•
የመንገዴ ፍጻሜ ነሽ
ከአድማስ የአድማስ መጨረሻ
የሀሰሳዬ ፍጻሜ የጉዞዬ መዳረሻ
✻‧
ባለፈው ወይኔ ጎድሎ
እቸረው (እሰጠው) ቢያጥረኝ
ማርያምን መስለሻት መጣሽ
በምልጃሽ ምልአትን ቸረኝ
"አይሆንም" ያልኩት ሆነልኝ
አያልፍም ያልኩት አለፈ
"ከበደኝ ታከተኝ" ያልኩት በፍቅርሽ እየታቀፈ ።
✻‧
ነውሬን አንቺው ሸፈንሽው
ጋረድሽው የሀፍረት ታሪኬን
የህይወት ማይ እየሆንሽኝ
አነጻው እድፋም መልኬን
ወደድኩሽ እስከ ጥ • ግ • ጥ • ጉ
ለፍቅርሽ ነፍሴን አስገዛሁ
አንድ ሆኜ መኖር ያቃተኝ
ዕልፍ ሆኜ በፍቅርሽ በ • ዛ • ሁ ።
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
የመንገዴ ፍጻሜ ነሽ
ከአድማስ የአድማስ መጨረሻ
የሀሰሳዬ ፍጻሜ የጉዞዬ መዳረሻ
✻‧
ባለፈው ወይኔ ጎድሎ
እቸረው (እሰጠው) ቢያጥረኝ
ማርያምን መስለሻት መጣሽ
በምልጃሽ ምልአትን ቸረኝ
"አይሆንም" ያልኩት ሆነልኝ
አያልፍም ያልኩት አለፈ
"ከበደኝ ታከተኝ" ያልኩት በፍቅርሽ እየታቀፈ ።
✻‧
ነውሬን አንቺው ሸፈንሽው
ጋረድሽው የሀፍረት ታሪኬን
የህይወት ማይ እየሆንሽኝ
አነጻው እድፋም መልኬን
ወደድኩሽ እስከ ጥ • ግ • ጥ • ጉ
ለፍቅርሽ ነፍሴን አስገዛሁ
አንድ ሆኜ መኖር ያቃተኝ
ዕልፍ ሆኜ በፍቅርሽ በ • ዛ • ሁ ።
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
❤24👍3
ያላንቺ ይቅርብኝ!
(የሞገሴ ልጅ)
ዐየሽ የኔ ናፍቆት-
ካንቺ በፊት እኔ - ኖሬአለሁ ለናቴ፣
ቆንጥጣ አባራኝ - በሚናፈቅ ቤቴ።
ያኔ ግን - ልጅነት-
ከጎኔ ስትለይ - ናፍቆት ቢቀጣኝም፣
አቅፋኝ እየተኛች፣
በናፍቆቷ መራብ - - ጭራሽ አያውቀኝም።
ጭራሽ አደግ ስል...
እሷን መውደድ ሳልተው - አንቺን በልብ ይዤ፣
አጠገቤ ሆነሽ፣
ናፍቆትሽን ፃፍኩት - ማግኘቴን ሰርዤ።
እንደው ግን የምልሽ?
እለት እለት ጾሜ፣
ያለኝን መፅውቼ፣
ከገነት ለመግባት - የምጠባበቀው፣
ካንቺ ጋራ ስሆን፣
ከሚሰማኝ ምቾት - እንዴት ነው ሚልቀው?
እንጃ ያሳስባል-
ካንቺ በላይ ናፍቆት የሚያስይዝ ቢመጣ፣
ከሆነ ነው እንጂ፣
አንችው ሰማይ ሆነሽ - ልቤ በልብሽ ላይ ገነት ተቀምጣ።
በዛ አትበይ እንጂ...
ካንቺ ተለይቶ - መኖር የሳት ባሕር፣
ካንቺጋራ ሆኖ - ሲኦል መግባት ክብር፣
ከነ’ንትንሽ መሳም - የዘላለም እረፍት፣
ማፍቀርሽን መግፋት - ኦሜጋ ስህተት፣
አንችን አለማሰብ - የድርቀትም አያት፣
ፈልጎሽ መኳተን - የክብር ኁሉ አናት፤
ይመስለኛል እኔ.....
ለገነት ለሲኦል - አንቺ ነሽ ሚዛኔ፣
ጨርሼ መጽደቄ - ወይም መኮነኔ፣
ፈዋሿ መስቀሌም - ገዳዩዋ መብረቄ፣
የሰማዩን እማ.........አልተወለድኩኝም በፅንፀት አውቄ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
(የሞገሴ ልጅ)
ዐየሽ የኔ ናፍቆት-
ካንቺ በፊት እኔ - ኖሬአለሁ ለናቴ፣
ቆንጥጣ አባራኝ - በሚናፈቅ ቤቴ።
ያኔ ግን - ልጅነት-
ከጎኔ ስትለይ - ናፍቆት ቢቀጣኝም፣
አቅፋኝ እየተኛች፣
በናፍቆቷ መራብ - - ጭራሽ አያውቀኝም።
ጭራሽ አደግ ስል...
እሷን መውደድ ሳልተው - አንቺን በልብ ይዤ፣
አጠገቤ ሆነሽ፣
ናፍቆትሽን ፃፍኩት - ማግኘቴን ሰርዤ።
እንደው ግን የምልሽ?
እለት እለት ጾሜ፣
ያለኝን መፅውቼ፣
ከገነት ለመግባት - የምጠባበቀው፣
ካንቺ ጋራ ስሆን፣
ከሚሰማኝ ምቾት - እንዴት ነው ሚልቀው?
እንጃ ያሳስባል-
ካንቺ በላይ ናፍቆት የሚያስይዝ ቢመጣ፣
ከሆነ ነው እንጂ፣
አንችው ሰማይ ሆነሽ - ልቤ በልብሽ ላይ ገነት ተቀምጣ።
በዛ አትበይ እንጂ...
ካንቺ ተለይቶ - መኖር የሳት ባሕር፣
ካንቺጋራ ሆኖ - ሲኦል መግባት ክብር፣
ከነ’ንትንሽ መሳም - የዘላለም እረፍት፣
ማፍቀርሽን መግፋት - ኦሜጋ ስህተት፣
አንችን አለማሰብ - የድርቀትም አያት፣
ፈልጎሽ መኳተን - የክብር ኁሉ አናት፤
ይመስለኛል እኔ.....
ለገነት ለሲኦል - አንቺ ነሽ ሚዛኔ፣
ጨርሼ መጽደቄ - ወይም መኮነኔ፣
ፈዋሿ መስቀሌም - ገዳዩዋ መብረቄ፣
የሰማዩን እማ.........አልተወለድኩኝም በፅንፀት አውቄ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤14🔥4👎1
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
የሚመሩን ሁሉ መምሪያ ሰነዳቸው
ምን ቢሆን አንድነት
በሬሳ አካላች ቄጤማ ነስንሰው ሰሩልን ሰገነት
ሰብከውን በኪዳን
ሰብከው በመንግስቱ
ተደመርን ብለው ምን ቢያጎበድዱ
የጀርባ ላይ እከክ ሆኑ አንዱ ጎሳ ላንዱ
በመስኮት በመስኩ ምንስ አሸብርቀው ፍቅር ፍቅር ቢሉ
እያቸው አለሜ
ጩቤ ተጨባብጠው ሰላም ሲባባሉ
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አዲስ ኪዳን ቢፈለሰፍ
አዲስ መንግስት ቢዋቀርም
ዱር ጫካ ገብቼ ሳላይሽ አልቀርም
የፈለገ ቢሆን ሰላም ለአደባባይ ለመንደሩ
ለሀገርህ ዝመት ብለው ገበሬን ነው ሚገብሩ
ሰርክ አራሽ መሬቱን
ሰርክ ቀዳሽ ታቦቱን
ነፍጠኛ ተኳሹን
ሀገር ሲሉት የሚነሳን
ወገን ሲሉት አለሁ የሚል
ምን ቢጨቆን አፉን ይዞ ትቅደም ባለ አንድ ሀገሩን
ሜዳ ላይ አጠፉት
ኪዳን ፍቅሩን ጥለው ሰበሩት ማገሩን
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አለሜ
አይንሽን ባላይም ቃልኪዳን አልፈታም
ሁሌ እወድሻለሁ
ሚያገናኘን መንግስት እስኪመጣ ድረስ
እናውርድ እላለሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
የሚመሩን ሁሉ መምሪያ ሰነዳቸው
ምን ቢሆን አንድነት
በሬሳ አካላች ቄጤማ ነስንሰው ሰሩልን ሰገነት
ሰብከውን በኪዳን
ሰብከው በመንግስቱ
ተደመርን ብለው ምን ቢያጎበድዱ
የጀርባ ላይ እከክ ሆኑ አንዱ ጎሳ ላንዱ
በመስኮት በመስኩ ምንስ አሸብርቀው ፍቅር ፍቅር ቢሉ
እያቸው አለሜ
ጩቤ ተጨባብጠው ሰላም ሲባባሉ
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አዲስ ኪዳን ቢፈለሰፍ
አዲስ መንግስት ቢዋቀርም
ዱር ጫካ ገብቼ ሳላይሽ አልቀርም
የፈለገ ቢሆን ሰላም ለአደባባይ ለመንደሩ
ለሀገርህ ዝመት ብለው ገበሬን ነው ሚገብሩ
ሰርክ አራሽ መሬቱን
ሰርክ ቀዳሽ ታቦቱን
ነፍጠኛ ተኳሹን
ሀገር ሲሉት የሚነሳን
ወገን ሲሉት አለሁ የሚል
ምን ቢጨቆን አፉን ይዞ ትቅደም ባለ አንድ ሀገሩን
ሜዳ ላይ አጠፉት
ኪዳን ፍቅሩን ጥለው ሰበሩት ማገሩን
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አለሜ
አይንሽን ባላይም ቃልኪዳን አልፈታም
ሁሌ እወድሻለሁ
ሚያገናኘን መንግስት እስኪመጣ ድረስ
እናውርድ እላለሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
❤19🔥4
መሔጃ የለኝ !
ካይኖችሽ ብሸሽ ፥ ቅንድብሽ ስር ነኝ ።
ወዴትም ብዞር
ገላሽ ብቻ ነው ፥ የሚያዋስነኝ ።
ቅርቤም - ሩቄ
ኩነኔም - ጽድቄ
ከህጎች በልጦ ፥ ልብሽ የሚያዘኝ
አይንሽ ብቻውን ፥ የሚያናዝዘኝ
ያንቺው ታሳሪ ፥ ግዞተኛሽ ነኝ ።
ካንቺው ቀምቼ ፥ ላንቺ ምሰጥሽ
ከገዛ ራስሽ ፥ የማስበልጥሽ
ምንም ቢሰማኝ ፥ የማላመልጥሽ
ወስልቼ ብሄድ ፥ ከገላሽ ምሕዋር
ተኝቼ ምገኝ ፥ ከትዝታሽ ጋር
ወዲህም ሳራ ፥ ወዲህም አጋር !
ካንቺ ጋር መሮኝ
ሌላ ሴት አምሮኝ
ጥዬሽ ለመሄድ ፥ አስር ብወራጭ
አንቺን ነው ማገኝ ፥ ልክ እንደ አማራጭ ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
ካይኖችሽ ብሸሽ ፥ ቅንድብሽ ስር ነኝ ።
ወዴትም ብዞር
ገላሽ ብቻ ነው ፥ የሚያዋስነኝ ።
ቅርቤም - ሩቄ
ኩነኔም - ጽድቄ
ከህጎች በልጦ ፥ ልብሽ የሚያዘኝ
አይንሽ ብቻውን ፥ የሚያናዝዘኝ
ያንቺው ታሳሪ ፥ ግዞተኛሽ ነኝ ።
ካንቺው ቀምቼ ፥ ላንቺ ምሰጥሽ
ከገዛ ራስሽ ፥ የማስበልጥሽ
ምንም ቢሰማኝ ፥ የማላመልጥሽ
ወስልቼ ብሄድ ፥ ከገላሽ ምሕዋር
ተኝቼ ምገኝ ፥ ከትዝታሽ ጋር
ወዲህም ሳራ ፥ ወዲህም አጋር !
ካንቺ ጋር መሮኝ
ሌላ ሴት አምሮኝ
ጥዬሽ ለመሄድ ፥ አስር ብወራጭ
አንቺን ነው ማገኝ ፥ ልክ እንደ አማራጭ ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
❤14
ያልወረደ እንባ
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....
በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤
መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤
በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤
አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....
በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤
መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤
በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤
አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
👍25❤18🔥8🤩1