞም የፍቅር ጡር ጣጣ
ሴቴ አበባ ያለወንዱ፤
አበባነቷ ቅጥ ሲያጣ
ወንዴ አበባም ያለሴቷ
በፀሀይ ሀሩር ሲቀጣ
እይው ቆንጅት እይውማ
ልቦና ፍቅር ሲጠማ
የፀሀይ ብርሀን ጠዋት የመሬትን ከንፈር ሲስም
በሙቀት እየዳበሰ ፈገግታዋን ሲያለመልም
ለዛው ሲፈካ ሲተም
የጨረቃ ጨረር ሞገድ
የባህርን ራቁት ገላ
በምሽት የእንቅልፍ ሰዓት
ይደበዝዛል እያጠላ
ስለዚህ አስተውይው
እኔን ሁኝ አንቺን ልሁን
በደም ስርሽ ደሜ ይፍሰስ፤
በደም ስርሽ ደሜ ይሁን፤
አንድ እንሁን፡፡

join @gGetem
@gGetem
@Leoyri
👏1🥱1
ከ'ራስ' ላይ እንውረድ
.
.
.
.
እንዲህ ይመስለኛል....
.
.
ነፍስሽ ብረት ምጣድ ፥ ነፍሴ የንጨት መቁሊያ
እሳት በሌለበት፥ ከማገላብጥሽ ፥ ወዲህና ወዲያ
በ'ታርራለች' ስጋት ፥ መብሰልሽን ከማግድ
ልሰባበርና ፥ ስርሽ ተወትፌ ፥ልቀጣጠል ልንደድ።
.
.
እንዲህ ይመስለኛል
.
ገብስሽ ለዛዛ ነው ... ሽምብራሽም ንክር
እሳት በሌለበት፥ ታርራለች እያልኩኝ፥ ላይ ታች ስዳክር
በቀኝ እንዳትደብኚ፥ ወደግራ ስገርፍ
በግራ እንዳይፈጅሽ፥ ወደቀኝ ስግፍ
ልጠብቅ መሰለሽ ፥ የዘጋኙን መዳፍ ?
.
.
ዘጋኝ ሞኝ አይደለም... ብልህ ነው ልንገርሽ
ጣቶቹን አይሰድም ፥ ዉሃ ላይ ቢያገኝሽ
.
.
ምጣዱ ነው ጌጥሽ፥ የመብሰልሽ ተስፋ
ዘጋኙን ጋፊውን፥ አፋሹን 'ሚያጋፋ
.
የተንጋለልሽበት፥ በንክር ቁንጅና
ምጣዱ ነው ጌጥሽ... ግን አልጋለም ገና
ከማገላበጥሽ... ከስርሽ ልቃጠል፥ ልሰባበርና
.
.
እንዲህ ይመስለኛል
.
.
ቁንጅና ቀለም ነው ፥ ፍቅር ደሞ ጮራ
አድናቂ የለሽም ፥ ልቦናሽ ካልበራ
.
ካንቺው የፈለቀው፥ አንቺኑ ካጠጣ
ጀንበርሽ ፀዳልሽ፥ ለራስሽ ከወጣ
.
ሽንብራና ገብስሽ ፥
ምን አፋሽ ቢቆልል፥ ምን ዘጋኝ ቢያጋፋ
እርጥብ ነው ንክር ነው ፥ ተቀምሶ 'ሚተፋ።
.
.
እንዲህ ይመስለኛል
.
.
መቁሊያ አያስፈልግም፥ ዘጋኙን ለማገድ
ከላይሽ ወርጄ ፥ ከስርሽ ልማገድ
ትርፍ ማጋዝ ሳይሆን ፥
ጎዶሎን መድፈን ነው ፥ እውነተኛ መውደድ !
.
.
[የዛሬ አመት]

#rediet_assefa
@gGetem
@gGetem
2👏1
2025/07/10 09:36:31
Back to Top
HTML Embed Code: