Telegram Web Link
( ፈቀቅ በል )
==========

ከቆይታህ ትዝላለህ
ከቆይታህ ይደክምሀል
ተስፋ ማጣት መጨላለም
የሀዘን እሾህ ይወጋሀል
ስትባክን እንደመሸ
ሌቱም እንዲያ .. ይነጋብሃል
ግዴለህም ' ፈቀቅ በል '
ብትሰማው ይሻልሀል !

ቸር መዳፉ .. ኋላ ደርሶ ለታመነ
ስንት ባርያ ዋስ ሲሆነው
የእረፍት ውሃ ሰላም ደስታን
ከደጃፉ ሲያዘግነው
አንተ ልጁ እስከመች ነው
በዓለም ጉያ ምትባክነው ??

(ጴጥሮስ ጓዴ)
እርሳ የቀን መከራህን
መረብህን ዳግም ጣለው
በባዶነት የሚሰራ
ቸር አምላክ ነው ፊትህ ያለው
'ፈቀቅ በል ' ጥቂት ስንዝር
ከትላንቱ ድካም ብክነት
የመከነ ተስፋህ ግቡ
በርሱ ቃል ነው ሚሰምርለት !!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@paappii
59👍11🔥3
"አማኝ ነን ባዬች"

ከአፍ ከክንድህ እየጠረቡ
በድንክ ህልማቸው
በዘር መትረው ሰውን ገነቡ
ከፈረሰ አምላክ
ፈጣሪ የሌለው ፍጡር ተሰራ
እንዳያምን ገፉት እንዳይሸሽህ ፈራ

°
°
እናም.  .  .  .  .
የዚህ ታሪክ ፍቺው ሲተነተን
ምድር አይገባም በዘር ለሚበተን
❛❛በብሄር ነው ቢባል
በቀለም ነው ቢባል
በሀገር ነው ቢባል ❜❜
በዘር መካፋፈል መንስኤ ምንነቱ
አንድ ላይ መሆን ነው የሰው ልዩነቱ
በሀገር ያጣመሩት በእምነት ይጣረሳል
በብሄር የገነቡት በቀለም ይፈርሳል
ልቡናው ያልቀናለት
ካፈርም ዘር መርጦ ከስጋው ይዋቀሳል
በማፍረስ አይጸናም
-------ኬላ 'ና ድንበር ስለ'ገረሰሱ
በመለያየት ነው አንድ የመሆን መልሱ
አንቺም ካለሽበት እኔም ካለሁበት
ባንድ ላይ ተጋርተን
የአንድ ዛፍ እስትንፋስ የአንድ ጸሀይ ጮራ
ገላሽም ገላዬን
ልብሽ ልቦናዬን ከሸሸ ከፈራ
ዘር በእንባ ቢወድም ሀገር ቢፈራርስ
ይቅርታ ብቻ ነው ፍቅርን የሚመልስ
በብሄር አይደለ
በቀለም አይደለ
በሀገር አይደለ የሰው ልዩነቱ
በፈረሰ እምነት ላይ ስለተገነባ
----------አይጸናም እውነቱ
አንዲት ጸሀይ ሞቀን
በአንዲት ጀንበር ደምቀን
ጦር የሚያማዝዘን
ሀገርም አይደለ ብሄርም  አይደለ
ከልባችን ላይ ነው ኬላው የተሳለ!

By  የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
47👍8🔥2🎉1🤩1
----------- ፀፀት --------------

ባጠፋዉት ጥፋት፥ ይቅርታ ስትይኝ
አስቀይሜሽ እንኳን፥ መች ልትቀየሚኝ?
ቀስ በቀስ ስሜቴ፥ እያደር ለዝቦ፣
በጥፋት ላይ ጥፋት፥ ቢያስገባኝም ስቦ፥
እፍረቴን አራግፎ፣ አሳድጎ ድፍረት
የምህረትሽ ብዛት፣ አስጠፋብኝ ፀፀት።

@getem
@getem
@paappii
62🔥12😢11😁2🎉2😱1
እሷን ይመስለኛል
.
.
በብሩሽ ቢቀለም የሴትነት መልኩ፤
ተለክቶ ቢሰፈር የቀሚሷ ልኩ፤

እሷን ይመስለኛል.........

በጥለቷ እራፊ እንባዋን ሸፍና፤
የልቧንን እህታ በሳቋ አፍና፤

ለደከሙት ሁሉ 'ምታበረታዋን፤
ራሷ ጀግና 'ምታጀግነዋን፤

የዘወትር አመስጋኝ ደጃፉን ናፋቂ፤
አድባር የመረቃት ጠበኛ አስታራቂ፤

ቃሏ 'ማይታበይ እዉነተኛይቱን፤
የአምላክን ወዳጅ ባለማተቢቱን።

እሷን ይመስለኛል........እ'..ሷ'..'ን

ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
48👍13
----------- ፈ ቅ ፍ ቆ ----------

የማይሆን ትውስታ ፥ ማይረሳ ፍቅር
አጉል አስለምደሽ፥ ይሄ ሁሉ ሊቀር፥

እያደር ሚፈካ፣ ፍቅርሽ ማይበረዝ
አልሆንልህ ቢለኝ ፣ መሰረዝ መደለዝ፣

ምን ስለት ላስገባ? ምን እጣንስ ላጭስ?
ትዝታን ፈ ቅ ፍ ቆ፣ ሚያጠፋ እንደ ላጲስ።

@getem
@getem
@paappii
65🔥7🤩5👍4😢4👎2😱2
◈━━━━━━━━━━━━━━━◈
       የብርሃን ዕድሜ
◈━━━━━━━━━━━━━━━◈

አየሽ ሊስትሮዬን
ነውሬን እንዲሸፍን በሰጠሁት ጫማ
ቁሱሉን ይጠግናል አቁስሎ እያደማ

በመኖሮ መንገድ ላይ
የጉጠቶች መብዛት ነፍሱን ሲያናጥበው
በጊዜ ፍላጻ ህይወት አያከመው
ሰውም እንደዚህ ነው ከህመም የሚጸና
የወደቁ ዕለት ነው መንገድ የሚቀና

(ጫማዬን እያየ
ልቤ እንዲህ ይለኛል....)


«ማን ቀማኝ ምርኩዜን?
ማን ሰበረው ክንፌን?

መኖርን ሳትጀምር
ምንድን ነው ያታከተህ?
የውጣ ውረዱን መብዛት ተመልክተህ
ህልምህን ከበዓት ስለምን ሰወርከው?
የአይምሮህን ፈኖስ በ«አልችልም» ሰርበከው
(አየህ.....)
ምርጫ ባይሆን እንኳ ማበብና መክሰም
ብርሃን ነው እድሜው የተሰራ ከሰም»።

by የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
43🔥10👍3
--------- የኳክብት ምስጢር ---------

የሰማይ ኳክብት
እያብለጨለጩ
አንዱ ከሌላኛዉ
ምንም ሳይገጩ፤

ለምን ይመስልሻል
መሬት ላይ ሚያፈጡት ?
እልፍ ዘመን አልፎም
እሚመለከቱት ?

ወዲ ነዉ ጉደዩ
ከላይ መሆናቸዉ
አንድ ነገር አለ
የሚያሳስባቸዉ፤

ጎን ለጎን ሆነዉ
አንዱ በሌላዉ ላይ
በፍቅር ተገርመዉ
ቁጭ ብለዉ ከሰማይ፤

አይነቸዉን ተክለዉ
በቅነት በስስት
በደስታ ተዉጠዉ
ቀን ሳይሉ ለሊት፤

ያንቺ ዉብ ቆንጅና
ስላማለላቸዉ
ስለዚ ነበረ
መሬት ማፍጠጣቸዉ።

@getem
@getem
@paappii
72😱8🤩7🔥2
እኔ ምን አውቄ
ፊደላት ሳታጥፊ
ቃል ሳትከለስፊ
ከሆሄያት አምባ
ሳትደክሚ ሳትለፊ
ሳትፈላሰፊ
ይደርሰኛል መልሱ
ለነብሴ ጥያቄ
አይንሽ ይመልሳል
ልብሽን ጠይቄ
እኔ ምን አውቄ።
       
By @poetkidus

@getem
@getem
@getem
40👍6
ባልጠብቅሽ ኖሮ

‎በድሮ ቦታችን በቀጠሮ ቀኑ፣
‎በትዝታ አምላክ በእግዜር እያመኑ፣
‎እንደተማመኑ፣
‎ልቤ ከልብሽ ጋር ፍቅር እንዳልሰሩ፣
‎ዛሬ ሲለያዩ ምነው ሁሉን ፈሩ፣
‎በራሳችን ጥፋት እግዜርን ሳንፈራ፣
‎ሰው አየኝ አላየኝ ያየነው መከራ፣
‎ትዝይልሽ እንደሆን በቀጠሮው እለት፣
‎ባልጠብቅሽ ኖሮ ወይ ባትመጭ ኖሮ፣
‎ባንገናኝ ኖሮ፣
‎ፍቅር አልቆ ነበር በጊዜ ቀጠሮ።

By @Eyob16m

@getem
@getem
@getem
48👍14🔥3👎1😱1
( አጭሯ ፍቅሬ )
===========

አሁን በቀደም ለት
ለሐምሌ መባቻ አንድ ሳምንት ሲቀር
ያቺ የቀድሞ ፍቅሬ
ሠርክ የምትጓጓለት ልደቷ ቀን ነበር ..

እንደ ሰው ምሰጣት
ኢምንት ባይኖረኝ
በዚህ የደስታ ቀን ከምትቀየመኝ
ለክፉ ቀን ብዬ ከሸሸግኩት ቃላት
ውዱን መርጬላት
ለዘመናት ይዤው ከቆየሁት ጥበብ
ጥቂት ሰውቼላት
ማንም የማይደርሰው
ድንቅ ረጅጅጅጅጅጅጅም ግጥም
ስጦታ ጻፍኩላት !

ግና ከዚያ ወዲያ ታሪክ ተቀየረ
ፍቅሬ አኮረፈችኝ ፈገግታዋም ቀረ
ስንት ተጨንቄ የዘረፍኩት ቅኔ
ልቧን ሰባበረ ...

ወዮ !
የልቤን ጭማቂ የከንፈሬን ፍሬ
ነበር ያቀበልኳት
አረ በሚካኤል የሰማ እስቲ ይፍረደኝ
ምን እንደበደልኳት
ብዬ ወገን ዘመድ ልኬ ሳስጠይቃት

(መልሷ እኔኑ አሳቀኝ)
ግጥሜ መርዘሙ ነበር ለካ ያስከፋት
የረሳሁት ነገር ... ፍቅሬ ለካ አጭር ናት
የረዘመ ሁሉ አሽሙር የሚመስላት !!

እኒያ ከዚያ ወዲያ
እንደ ጎልማሳ ጢም ግጥም ስከረክም
አንድ ሃረግ ሳወጣ አንድ ሃሳብ ሲደክም
እንደኛው ሲጎላ አንደኛው ሲጨልም
እንደነበር ተውኩት
በእርሷም ጨከንኩባት
ምን ልታረግልኝ ሀሳብ ካማሳጠር
የሷን ቁመት ማርዘም መቅለሉ ካልገባት !!!

By @kiyorna

@getem
@getem
@getem
75😁44👍7🔥3👎1
‎ ጉድፍ ሳይታከለው ሳይኖረው ጥላሸት
‎ መልኩን ሳይለዋውጥ በቀንም በመሸት
‎ ምላስ ያልበዛበት የሽንገላዎች ቃል
‎ ልብሽን ማፍቀሬ ከአይኖቼ ያስታውቃል

‎ ፀሃይ ከጨረቃ ከዋክብት ደመና
‎ ሰማይና ጠፈር ጎህ አየር ቀረና
‎ ላንቺነትሽ ቃላት ላንቺነት ምሳሌ
‎ ረቂቅ ሆኖበት ምላሴና ቃሌ
‎ ምንም ባደርግ ምንም
‎    ከጥጎች እስከ ጥግ
‎ ለንዳንቺ አይነት ቆንጆ
‎     የለውምና ህግ
‎ መሰየሜን ተውኩት
‎ ቃላት አያገኙም ልብሽን ለሚያውቁት

‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz


@getem
@getem
@getem
34🔥6👍4
-------------- ጊዜ -------------

ጊዜ ለማይበቃን በጣም ላነሰብን
ሞልቶ ተትራፍርፎ ደግሞ ለበዛብን፤

ገዝቶ ተቀብሎ መኖር ተደራድሮ
በነዋይ በልዋጭ ወይም ተዋዳድሮ፤

በጉሊት ገበያ ታሽጎ እንደ ሸቀጥ
ቢቻል ምን አለበት ጊዜን መግዛት መሸጥ።

@getem
@getem
@paappii
40👍8🔥5😁5👎2🤩2
‎ ከ ልክ በላይ ነብስን ማጥፋት
‎ ለማይሆኑ ልብን ማልፋት
‎ ሰርክ ማለም ተንቀልቅሎ
‎ ቀልብን ልብን ላንድ ጥሎ

‎ በነሱ ዘንድ አለመዋል
‎        በሳቅ ብቻ ለይስሙላ
‎ ትርፉ ድካም ትርፉ ብክነት
‎      መውደቅ ብቻ ወደኋላ
‎ ኑሮን መሳል ካንድ ወገን
‎      አሳብቦ አሳብዶ
‎ ከሁለት ባንዳቸው
‎ አንዱ ብቻ ጠልቶ
‎ አንዱ ብቻ ወዶ።

‎ ልክ ላልሆነ መፈላለግ
‎ እንደገባኝ እንደገባን
‎ ባይን ብቻ ቀርቶ
‎ ቃላት ካላግባባን
‎ ለይስሙላ መኖር አንድ ሆንን እያሉ
‎ አይሰምረውምና ፍቅር ይዘት ውሉ
‎          ልክን ለማበጀት
‎ እቅድን አስምርን ለአንድ አመት በጀት
‎     እንሞክር ግድ የለም
‎  ብዙ ማፍቀር ልክ አይደለም።


‎ ዮኒ
‎      ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
42🔥4🤩1
ትተነው ላልመጣነው ልጅነት
.
መክሰስ አትሆንም ለራት አትበቃም
መርጠህ አታውቅም ፈቅደህ አትነቃም
ብዬ ላፈንኩህ ሳላመነታ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!

ልትስቅ ስትል ላልኩህ በኩርኩም
ልራመድ ስትል
አርፈህ ተቀመጥ ላልኩህ አትቁም
በሳቅህ ግርጌ ቁጣ ፀንሼ
ትልቁን ህፃን
አዋቂ ላልኩህ ከድሜህ ቀንሼ!
ሌት ባታሸንፍ ቀን ባትረታ
አብራኝ በቀረች አንዲት ትርታ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!

አንጠልጥዬህ ባልፍ በትዝታ ቋት
የጊዜን መንገድ
ሊጓዟት እንጂ ከቶ ላይርቋት
ትቼህ የመጣሁ ጥንት ቢሆንም
የርምጃ ያህል አልተራራቅንም።

ለተሞላበት ችኮላ ጥድፊያ
እሰጥ ይመስል ምቹ ማረፊያ
ስላመጣሁህ
ወደማይገባህ የማደግ ልፊያ
ልጅነቴ ሆይ ባክህ ይቅርታ!

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
55👍12😢3🔥2
ያኔ ...ትምህርት ቤት ሳለን፤
ሰዓት አሳለፉ አረፈዱ ተብለን፤
በደረቅ አርጬሜ እንገረፋለን፤

ነገር ግን በህይወት.....

ይደርሳል እያልን፤
ጥቂት ካረፈድን፤

ህይወታችን ሁሉ ይመሰቃቀላል፤
ዳግም ላይመለስ ይዘበራረቃል።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
52😢10🔥4👍1👎1
፨፨፨ ፨፨፨

አጥቤ እንዳነፃው
በምህረት ተሰጥቶኝ
ተጨማሪ እድል፡
ጨለማ አይደለውም
ሚስተካከል ቀኔን
በእንባ የምገድል

ስህተት አትቁጠሩ
ጣታቹ የኔን ግብር
እያመለከተ፦

ምንም ልምድ የለኝም፥
መጀመሪያዬ ነው
ስኖር እንደናንተ።

@mikiyas_feyisa
@getem
@paappii
47👍7🔥4😱3
[የእንባ
  ቅብብል]

ይታየኛል ከአድማሱ ስር ከጀንበሯ ፈቀቅ ብሎ
ድል ነው ብሎ የሚሸል የወዳጁን ስጋ ጥሎ
ለጋ ሚስኪን እናቱ የሀዘን ማቋን ለብሳ
ልጇን ትጠብቃለች የባሏን አፈር መልሳ

የእንባ ቅብብል ነው ደም እያፈሰሱ
ለቅሶ ይቀመጣሉ ከድል ሲመለሱ
የሰው ልጅ በቃሉ መቼ ፍሬ ያፈራል?
ሰይፍ እየመዘዘ ለሞት ይጠራራል?

ይብቃ! ግድ አይደለም!
ሽንፈት አይደለም!
ያቃቃረን የቂም ቁርሾ
ያዘማመተን ለበቀል

በአንዲት ጀንበር ባይካስም
ግዳይ ጠርቶ ሰውን መጣል
      ----ጨለማውን አይመልስም!


የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
42👍9🔥1
የህይወት ምሳሌ
የተወላገደው ትቢያ የረገጠው
አቤን በሶ ሰቶ
ለጫላችን ደሞ ጩቤ ሲያስጨብጠው!

እናም ይኀው ህዝብህ
   ---ከምክሩ ብኋላ
አይኑን አውሮበት ተካፍሎ እንዳይበላ
ወይ እሮጠህ አምልጥ
ወይ አሳደህ ብላ!

ሲሆን ስንት ዘመን
አበበ ይሸሻል ጫላም ያሳድዳል
ይሙላልህ  ያላለው
መረቡን ዘርግቶ ባዶነት ያጠምዳል!


የአብስራ ሳሙኤል

@getem
@getem
@getem
54🔥5😁5🤩3😱2
ሀገሬስ ገንፎ ናት
በስልጣን ማንኪያቸው የሚቆራርሷት

ቂቤ ወሬያቸውን በርበሬ ስራቸው
ጨመር አርገውባት

እሷ ያዝኩት ስትል
የስጧትን ሁሉ አጣቅሰው አላውሰው

በዛ ስልጣን ማንኪያ በህብረት አብረው
ያውም ክብ ሰርተው

እንደ ጉድ ሚበሏት የሚጎራረሷት

ሀገሬ ለእነርሱ ገንፎ ብቻ እኮ ናት
@topazionnn
@getem
@getem
👍3816😢9🔥2
አለሁ ጥሩ አለሁ መልካም
‎መኖር እኔን አያስለካም
‎ብይ ግጥም ፅፌ የሰጠሁሽ ለታ
‎እንደዚህ ነበረ የኔ መልእክቱ መግቢያ
‎ባለፈው ባለፈው ከተለየንበት፣
‎ካገኘሁሽ ብየ ከተጣላንበት፣
‎ልመጣ ፈልጌ አንድ ነገር ያዘኝ
‎የኩራት አባዜ አዙሮ ደበቀኝ
‎ግን አልቻለም ልቤ ፈለገ ሊመጣ
‎ኩራት ተወገደ እግሬ ከቤት ወጣ
‎አጥቼሽ ድጋሚ ከምሰብር ብየ
‎ደውየ ጠራሁሽ ናፈቅሽኝ አንችየ
‎ለማውራት ብፈራ ባልችልም መናገር
‎እወድሻለሁ ማለት መቼስ ኩራት አይደል።

‎            by @Eyob16m

@getem
@getem
@getem
33👍13🔥4🎉2
2025/10/22 15:51:50
Back to Top
HTML Embed Code: