( እልፍ ሰላም )
============
ሲፈለግ የማይታጣ
ሲታሰብ የማይዘገይ
ታይቶ የማይሰወር
ሰጥቶ የማይታበይ
ማግኘት ማጣት ማይለውጠው
መሄድ መምጣት ማይቀይረው
በቅንጣት ጽድቅ ሚያሞጋግስ
ግዙፍ በደል የማይቆጥረው
ባዶነትን ማያናንቅ
መገፋትን ማይሰቀቅ
እርሱ ብቻ ተነጥሎ
ሁል ጊዜ የሚናፈቅ
የጎደፈን ማይጠየፍ
የሸሸውን ማይጥል ማይተው
ከወደደ እስከ ህይወት ጥግ
ይቅር ማለት ማይታክተው
መለያየት በሌለበት
በሱ ግዛት በሱ ዓለም
እልፍ ሰላም ካልሆን በቀር
ሞት ጥላቻ ክህደት የለም !!
By @kiyornad
@getem
@getem
@paappii
============
ሲፈለግ የማይታጣ
ሲታሰብ የማይዘገይ
ታይቶ የማይሰወር
ሰጥቶ የማይታበይ
ማግኘት ማጣት ማይለውጠው
መሄድ መምጣት ማይቀይረው
በቅንጣት ጽድቅ ሚያሞጋግስ
ግዙፍ በደል የማይቆጥረው
ባዶነትን ማያናንቅ
መገፋትን ማይሰቀቅ
እርሱ ብቻ ተነጥሎ
ሁል ጊዜ የሚናፈቅ
የጎደፈን ማይጠየፍ
የሸሸውን ማይጥል ማይተው
ከወደደ እስከ ህይወት ጥግ
ይቅር ማለት ማይታክተው
መለያየት በሌለበት
በሱ ግዛት በሱ ዓለም
እልፍ ሰላም ካልሆን በቀር
ሞት ጥላቻ ክህደት የለም !!
By @kiyornad
@getem
@getem
@paappii
❤20🔥2🤩2