Telegram Web Link
እንዴት ነሽ  ስላት
ሳቅ ታበዛለች
ትጫወታለች ፤

< አለሁ ! > 
ትላለች - እንደሞላላት
ቁስሏን የማላውቅ እዬመሰላት ፤

የዐይኗ መደፍረስ
የገጿ ሽክረት
የአንጀቷ ማረር
የልቧ ቁስለት

ጥልቅ ስቃይዋን እዬነገረኝ ፤
እርሷ ግን ሁሌም አንድ የምትለኝ ፤

- - - - - - - - -  አለሁ ደህና ነኝ !

ልዩ ፍጥረት ናት
አይደረሱባትም ፤

ስሟ ሕይወት ነው
ካልተሸከሟት አይረዷትም ፤

በሕመሟ መሳቅ
በቁስሏ ማጌጥ
ታውቅበታለች ፤

ልክ እንደ መሬት
ውኃ'ን ከእሳት ጋር ታቻችላለች ፤

ከራስ ቅራኔ
ከራስ ጋር ሙግት ቢኖርባትም ፤
ከመሳቅ በቀር
በሰው ፊት ማልቀስ አይኾንላትም  ፤

ደህና ነኝ ከሚል
ከአንድ ቃል በቀር ——
  ሌላ አይወጣትም ፤

እወድዳታለሁ ፤

ደህና ነኝ ስትል
ደህና እንዳልሆነች አውቅባታለሁ።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
28😢7🔥3🤩1
2025/07/09 04:20:03
Back to Top
HTML Embed Code: