" በረከተ-መንግስት"
( ግዮናይ ነኝ)!፧
ምስኪን ያገሬ ሰው...
ቀኑን ሲሮጥ ውሎ ሌሊት ይሸሸጋል፣
ተፈጥሮ ነውና...
በወፎች ዝማሬ አይቀርም ይነጋል።
ይኸው ደሞ ነጋ...
መስከረም ይመስል መድፉ ተተኮሰ፣
ከምንሸሽበቱ...
እየተከተለን ውጊያው ተለኮሰ።
* * * * * * * * *
ይኸውና ሞርተር...
አዲሱን ቆርቆሮ ባንድ'ዜ ቀደደ፣
እናት ታለቅሳለች...
የዘመናት ወዟ ቤቷ እየነደደ።
ሰብአዊነት ጠፋ...
እንደ ውሻ ሆነ የህዝቤ ክቡር ደም፣
ለቀብራችን እንኳን...
በነጋሢ ቄሳር ለቅሶ አልተፈቀደም።
* * * * * * * * *
እርሻ የሄደ ሰው...
ቀንበር ተሸክሞ በወጣበት ሲቀር፣
ምን እናደርጋለን...
ለላይኛው ጌታ ከማዳኘት በቀር።
@getem
@getem
@getem
( ግዮናይ ነኝ)!፧
ምስኪን ያገሬ ሰው...
ቀኑን ሲሮጥ ውሎ ሌሊት ይሸሸጋል፣
ተፈጥሮ ነውና...
በወፎች ዝማሬ አይቀርም ይነጋል።
ይኸው ደሞ ነጋ...
መስከረም ይመስል መድፉ ተተኮሰ፣
ከምንሸሽበቱ...
እየተከተለን ውጊያው ተለኮሰ።
* * * * * * * * *
ይኸውና ሞርተር...
አዲሱን ቆርቆሮ ባንድ'ዜ ቀደደ፣
እናት ታለቅሳለች...
የዘመናት ወዟ ቤቷ እየነደደ።
ሰብአዊነት ጠፋ...
እንደ ውሻ ሆነ የህዝቤ ክቡር ደም፣
ለቀብራችን እንኳን...
በነጋሢ ቄሳር ለቅሶ አልተፈቀደም።
* * * * * * * * *
እርሻ የሄደ ሰው...
ቀንበር ተሸክሞ በወጣበት ሲቀር፣
ምን እናደርጋለን...
ለላይኛው ጌታ ከማዳኘት በቀር።
@getem
@getem
@getem