Telegram Web Link
ሚስጥረኛ ብዬ
ሚስጥሬን ብነግርሽ፣

ሚስጥሩ ነው ብለሽ
በሚስጥር ተናገርሽ፤

ያ ሚስጥር በሚስጥር
ሲዞር ሲዞር ውሎ፣

በሚስጥር ነገሩኝ
ሚስጥር ነው ተብሎ።

@getem
@getem
@paappii
😁14765👍13🔥8👎3
የልብ ልሳኑ ስሜትና ቅፅበት
ማሰብ፣ማመዛዘን የአይምሮ አንደበት

(ሆነና ነገሩ)

ሲሰናዳ አፍቃሪ
ፍቅር ባቢሎን ላይ አርማውን ሊሰቅል

ጊዜ አምላክ ሲፈርድ
ልብና አይምሮ ቋንቋቸው ለየቅል

By @Absari_seven

@getem
@getem
37🔥6👍5
( እወቅ ... )
=========

የትላንትህ ሞገስ
ከመንደር ከቀዬው አዛውንት ሲጠፉ
እወቅ ታሪኮችህ በሀሩር ጠውልገው
እንደረጋገፉ ...

ነገን የሚያበሩ
ሕጻናት ረብሻ ሲናፈቅ በሀገሩ
እወቅ ተስፋዎችህ ያለ አቅም ተጭነው
እንደተሰበሩ ...

እናማ አሁንህ
ቢተልቅ ቢገዝፍ በጊዜ ሲተለም
መቼም አትኮፈስ
ከትላንት ያልመጣ ወደ ነገ ማይሄድ
ብርቱ ' ዛሬ ' የለም !!!

By @Kiyorna

@getem
@getem
@getem
37👍27🤩4
እላለሁ ተከዳው እላለሁ ተካድኩኝ
እላለሁ ተሰበርኩ እላለሁ ወደኩኝ
እዘረዝራለሁ ሆነብኝ ያልኩትን
ረሳሁት መሰል አንተን ያረኩትን

[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
69🔥18👍4🎉2
ላንቺ ብፅፍ ግጥም
ቆረጥኩኝ የሴት ጥም
እንደው ባየሺልኝ
1 አንቺ ስትሄጂ ናፍቀሺኛል ብልሽ
በስንኜ በኩል
የእንስት ጋጋታ ህይወቴን ሞላልሽ
የምን በትዝታ ሰክሮ መንገዳገድ
ሀሳብ ውሎ ይግባ በብዕሬ መንገድ

(ይህንን አትርሺ)

ሰው በቃል ይረሳል
ሰው በቃል ይፈርሳል ሰው በቃል ይሰራል
ባለቀሰበትም ድንኳን ይሞሸራል

By @Absari_seven

@getem
@getem
61🔥12👍5😱2
የራበህም ብላ የጠማህም ጠጣ ፣
       ከዚህ የተሻለ ምንም ቀን አይመጣ ፤
       ላገኝ ነው በማለት ሞትኩኝ በሰቀቀን ፣
       ሔዶ ሔዶ አለቀ የምጠብቀው ቀን ፤

     በእውቀቱ  ስዩም

@getem
@getem
@paappii
67👍21😢2
በቀል የእግዚአብሔር ነው ብለን ብንተዋቹ
ትሳፈጡን ጀመር ሞኝነት መስሏቹ
አይ አለማወቅ
አይ አለመረዳት
አልገባቹም መሰል ተንቆ መረሳት


[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr

@getem
@getem
@getem
55👍12😁5🔥4😱2
ወደግራ ወድቆ
ፍቅራችን ዳመራው
የትዝታሽ ጭሱን  ናፍቆት ሰማይ ጠራው

እሄዳለሁ ብዬ ሶዶ ወይ ጉራጌ
አንቺ የሌለሽበት
መስቀል እንዴት ላክብር እንደምን አድርጌ


By @Absari_seven

@getem
@getem
48😁14👎2
ወራቱ ቀኑ ጠዋቱ ምሽቱ ፤
እንደከርሞው ነው እንደትናንቱ ፤

ጣዕሙም ጠረኑም አልተቀየረም ፤
ለእኔ አዲስ ዓመት አዲስ አይደለም ፤

ያው ነው አበባው ያው ነው ዘፈኑ
ያው ነው ደመራው ያው ነው እጣኑ ፤

አልተቀየረም እጣና ዕድሌ
አልዳነም ጎኔ አልሻረም ቁስሌ ፤

ዛሬም እንዳምናው . . .

ጭጋግ አጥልቷል ፍዝ ነው ቀኔ ፤
በአበባ ብቻ የሚሻር ዘመን አላውቅም እኔ።

By Tewodros kassa

@getem
@getem
@paappii
45🔥11😢8😱5👍1
ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ

ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!

ለካስ...

ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!

@getem
@getem
@paappii
66🔥20👍6🎉1
በህይወት መንገድ ላይ
በኑሮ ትሩፋት
ማስተዋል ከሌለ
በጥልቀት በስፋት
በእብዶች መንደር ውስጥ
ጤነኞች ከሌሉ
ጤነኞች ለእብዶች
እብዶች ይሆናሉ።

@getem
@getem
@paappii
74👍9🔥7🤩3
‎የሴትነት እጣ ክፍልሽ
‎ ምን ቢደብቅ ማፍቀርሽን
‎አይንሽ አጋልጦሻል
‎ አላምነውም ምግባርሽን

‎የወንድነት ወጌን
‎ ምን ባስቀድም አንደበቴን
‎መጠራጠር ሰርክ ልማድሽ
‎ አላመንሽም እኔነቴን

‎ እወድሻለሁ

‎ ብትሸሸጊው ያንቺን ስሜት
‎  አይንሽ ሁሉን ይነግረኛል
‎  አትደብቂኝ....ወደሽኛል


‎ዮኒ
‎     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
👍2521
ስወደው ነው የጠላሁት
ሳፈቅረዉ ነው የሸሸሁት

የጠላሁትን እሹሩሩ የተካንኩበት
እንደጦረኛ ገፊዬን ማቅረቡ’ን ሳዉቅበት

በል…….
ወደድኩሽ ባልክበት አፍህ ጠላሁ በል
ናፈቀሺኝ ያለአንደበትህ - ላይ ታበል

እሾህን በእሾህ
ፍቅርን በመጥላት
እየወደዱ በመገፋፋት
እናስቀጥለዉ

ሰይጣኔን ሰይጣንን መስለህ ግፈፈዉ
አይነ ጥላዬን ናና እንሸዉደዉ።


ትዝታ ወልዴ✍️

@getem
@getem
@Tizita21
49👍8👎4🔥2
ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ
ፍቅር ተሰናብቶ መለያየት መጣ
ቻው እንኳን ሳይሉኝ
ሁሉም አገለሉኝ

እኔ ብቻ ሆነ እኔን የወደደው
እሱስ ተራው ደርሶ መች ይሆን ሚሄደው

By @Absari_seven

@getem
@getem
38🤩9🔥5
የአንተም ልብ ድንጋይ
የኔም ልብ ድንጋይ ...
(ለዚያ ነው መሰለኝ )
በተጋጨን ቁጥር በፍቅር የምንጋይ።

By meron ghetnet

@getem
@getem
@paappii
58🔥20🤩15👍7
ራሱ’ንደማይጠጣ - የውሃ ማሰሮ፣
መሆን ላልተቻለው - ክው ያለ ጉሮሮ፤
አስመሳይ ደጋጎች - ውሃ ሰጡት’ና፣
የሞት ሞቱን ሲኖር - ችግሩ እንደጠና፤
ጉሮሮ ማሰሮ - ተመሳስሎባቸው፣
ያጠጡትን ቀድተው - መውሰድ ላቃታቸው፤
ረሃብ አንጎራጉሮ - ለለመደው ውሃ፣
ሰጥቶ ተቀባዮች አስቀየመልሃ!

(የሞገሴ ልጅ)
@eyadermoges

@getem
@getem
@getem
19👍14🔥1
ላውሊያ ንጉስ ለጠቋሪት ደጋሽ
ዚያራ: ላይ ካድመሽ
ህልሜን ግራ አጋባሽ
የፅልመት እጆቼን ለኑሮሽ: ከነዳሽ
በኔ ጉሜ: ይዘሽ ተፋሽው ልብሽን
ካድመሽ: አገባሽው የልደት: ቀንሽን
ድቤው ስራ አልፈታ: ከህልሜ አለው ጋንታ
ላንቺ ኑሮ ሰቶ እኔን እሚያፋታ::
  
                                            by አለምሰገድ ወልዴ

@getem
@getem
@getem
23👍3
ዛሬ ሌላ ሰው ነኝ።

ያኔ ትንሽ ሆኜ-
በእድሜዬ ለጋ - በበሓሪ ችኩል፣
አፍንጫ አሽትቻለሁ፣
ቀድሞኝ ከበሰለው - ለመታየት እኩል።

ልጅነትን ሳልፈው-
ሌላን ማየት ትቼ - ራሴን ዐየሁ እና፣
ገደብ ሰራሁለት፣
ጉጉቴ ልክ አልፎ -ስጎድል እንዳይቀና።

ልልሽ የፈለግሁት-
አንቺ ላታስቢኝ አትበይ “ረስተኸኛል”፣
የሰርግሽን ፎቶ-
ከልቤ ሳደንቀው እራሴም ገርሞኛል።
ምክንያት፣...
ያኔ ወጣትነት - ኩራት የኮፈሰኝ፣
ትእቢት ላንዳፍታ - ወስዶ የመለሰኝ፤
እልህ እየጋተ - ምላጭ የሚያስውጠኝ፣
“ዛሬ ብቻ” ባይ ኅዝብ - አስሶ እሚመርጠኝ፤
ዛሬ...
አንቺ የኖርሽውን - ዘመን የኖርኩ እኔ፣
እራሴን ያስተማርኩ - በሕይወት ጠመኔ፤
አንቺ “ፈልጉኝ” ባይ - እኔ ራሴን መሪ፣
አንቺ ላይሽ ፋኖስ - እኔ ውስጤ በሪ፤
ከመንገድሽ እሩቅ - መንገዴ ወስዶኛል፣
ሺህ ግዜ አግብተሽ - ሺህ ግዜ ብትፈቺ ምን ያናድደኛል?

በርቺ 😐
@eyadermoges

@getem
@getem
@getem
27👍21😁2🔥1
የማመንታት ፍቅር
ልሂድ ወይስ ልቅር

(ያለበት)

ጓዝሽን ጠቅልለሽ በስንብትሽ እለት
ደግሞ ተመልሶ
ከበቃኸኝ በኃላ ካልበላሁ ማለት

(ምን ይሉታል አሁን)

ተፍተሺኝ አንቅረሽ
ጥላቻን አፍቅረሽ
ባፍንጫሽ ወጥቼ
ለፍቺያችን ድግስ የወይን ጠጅ ጠጥቼ

(ችርስ ተባብለን)

ወይ መተሽ አትመጪ ወይ ቀርተሽ አትቀሪ
ድንገት ትገኛለሽ ለፍቅር ከፊቴ ስትደነቀሪ

By @Absari_seven

@getem
@getem
33👍11🔥4
‎ቆርጦልኝ ነበረ ነግሬሽ የልቤን ወድሻለሁ ብዬ
‎የምትወጂኝ መስሎኝ ስጠብቅሽ ቀረሁ ካደርኩበት ውዬ
‎ነካክተሽ ነካክሽ ልቤን አደረግሽው የፍቅርሽ ምርኮኛ
‎የማትወጂኝ ከሆን ለምን ቀሰቀስሽው ይቅር እንደተኛ

‎አይቀርም አንድ ቀን ያፈቀረሽ ልቤ የጎኑን ማግኘቱ
‎ህይወት ይቀጥላል ምን ልቤ ቢደክም አንቺን በማጣቱ
‎አገኘሽኝ እንጂ ሆኜ ያንቺ ወዳጅ
‎ከፍቅርሽ አለም ውስጥ
‎ሳላውቀው ገብቼ እንደ ባህር ሰርጓጅ

‎ግን ...

‎ያሳሰበኝ ፍቅር
‎ካንቺ ስር ያዋለኝ እንዲህ እንደከረረ
‎ሌላ ሲያይሽ ጊዜ ቀንቼ ነበረ
‎አፈቀርኩሽ ያልኩት
‎የኔ ያልኩትን ሰው በሌላ ሲታቀፍ
‎እንዴት ብዬ ልለፍ

‎የመነጠቅ መንፈስ
‎ውስጤን እንገብግቦት አላመጣሁሽም
‎እውነቱን ስነግርሽ
‎ቀንቼ ነው እንጂ አላፈቀርኩሽም

‎አልልሽም ይህን ቃሌን ድፍረት የለኝ የምልበት
‎ያጠፋዋልና የወንድነት ልኩን ይህን ያልኩሽ እለት

‎እንደገባኝ ቢሆን ከዚህ ሁሉ ነገር
‎ቅናት መንፈስ እንጂ አልነበረም ማፍቀር



‎ ዮርዳኖስ @JorDanos7

@getem
@getem
@getem
👍3528🤩6🔥3
2025/10/20 07:48:00
Back to Top
HTML Embed Code: