Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"Cidea Tab"
Battery 10000 MAP
Storage 512GB
RAM 8GB
12 android
10 inch full HD touch screen
2 SIM, 1 memory, 5G network

Additional gifts included
Teb cover
Mini speaker
Bluetooth Smart keyboard
Wireless mouth
Tab pen
Airpod
ይሄን ሁሉ በአንድ ላይ በማይታመን ዋጋ 15,000 ብር (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ)
ለማዝዝ በዚህ ስልክ ይጠቀሙ
+251912319263 ቤትዎ ድረስ ያለምንም የማድረሻ ክፍያ (free delivery) እናመጣልዎታለን
#ችግሩ_አንተ_ራስህ_ነህ!

በሕይወት ውስጥ የሚያናድዱ፣ የሚያበሳጩ፣ የሚያሳዝኑና የሚያበሽቁ ሰዎችና ሁኔታዎች የመኖራቸውን ያህል፤ አነቃቂ፣ ተስፋ ሰጪ፣ አጋዥ እንዲሁም ለሕይወት አላማና ትርጉም የሚሰጡ ሰዎችና ሁኔታዎችም ይኖራሉ።

ከስሜቶችህ ግማሹን ብቻ እያስተናገድክ ከቀጠልክ፣ ራስህን ባጭር ታስቀረዋለህ። የሚያበሳጭና የማይመች ነገርን ሊያመጣ የሚችል ማንኛውንም ሁኔታ ሲያጋጥምህ፣ ያንን ስሜት ለመቋቋም የሚያስችል መሳሪያ ስለሌለህ ሁኔታውን ለማስወገድ ከመንገድህ ወጥተህ መሄድ ትጀምራለህ። ይህ ማለት በመጨረሻ ሕይወትህን ወደተሻለ ሁኔታ የሚቀይሩትን አጋጣሚዎችና ድርጊቶች ማስወገድ ትጀምራለህ ማለት ነው።

በተጨማሪም ስሜቶችህን ማስተናገድ አለመቻል ማለት፣ ከእነሱ ጋር ተጣብቀሃል ማለት ነው። ቁጣህንና ሀዘንህን እንዴት ማስወገድ እንዳለብህ ስለማታውቅ በእነርሱ እንደተሞላህ ትቀመጣለህ። ግማሹን ስሜትህን ብቻ ማስተናገድ የምትችል ከሆነ፣ በመጨረሻ የምትኖረው ከምትፈልገው ሕይወት ግማሹን ብቻ ነው።

#ችግሩ_እና_ተራራው_አንተ_ራስህ ነህና ረጋ ብለህ ሙሉ ስሜትህን አስተናግድ፤ ለዚህ ደግሞ ተራራው ራስህ መሆንህንና እንዴት ደልዳላ ሜዳ እንደምታደርገው መጽሐፉ ያስተምርሀል።

መጽሐፉን በአማርኛም በእንግሊዝኛም ገበያ ላይ ያገኙታል።
ውሻ ጮኸ ብለህ መልሰህ አትጮህበትም

ከ1930 ዓ.ም ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ ገዥ የነበሩት ኃይለ ሥላሴ በአንድ ወቅት ልጅ ተፈሪ የሚባል ወጣት ነበሩ።

ከተከበረ ቤተሰብ የመጡ ቢሆንም፣ ዙፋን የመውረስ ተተኪነት መስመራቸው በዙፋን ላይ ከነበሩት ንጉስ ዳግማዊ ምኒልክ ብዙ የራቀ ነበርና ወደ ስልጣን የመምጣት እድል አልነበራቸውም። ነገር ግን ከልጅነታቸው ጀምሮ በራስ የመተማመን መንፈስ የሚያሳዩና  በዙሪያቸው ያሉትን ሁሉ የሚያስገርም ንጉሳዊ ባህርይ የነበራቸው ነበሩ፡፡

ከዓመታት በኋላ በ1936 የጣሊያን ፋሽስቶች ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ እና አሁን ኃይለስላሴ እየተባሉ የሚጠሩት ተፈሪ በስደት እያሉ የሀገራቸውን ጉዳይ በተመለከተ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ ንግግር አድርገው ነበር።

በተሰብሳቢዎቹ ውስጥ የነበሩት ጣሊያኖች ጸያፍ ስድብ ሲሰድቧቸው፣ እሳቸው ግን ምንም ያልተነኩ መስለውና ክብራቸውን እንደጠበቁ ነበሩ። ይህም እሳቸውን ከፍ ያደረገና ተቃዋሚዎቹን ይበልጥ ጋጠ ወጥ ሆነው እንዲታዩ ያደረገ ክስተት ነበር፡፡

አንተም ልክ እንደ  ኃይለ ሥላሴ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች  ውስጥም ብትሆን ምንም ነገር ሊነካህ እንደማይችል ሁን። መስከንህን በውሻዎች ጩኸት አትረብሸው። ክብርህን ለማንም አሳልፈህ አትስጥ፤ ከተጨቃጨቀህ ሁሉ ተጨቃጭቀህ፣ ከሰደበ ሁሉ ጋር ተሰዳድበህ ወደ ታላቅነት አትደርስምና።


ጄዚ ፣ካንዬ ዌስት ፣ፊደል ካስትሮ ፣ጆርዳን ፒተርሰን ፣ባራክ ኦባማ ፣ኤለን መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ኃያል ግለሰቦች ለስኬታቸው እንደምክንያት የሚጠቅሱት ነው። እናም አንተም ያቀድከውና ያሰብከው የስኬት መዳረሻ ላይ ለመውጣት ይህን መጽሐፍ እንደ መሰላል ተጠቀመው፡፡

48ቱ የኃያልነት ሕጎች (THE 48 LAWS OF POWER) ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ!!!
በንግድ ስራህ እንዴት ውጤታማ መሆን ትችላለህ?  ብዙ ሰዎች በመንገድህ የሚመጡትን ማንኛውም እድሎችን ያለ ርህራሄ መጠቀም አለብህ ይላሉ። እንደነሱ ከሆነ፣ ለንግድ ስራህ ዋናው ነገር ለራስህ የሚበጅህን ነገር ማግኘት ላይ ማተኮር ብቻ ነው።

ይህ አመለካከት ምንም እንኳን ታዋቂ ቢሆንም፣ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ነው። ንግድህ የሚሳካው ሌሎች የሚፈልጉትን ስታውቅ እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት ስትሞክር ነው። ባጭሩ ለመግለፅ፣ መንታፊ መሆንህን አቁመህ ለጋስ መሆን መጀመር አለብህ።

ዘ ጎ-ጊቨር ሌሎችን ማስቀደም ያለውን ጥቅም ያሳይሃል ምክንያቱም ብዙ በሰጠህ ቁጥር በምላሹ ብዙ ታገኛለህና።
በቅርቡ በጥራት ታትመው ለገበያ የሚቀቡ ሁለት ድንቅ መጽሐፍት!!! Coming soon.
The Five Dysfunctions of a Team

ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ የተወሰኑ ቡድኖች አባል ነን። የአንድ ቡድን አባል ወይም መሪ ስንሆን ለምን ቡድናችን የተፈለገውን ውጤታማነት አላመጣም? እንዴት ቡድናችንን ውጤታማ ማድረግ እንችላለን? ብለን ከተነሳን ይህ መጽሐፍ ያስፈልገናል።

The Five Dysfunctions of a Team
(ዘ ፋይቭ ዲስፈንክሽንስ ኦፍ ኤ ቲም) የDecisionTech ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆነችው ካትሪን ፒተርሰን ከባድ የአመራር ችግር ሲገጥማት የሚያሳይ ታሪክ ፈጥሮ፣ ለሃያ ዓመታት ያህል አንባቢዎችን ሰቅዞ የሚይዝና እሙን የሆነውን ውጣውረዷን ሲያስነብብ ቆይቷል።

ይህ መጽሐፍ ግማሹ  የአመራር ክህሎት ታሪክ ግማሹ ደግሞ  የንግድ ሥራ መመሪያ ነው።  ይህ የቡድን ስራ ላይ ወሳኝ ማጣቀሻ የሆነው የፓትሪክ ሌንሲዮኒ መጽሐፍ፣ ምርጥ የተባሉት ቡድኖች እንኳ ውጤታማ መሆን የሚያዳግታችው አምስቱ የባህርይ ዝንባሌዎች ሲኖራችው መሆኑን በደንብ ያሳየናል። እነዚያን ጉድለቶች ለማሸነፍ እና ሁሉንም የቡድን አባላት ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲቀዝፉ ለማድረግ የሚያስችል ሞዴል እና መመሪያ ይሰጠናል።

ዛሬም፣ The Five Dysfunctions of a Team የሚሰጠን ትምህርቶች ከምንጊዜውም በበለጠ አስፈላጊ ናቸው። ከሀያ አመታት በኋላም ከፍተኛ ሽያጭ ያለው የቢዝነስ መጽሐፍ ነው።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Modvel Knee Braces for Knee Pain Women & Men - 2 Pack Knee Brace for Knee Pain Set, Knee Brace Compression Sleeve, Knee Support for Knee Pain Meniscus Tear, ACL & Arthritis Pain Relief,Pink M. Size XL

@Guramayelie   0912319263
               ዋጋ = 3800 ብር
(በእውቀቱ ስዩም)

የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳለን መሰለኝ፤ የሆነ አርብ ቀን ፥  ስድስት ኪሎ ባህል ማእከል  ውስጥ እንደ ልማዳችን  ታድመናል፤ የቀኑ የክብር እንግዶች ወደ አዳራሹ ሲገቡ ጭብጨባውና ፉጨቱ ደመቀ፤ የመጀመርያው  ፥ እግሮቹን እየጎተተ የሚራመድ ፥ የተወቀጠ እሚመስል ኮት  የለበሰ ሰውየ ነው፤  ዘናጭ፥ ፊቱ ላይ ፈገግታ የማይለየው ደልዳላ ወጣት ከሁዋላው ተከትሎታል፤

የመጀመርያው ሰውየ ስብሀት ገብረእግዚአብሄር፥ ሁለተኛው ፍቅረማርቆስ ደስታ እንደሚባሉ ተረዳሁ ፤

ዝግጅቱ ተጠናቆ ታዳሚው መበተን ሲጀምር እኛ   ተማሮች በሁለቱ ደራሲያን ፊት ተሰልፈን ደብተራችን ላይ ፊርማቸውን ለማስቀረት መራኮት ጀመርን ፤

በመሀል፥ ፍቅረማርቆስ ከተደናቂነት ወደ አድናቂነት ዞሮ ፥ስብሀትን  ፊርማ ጠየቀው፤ ስብሀት፥ አሁን በማላስታውሰው  መጽሀፍ ገጽ ላይ “ለወጣቱ ደራሲ” ብሎ ፈረመለት፤

አብዛኛው ደራሲ የብእሩን አፍ የሚፈታው ስለ ተወለደበትና ስላደገበት አካባቢ በመጻፍ ነው፤  ፍቅረማርቆስ ከዚህ በተለየ መንገድ ሄደ!  ” ኢትዮጵያ በረሳቻቸው እና ኢትየጵያን ረስተው በሚኖሩ ብሄረሰቦች’ ኑሮ ዙርያ የሚያጠነጥን ልቦለድ ጻፈ፤ ብዙ ሰው ወደደው! በብዙ አንባቢያን ፥ ወጣት ደራሲያን፥ ዘፋኞች ላይ ሳይቀር ተጽእኖ ፈጠረ፤


አመቶች አለፉ፤

ከእለታት አንድ ቀን ፥ ፍቅረማርቆስ ደስታ ፥ ከመለስ ዜናዊ እጅ ሽልማት ሲቀበል  በቲቪ አየሁ፤ ካልተሳሳትሁ፥ ከበአሉ ግርማ ቀጥሎ  መለስ ያከበረው የመጀመርያው ደራሲ ይመስለኛል ፤ብዙ አልቆየም፤ አገር ጥሎ መሰደዱን የሚገልጽ ዜና ሰማን፤

ነገሩ ግራ  አጋብቶኝ ፥ ካንድ ወዳጄ ጋራ ስናወራ፥

“ ፍቅረማርቆስ ፥ ምን  ብሎ ነው ጥገኝነት የሚጠይቀው ?” ስለው

“ መንግስት እያሳደደ ይሸልመኛል ፥ ብሎ ነዋ”  ብሎ መለሰልኝ ፤

ዘመናት ሳያስፎግሩ በጽጥታ  ነጎዱ!

በቅርቡ፥ ፍቅረማርቆስን አሜሪካን አገር  ቦስተን ውስጥ ወዳጆቼ ብሩክ እና ሕይወት ቤት ውስጥ  አገኘሁት፤ ግለታሪኩን  ጽፎ እያጠናቀቀ ነበር፤  መጽሀፉን ትናንት ማታ ጀመርኩት፤ እየጣመኝ፥ ገጾች ቶሎ እንዳያልቁብኝ እየቆጠብሁ ዛሬ ረፋድ ላይ ጨረስኩት፤

“የሚሳም ተራራ “  ግለታሪክ ነው፤ ግን በተለመደው መንገድ የሰውየውን ህይወት ከልደት እስከ ደረሰበት የሚተርክ አይደለም፤ ካሳለፈው ሕይወቱ ውስጥ የተወሰኑ  የትዝታ ቅንጣቶችን ቆንጥሮ  ይተርክና ኑሮ ያስጨበጠውን እውቀት ያካፍለናል ፤

ፍቅረ ማርቆስ በጊዜው  ፥ ተወዳዳሪዎቹ  ያልደረሱበት የሀብት እና የዝና  ከፍታ መውጣት ችሏል ፤ ከዚያ ደግሞ፥ ያልሰመረ ትዳር ፥ከስደት ጋር ተባብሮ   ወደ አስፈሪ አዘቅት  አውርዶታል፤ ግን ያሳለፋቸው ፈተናዎች  መራር አላደረጉትም፤ እንዲያውም እውቀት፥ ብስለትና የህይወት ፍቅር ጨምረውለታል፤

ለማንኛውም ሸጋ መጽሀፍ ማንበብ የናፈቃችሁ ባለንጀሮቼ  “የሚሳም ተራራን “  ጋበዝኳችሁ፤ መልካም ሰንበት!
የተወዳጁ ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ አዲስ መጽሐፍ "የሚሳም ተራራ" (ግለ ታሪክ) እና ቆየት ያሉት ሶስቱ ስራዎቹ በድጋሚ ታትመው ለገበያ ቀረቡ።

የሚሳም ተራራ ዋጋ 410 ብር
ከቡስካው በስተጀርባ ዋጋ 310 ብር
የዘርሲዎች ፍቅር ዋጋ 280 ብር
ኢቫንጋዲ ዋጋ 350 ብር
“ሰው የቱን ነው? አንድ ሰው ማንን ነኝ ብሎ ነው መናገር የሚችለው? 
የመረጠውን? እርሱ ብቻ የፈለገውን? ወይንስ ሰው ሁሉንም ነው? የኖረውን 
ግብስብስ ሁሉ? ከሆነስ የትኛው ነው ልኩ? በእርግጥ ሕይወት አንድ ቀን 
አይደለችም። የአንድ ቀን ውሎም አይደለችም። ትላንት ዛሬና ወደፊት ያላት 
ናት። ታዲያ ሁሉንም እንዴት በአንዴ መሆን ይቻላል? ማን በድፍረት ‘እኔ 
ይህን ነኝ’ ብሎ ስለራሱ ይናገራል? ‘ክፉ ሰው፣ መልካም ሰው’ ሊባል 
የሚችል ሰው ዓለም ላይ አለ?”
ፓርታ፥ ገጽ 194

በቅጡ አልተዋወቅንም። የወረስነው አንዳች ነገር ሳይኖር ‘ወራሾች’ ግን ተብለናል። ሞት ሞት ሆኖ አልተሰጠንም። ሞትን ግን ሞት ያደረግነው እኛው ነን። በሌሎች ውስጥ ራሳችንን አልሆንም። ከመለስነው ዓለም ይልቅ ያልመለስነው ይበዛል። መቼ እና እንዴት ጎዶሎነታችን እንደሚያበቃ እንጃ። መሆን ግን አልነበረበትም። ...ሞታችን ሞት የሆነው በነጠላነታችን፣ በጎዶሎነታችን፣ ባለመደገማችን ውስጥ ነው። የሐሳብና የዕውቀት ተነጥሎ ነው። ለብቻችን፣ ተደብቀን ያደረግነው ይበዛል። ለብቻችን ተደብቀን ያሰብነው ብዙ ነው። የሐሳባችን ጎተራ ምስጢራዊ ነው። የተጋራነው ሕልም የለም። ይህ ሞታችንን ሞት አድርጎታል።
ፓርታ፥ ገጽ 190
"በእውነቱ የዚህ ታሪካዊ:ሃይማኖታዊና ጥበባዊ በአእምሮ ልህቀት የሰውን ልጅ ራሱ አእምሮውን በዚህ ብሩህ ጎዳና እንዲመራ የጥንቱን የኢትዮጵያ ነገር ከአሁኑ ጋር አዋህዶ እያሰላሰለ:በምክንያታዊ መሳጭ ጭብጦች እንደ እንዝርት የሚሽከረከር የትንሳኤችን መነሻና መድረሻ መጽሐፍ በመተረኬ ታላቅ ኩራትና ደስታ ይሰማኛል።
"ድራጎን በኢትዮጵያ ሰማይ " ሰው ርዕሱን አይቶ ሰው በትክክል አውሬ ድራጎን ይጠብቃል። የብዙ ሰወች አጻጻፍ ርዕሱ አይቶ የሚገመት መጽሐፍ ነው የሚጽፉት።
እዚህ ርዕስ ውስጥ ከርዕሱ ተቃራኒ ብቻ ሳይሆን ያልገመትናቸው በርካታ ሀሳቦች ታጭቀዋል።
አንድ የተረዳሁት እውነት ደራሲው ርዕስ ሲሰጥ ያመነበትንና የራሱን መንገድ ተከትሎ መጓዝ መቻሉ ነው።
ለአዲስ ትውልድ የተጻፈ ገጸ በረከት ብየዋለሁ።

ጋዜጠኛና ተራኪ ተሾመ ሽፈራው::
ቼዝ ለምትፈልጉ ሰዎች
3800 ብር
የቆዩ መጽሐፍት በብዛት ያላችሁ ሰዎች መሸጥ የምትፈልጉ ከሆነ ያናግሩን ያሉበት መጥተን እንገዛዎታለን። መጀመሪያ ግን የመጽሐፍቶቹን ፎቶ ይልኩልና።

@Guramayelie  
0912319263
2024/05/03 02:43:29
Back to Top
HTML Embed Code: