ለምን ትመጫለሽ?
ወና መሆን ለምዷል
ባይተዋር ነው ሆዴ
ትራስ አቅፎ ማደር
ለምዶበታል ክንዴ።
ገላዬ ቀዝቅዟል
ልቤ ተሰቅዟል
እንስት ላለማመን
ዜሮ ነኝ ስተመን
ብትመጭም ከንቱ ነው
መመለስሽ ምንም
ስታወሪ አልስቅም
በእንባሽ አልቆዝምም
በድን ነኝ አልድንም ።
ለምን ትመጫለሽ?
የለሁም በድሮ
ሌላ ነኝ ዘንድሮ
ግዴ አይደለም ነገ
አትገርመኝም ጀንበር
ብራና ክረምቱ …
ቢዛወር ዓመቱ
ጨፍሬ አልደክርም
አልመታም አታሞ
ዓመት አንድ ቀን ነው
ለከሸፈ ታሞ ።
ለምን ትመጫለሽ ?
መምጣትሽ እንደ ቧልት
መመለስሽ ምንም ...
፡
ይህንን እያልኩኝ
ብናገር ብገጥምም
ስትመጪ ስዳበስ
በጣት በመዳፍሽ
ያልኩትን ዘንግቼ
አዲስ ሰው ሆንኩልሽ።
አትሄጂም አይደለ ?🙄
By (ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@paappii
ወና መሆን ለምዷል
ባይተዋር ነው ሆዴ
ትራስ አቅፎ ማደር
ለምዶበታል ክንዴ።
ገላዬ ቀዝቅዟል
ልቤ ተሰቅዟል
እንስት ላለማመን
ዜሮ ነኝ ስተመን
ብትመጭም ከንቱ ነው
መመለስሽ ምንም
ስታወሪ አልስቅም
በእንባሽ አልቆዝምም
በድን ነኝ አልድንም ።
ለምን ትመጫለሽ?
የለሁም በድሮ
ሌላ ነኝ ዘንድሮ
ግዴ አይደለም ነገ
አትገርመኝም ጀንበር
ብራና ክረምቱ …
ቢዛወር ዓመቱ
ጨፍሬ አልደክርም
አልመታም አታሞ
ዓመት አንድ ቀን ነው
ለከሸፈ ታሞ ።
ለምን ትመጫለሽ ?
መምጣትሽ እንደ ቧልት
መመለስሽ ምንም ...
፡
ይህንን እያልኩኝ
ብናገር ብገጥምም
ስትመጪ ስዳበስ
በጣት በመዳፍሽ
ያልኩትን ዘንግቼ
አዲስ ሰው ሆንኩልሽ።
አትሄጂም አይደለ ?🙄
By (ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@paappii
❤28😁5👍4🔥2🤩1
