Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥀🌸 اللهم صلى وسلم على سيدنا ونبينا وحبيبنا محمد صلى الله عليه وسلم🌸🥀 🤎💖🖤
🔹የአንድ ሰው የሰብዓዊነቱ ምልዓት በሁለት መሰረቶች ላይ የተካበ ነው። ሐቅን ከባጢል ለይቶ ማወቅ እና ከባጢል ሸሽቶ ሐቅን ማስቀደም።

🍂ኢብኑል ቀይዪም
ወህብ ኢብኑ ሙነቢህ የሚከተለውን ገራሚ መልዕክት አስተላልፈዋል፦
«የገንዘብ ጥጋብ እንዳለ ሁሉ የኢልምም ጥጋብ ኣለው» አሉ።
አዝ-ዙህ ሊልዒማሚ አህመድ(516)

አንዳንድ ደህና ገንዘብ በእጃቸው ይዘው የመያውቁ ጠባቦች የተወሰነ ገንዘብ በእጃቸው ሲገባ ሰማይ ምድሩን ሳይቀር በገንዘባቸው የሚገዙት ይመስላቸዋል፣ጥጋባቸውም ጣሪያ ይነካል።

የተወሰኑ ሰዎች ዘንድ ዕውቀትም እንደዝህ ዓይነት ነገር ኣለው።ምንም የማያውቁና ባዶ የሆኑ አካላት በሆነ ርዕስ ላይ አንድ ዓሊም የፃፈውን ሪሳላ ካነበቡ ራሳቸውን ልክ እንደ ትልቅ ዓሊም አድርገው በመቁጠር እጅግ ከታፈሩ ሊቆች ተርታም አድርገው ያስባሉ፣ይሄ የትንሽዬ ዕውቀት ስካር እንጂ ሌላ ምንም አይደለም።

ይሄንን ስል አንድ ነገር ትዝ ኣለኝ፣በልጅነታችን World ቴኳንዶ መሰልጠን በጀመርን ሰሞን እርስ በርስ በቃላት ሁላ ሳንግባባ ስንቀር መጀመሪያ የምናደርገው ነገር እግር ማንሳት ነበር፣ሃሃሃ። ብዙዎቻችሁም ላይ ያለፈ ጉዳይ ይመስለኛል።ከዝያም በሂደት እየተሰራ ቢጫ፣አረንጓዴ፣ሰማያዊ...ብላክ ቀበቶ ጋር ስትደርስ ግን ሰው ቀና ብለህ ለማየት እንኳን ማፈር ትጀምራለህ።ስፖርትም ለጤንነትና ራስን ለመከላከል እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው ትረዳለህ።

አሁን አሁን ከሆነ ጎሬ ወጥተው የሆነች ነገር ማንበብ ሲጀምሩ፣ሀሳቡ እንኳን በአዕምሬቸው እስኪብላላ ሳይጠብቁ በጥድፊያ ወደ ሚዲያ (እንደ ቲክቶክ ባለ) መጥቶ መለፈፍ እየተለመደ ነው።ሰው እውቀቱ በጨመረ ቁጥር እየተረጋጋ ስሄድ፣ባዶ ጋን የሆኑት ግን Google አድርገው በሆነ ነገር ላይ ተራ(ሙዕተበር) ያልሆነ ኺላፍ እንኳን ኣለ ከተባሉ እሷኑ እስከሚያሰራጩ ይጨንቃቸዋል።

ሁላችሁም ማወቅ ያለባችሁ አንድ ነጥብ ኣለ፦ አልአቅላኒየቱልሙዓሲራ( አሁን ሚዲያውን እያወኩ ያሉት ዓይነቶቹ) ዋነኛ አላማቸው ሐቅን ይፋ ማድረግ አይደለም።ይሄ ያልታሰበበትና በድንገት የተጀመረ ጉዳይ ከመሰለህ አታነብም ማለት ነው፣ሰዎቹም ሐሳባቸውን ከዬት እንደሚቀዱ አታውቅም ማለት ነው።አሁን እነ ኤገሌ የሚለፍፉት አጀንዳ በአረቡ ዓለም እንደ ግብፅ፣ሊባኖስ፣ሲሪያ... ዘንድ በአስራ ዘጠነኛው ክፍለዘመን ፍንትው ብሎ የነበረና በ Orientalistቶች መሪነት ሙስተግሪቦቹ ያቀነቅኑት የነበረ ጉዳይ ነው።መቼም ኢስቲሽራቅ፣ኢስቲግራብ...ወዘተ ለኛ አድስ ሊሆኑ ይችላሉ።ግን ሂነው ያለፉ አሁን ለደረስንበት ዝቅጠትም ትልቁን ሚና የተጫወቀቱ የምዕራባዊያን ሴራ ጥንስሶች ናቸው።

ከላይ እንደ ነገርኩህ ዋና ኣላማው፦ በኢስላም ምንም ሰዋቢት እንደሌለና በሁሉም መስዓላዎች ላይ ኺላፍ ያለ በማስመሰል፣ሁሉም ሙስሊም በመሰለው ርዕዮተ-ዓለም እንዲጓዝና የተሳሳተ መስሎት ተውበት ከማድረግ ይልቅ ኢስላምን ከዘመኑ ተጨባጭ ሳይጋጭበት እንደፍላጎቱ እየጠመዘዘው እንዲጓዝ ማስቻል ነው።አሁንስ የተወሰነ ተረዳችሁ?።

ልክ ቅድም እንዳልኳችሁ እንደ ቴኳንዶ ቤት ጀማሪዎች እግር ማንሳት አይነት ማለት ነው።ለሙስሊም ወንድሞቼ እኔ በግሌ አሁንም የምለው «አቋማችሁን ሚዲያ ከሚደረግ ውርርድና ክርክር እንወስዳለን» ብላችሁ የምታስቡ ወንድሞቼ አደጋ ላይ መሆናችሁን እወቁ ወላሂ።ዲናችሁን በዝህ ልክ ርካሽና የማንንም ኢንቶፈንቶ ሰምታችሁ የምትለዋውጡት ተራ ነገር ካደረጋችሁት ወላሂ ታሳዝናላችሁ።

ዲንህን ለመረዳት፣ቁርዓንን በአግባቡ ለመገንዘብ፣ሐዲስን በቀደምቶቹ አካሄድ ለመማርም ሆነ በአጠቃላይ ኢስላማዊ ስብዕናን ለመላበስ እንደኳስ ግጥሚያ ሚዲያ ላይ መመልከት ብቻውን በቂ አይደለም።ጎንበስ ብለህ ትክክለኛ ዓሊሞች ጋር ቅራ።እነዝህ በሚዲያ የሚያወዛግቡህ ወሮበሎች፦ ከፊላቸው በስልጣን፣ሌላው በገንዘብ...ወዘተ ያኮረፉና ተሰሚነትንና የሚሹ ቁጣዑ-ጡሩቅ ናቸው።በኢስላማዊ ርዕሶች ላይ መከራከር ጥቅም ቢኖረው እነ ማሊክ፣ሀሰነልበስሪይ፣ኢማሙ አህመድ ...ወዘተ ያሉ ከተራራ የገዘፉ ሊቆች እምቢኝ አይሉም ነበር።እነዝህን የምታውቃቸው ከሆነ «መቼም እውቀት ስሌላቸው ነው» አትለኝም።

አስፈላጊ በሆነ ቦታ፣ከተገቢው ሰው፣መስፈርቱ ተሟልቶ...ወዘተ ከሆነ ኣዎ ክርክር ሊኖርም ሊደረግም ይችላል።ይሄንን መስለሓና መፍሰዳ የሚገምቱት ደግሞ ዑለማዕ እንጂ አክቲቪስቶች አይደሉም።ከኛ በዕቀትም በልምድም የሚበልጡት ዓሊሞች ፊትናን ማጥፋት የሚቻለው በተጃሁል ነው ካሉ እኛ ትንንሾቹም ከኋላቸው ነን።ያስፈልጋል ያሉን ቀን ያኔ እንተያያለን ኢንሻአላህ።

ኡስታዝ ሙከሚል ከማል
🔸 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“ይህ ገንዘብ ጣፋጭና ለምለም ነው። በሚገባ (በሐላል) ያገኘውና ተገቢ ቦታ ላይ ያዋለው ሰው እሱ ምንኛ ያማረ አጋዥ ነው። ያለ አግባብ (በሐራም) ያገኘው ሰው ደግሞ ምሳሌው ልክ በልቶ እንደማይጠግብ ሰው ነው።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6427
🥀🌸የጓደኛ ጥሩ አላህ ይወፍቀን 🌸🥀
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“በህዝቦቼ ላይ ከምፈራው ሁሉ ይበልጡኑ የሚያሰፈራኝ የምላስ አዋቂ (አንደበተርእቱ) የሆኑ ሙናፊቆችን ነው።”
📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 239
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥀🌸 اللهم صلى وسلم على سيدنا ونبينا وحبيبنا محمد صلى الله عليه وسلم🌸🥀 🤎💖🖤
የጁሙዓ ግዴታዎች ሱናዎችና ስነ- ስርዓቶች‼️
===============//==============
#ገላን መታጠብ
#ጥርስን መፋቅ
#ሽቶ መሻተት
#ፀጉርን ማሳመር
#ወደ ኢማሙ መቃረብ
#ከጁሙዓ ቡኋላ ናፊላ መስገድ
#ሱረቱ-ል ከህፍን መቅራት
#ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ
#በግዜ ወደ መስጂድ መጓዝና በእግር እየተራመዱ መሄድ
#ኹጥባ እስኪጀምር በዚክር፣ በቂርኣት ቢዚ መሆን
#ሰለዋት ማውረድ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
أهمية قراءة سورة الكهف يوم الجمعة |

الشيخ سليمان الرحيلي
حفظه الله
👉 ገንዘብ ከሚገዛቸው ነገሮች ይልቅ የማይገዛቸው ነገሮች የላቁና የበረከቱ ናቸው። ፍቅርን፣ ጤናን፣ ሰላምን፣ እውቀትን፣ መረጋጋትን፣ መልካም ስነ-ምግባሮችን .....የመሳሰሉ በገንዘባችን ገበያ ወጥተን መሸመት አንችልም። የሚያስቆጨው ግን ገንዘብ ለማግኘት ስንታትርና ሰርክ ስንጋጋጥ እነዚህን በገንዘብ የማይተመኑ አልያም የማይገኙ ውድ ስጦታዎች ማጣታችን ነው። እናም እያስተዋልን ሚዛናዊ እንሁን‼️
መልካምን ተናገሩ አትራፊ ትሆናላችሁ፤ ክፉን ከመናገር ተቆጠቡ ሰላም ትሆናላችሁ።

ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
ሁሉም በዙርያዬ ያለ ሰው ስለኔ ያስብ ይሆን? ምን እያለ ነው? ብላቹህ አትጨናነቁ በዋናነት ከአላህ ጋር ብቻ ያላቹን ነገር ብቻ አበጃጁ። ሰው ሰው ነው። በራሱ የተጨናነቀ በርካታ መከራና ብዙ የሚያሳስበው የኑሮ ኮተት ያለበት ጨርቅ ጣል አድርጎ ዞር ዞር የሚል ፍጡር ነው ። በተለይ ላጤ የሆነ ብዙ ልብ የለውም። እናም focus on your self በራስህ ላይ በርታ ! ተጨነቅ! ጃል!።😍
እውነት ዘላለም የሚፈለግ የጠፋ እቃ አይደለም። እውነት ሰዎች በማስረጃ ካወቁት በኋላ የሚይዙትና የሚፀኑበት ነገር መሆን አለበት።
__
ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
አንድትን ቃል ተናገረ፤ መልካም ስራዎቹን አሰረዘችበት።

እሷም
አላህማ እከሌን ፍጹም አይምረውም በማለቱ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌸🥀 Beautiful View Haram Makkah Saudi Arabia🖤♥️🤎 🥰🤲🕋
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥀🌸 اللهم صلى وسلم على سيدنا ونبينا وحبيبنا محمد صلى الله عليه وسلم🌸🥀 🤎💖🖤
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ይላሉ፦
“አላህን በጌትነት፣ ኢስላምን በሀይማኖትነት ሙሀመድን በነቢይነት ወዶ የተቀበለ፤ ጀነት ለሱ የተገባች ሆነች።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1884
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአላህ ታጋሽነት ወደር ዬለው። አላህ ጀሓነምን ለከንቱ አልፈጠራትም እነዚህ እርኩሶች በነሱ ቤት በፍልስጤማውያን እያላገጡና እያሾፉባቸው ነው።
2025/10/27 16:04:28
Back to Top
HTML Embed Code: