Telegram Web Link
እንደ እግር ጣት ስር ሙጀሌ
ተሸጉጠው ደሜን ጠጡት
እንደ ወገብ ላይ ቅማል
አካሄዴን ቅጥ አሳጡት
የቋንጃ እከክ ሆነውብኝ
ጥፍሬ ችሎ 'ማይዛቸው
አገባሁ እንጂ አልገደልኩህ
ቆይ ምንድነው ችግራቸው?
አላስራብኩህ ወይ አልጠማህ
ወይ መኝታ አልከለከልኩ
አልባለግሁኝ ፍሬ አልነሳሁ
አላረጥኩኝ ወይ አልመከንኩ...
ጡት አጥብተው ባያስገሱኝ
ከአብራካቸው ባልወለድ
ሚስትህ መሆኔ አይበቃም ወይ
በናትህ ዘንድ ለመወደድ?
አቦ እናትህ አበዙት ኤጭ!

ዘማርቆስ
@wogegnit

@getem
@getem
@getem
20👍15😁13👎2🔥1🤩1
እንደውም አንገሽግሾኛል
ጓዝሽን ጠቅልለሽ ውጪ
ስንት አመት የከረምሽበት
ልብ ኪራዬን ብቻ አምጪ

የትም ኬትም ኖረሽ
እንደተረፈው ሰው ፍቅር ስትበትኚ
አሁን ኪራዬን ስል
እንዳልኖረበት ሰው ተበዳይ አትሁኚ
ከፋፍዬው እንኳን
ሌላ ምስኪን እንስት እንዳላስገባበት
ልቤ ዳር እስከ ዳር
እንዳትነኩኝ የሚል ፡ ዳናሽ ነበረበት።

አሁን ጥርግ በይ
እንኳን ሌላ ሰው ልብ
    እንጦሮጦስ ሂጂ፥
ብቻ ኡኡ ሳልል
ኪራዬን ውለጂ!!

❗️ @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
😁68👍135🔥3🤩3
¹
አላያትም እይልኝ
አልጠብቃት ጠብቅልኝ
ሳሳሁላት ፈራሁላት
አልደረስኩም ድረስላት ።
²
እኔ ከንቱ ሰው.....
የዓለምን እንጂ መውደድ ናፍቆቱን
መቼ ችዬበት የመለኮቱን ?!
ክንፍ የለኝ አልበር ሰይፍ አልሰጠኸኝ
ጎድያለሁ ስል ፍቅር ሞልተኸኝ
ደከምኩኝ አሁን ሆኜ አቅም አልባ
የቀረኝ ጥሪት ጸሎትና እንባ ።
³
ወዳጅ ነኝ ከሚል ሰው....
በድኩም ትከሻ ፍቅር ካነገተ
ትቀርባት የለም ወይ የፈጠርካት አንተ?!

ከፊቷ ገበታ ሳቋ እንዳይጓደል
ሳር እየመሰላት እንዳትገባ ገደል
(ክንፉን አንጥፎላት እንድትደላደል)
ገብርኤልን ብትልከው
እምቢ አይልህም አይደል?
_
By @Bekalushumye

@getem
@getem
@paappii
71👍17😁4👎1
(የአብስራ ሳሙኤል)

ይሄ የምታይው
የፈረሰ መንገድ ታሪክ እንዳይመስልሽ
እዚህ ጋ'ነው ቃሌ እዚህ ጋ'ነው ቃልሽ
ስጋ የለበሰው
እንደ ሰው እንደ ሰው
ግና......ዛሬ
ስጋሽም በሰበሰ
መንገዱም ፈረሰ
እኔና ትዝታ ብቻ ባለመኖር ውስጥ አለን
ከፈራረሰ ማንነት የህይወትን አጸድ ተክለን!


By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@getem
15👍8
( ያ ውሻ ... )
===========

ሰዎች ያባረሩት
ከመንደር ያስወጡት የሌለው መድረሻ
አቻውን ፍለጋ ሚንከራተት ዘውትር
በጫካ በጥሻ ....
የጭንቅ አማላጇ
ምህረት ተጠምቶ ጫማሽን ሚናፍቅ
እኔ ነኝ ያ ውሻ .....
:
መቼ ትመጫለሽ
መች ታልፍያለሽ በዚያ በተጣልኩበት በር
መባዘን መድከሜ ፊትሽን አይቼ
መቼ ነው የሚቀር  ???
ረዘመ ቀኑ ....
መላው ጠፋ ሀሳቤ አላልቅ አለኝ ሌቱ
ጉልበቴ ሲደክም .....
ወዜ ሲንጠፈጠፍ በረታ እንግልቱ
ከወርቁ ጫማሽ ላይ
ውሀ ምታጠጭኝ
መች ነው አዛኝቱ  ?

መከረኛው ልጅሽ ጥቂት ቅድስና
ወይ ምግባር የሌለኝ
ባውቅም እንደ ግብሬ
ጫማሽን ልነካ አቅም እንደሌለኝ
አምናለሁ ስጠራሽ አልፈሽኝ አትሄጂም
አትጨክኚብኝም
ለውሻ ሚራራ እንስፍስፍ አንጀትሽ
ጥርኝ አይነሳኝም !
:
ግን ደግሞ ከብዶኛል
ግን ደግሞ ጠምቶኛል
ውሃ ልታጠጪኝ መቼ ትመጫለሽ
ያ ጫማሽ ናፍቆኛል 😔😔

By @Kiyorna
( ፲፱ - ፮ - ፳፲፮ )

@getem
@getem
@paappii
60👍23😢6
ማዘን ሲገባኝ ፥ ስትጠፊ ካይኔ
መጻፍ ሲገባኝ ፥ ሙሾ ወይ ቅኔ
(እንጃልኝ እኔ ...)
የጤና አይመስልም ፥ ደህና መሆኔ ።

ትዝ አትዪኝም ወይ ለትንሽ ደቂቃ ?
አትናፍቂኝም ወይ ሳዳምጥ ሙዚቃ ?
ረሳሁሽ በቃ ?

እንጃልኝ
እንጃልኝ
ናፍቆትሽ በኋላ ምን እንዳሰበልኝ ።

ሰው ባይገባው እንጂ አዕምሮው ደንዘዞ
እንዴት 'እፎይ' ይላል  ስንት ኮተት ይዞ ?

እባክሽ አታዘግዪብኝ ፥ ስቃዬን ዛሬ ልወጣው
አንቺስ ሄደሻል እሺ
ናፍቆትሽ መች ነው ሚመጣው ?

By Hab HD

@getem
@getem
@paappii
38👍17🔥5
(የአብስራ ሳሙኤል)


ስንኝና ቀለም
ከምእናብ አለም
ገጣሚ ሲጽፍሽ
ሰአሊ ሲስልሽ
አርቅቀው
አድንቀው
ለገሀድ ነጸብራቅ
የተፈጥሮሽን ሀቅ
እየተጣረሱ
አንቺን ሲያወድሱ
እንዲ ብለው ነበር
ፍክት ያለች ጀምበር
ጨረቃ የምታቅፍ
ዉሀ ላይ የምትጽፍ
ድምጿ የወፍ ዜማ
ጸጉሯ ጥቁር ዞማ
አይኖቿ እንደ ባህር
ሳቋ የሚያሰግር
ከሴትም አንድ ሴት
..
....
የሀሳባቸው ደሴት
ጎዳሽን አልነካም
ማጣትሽን አልተካም
በሀሳባቸው ልክ
በታጠቁት ብዕር
ምኞት ስትሰክር
ያድሉሽ ጀመረ
ውበት ተሳከረ
እውነት ተሳከረ
የለሽም ጨረቃ
ጨለማ ናት ጠልቃ
ፀጉርሽ ተበታትኖ
መልክሽን አደፈ
ይሄ መች ተጻፈ
አልተሳለም ሀቅሽ
የጎደፈ ሳቅሽ
አለቱ ተራራ ቤትሽን የከለለ
ሊያፈርሰው ማን አለ?
ደርሶ ይደበቃል ከምዕናቡ አለም
ሊንደው በስንኝ ሊነቅለው በቀለም
ማን ነበር ከጓዳሽ ?
ማን ነበር የጎዳሽ ?
ሸራ ላይ ስቃሻል
ተጽፈሽ አልቀሻል
ደስታሽ ከአደባባይ
ለገበያ ዋለ
"አሰየው ተባለ"
"ሸጋ ነው ተባለ"
ደርሶ ያየሽ የለ
ባነበቡት ልኬት
ገላሽን ተመኙ
በተረዱሽ መጠን
ደርሰው እየተቀኙ
ያወድሱሽ ጀመር
መፋለስ ሲጀመር
ሀሳብ የወለዳት
አንዲት ስንኩል ፊደል
የሰኣሊው በደል
አምላክ መሆን ቀላል
ሰሪ መሆን ክፉ
ሀዘን ሲጠየፉ
አይዞሽ አላሉሽም
አላስታመሙሽም
ይልቅ በሃሳባቸው
ሸራ ላይ አሳቁሽ
በቃል አደመቁሽ
ለገሀድ ነጸብራቅ
የተፈጥሮሽን ሀቅ
እየተጣረሱ
አንቺን ሲያወድሱ
ጨረቃን አቅፈሻል
ሞተሽም ስቀሻል
በድን ቢሆን አንኳ
የሙት መንፈስ መልኳ
ተያቸው በምዕናብ
ካቀፉሽ በሀሳብ
ይፈላሰፉልሽ ቃል እየመረጡ
እንስራሽ ሲሉ ነው ስሪትሽን ያጡ


By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
38👍22🔥7
ትናንትና ማታ እጅጉን ናፍቀሽኝ
ያ ክፉ ትዝታሽ አላስተኛህ ብሎኝ
ድምፄን ከፍ አድርጌ ስምሽን ጠራሁኝ
እንደ ደብተራ አስማት እንደ ጴጥሮስ ክህደት
በአንዴ ባይሆንልኝ ሶስቴ ደጋገምኩት
ሰልስቱም አልሆነ ሃያ አንዴ ጮኬ በማርያም ለመንኩኝ
አርባ አንድ አድርጌ ኪሪያላየሶን አልኩኝ
ጠራሁሽ በናፍቆት ጠራሁሽ በፍቅር
ወይ አንቺ ነይልኝ ወይ ትዝታሽ ይቅር
                 
                     by አለምሰገድ ወልዴ

@getem
@getem
@getem
54👍14🔥5
ይቅርታ !

ስታቀርቢኝ
ስለራቅኩሽ ፤

ስትወጂኝ
ችላ ስላልኩሽ ፤

ስታንሽልኝ
ስለናቅኩሽ ፤

ኮኮብ
ሰማይ
ፀሐይ
ጨረቃ ... ስታደርጊኝ
እንደ ሰው ስላልቆጠርኩሽ ፤

በነፍስሽ ላይ ስለቀለድኩ
በዕድሜሽ ላይ ስለተጫወትኩ ፤

ውብ ነፍስሽን ስላሳደፍኩ
ስስ ልብሽን ስለሰበርኩ ፤

ልኬ ድረስ ስትመጭ
ልክሽ ድረስ ስላልወረድኩ ፤

ገላሽን
እንደ ትቢያ አፈር
ነፍስሽን
እንደ ዕድፍ ምንጣፍ

ተራ አድርጌ ስለቆጠርኩ ፤

ይቅርታ !
____

አዬሽ
የሰው ስቃዩ ይሄው ነው፤

እኔም ለወደድኳት ያዬሁት መከራ
ያንቺኑ ያኽል ነው ።

By Tewodros kasa

@getem
@getem
@paappii
60😢31👍21👎13🔥3
ዳግም እብደት
ፍቅር ስክነት
ዳግም ክንፈት
ፍቅር ጥልፈት

ክንፍ ንፍ ንፍ
    እርፍ

ሩቅ ሀገር ካለሁበት
ዳግም እብደት

ዳግም ማደር ሰርክ ርቆ
ፍቅር ቅዠት ክንፍ ታጥቆ

ብርር ብርር እንደ ልቡ
     መልከ ግቡ

መቅዘፍ መክነፍ
ካለችበት ካለሁበት
ፍቅር ቅዠት ፍቅር እብደት

ሰርክ መሮጥ ከንፎ ማደር
   እሷ ሮቤ እኔ ጎንደር።


ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍3228
. . .
ባይፈካ - ንጋት ለአመሉ
ያምፃል ዝም ያለው ሁሉ

አይደለ? ወትሮስ ተረቱ
ይረጋል ? የፍጥረት ሞቱ?

ሰው ልቡ ቢያስበው ደጉን
ያመልጣል ስብራት ህጉን?
ይሸሻል ከሞት ድለቃ
ከመከራ ዶፍ ከዕድል ሰበቃ?

ይሸሻል በስሟ ምሎ
እንደእኔ ልብ ይስጣት ብሎ?

ከሸሸም ይሁን ይሸሻል!

እኔ ግን ምን ያጓጓኛል?

ከመኖር ፍቅር አውድማ
ቢነግሩት ጆሮ ካልሰማ
ቢጠሩት እግር ከዛለ
መተውን ያህል ምን አለ?

By Sirak Wondemu

@getem
@getem
@paappii
👍2214🔥3
--ብታዉቂ--

(በእዉቀቱ ስዩም)

ስትሥቂ
ጠፈርንእንደምታደምቂ
መንፈስን ካዚም እስራት እንደምታላቅቂ
ስትስሚ
አጥንት እንደምታለመልሚ ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታዉቂ
ስታወሪ
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኪሴዉን ከሱባኤ
ፈላስፋውን ከጉባኤ እንደምትጠሪ
ብታዉቂ
እንኯንስ በኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋራ ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበረ ስትማቅቂ

By bewuketu seyoum

@getem
@getem
@paappii
31👍6🔥4
__
የመኖር ምክንያቶች —
ምኞት ፍላጎቶች  ከ
ኔ ላይ ይነሱ ፤
እንደ ጎርፍ — እንደ ወንዝ.....
በመሬት ይፍሰሱ ።

እኔ እንደሁ....  እኔ እንደሁ.....
ቢቃና ቢሰበር — ቢጎድል ቢሞላ ፤
አንዳች ግድ የለኝም ከእንግዲህ በኋላ ።

ጫጩት ምኞቶቼ —
ጅማሬ ህልሞቼ  ባልጠና ክንፋቸው....
ከዛፉ ልቤ ላይ — ተነስተው ይብረሩ ፤
እኔ ምን ተዳዬ ወድቀው ቢሰበሩ ።

አረም ይብቀልበት —·· ሸረሪት ያድራበት
የምመኘው ኑሮ —
ምጓጓለት ፍቅር ፤
“ና” ያልኩት አይምጣ `ምጠብቀው ይቅር ።

ይሄ ሁሉ ቢሆን....
አይታወቀኝም — ( የሆነ አይመስለኝም)
እንኳንስ ልከፋ ፤
የካብኩት ይደርመስ ያገኘሁት ይጥፋ ።
የጣድኩት ይገንፍል — ያበረድኩት ይፍላ ፣
የምወዳት ጉብል — ትሂድ ወደ ሌላ ፣
ግድም አይሰጠኝም ከእንግዲህ በኋላ ።

እንዳሻው እንዳሻው —
ሁሉ እንደ መድረሻው እንደ ፍላጎቱ ፤
ዘመን ሽምጥ ይጋልብ..
ይሸከርከር ሰዓቱ ።
ምንም አይመስለኝም !
ላድርገው (ልድረሰው) የምለው የለኝም ።

ይሁን ልቤ ባዶ — ይሁን ልቤ ኦና፤
የሕይወትን መንገድ — ገና ሳልጀምረው
ደክሜያለሁና ።
_
By @Bekalushumye

@getem
@getem
@paappii
45👍12🔥3
------ነው የምሆነው

"በሰማዩ ፈረስ ተጓዥን አድርሼ
በተካንኩት ጥበብ ታማሚን ፈውሼ
ለሀገሬ ቆሜ ማስጠራት ነው ስሜ
መሀንዲስ መሆን ነው የወደፊት ህልሜ
ብዬ ነበር ያኔ በልጅነት ወዜ
ሳድግ ምሆነውን በተጠየቅሁ ጊዜ።
ጥብቅና በመቆም ፍትህ ለተጠማ
እውነት እሰብካለሁ በውሸት ከተማ።
ብልሃተኛ ሆኜ ችግርን መርማሪ
በነጋ በጠባ ሰላምን አብሳሪ
ጥበብን ከቀለም ለትውልድ ነጋሪ።
ብዬ ነበር ያኔ በልጅነት ወዜ
ወዳጆቼ ሁሉ በጠየቁኝ ጊዜ፡፡
ወጥቼ እያደርኩ ለሀገር እሰ'ዋለሁ
ባይኖረኝም በትር ህዝብ አሻግራለሁ
ፍጥረቴ ሰው አይደል ለሰው እኖራለሁ።
አቀነቅናለሁ ለምንዱብ ድምፅ ሆኜ
በጥበቡ አለም ገሀዱን ተውኜ
በሰፈርኩት ቁና 'ሰፍራለሁ መዝኜ፡፡
በፍ'ቅር ሮጣለሁ ለሰንደቅ ዓለማ
የእምዬን ክብር ለአለም እንዲሰማ"።
ብዬ ነበር ያኔ በተጠየቅሁ ጊዜ
የወደፊት ህልሜ በልጅነት ወዜ።
            
by Abuugida

@getem
@getem
@getem
👍3210🔥1🤩1

ካባ ጫንኩኝ ለሷ ብዬ፡
ዘውድ ገፋች ለኔ ብላ፥
የኋላዬን ኋሏ ትቼ
የተክሊሉን ምኞት ጥላ፤
አብረን ቆመን አስቀደስን
ተዋሃድን በኢየሱስ ደም፡
እሰይ አለፍን ተያይዘን
ያቃቃረን ወጥመድ ይውደም።

ሳያት ግና ደነገጥኩኝ
የናፍቆቴን  ትንሽ ዞሬ
ይህ እምባዋን አላየውም
አብረን ሆነን እስከዛሬ
ጠይም መልኳ ማጀት ሆኖ
የባዶነት ግጥም ፅፏል
ወትሮ ሚስቅ ትንሽ አይኗ
ትኩስ እምባን አቸፍችፏል፤
መሪር ሀዘን የጥቁር ቅብ
የእምባ ጅረት ግድብ ላይኔ
ሀ,ለ የሚል፡ ቃል የሌለው
ያልተፈታ ባዶ ቅኔ።

ተሸበረ አንጀት ልቤ
ተሸሽጎ የነበረው
ፀፀት ወቶ በሀይል ገፋው፤
መቅደስ መሃል እንደቆምኩኝ
ካለውበት አለም ጠፋው።
ከሰማያት ሰማይ በላይ
በደመና ሽቅብ ሄጄ
ቁልቁል ነፍሴን ወረወርኩት፤
ከርሷ ጋራ ለመሆን ስል
አንድ ህልሟን ነው የነጠኩት።
ምንአለበት ፍቅር አይደለ
ባልቋደስ የሰው መባ
እንደህልሟ እናቷ ፊት
ተክሊል ደፍታ ብታገባ?

ምናለበት ባላገኛት
ባይበዛብኝ የኔ በደል
ለርሷ ሚሆን ትጉህ ንፁህ
በከተማው ሞልቶ አይደል?

ምን ነበረ ባላገኛት
ምን ነበረ ባልመኛት
እንዲህ እንዲህ ባለ ምሬት
ምትዋከብ ልቤ ጋለች
የኔ አበባ እኔን ስታይ
የውሸቷን ፈገግ አለች።

ከሰምኩላት
ወደኩላት
ንፁህ ፍቅሯ
መቅደስ መሃል
ዳግመኛ ልቤን ገዛው ፤
እዩዋት ጭንቄን ስታበዛው።
እዩዋት ፍርዴን ስታበዛው።

የዘመናት አንድያ ህልሟ
ያጠለልኩት እንደ ወንፊት
በምጢረ ተክሊል ከብሮ
መዳር ነበር አባቷ ፊት።
ላስተማራት የጌታን ቃል
ሽፍን አርጎ  ካለም ስጋት
ለውለታው ምላሽ ነበር
አቅፎ ስሞ ላሳደጋት።
ጥሎሽ ድግስ ብልጭልጩ
አይፈልግም ለምን ጥቅም
ካህን አይደል ካንድ ልጁ
ከክብር ውጪ አይጠብቅም።

እሷም ብትሆን አልማለች
አንድ እያለች አመታቷን
እንደ ባሪያ ወርዳ ኖራ
ዛሬ ልትወስድ ሽልማቷን
ብትመጣም እምቢ አለች
እኔም ክፉ እጇን ያዝኩኝ
የተክሊሉ ኒሻን ቀርቶ
ሽልማቷ እኔ ሆንኩኝ።

ለምን እኔን ?
ለምን ለሷ?
አዳፋ አይደል ማንነቴ
ንፁህ አይደል ገላ ልብሷ
እሰጋለው ዛሬም እንኳን
ማንነቷን እንዳልቀማት
ጭራሽ በቃው ለሽልማት?

እሺ እምባዋስ?
እሺ አባቷስ?
ወዳጅ፣ ዘመድ ጎረቤቷስ?

አይ እዳዋ

ዝቅ ብላ አንገት ደፍታ
ምሽት ገብታ በሌት ወታ
አንዴ ዳዊት አንዴ ጥምቀት
አንዴ ቅኔ  አንዴ ሰንበት
ብላ ኖራ ቤተ መቅደስ
እንደበራች የጧፍ ግማጅ
እምነት ፍቅሯን ሳትቀንሰው
ገላ ክብሯን ጠብቃ አድጋ
ሽልማቷ ፦ "ዘማዊ ሰው!"።

© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
52👍18🔥4😢2
(የአብስራ ሳሙኤል)

በለስ ሆነበት
እውነት
ስትነግረው
ሰበረው
ውሸት ምን ያህል ውብ ነበረ
ተሰበረ
የነፍሱን ሀቅ
ሳቅ
ነጠቀችው
ነገረችው
የሄደ ጊዜ
ነጠላ ረግጦ
አማግጦ
ጭኗን ሲተካው
ምርጫ ሲያስመካው
ጠረኗን ተፍቶ
ትቶ
የሄደ ጊዜ
የሄደ ለታ
ተስፋዋን ትታ
ዘሟች ፍቅሩን
ክብሩን
ልጠብቅ ብላ
እኔ ነኝ አለች
ፍቅሩን የገፋው
ስቼ ያጠፋው
የማገጥኩበት
ቁስል የሆንኩበት
እንጂማ የእሱ
ጻድቅ ነው ነፍሱ
አያቅም ነበር ክፉ ተናግሮ
ስድብ ወርውሮ
አያይም ነበር የሌላ ገላ
ከእኔ ሌላ
እንጂማ የእሱ
ጻድቅ ነው ነፍሱ
ለመጣሁ ሁሉ ምን ሆነሽ ላላት
ለስምህ የጻፈች ገድል ነበራት
የምትነግረው
የምታበስረው
መቼ ሆኖላት ስሙን አጥፍታ
አውርታ
ለመጣው ሁሉ ትኩውለው ነበር
ክፋ ማን ነበር ?
እሷ
የረከሰች ነፍሷ
በነገረቻቸው ልኬት
አበጁላት ስፌት
ነጠላዋን ቀደው
ክብሯን ንደው
የውርደት ቃል ነሰነሱ
እንጂማ የእሱ
እንጂማ የእሷ
ጣት ቀስሯ አታቅ
ታማኝ ነች ነፍሷ
ብቻ ለሱ ነገረችው
ይመጣ ይሆን ብላ መሰል
የሱን ሀጥያት እሷ መምሰል
የሱን ውርደት ዝሙት ሀቁን
እንዳለቀሰች ተውሳ ሳቁን
ሱሪ አስታጥቃው
ቀሚስ መቅደዷን
መዋረዷን
ለጠየቋት ሁሉ
እምነቷ መቅለሉ
ለሱ ብቻ ነገረችው
ያዝን ይሆን ብላ መሰል
ጽድቋን ችራ
የሱን ሀጥያት እሷ መምሰል
ብትነግረው
ሰበረው
ውሸት ምን ያህል ውብ ነበረ
ተሰበረ
በሀቋ
ባዳፋ ሳቋ
ስሟን አጉድፋ ስም ብትቸረው
ረግጧት ሲሄድ
የምትጽፍለት ገድል ነበረው

By @yabisrasamuel

@getem
@getem
@paappii
👍2613🔥2
አምላኬ
ጣሉኝ አጣጣሉኝ ከሞት ተጋፈጥኩኝ
እንደ ቸርነትህ ሁሉም አልፎ ቆምኩኝ
ዕንባዬ ታብሶ ጤናዬ ሲመለስ
ለምን ይሆን እንደው
አናንቆ የገፋኝ ከበሬ ሚመለስ?
.
ታውቀው የለ ዐቅ እወነቴን
ስጠኝ እንዳልኩ ስንቴ ሞቴን
ታውቀው የለ የኔን ቁስል
ለምን መጡ ፈገግ ስል?

[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
42👍26🔥12
(የአብስራ ሳሙኤል)

ሰውና አምላኩ ሸንጎ ገጠሙ
ዳኛ እንዲሆኑ ጻድቃን ታደሙ
ገብርኤል ክንፉን እያናጠፈ
ሰጋሪው ውሀን እየቀዘፈ
ጸሀይ ከገባኦት
ጌታ ከጸባኦት
ህያዋን ሁሉ ተሰበሰቡ
እንዴት የሰው ልጅ
ጣት ለመቀሰር ደፈረ ልቡ
ጌታም ከዙፋን ቢያቀውም ድሉን
ይሞክር ብሎ ፍጡር የድሉን
ሸንጎ ቀረበ እንደገደፈ
°°°°°°°°°°°እንደቀጠፈ
ጸጥ እረጭ አለ ከንቱው ጫጫታ
መቼም ታላቅ ነው በል ጀምር ጌታ

1 .ተከሳሽ

በዕለተ ሰንበት ከመቅደስ ቆሜ
ወንጌል ሳስተምር ስሰብክ በስሜ
አንዲት መጻጉ ፩፮ አመት ደም የፈሰሳት
በጄ ዳስሼ እንድፈውሳት
መባ ጸሎቷ እውን እንዲሆን
እስቲ ትጠየቅ
ይሄን መፈጸም ቅጥፈት እንደሆን

2.ከሳሽ

መቼም ታቃለህ የልብ የሆዴን
ኖረህ ቃኝተሀል የዕድሜ መንገዴን
ለታመመ ሰው
በሰአት ስቅታ ደም ለሚፈሰው
ልጅነት ሳቁን በህመም በጣር ለተነጠቀ
ሄዋን ገላውን ፍቅር ተገፍቶ እንደወደቀ
በጭቃው ሰርቶ ምኞት ሀሳቡን
ትንፋሽ ስትነሳው የህይወት ቀለቡን
ሸንጎ ብሰይም ከቶ አትገረም
አረፈድክ እንጂ ቀረ አልተባለም


3.ዳኛ

ግራና ቀኙን እንዳደመጥነው
ጥፋተኛ ነው ብለን የወሰነው
ጌታን አይደለም
ሞልታ አትሞላም አንዲ ናት አለም
ስለዚህ ጌታን ወደዙፋኑ አሰናብተናል
ያንቺንም ሀዘን ሰምተን አዝነናል

4.????

ግን ምን ይደረግ
አማኞች ፈራጅ በሆኗት አለም
አሜን ነው እንጂ ለምን! ቃል የለም

@getem
@getem
@getem
👍4515🔥3
**የአብስራ ሳሙኤል**

**የማርያም መንገድ ስጪኝ** 
ደክሚያለው አንቺው አውጪኝ! 
የማርፍ የምሸሸግበት 
ትንሽ ቦታ ትንሽ ህይወት 
የስቃይ አውዱን ማለፊያ 
የጊዜን መልህቅ መቅዘፊያ 
**የማርያም መንገድ አበጂ** 
የእድሜዬን ስንዝሯን ሂጂ 
ኩሬ ነው ያልኩት ባህር ካከለ 
ወዳጅ ነው ያልኩት ጦሩን ከሳለ 
በምን ልታገል አቅም አነሰኝ 
ያመንኩት ገላ ፍም ካንተራሰኝ 
ካልሞላ ጽዋው የዘር እዳዬ 
ወድቆ አፈር ይሁን በምን ተዳዬ 
በምን ልጋፋው በምን ልታገል 
መንገድሽን ስጪኝ እንድገላገል 
ደካማ ጎኔን ልመሽግበት 
ክፉ ቀናቴን ልሸሸግበት 
አላውቅም ልበል የለሁም ልበል 
አልችልም በቃኝ አቃተኝ ልበል 
ወደ ማረፊያው ምሪኝ 
ትግል ከሌለበት ጥሪኝ 
የአበባ ገላ ከማይረግፍበት 
ማላዳ ኮከብ ከማይጎልበት 
**ሁሉ ባይሞላም ከማይጎድልበት** 
**ምሪኝ ልሸሸግበት** 
**የማርያም መንገድ ስጪኝ** 
**ደክሚያለው አንቺው አውጪኝ!**


@getem
@getem
@paappii
38👍15🔥4🤩1
( ፍቅርማ .... )
===============

ፍቅር መጣ ፍቅር ጠፋ
አምና ከሳ ዛሬ ፋፋ
አንዱን ሳበ አንዱን ገፋ

ሲለው ሞላ ከዚያ አነሰ
አንዴ ጋለ አንዴ ጨሰ
እያለ ሰው ስንት ዘመን ተዋቀሰ
ግና እውነት ከከፍታው ማን ደረሰ ??

ፍቅርማ ....
ያኔ እንደገፋነው ተቸግሮ ሳለ
በእሾሀችን ውጋት እንደቆሳሰለ
አንገት እንደደፋ እንዳዘነበለ
የሚያወርደው አጥቶ
ዛሬም አርብ ላይ ነው ... እንደተሰቀለ !!

By @kiyorna

@getem
@getem
@paappii
100👍18🔥10😢7
2025/07/08 17:18:18
Back to Top
HTML Embed Code: