ሚዛኑ ቢያደላ፤ ጊዜ ሆኖ ዳኛ
ቋንቋ ቀለም ሆነ፤ የሰው መመዘኛ።
ትገል እደው ግደል፤ ታድን እንደው አድን
ጠባሳ አይዝም፤ መርቅዞ የሚድን።
ብዬ ባዜምበት ....
ይፈትለው ጀመረ ቃል አጠቃቀሜን
ምንሽር አንስቼ ላላሳየው አቅሜን
ማንስ ገሎ ዳነ ማን ሞቶ ተረሳ ?
ፍጻሜው ሰይፍ ነው፤ ሰይፍ ለሚያነሳ።
***
ስለዚህ፤ ትርጉሙን
"ሀገር" ማለት ብባል?
"ሀገር" ማለት "ሰው ነው" አልልም ደፍሬ።
ሀገር የሚሆን ሰው፤ አታለች ሀገሬ።
By @YabisraSamuel
@getem
@getem
@paappii
❤70🔥16👍7😢2
እኔ እና ገጣሚው
(Desu Fikriel)
ዛሬም ባይገባኝም - እንዴት እንዳመንኩሽ - እንዴት እንዳሳትሽኝ
"ፍቅር ይኑር እንጅ ገንዘብ ምን ያደርጋል" ብለሽ አሳመንሽኝ።
ካመንኩሽ በኋላ...
በቅጡ ሳንኖር ሳምንት ሳይሞላ
"ዋናው ገንዘቡ ነው ፍቅር አይበላ"
ብለሽ ክደሽኛል
ፍቅር ባያውረኝ - እንኳን ለኔ ቀርቶ - ለልጅ አይሳትም
የዘመን ሀቅ ነው - ፍቅር 'በድሀ ደንብ' - አይመሰረትም
ከካድሽኝ በኋላ
ሱራፌል መልአኩን - ከ'ሳት ሰይፉ ጋራ - ልቤ ዳር አቁሜ
ሴት ውስጤ ላትገባ - ዳግም ላላፈቅር - ማልኩኝ ደጋግሜ
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
በርግጥ አታነቢም (ምናልባት ከሰማሽ)
አንድ ባለቅኔ
ፍቅረኛውን ቀጥሮ - ትንሽ በማርፈዷ - ብዙ የበሸቀ
ምድሩ አልበቃ ብሎት ከጨረቃዋ ጋር በእልህ ተናነቀ
ፍቅረኛውን መክራ ያስቀረች ይመስል ዓለምን ጠልቷታል
የሚቀኝላትን
የሚሳሳላትን ጨረቃዋን እንኳ 'እናቷን' ብሏታል
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
ይሄን ባለቅኔ
ያረፈደችው ሴት (አንቺ እንዳደረግሽው) ከድታው ቢሆን ኖሮ
ከፈጣሪው ጋራ መሟገቱ አይቀርም ፍጡሩን ተሻግሮ
እያልኩ አስባለሁ
ህመም በወለደው አስታማሚ ቅኔ ቁስሌን አሻሻለሁ
የሚገርምሽ ነገር
ግጥም ልፅፍ ነበር
'ያማል' የሚል ርዕስ ከዚህ ሰው አንስቼ
ግን አስቢው እስኪ የእሱ ሴት አርፍዳ እኔ ተከድቼ
አንድ አይነት ስንቀኝ
ሳስበው ራሱ ብቻየን ቁጭ ብዬ እንደ ጅል አሳቀኝ
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
@getem
@getem
@paappii
(Desu Fikriel)
ዛሬም ባይገባኝም - እንዴት እንዳመንኩሽ - እንዴት እንዳሳትሽኝ
"ፍቅር ይኑር እንጅ ገንዘብ ምን ያደርጋል" ብለሽ አሳመንሽኝ።
ካመንኩሽ በኋላ...
በቅጡ ሳንኖር ሳምንት ሳይሞላ
"ዋናው ገንዘቡ ነው ፍቅር አይበላ"
ብለሽ ክደሽኛል
ፍቅር ባያውረኝ - እንኳን ለኔ ቀርቶ - ለልጅ አይሳትም
የዘመን ሀቅ ነው - ፍቅር 'በድሀ ደንብ' - አይመሰረትም
ከካድሽኝ በኋላ
ሱራፌል መልአኩን - ከ'ሳት ሰይፉ ጋራ - ልቤ ዳር አቁሜ
ሴት ውስጤ ላትገባ - ዳግም ላላፈቅር - ማልኩኝ ደጋግሜ
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
በርግጥ አታነቢም (ምናልባት ከሰማሽ)
አንድ ባለቅኔ
ፍቅረኛውን ቀጥሮ - ትንሽ በማርፈዷ - ብዙ የበሸቀ
ምድሩ አልበቃ ብሎት ከጨረቃዋ ጋር በእልህ ተናነቀ
ፍቅረኛውን መክራ ያስቀረች ይመስል ዓለምን ጠልቷታል
የሚቀኝላትን
የሚሳሳላትን ጨረቃዋን እንኳ 'እናቷን' ብሏታል
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
ይሄን ባለቅኔ
ያረፈደችው ሴት (አንቺ እንዳደረግሽው) ከድታው ቢሆን ኖሮ
ከፈጣሪው ጋራ መሟገቱ አይቀርም ፍጡሩን ተሻግሮ
እያልኩ አስባለሁ
ህመም በወለደው አስታማሚ ቅኔ ቁስሌን አሻሻለሁ
የሚገርምሽ ነገር
ግጥም ልፅፍ ነበር
'ያማል' የሚል ርዕስ ከዚህ ሰው አንስቼ
ግን አስቢው እስኪ የእሱ ሴት አርፍዳ እኔ ተከድቼ
አንድ አይነት ስንቀኝ
ሳስበው ራሱ ብቻየን ቁጭ ብዬ እንደ ጅል አሳቀኝ
የምልሽ ገብቶሻል?
ለነገሩ ተይው
ቢገባሽም እንኳን - ገብቶኛል አትይም - መካድ ለምዶብሻል
@getem
@getem
@paappii
❤87🔥21👍8😱5
የምርቃና_ግፉ
(በረከት በላይነህ)
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ" ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ፃፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው፣
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ ፣ እኩል አልቃሙማ።
@getem
@getem
@paappii
(በረከት በላይነህ)
የሙዚቃ ሊቁ፣
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ
ጠባቧ "ስቲዲዮ" ጫት ሞልቷት ነበረ።
ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ
ሊቅም ቁርሱን በላ።
ሹማምንቶቻችን ፣
ገንቢ አፍራሾቻችን ፣
ዕቅዱን ሲጽፉ ፣
በትዕዛዝ ያደገ አወደይ ቀጠፉ።
ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ፣
ደብዳቤ ፃፈልሽ ከገረባ መሃል
ምርቅን ቃላት ለቅሞ።
እናስ!
መሪ ከተከታይ፣
ፍትህ ከተበዳይ፣
ጥበብ ከአድናቂው፣
መላሽ ከጠያቂው፣
የነቃ ከእውኑ
የተኛ ከሕመሙ
ውበት ከቀለሙ
እኮ በምን ስሌት? እንደምን ይስማማ?
ሰጪና ተቀባይ ፣ እኩል አልቃሙማ።
@getem
@getem
@paappii
❤45😁27🔥5👍4🤩2
አንተ ማለት እኮ......
.
.
የአይኖችህ ማማር፤
ዉስጥ የሚሰረስር፤
የጥርሶችህ ፀዳል ልብ የሚሰነጥቅ፤
ፈገግታህ ሚወደድ መንፈስን የሚሰርቅ፤
አንተ ማለት እኮ......
የሹማምንት አብራክ የመኳንንት ዘር፤
ነቅዕ ያልተገኘብህ የዉቦች ሀሉ ዳር፤
ልቡ 'ሚደነግጥ ያየ የሚመኝህ፤
በነጋ በጠባ ሁሉ የሚያልምህ፤
አንተ ማለት እኮ........
በፈራሽ ዉበትህ ሠርክ የምትመካ፤
በለበስከዉ አልባስ ሰዉን የምትለካ፤
ከራስህ ተጣልተህ ሰላምህን ያጣህ፤
መደሰት የራቀህ አንተ ማለት ይህ ነህ።
...............................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
የአይኖችህ ማማር፤
ዉስጥ የሚሰረስር፤
የጥርሶችህ ፀዳል ልብ የሚሰነጥቅ፤
ፈገግታህ ሚወደድ መንፈስን የሚሰርቅ፤
አንተ ማለት እኮ......
የሹማምንት አብራክ የመኳንንት ዘር፤
ነቅዕ ያልተገኘብህ የዉቦች ሀሉ ዳር፤
ልቡ 'ሚደነግጥ ያየ የሚመኝህ፤
በነጋ በጠባ ሁሉ የሚያልምህ፤
አንተ ማለት እኮ........
በፈራሽ ዉበትህ ሠርክ የምትመካ፤
በለበስከዉ አልባስ ሰዉን የምትለካ፤
ከራስህ ተጣልተህ ሰላምህን ያጣህ፤
መደሰት የራቀህ አንተ ማለት ይህ ነህ።
...............................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤43👍5🔥5
ይህ ቀዥቃዣ ዝናብ - ገላሽን ይንካና
ወዮለት ሰማዩ - ወዮለት ደመና !
ወፍ አይዘምርልሽ - ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ !
ደግሞ ይሄን እወቂ !
ሆዴ እንደሚበላኝ ፥ ካለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ ፥ በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር ፥ በእግዜር ስትመኪ !
እኔ ነኝ ጠባቂሽ !
እኔ ደስታሽ !
እኔ ፈገግታሽ !
ሁሉንም የምሆን ... !
እግዜር ፥ አላህ ፥ ሰማይ
ንፋስ ፥ ውሃ ፥ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ !
ያንቺ ብቻ ታጋይ !
"ክነፍ !" በዪኝ - ልክነፍ
"እረፍ !" በዪኝ - ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ ፥ በእኔ በኩል ይለፍ !!!
by Habtamu hadera
@getem
@getem
@paappii
ወዮለት ሰማዩ - ወዮለት ደመና !
ወፍ አይዘምርልሽ - ዛፍ አያስጠልልሽ
በቃ እኔ አለሁልሽ !
ደግሞ ይሄን እወቂ !
ሆዴ እንደሚበላኝ ፥ ካለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ ፥ በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር ፥ በእግዜር ስትመኪ !
እኔ ነኝ ጠባቂሽ !
እኔ ደስታሽ !
እኔ ፈገግታሽ !
ሁሉንም የምሆን ... !
እግዜር ፥ አላህ ፥ ሰማይ
ንፋስ ፥ ውሃ ፥ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ !
ያንቺ ብቻ ታጋይ !
"ክነፍ !" በዪኝ - ልክነፍ
"እረፍ !" በዪኝ - ልረፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ ፥ በእኔ በኩል ይለፍ !!!
by Habtamu hadera
@getem
@getem
@paappii
❤70👎13🤩12👍10😁8🔥5😱5🎉2
ጥያቄ??
አሁን በእኛ ዘመን ፍቅር የምንለዉ፤
በቅዱስ መፅሐፍ ሠርክ የምናነበዉ፤
ካፋችን ማይጠፋ ቀን በቀን ምንጠራዉ፤
ፍቺዉ የጠፋብን ፍቅር ግን ምንድነዉ??
..................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
አሁን በእኛ ዘመን ፍቅር የምንለዉ፤
በቅዱስ መፅሐፍ ሠርክ የምናነበዉ፤
ካፋችን ማይጠፋ ቀን በቀን ምንጠራዉ፤
ፍቺዉ የጠፋብን ፍቅር ግን ምንድነዉ??
..................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤44👍7🔥4👎3😁1
መንገደኛው ልቤ ቅጽበት'ዓት ከአንቺ ያደረ
መሄድ አመል ሆኖበት ደሞ ሌላ አፈቀረ
ደሞ ከሌላ አደረ አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ
‧˚‧༘
ቀን ያሻገረኝ ዛጎሌን ጥዬ
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ብዬ
ነፍሴን ላጽናናት ወይ ልደልላት
ናፍቆት ትዝታው ይበቃል ስላት
༄
ተቀበለቺኝ
❛❛ይሁና አለቺኝ❜❜
በል ሂድ እንግዲ...
⸻
#ከአዲስ መስክ ላይ
ልዬ የሆነ ብስራት አይጠፋም
ከንፎ መሰበር ሮጦ መውደቅ
ህልምን ከመስበር ፍጹም አይከፋም
✨
ደሞ ወደ አዲስ ጠረን
ደሞ ወደ አዲስ ገላ
ይሁን ብላ ህይወት ስታባብለኝ
⸻•⸻
ይኀው ደሞ ትዝ አለኝ
ተሳሰረብኝ እግሬ
በአንቺም ጊዜ አኮብኩቧል
ክንፎቹን ልክ እንደ ዛሬ
💧
ትዝ አለሽ ያኔ?
በሀዘን በእንባ የተማጸንኩሽ
የበደሌ ስር ቅሉ ሳይገባኝ
ይቅርታ ያልኩሽ
🕯
ገፍተሽ መሄድሽ
ብቻዬን ስሆን ዛሬም ያመኛል
አንዴ የቆሰለ ማደሪያስ
ቢያገኝ መች አምኖ ይተኛል?
✨
ግና ፍቅሬ...
ቢሆንም ባይሆንም
ክንፋም ህልሞች እንጂ
ጨለማ አልለምንም
ትሏ ህይወቴ
በጀንበር ብስራት ክንፍ ያበቀለ
☾
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ያለ
ደሞ ሌላ አፈቀረ
አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ
𓇢
አንድ አይኑን ለመንገድ ገልጦ
ከሌላ ልቡ ውስጥ አደረ...
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
መሄድ አመል ሆኖበት ደሞ ሌላ አፈቀረ
ደሞ ከሌላ አደረ አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ
‧˚‧༘
ቀን ያሻገረኝ ዛጎሌን ጥዬ
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ብዬ
ነፍሴን ላጽናናት ወይ ልደልላት
ናፍቆት ትዝታው ይበቃል ስላት
༄
ተቀበለቺኝ
❛❛ይሁና አለቺኝ❜❜
በል ሂድ እንግዲ...
⸻
#ከአዲስ መስክ ላይ
ልዬ የሆነ ብስራት አይጠፋም
ከንፎ መሰበር ሮጦ መውደቅ
ህልምን ከመስበር ፍጹም አይከፋም
✨
ደሞ ወደ አዲስ ጠረን
ደሞ ወደ አዲስ ገላ
ይሁን ብላ ህይወት ስታባብለኝ
⸻•⸻
ይኀው ደሞ ትዝ አለኝ
ተሳሰረብኝ እግሬ
በአንቺም ጊዜ አኮብኩቧል
ክንፎቹን ልክ እንደ ዛሬ
💧
ትዝ አለሽ ያኔ?
በሀዘን በእንባ የተማጸንኩሽ
የበደሌ ስር ቅሉ ሳይገባኝ
ይቅርታ ያልኩሽ
🕯
ገፍተሽ መሄድሽ
ብቻዬን ስሆን ዛሬም ያመኛል
አንዴ የቆሰለ ማደሪያስ
ቢያገኝ መች አምኖ ይተኛል?
✨
ግና ፍቅሬ...
ቢሆንም ባይሆንም
ክንፋም ህልሞች እንጂ
ጨለማ አልለምንም
ትሏ ህይወቴ
በጀንበር ብስራት ክንፍ ያበቀለ
☾
ሁሉም እንዳንቺ አይደለም ያለ
ደሞ ሌላ አፈቀረ
አዲስ ምዕራፍ ተጀመረ
𓇢
አንድ አይኑን ለመንገድ ገልጦ
ከሌላ ልቡ ውስጥ አደረ...
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
❤24👍15😱2
(በዕምዓዕላፍ)
ወደ ውስጥ ፈሶ
ወደ ውስጥ አልቅሶ
መሬት ሳትረሰርስ
እምባውን ጨርሶ
ይሆናል እያልኩኝ በመላምት ተስፋ
ምኞት ላያፀናኝ ነፍሴ ተቀስፋ
የልቤ መናወዝ
የኔ መንጠራወዝ
ስለ አንቺ ነበረ
ፍቅርሽ መስቀል ሆኖ የተቸነከረ
በጠባብ ማነቆ ቀንበር ተሸክሜ
የፍቅርን መቀነት በተስፋ አገልድሜ
ከእድሜ
ቀድሜ
እንሆ አሰስኩሽ.......
ለዘመናት ባጀሁ
አመታትን ፈጀሁ
አንጋጥጬ እያዬሁ የማይወርድ መና
ሰማዩን ከልሎት የማይዘንብ ደመና
እያዬሁ ሳላምን
እግዜርን ስለምን
እኔ ወበከንቱ
የትም ቀረሁ እቱ
@getem
@getem
@getem
ወደ ውስጥ ፈሶ
ወደ ውስጥ አልቅሶ
መሬት ሳትረሰርስ
እምባውን ጨርሶ
ይሆናል እያልኩኝ በመላምት ተስፋ
ምኞት ላያፀናኝ ነፍሴ ተቀስፋ
የልቤ መናወዝ
የኔ መንጠራወዝ
ስለ አንቺ ነበረ
ፍቅርሽ መስቀል ሆኖ የተቸነከረ
በጠባብ ማነቆ ቀንበር ተሸክሜ
የፍቅርን መቀነት በተስፋ አገልድሜ
ከእድሜ
ቀድሜ
እንሆ አሰስኩሽ.......
ለዘመናት ባጀሁ
አመታትን ፈጀሁ
አንጋጥጬ እያዬሁ የማይወርድ መና
ሰማዩን ከልሎት የማይዘንብ ደመና
እያዬሁ ሳላምን
እግዜርን ስለምን
እኔ ወበከንቱ
የትም ቀረሁ እቱ
@getem
@getem
@getem
👍38❤35🔥2😢2🎉1
የማርያም መንገድ
.
.
መንፈሴ ሲዝል ሰላሜ ጠፍቶ፤
ልቤ ሲታወክ ዉስጤ ተረትቶ፤
ቢጨንቀኝ ጊዜ........
አጥብቄ ለመንኩ የማርያም መንገድ፤
ካለሁበት ማጥ ያሻግረኝ ዘንድ።
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
.
.
መንፈሴ ሲዝል ሰላሜ ጠፍቶ፤
ልቤ ሲታወክ ዉስጤ ተረትቶ፤
ቢጨንቀኝ ጊዜ........
አጥብቄ ለመንኩ የማርያም መንገድ፤
ካለሁበት ማጥ ያሻግረኝ ዘንድ።
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
❤63🔥7👍6
ኤሊና ጥንቸል ተቀጣጠሩ
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
— አዝማሪው —
በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ
መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ
፩
አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል
አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።
ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።
ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል
አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል
#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
ማራቶን ሩጫ ሊወዳደሩ።
የውድድሩ ሲያበቃ ሩጫ
እስቲ ገምቱ የማነው ዋንጫ?
— አዝማሪው —
በብላቴና ዕድሜዬ ስለ ህይወት ሲቀኙልኝ
ኤሊም ሆኜ እንድ'ቀድም
ጥንቸሎቼን አስተኙልኝ
መኖር መልካም ቀና ጥበብ የምትሻ
አሁን ባይገባንም
ትርጉም አይታጣም በስተ'መጨረሻ
፩
አየሽ በዚህ ተረት መኖር እንዲህ ይቀኛል
ሸክም ያልከው ዛጎል ጌጥህ ነው ይለኛል
አልችልም ካልክበት
አበቃ ካልክበት
ደሞ በአዲስ ፈና መንገድህን ቀጥል
የናቁት ጠጠር ነው ግዙፉን የሚጥል
ያቅተኛል ብለህ
ይከብደኛል ብለህ
በፍጹም አትፍራ።
ነበልባል ህልምህን
በእንቅልፋም ልቧች ላይ
ጎጆ አድርገህ ስራ።
ልቦናው የበራለት ከትልም ይማራል
ባሪያ ብለው የናቁት በጊዜው ይከብራል
አትፍራ! ግድየለም!
ሰጋር እግሩን አይተህ
❛❛አልቀድመውም አትበል❜❜
የኑሮን ውርርድ ሳትታክት ተቀበል
#ህይወት ጥበበኛው
መልካም ቅኔ አያጣም
ላሸነፈው ዋንጫ
ለደከመው ደሞ እንቅልፍ አይታጣም።
የአብስራ ሳሙኤል
@getem
@getem
@getem
❤56👍11🔥3
አብሮ መጥፋት
በፍቅር ሰንሰለት እኔን ላንቺ ድሮ፣
ያለፈ ታሪክሽን
የኀጢአቴን ግርሻት ሊያጠፋ ቀን ቀጥሮ፤
"ወደ ኋላ መዞር ላ'ፍታ ሳትመኙ፣
ወደ ፊት ተጓዙ ነጋችሁን ቃኙ!
ለፍቅር ታመኑ ለፍቅር ተቀኙ!"
የሚል ትእዛዝ ሰጥቶን
ትናንትናችን ላይ እቶን እሳት ቢለቅ፣
ወላዋይ መንፈስሽ
ልክ እንደ ሎጥ ሚስት ታየ ሲፍረከረክ፡፡
የቀድሞ ፍቅረኛሽ…
ያ ሁሉ ትዝታ
መጥፋት አብከንክኖሽ በድንገት ስትዞሪ፣
የጨው ሐውልት ግግር
አድርጎ ቢያስቀርሽ የፍጥረት ፈጣሪ፤
ሎጥን ልምሰል ብዬ…
የፍቅርሽ እርምጃ
ከኋላዬ ሲቀር ወደ ፊት አልሄድም፣
አይቼሽ ለማልቀስ
አይቼሽ ለመድረቅ
ያ'ምላኬን ቃል ሽሬ መዞሬ አይቀርም፡፡
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
በፍቅር ሰንሰለት እኔን ላንቺ ድሮ፣
ያለፈ ታሪክሽን
የኀጢአቴን ግርሻት ሊያጠፋ ቀን ቀጥሮ፤
"ወደ ኋላ መዞር ላ'ፍታ ሳትመኙ፣
ወደ ፊት ተጓዙ ነጋችሁን ቃኙ!
ለፍቅር ታመኑ ለፍቅር ተቀኙ!"
የሚል ትእዛዝ ሰጥቶን
ትናንትናችን ላይ እቶን እሳት ቢለቅ፣
ወላዋይ መንፈስሽ
ልክ እንደ ሎጥ ሚስት ታየ ሲፍረከረክ፡፡
የቀድሞ ፍቅረኛሽ…
ያ ሁሉ ትዝታ
መጥፋት አብከንክኖሽ በድንገት ስትዞሪ፣
የጨው ሐውልት ግግር
አድርጎ ቢያስቀርሽ የፍጥረት ፈጣሪ፤
ሎጥን ልምሰል ብዬ…
የፍቅርሽ እርምጃ
ከኋላዬ ሲቀር ወደ ፊት አልሄድም፣
አይቼሽ ለማልቀስ
አይቼሽ ለመድረቅ
ያ'ምላኬን ቃል ሽሬ መዞሬ አይቀርም፡፡
#ኤልዳን
@eldan29
@getem
@getem
@getem
❤42🔥5👍2🤩2
(የሞገሴ ልጅ)
ከእኔ ካልመጣ
ሂጂልኝ ማለትን - አፌ ካልተማረ፣
ካልሄድኩ ካለ ልብሽ፣
ብከለክለውስ - መቼ ትቶት ቀረ?
ኁሌ አትሂጂ ባይ
ኁሌ ልሂድ በሚል ረባሽ ከተገፋ፣
ሰይጣንን ያስቀናል፣
እንኳንስ በሌላው በራሱ ሲከፋ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
ከእኔ ካልመጣ
ሂጂልኝ ማለትን - አፌ ካልተማረ፣
ካልሄድኩ ካለ ልብሽ፣
ብከለክለውስ - መቼ ትቶት ቀረ?
ኁሌ አትሂጂ ባይ
ኁሌ ልሂድ በሚል ረባሽ ከተገፋ፣
ሰይጣንን ያስቀናል፣
እንኳንስ በሌላው በራሱ ሲከፋ!
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
❤30🔥5👍2🤩1