Telegram Web Link
ቦግ.....እልም
.

.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤

ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤


የኔም ህይወት እንዲሁ......

አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤

አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........

የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
46👍9🔥6
አልጋዬ የምኞት በሀር ወዝሽ የፈሰሰበት
ማጀቴ የፈኖስ ብርሀን ሳቅሽ የደመቀበት
የጂጂ የመውደድ ዜማ
ተቃቅፈን የደነስንበት
ጎዳናው የተጓዝንበት
#አንቺን_ያስታውሰኛል!
¹
የታክሲው ጥግ ላይ ወንበር
ከፍተሽ የምተገቢው በር
የቡና የዕጣን አውዱ
የቤተስክያን አጸዱ
የጧፏ ደቂቅ ብልጭታ
ያስቀደስንበት ቦታ
#አንቺን_ያስታውሰኛል!
²
የትኩስ መቃብር ሽታ የተቆፈረ አፈር
ድንኳን የተጣለበት ሰፈር
የአበባ እቅፎች መቃብር ግርጌ የረገፉ
የዕድር ጥሩንባዋች ሞት የሚለፍፉ
#አንቺን_ያስታውሰኛል!

#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel

@getem
@getem
@getem
29😢1
ሁሉም ይለወጣል

በአበባ ይተካል
ሸክሙም ቀንበሩም፤
ዘንበል ይሉልኛል
ድንግዝግዝ ቀናቶች፡
ችክ እንዳሉ አይቀሩም።

አምናለሁኝ እኮ፡
በኔ ላይ ይሆናል
ፍፁም የማይሆነው! ፤
እኔን የጨነቀኝ፡
እንዴት አድርጌ ነው
የማመሰግነው ?።

By @mikiyas_feyisa

@getem
@getem
@paappii
66🎉1
------- ቀን --------

ቀን ቀንን አርግዞ
ቀን እየወለደ፣
አንድ ቀን ሌላን ቀን
አልፎት እየሄደ፤

በቀናት መካከል
ቀናት ተደራርቦ፣
የቀናት ክምችት
የቀናት ርብራቦ፤

ቀናቶች ስንቆጥር
ቀናት ስንመነዝር፣
ቀናት ስንዘራዝር
ቀናቶች ስንገብር፤

ቀኖች እያሰብን
ዝክር ስናዋጣ፣
ቀንን ሳንጠቀም
ምፅአት ቀን መጣ።

@getem
@getem
@paappii
63👍13🔥6😁2😢2👎1
ጥርሷ ሰዋሪ
ሳቋ ነዳፊ ፤
ከንፈሯ ገዳይ
ዐይኗ ገራፊ ፤

ፀጉሯ ሐመልማል
ልብሷ ደመና ፤
ገላዋ አበባ
ቃናዋ ናና ፤

ልክ እንደ ሰንደል
ልክ እንደ ብርጉድ ፤
የቀመሷት ለት የምታስብል ጉድ !

ከሰማይ በቀር
የምድር አፈር የማይመጥናት ፤
ከመለዓክ በቀር
በሳር በቅጠል የማይመስሏት ፤

ልጅማ ልጅ ናት !

ጨረቃ ኮኮብ የሚሰግዱላት
አበቦች ከዱር የሚያረግዱላት ፤

የሚገድሉላት
የሚሞቱላት
ከአንቺ ጋ አድሬ ሲነጋ ልሙት የሚዘፍኑላት ፤

ልጅማ ልጅ ናት !

ሲሻት በምድር
ሲሻት በሰማይ የምታበራ ፤
ነፍስ የምታስት ስትስቅ ስትኮራ ፤

እንኳን ለአዘቦት
ለክት ለዓመት ባል የሚሸሽጓት ፤
እንኳን በፀሐይ
ሌት በጨረቃ በሩቅ የሚያውቋት ፤

ልጅማ ልጅ ናት !

እንኳን ቁሞ ሃጅ
ሙቶ የተኛን ታሳብዳለች ፤
እንኳን የሰው ዘር
ባህሩን ወንዙን ታስረግዳለች ፤

ከፍቅር በቀር
ሌላ አይችላትም ፤
ከራሷ በቀር
የቱም አበባ አይመጥናትም ፤

የምድር ዕንቁ ናት
የምድር አበባ ፤
እንዲሁ ታይታ ዐይን የምትገባ ፤

እንዲሁ ታይታ ቀን ታፈካለች ፤
በዐይኖቿ ብቻ
ውኃን ወደ ወይን ትቀይራለች ፤

ለባህር ዛጎል
ለሰማይ ኮኮብ
ለምድር አደይ ናት ፤

እንኳንስ ቁሜ
ስሞት ከጎኔ ትብቀል የሚሏት ፤

ልጅማ ልጅ ናት
ከአንድ እኔ በቀር
ሌላ የሰው ዘር የማይመጥናት ።

by Tewodros Kassa

@getem
@getem
@paappii
76👍16😁10🔥5👎2
Forwarded from የሕይወት ዛፍ......Tree Of Life (Yoseph Yid.)
ሰላም ወዳጆች ዛሬ 9:30 አራት ኪሎ በዋልያ ቡክስ አዳራሽ የወዳጄ የኪሩቤልን መፅሐፍ እናስመርቃለን።

የምትችሉ እዛው እንገናኝ።

ማስታወሻ የኔን ምስል እዚ ውስጥ ፈልጎ ላገኘ የመጀመሪያው ሰው መፅሐፉን እሸልማለሁ...😅🙏
21
      "ይጠፋል"
---------------------------

ፀጉሬን ሽበት ወሮት
ፊቴም ቢጨማደድ፣
የወጣትነቴ ወዛናው ቢጠፋ
ምን ቢመስል አመድ፣

ክንዴም አቅመ ቢስ
ወኔዬም የከዳኝ፣
ያለኝ ጥቂት እድሜ
ያለኩኝ አለም በቃኝ፣

እርጅና እንደ ከንፈር
ቢመጣ አሞጥሙጦ፣

እንዴት ብወድሽ ነዉ

አንቺን ባሰብኩ ቁጥር፣
ሚጠፋው ደንግጦ።

@getem
@getem
@paappii
46👍13😱1
የኔ ሳቅ
.
.
ሁሉም ለየብቻዉ
             እንደተለያየ
የኔ ሳቅ ለብቻው
              ከኔ ጋራ ቆየ

አየሁት ሰማሁት
          ሁሉን ተረዳሁት
ሳቄን ለማርከሻ
             ቢቸግር ጠጣሁት
             ቢቸግር በላሁት
             እንደ ጎሽ ጠላ
             እንደ 'ባር ማሽላ

ሳቄን ለማርከሻ
              ከነገዉ መድረሻ

              መረጥኩት ጠላሁት
               ይስቃል እንዲሉኝ
              ጥርሴን ተነቀስኩት

@topazionnn
@getem
@getem
42🔥4😢4👍2😱1
------------------------
የለት ተቀን ስራ
ድግግሞሽ ብዛት፣
ጥሩም ቢሆን መጥፎ
ያሳለፍነዉ ግዚያት፣

አንድ አንዴ በፌሽታ
በደስተ መፍለቅለቅ፣
ደግሞ ሌላ ግዜ
በእንባ መንሰቅሰቅ፣

ለዚ ዉጣ ውረድ
ባናገኝ ተማጽኖ፣
ምንም እንኳን እድል
ቢኖረዉም ተጽኖ፣

ከሁሉም ሚሻለዉ
ከሚመጣዉ ክስረት፣
ከሴጣንም በላይ
ልማድን ነዉ መፍራት።

@getem
@getem
@paappii
35👍14🔥4😢1🤩1
[ #ለእሷ! ]

የመዋደዳችን አበቃ ምዕራፉ
የመገናኛችን ተዘጋ በራፉ
ለምለም ምኞታችን እንደ ጉም በነነ
ዘላለም ነው ያልነው ቅጽበታችን ሆነ።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━

ያኔ
በመስታወት ጡቦች በታሰረ ብርሀን 
ጎጆ'ችንን መልተን
ከገበታችን ላይ ፍቅርን ዘርግተን
መውደድ በትኩሱ የተቋደስንበት
ነፍሳችን ጥለን ህጻን የሆንበት

ዛሬ እንደ ትዝታ በምኞት ይገርፋል
አየሩ ንፋሱ "የለሽም" ብሎ ያልፋል ።

━・・・━ ★ ━・・・━

የለሽም የለሽም

የመስታወት ጡቡ ወድቆ ተሰበረ 
ብርሀን ጸዳሉ ወዳንቺ በረረ 
በስብርባሪ ውስጥ ጸጸት ብቻ ቀረ
በጊዜ ጠብታ ትዝታን ያዘለ.  .  .



ይኀው እዛች'ጋ 
የገጽሽ ሀመልማል ጽልመቱን ይቀዳል 
ከሳቅ ከጭዋታሽ ብርሀን ይወለዳል
እንደ ጀንበር ውበት በማለዳው ይሄዳል።

ይኀው እዛች'ጋ
የዳናሽ ማህሌ' ሀዘኔን ሳያስረሳኝ 
ኮልታፋ አንድበትሽ በፍቅር ሲያነሳኝ
ህይወት እንደ ምንጣፍ እየጠቀለለው 
ከትዝታ መቅረዝ ሰብስቦ ሲጥለው ።



ይኀው ወደ አንቺ ጋር 
ዛሬም እንደ ትናንት ልቤ ይሰደዳል 
ተስፋውን ሰንቆ ለምኞቱ ይሄዳል

ከንፋስ ከአየሩ ♡ 
ከዛፍ ከቅጠሉ ♡

የለሽም የለሽም
የሚል ኦና ቃላት በምጥ ይወለዳል!።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━

#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel

@getem
@getem
@getem
54👍7🔥5
አካልን ቢያስጠብቁት
  በድካም ቢወቁት

ልብ የጠበቀ ለታ
ህመምና ዋይታ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
16😢9👍2
ሥትገቢ ሥትወጪ-
ዐይኔ ተደሥቶ ልቤን የሚያሞቀው፣
ዝቅ በል ሥትይኝ፣
መውረዴ ተክቦ - ክብሬን የሚንቀው።

በመናኛ ቀልድሽ-
እንድያ የምሥቀው - ድዴ እሥኪሠበር፣
አሁን የማይገባኝ፣
ያን ሠሞን ግን ካንቺ - ምን ፈልጌ ነበር?

(የሞገሤ ልጅ)
By @eyadermoges

@getem
@getem
@getem
28😁23🔥5
ህይወት ግን ምንድ ነው?

ህይወት ግን ምንድ ነው
ከዉስብስቡ አለም ግንኙነት ያለው

እንደፈለገ የሚያስደስት የሚያሳዝነው
ህይወት ግን ምንድን ነው

ለብዙ ነገሮች ጥያቄ የሆነው
ከጥልቁ ባህር አጥልቆ ሚያስቀረው
ግን ህይወት ምንድን ነው???????

አልቅሶ አለመሳቅ አቶ አለማግኘት
አዝኖ አለመደሰት ነው አይደል? ህይወት 😊😊😊
Kal..... @pilopater
@getem
@getem
@getem
35👎12👍7🔥1
ጷግሜ
.
.

'ያመት ማካታቻ የቀናት ጭማሪ፤
የተስፋን ፀዳል ንጋት አብሳሪ፤

በሩፋኤል ጠበል ከበራችን ወተን፤
የዝናቡ ወጨፎ ብርዱ ሳይበግረን፤

በጉጉት ስንጠብቅ እስኪደርስ ቀኑ፤
አደይዋ እስክትፈካ ሲለወጥ ዘመኑ፤


በአዲሱ ልብሳችን እጅጉን ተዉበን፤
አበባዮሽ ስንል የክቱን ለባብሰን፤

የልጅነት ጊዜ.....
በትዝታ አስጉዞ ሁሌም ይናፈቃል፤
እንደ እንቦሳ ጥጆች ዘወትር ያስቦርቃል።
.....................................
ዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
89🤩6👍2
ዉስጤ ረቂቅ ነበር ፣ ጣፍጦ የጎመራ፣
ትልቅ ምትሀት ያለው፣ ማንንም ሚጠራ።
አንቺ ደግሞ ጥሬ፣ ለመብሰል ሚቀርሽ፣
ገና ለጋ ቅጠል፣ የማይስብ ወዘናሽ።

ምንም ብስል ቢሆን፣ አንድ ጣፋጭ ፍሬ
ምንም ለምለም ቢሆን፣ ቢጣፍጥም ዛሬ።
ግዜ፣ ቦታ፣ ምክንያት፣ ካልተገጣጠሙ
ፍሬውም፣ ይረግፋል፣ ደስ አይልም ጣሙ።

ፍሬሽ ፍሬ አፍርቶ፣ ቢጣፍጥም አድጎ፣
አንቺን ለማብሰል ስል፣
ለካስ መሬት ነበር ፣ የኔማ ጠዎልጎ።

@getem
@getem
@paappii
52👍9😱3🔥1
ቄጠማ ሆነብኝ እግሬ| አቃተኝ ነፍሴን ማበርታት
በይግባኝ ሸንጎ ገጥሜህ
   ---በአርምሞህ ቃሌን በመርታት
ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀኝ ለመከራ ቁር
ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!።
°
በል ግባ እንደ አብርሃም ቤት
ጓዳዬን ማጀቴን ቃኘው
ሰባራ ሸክላዬን ጥጄ
በምኞት ሆዴን ሳሞኘው
አረፍ በል ከሳር ፍራሼ
አይመች ለገላ አይመጥን
ሳለቅስ ሳነባ አድራለሁ
ውል አልባ ህልሜን ስወጥን
በል ባርካት ደሳሳ ዳሴን
በፍቅርህ መሰረት አጽናት
ካልሆነም ስጋን አፍርሰህ
የዛለች ነፍሴን አድናት!።

°
ተመልክት የዓለም መልኩን
ተለምዷል ወድቆ መረሳት
ጎዳናው ዕንባ ጠገበ
ይፋጃል ዕግርን እንደ እሳት!!!
ስታውቀው የዓለም መልኩን አጨኀን ለመከራ ቁር
ክፍት ነው ደጄን አትቆርቁር!።

#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel

@getem
@getem
@getem
59😢8🔥7🎉3

    ኔ
       ም!

ሙሴን ስትሰጠው ባህርን ሚከፍል
ለዳዊት ጠጠር ጎሊያድን የሚጥል
ምን አል በሰጠኸኝ ለኔም ልዩ አቅም
ቁስሏን ማድንበት ሀገሬን የሚጠቅም፡፡
            
          by   @Abuugida ᵗˢᵉᵍˢʰ

@getem
@getem
@getem
89🔥18👍15🤩2
ከጭፈራው መሐል

አበባዮሽ እያልን ስንዞር ከየቤቱ፣
ቄጠማ ተይዞ ተለብሶ የክቱ።

ጨዋታዉ ሲደራ የከበሮዉ ድልቂያ፣
የድምድምታዉ ጩኸት ሆኖ ፈንጠዝያ።

ከጭፈራዉ መሐል ስትወርድ በእስክስታ፣
መቀነት ታጥቄ ሳይህ በስርቅታ።

በነፋስ ሽዉታ አይናችን ተጋጭቶ፣
በሴኮንድ እይታ ልባችን አዉግቶ።

ፀሐይ ስታበስር የድል ብስራት ዜማ፣
እስክስታዉ ሰደደን ወደ ፍቅር ማማ።

           በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
48🔥5😁3👎2
(በዕምዓዕላፍ)

            የማፍቀርን ያክል
            መውደድን የሚያክል
            ምን አለ ትክክል ?

የፍቅር  ምትሀት   ካባውን ደርቦ
በወዳጅ አይን ላይ  ማሳዬት አስውቦ

            ገላ ኩንስንሱን
             ደርቦ ሞገሱን
ግዘፍ    ረቂቀ ስልቱ
ማብቃት  ፍቅር ምትሀቱ

                    እንከን የለሽ ውበት
                    ፅንፍ የለሽ መለኮት
እፁብ ድንቅ

       ፍቅር  እምነታችን
       መቅደሱ ገላችን
       መሲህ ለምናችን
      ህያው ናት ነፍሳችን                    
___እፁብ ድንቅ
                                       እፁብ ድንቅ____

@getem
@getem
@getem
43👍5🎉1
በማያልቅ ሩጫ
በማይበርድ ፍጥጫ
መርጋት በሌለበት
መዋተት.....
ሁልጊዜ መጣደፍ
በቁስአለም መክነፍ
እፍፍፍፍ......
በጎዶሎ ፅዋ
በሰባራ ፎሌ
ደጋግሞ መጨለፍ
መንጠፍ........
መኖር እንዲ ሆኖ
ያለረፍት መክነፍ
መሞት ሆኗል ማረፍ።

          

By @poetkidus

@getem
@getem
@getem
50👍16🔥3🤩1
2025/10/19 19:17:20
Back to Top
HTML Embed Code: