ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ ውሳኔ
1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ

፩ኛ. አባ ሳዊሮስ
2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ
3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 26 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በማኅህበራዊ እና በብሮድካስት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡

በመሆኑም፡-
ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤

ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡

ሐ. በነዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ አውግዞ በለያቸው ግለሰቦች ይመሯቸው በነበሩ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ አገልግሎት በማከናወን ሀገረ ስብከቱን የሚመሩ ብፁዐን አባቶችን

፩. ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት
፪. ለኬንያ፤ኡጋንዳ፤ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ሀገረ ስብከት
፫. ለኢሉ አባቦራ እና በኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
፬. በሰሜን አሜሪካ ለሜኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት
፭. ለጉጂ፤ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት
፮. ለምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ገዳም

በአባትነት የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመደቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

 ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤

2. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሺመት አግኝተናል፤ ተሸመናል እያሉ የሚገኙ 25 መነኰሳት በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተ ክርስቲያን ተለይተዋል፡፡

3. ከነዚሁ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አባ ጸጋዘአብ አዱኛን ከቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ ስብሰባ በፊት የቀኖና ጥሰቱንና ሕገ ወጥ አድራጎቱን በመረዳትና በመጸጸት ድርጊቱን በመቃወም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ባቀረቡት የይቅርታ አቤቱታ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይቅርታውን የተቀበላቸው ሲሆን እንደሳቸው ሁሉ ከላይ የተወገዙት 25 ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን እንገልጻለን

4. በዚህ ጸረ ቤተ ክርስቲያን እና ኢ-ቀኖናዊ ድርጊት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ እየኖሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወይም በቦታው በመገኘት የጥፋት ድርጊቱ ተባባሪ የሆኑ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞችን በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተገቢውን ክትትልና አስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲሰጥ፤

5. ይህን ታሪክ ይቅር የማይለውን ሕገ ወጥ አድራጎት እና የቀኖና ጥሰት በሐሳብ፤ በገንዘብ እና በሌላ በማንኛውም ሁኔታ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ እና በማድረግ ላይ ያሉ ማናቸውም ተቋማት እና ግለሰቦች ከዚህ ሕገ ወጥ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ እያሳሰበ ይህ ባይሆን በሕግ አግባብ ተገቢው እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. አሁን የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ ዝርዝር ጥናት እና የመፍትሔ ሐሳብ የሚያቀርብ አንድ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲሰየም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ያሳለፈውን ውሳኔ ከክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጀምሮ በየደረጃው ላሉት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች እንዲከናወኑ እና ይህ ውሳኔ ከሸኚ ደብዳቤ ጋር እንዲደርሳቸው ተወስኗል፡፡

10. ይህን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ክፍለ ዓለማት ለሚገኙ የቤተ ክርስቲኒቱ አገልጋዮች እና ምእመናን የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መድረኮች እንዲካሔዱ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ በማእከል የአህጉረ ስብከት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ታላቅ የንቅናቄ እና የግንዛቤ መድረክ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. እነዚህ ግለሰቦች ከሚሰጡት የተሳሳተ መረጃ አንዱ እኩይ ተግባራቸው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ማስመሰል ሲሆን ይኽ ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የኦሮሞ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ

ጥር 18 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በአዲሱ ባስ የተሳፈረ ሰዉ ምስክርነት !
****************. 🙈 😄
ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር።
...
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ። በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።
...
በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውኑ ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው። በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።
...
ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።
...
ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።
...
በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።
...
ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል። የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።
...
በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ 60 60 ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መኔገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል። Thank you አዴክስ ጭሷ!

ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማዶ :))

           @dagmawi dagmawi
ይህች አንዲት ፍሬ ልጅ በእልህና ሲቃ ውስጥ ሆና የዛሬ አሳዛኝ ሁነትን የተጋፈጠችበት አጭር ቪዲዮን አየሁ። በቪዲዮው ይህች አንዲት ፍሬ ልጅ በፖሊስ ተግባር ተናዳ፣ ተበሳጭታ፣ በእንባ ሲቃ ውስጥ ሆና የጠላት ወረዳ በድንገት እንደገባ ሁሉ ሰዉ የጪስ ቦምብ ተወርውሮበት ሲደበደብና ሲሮጥ እንዲህ ትላለች፣

"ቅዱስ ጊዮርጊስ ያድናችኋል፤
አትሩጡ ፈረሰኛው ይመጣል።
እንደዚህ እንዳስለቀሱን አይቀርም"

ይህን ካየሁ በኋላ፣

ልኩራ? ልደነቅ? ልዘን? ላልቅስ? ተስፋ ልሰንቅ፣ ተስፋ ልቁረጥ፣ በሀገሬ ሁኔታ ሆድ ይባሰኝ?

ይህች አንዲት ፍሬ ልጅ፣ የአድዋ ድል በዓልን ለማክበር በሄደችበት የተመለከተችው ጭካኔ እምነቷን፣ ሀገሯን መውደዷን፣ እልህና ተስፋዋን፣ ጀግንነቷን በአንድነት ወለል አድርጎ አሳየኝ።

የስርዓቱን የሞራል መሰረት የነቀነቀ ሆኖ አገኘሁት።

በልጅቷ ላይ ያየሁት የመንፈስ ወኔ የሚያስቀና ነው። እምነትና ተስፋዋ ምድር የሚያርድ ነው።

የስርዓቱን የሞራል መሰረት ነቀነቀችው

መንግስት ከዚህች ልጅ ጋር መጋጠሙ እጅግ የሚያሳፍር ነው

MuKtarovich Ustanova
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለትግራይ ክልል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች
=======#=======

ሰኞ ሐምሌ 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ለደረሰበት የትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ እና ለመልሶ ግንባታ የሚውል የ 20 ሚልየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የተመራውና የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአገር ሽማግሌዎችና ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች ያሉት የሰላም ልዑክ፤ ይህንን ድጋፍ ለማስረከብ እና በትግራይ ክልል ከሚገኙ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ለመወያየት ወደ መቐለ ማቅናቱ ይታወቃል፡፡

ቅዱስነታቸው ልዑካኖቹን መርተው መቀሌ ዓለም ዓቀፍ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፤ የትግራይ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የፈቀደውን ሃያ ሚሊዮን ብር የሰላም ልዑኩ ለክልሉ ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አስረክቧል፡፡

በድጋፍ ርክክብ መርሐ ግብሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ልዑካን ቡድኑ ተገኝተዋል፡፡
"ዛሬ የተሾማችሁ ኤጲስ ቆጶሳት ቤተሰብን ፣ ዘውግን ፣ ብሔርን እና ዘመድ አዝማድን ብቻ ሳይሆን ራሳችሁንም ጭምር እንድትክዱ እናዝዛችኋለን ፤ አደራም እንላችኋለን ''
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በዛሬው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መርሐ ግብር ላይ ካስተላለፉት የተወሰደ

ቦ እዝነ ሰሚዐ ይስማዕ፦ የሚሰማ ዦሮ ያለው ይስማ

የቅዱስ አባታችን ለዛሬው ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ማሳሰቢያ/ ማስጠንቀቂያ ይሆን ዘንድ ከላይ ያስቀመጡት ዐቢይ መልእክት ወንጌልን መሠረት ያደረገ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ፣ በማርቆስና በሉቃስ ወንጌላት ተመሳሳይ ዐውድ ያላቸውን መልእክታት ለሐዋርያት አስተምሯል። ይኸውም፦

ዘይፈቅድ ይትልወኒ ይጽላእ ነፍሶ ወያጥብዕ ወይንሣእ መስቀለ ሞቱ ወይትልወኒ። ወዘኢይፈቅድ ያድኅና ለነፍሱ ይገድፉ።
እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

ወዘሰ ገደፋ ለነፍሱ በእንቲአየ ይረክባ። ወምንተኑ ይበቊዖ ለሰብእ ለእመ ኩሎ ዓለመ ረብሐ ወነፍሶ ሐጒለ።
ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።

ወምንተኑ እምወሀበ ሰብእ ቤዛሀ ነፍሱ።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?

እስመ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይምጻእ ወስብሓተ አቡሁ ምስለ መላእክቲሁ። ወአሜሃ የዐስዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ።
የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።

አማን እብለክሙ ቦእለ ሀለዉ እምእለ ይቀውሙ ዝየ እለ ኢይጥዕምዎ ለሞት እስከ እመ ይሬእይዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው በስብሓተ አቡሁ።
እውነት እላችኋለሁ፥ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ።
(ማቴ.16፥24፣ ማር.8፥34፣ ሉቃ.9፥23)
_#ድኅነትን ለሚሻት ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ትድረስ።
ሲመተ መለካውያን ወሲሞናውያን ቢፈጸም፦
_ሐዋርያዊ የመዳን ሰንሰለት የተለየው በመሆኑ፣ ሿሚውም ተሿሚውም የእግዚአብሔርን የማዳን ሐዋርያዊ እጅ በመለካዊነት ላይ በመጫናቸውና በመቀበላቸው ፣ ድኅነተ ነፍስ ይቋረጣል።
_መስለው የተቀበሉት ሁሉ ከርቱዓዊ የመዳን መስመር የወጡ ናቸው።
_ከሁሉ በላይ የሆነች ርትዕት ሐዋርያዊት አንዲት ቤተ ክርስቲያን አለችን ማለት አይችሉም።
_ቤተ ክርስቲያን የባህርይ መገለጫዋ በማይፈቅደው አትገለጽምና።
_ሐዋርያዊ አንብርተ እድ በመለካዊ ራስ ላይ ቢጫን ልዮንን እንጂ ዲዮስቆሮስን አይተካም።
ጌታችን በአንብሮተ እድ ሐዋርያትን እንጂ ፈሪሳውያንን ባርኮ አልሾማቸውም።ሉቃ 24፥51።
_በዚያም በዚያም የምንሰማቸው የሿሚና ተሿሚ ሩጫዎች ቅብብሎሻዊ ጸጋ ክህነትን መታሪዎች ናቸው።
_በሁሉም ዘርፍ እየሆነ ያለው የእግዚአብሔርን የማዳን በር የሚዘጋ ሹመት ነው።
_ሲመቱ በምንም መስፈርት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያናዊ አይደለም ።
ባዶ ተቅዋማዊ ግን ሊሆን ይችላል።
_በሐዋርያት በር መግባት የሚቻለው በሐዋርያት የክህነት ቁልፍ ነው እንጂ በመለካዊ ሹመት አይደለም።
_ከዚህ በኋላ ማን ስቶ ማንንስ ማን ያወግዘዋል?በየትኛው የክህነት ሰንሰለት?
ይህ ሁሉ የሰይጣን ሩጫ ድኅነተ ነፍሱን ለማቋረጥ ነው።
_ጩኸታችን ይህ ከመሆኑ በፊት መስመሩ ይስተካከል በበሩ ይገባ።በማለት ነው።
" የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።"የማር 4፥23
"በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል ። በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል"ዮሐ 10፥1-4 ።
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።
**********************
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስትና በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ቁጥር 3 አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን አንድ አድርጋ የሰው ልጆች ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ ተጠምቀው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በመሆን ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ስትሆን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤ 

  ምንም እንኳ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት የዶግማ፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት ቅዱስ ሲኖዶስን እጅግ አሳዝኖታል፤ 

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሀገር አንድነት፣ ለፍትሕ፣ ለጥበብ፣ ለሕዝብ ትስስር፣ ለማኅበራዊ ዕድገት፣ ለጤና፣ ለሥነ-ምግባር መሠረትና ዐምድ፤  ሆና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈራች፣ የተከበረችና የተወደደች፤ ዕሴቷ እና ዕምቅ የዕውቀት ሀብቷ በምሁራን የታወቀ፣ በትምህርተ ዓለም ሳይቀር የተቀረጸ፤ በእውነተኛ ሊቃውንት የተመሠከረ፣ ቅርሶቿ የተመዘገቡላት ስትሆን፤ ከፍተኛውን ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር በቆመች፣ ከፖለቲካ በጸዳች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊትና ተቋምን የመናድ እንደሁም መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኗል፡-  

በዚሁ መሠረት፡-

ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ/ም በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም ውስጥ የተፈጸመውን ሕገወጥ የሆነ አስነዋሪ፤ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐምሌ 26ቀን 2015 ዓ/ም አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ አድርጓል፤ 

   ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደመ ክርስቶስ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ ቅዱሳት መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ሲመሰክሩ በዘመነ ሐዋርያት ቢጽ ሐሳውያን፣ በዘመነ ሊቃውንት የተለያዩ መናፍቃን፣… በየጊዜው እየተነሡ ሲፈታተኗት ኑረዋል፡፡ አሁንም በግልጽ እንደሚታየው ከውጭም ከውስጥም በተደራጁ ምንደኞች በመፈተን ላይ ትገኛለች፡፡ ይህንኑ በመረዳትም ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ፣ የሊቃውንት ጉባኤ፤ የሕግ አገልግሎት መምሪያና የህግ ባለሙያዎች አቢይ ኮሚቴ፤ የውጪ ግንኙነት መምሪያ፣ ካቀረቡት ዶግማዊ፣ቀኖናዊ፣ታሪካዊና ትውፊታዊ ሰነዶች በመነሣት የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ለማስከበር ያስችል ዘንድ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡
  
  በዚህም መሠረት ሐምሌ 16 እና 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በክልል ትግራይ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ገዳም ውስጥ በትግራይ ክልል በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፡-

1. አባ ኢሳይያስ
2 አባ መቃርዮስ
3. አባ መርሐ ክርስቶስ
4 አባ ጴጥሮስ  መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም 10 መነኮሳትን በእጩነት በመምረጥና ለዘጠኙ ህገወጥ ሲመት በመፈጸም፣ ሥርወ ትውፊት ዘሐዋርያት የሆነውን የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር በመካድ "መንበረ ሰላማ" የሚባል ህገወጥ መንበር በመሠየምና በህገወጥ መንገድ የሾሟቸውን ግለሰቦች ሊቃነ ጳጳሳት በሚመሯቸው በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ በመመደብ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አልፎ አንዲት ኩላዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሚከፋፍል፤ የሀገር አንድነትን የሚሸረሽር እና የሚያፈርስ፣ ምእመናንን ከምእመናን፣ ካህናትን ከካህናት፣ ሊቃውንትን ከሊቃውንት ወጣትን ከወጣት የሚያጋጭ ሰላም የሚያናጋ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቧል። በመሆኑም፤ 


- የቤተ ክርስቲያን መንበር ሐዋርያዊ ነው፡፡ ሐዋርያዊ መንበር ጌታችን አስተምሮ ከሾማቸው ከዐሥራ ሁለቱ ከሐዋርያት የወጣ አይደለም፤ ሥልጣነ ክህነት የሚተላለፍበት፣ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትምህርተ ሃይማኖት እና ቀኖና ምንጩ ወይም ሥሩ የሚነገርበት፣ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን አማናዊና ሐዋርያዊ ታሪክ፣ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት የሚጀመርበት መነሻ ነው፡፡ 


- ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በሐዋርያት ሥልጣነ ክህነት ነው፤ ይኽንን ሥልጣን ማንም እንደፈለገው ሊከፋፍለው አይችልም፤ በየትም ቦታ ያሉ ጳጳሳት ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከቅዱስ ፓትርያርክ ዕውቅና ውጭ እንደፈለጉ በቡድኑ እየሆኑ መንበር አቋቁመናል ሊሉ አይችሉም፤ ይህ ከቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ታሪካዊ ቅብብል ውጭ የሆነ መናፍቅነት ነው፡፡ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ እና ሥርዓት ውጭ መውጣት ሕገ ወጥነት፣ ቀኖናን መሻር፣ ኃይማኖትን ማፍረስ ነው፡፡ የገቡትን ቃል መጣስ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ መንበር ያለ ፓትርያርክና ከሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ውጭ  የማይሰየም መሆኑ እየታወቀ መንበር አቋቁመናል ማለት የፓትርያርክን እና የሲኖዶስን ሥልጣን መቃወም፤ ከሃይማኖትም፣ ከቀኖናዊ ትውፊትም፣ ከአስተዳደራዊ መዋቅርም መውጣትና ራሳቸውን ከቤተ ክርስቲያን መንበር የለዩ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ድርጊቱን አውግዟል፡፡  

  ይህን ህገወጥ ተግባር ለመፈጸም በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ጦርነት እንደ ምክንያት የተጠቀሰ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ከጦርነቱ በፊት ጦርነት እንዳይከሰት ያደረገችውን ጥረት በጦርነቱ ወቅት ለተደረጉ ድጋፎችና ከጦርነቱ በኋላ ለተደረጉ የእንወያይ ጥረቶች እንዲሁም በቤተክርስቲያን በኩል የተዘረጋውን የሰላምና የእርቅ በር ይልቁንም ለሰላም ሲባል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የተጠየቀውን ይፋዊ ይቅርታ በመግፋት የተደረገ ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባር ነው።
  
  በመሆኑም

•  በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 30 የአጲስ ቀጶሳት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት እንዲመረጡና እንዲሾሙ የመወሰን ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ መሆን የሚደነግገውን ክፍል በግልጽ የጣሰ በመሆኑ

•  በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 31 ንዑስ ቁ 1 እና 3 የቅዱስ ፓትርያርኩን የመዓርግ ስምና መንበር በተመለከተ የተደነገገውን ድንጋጌ የሚያፋልስ ህገወጥ ተግባር የተፈጸመ በመሆኑ
 
• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 ንዑስ ቁ.1 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስፈላጊ መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን ብቻ እንደሚፈጸምና መደንገጉ፤ 
• በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 18 ንዑስ ቁጥር 5 የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትንና ቀኖናን የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ከአባልነት እንደሚሰረዝ በመደንገጉ፤ 

• በአጠቃላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር በሕገ ሰብእም ሆነ በሕገ እግዚአብሔር ሚዛን የተወገዘ ከመሠረተ እምነት የተለየ፣ በአበው ቀኖና፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር  ተቀባይት የሌለው ነው፡፡ ስለዚህ
1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ሐምሌ 16 እና ሐምሌ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በክልል ትግራይ በማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥ 

1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ

2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

   የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 9 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫና በክልሉ መንግሥት ሚዲያ በተላለፈው የቀጥታ ስርጭት የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡
 
በመሆኑም፡- 

ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤

ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡

• ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤  
  
2ኛ. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት

፩. አባ ዘሥላሴ ማርቆስ

፪. አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ

፫. አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ

፬. አባ መሓሪ ሀብቶ
  
፭. አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን

፮. አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ

፯. አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ

፰. አባ ዮሐንስ ከበደ

፱.  አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል
በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
  
3ኛ. ይህ ህገወጥ ሢመት እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ በመሆን ኢትዮጵያን ኤልዛቤል በማለትና ስሟን የሚጠራ የተረገመ ይሁን በማለት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጋር የዶግማ ልዩነት አለን በማለት የኑፋቄ ትምህርት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተናገሩትና በህገወጥ ሢመቱ ላይም በእጩነት ተመርጠው በሂደት ላይ ያሉት አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል።

ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል።

4ኛ. “መንበረ ሰላማ” የሚለው ሕገወጥ ሥያሜን በተመለከተ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፤ በተጨማሪም ከአንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊትየሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ መንበር መሠረተ እምነት፣ ታሪክና ቀኖና፣ ከአስተዳደር እና ሕግ ባፈነገጠ ሁኔታ ትውፊትን በመዳፈር ጎሣን መሠረት አድርጎ የተፈጠረ ሕገ ወጥ አደረጃጀት በመሆኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞታል፡፡ ይሕንንም የክርስትናን ትውፊት እና ሐዋርያዊ መሠረት የሚዛባና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል መሆኑ ታውቆ በመላው ዓለም ለሚመለከተው ሁሉ በደብዳቤ እንዲገለጽ እንዲደረግ፤

6. በየደረጃው የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ማህበራት እና ምእመናን እና ምእመናት ይህን ሕገ ወጥ አድራጎት ከመከላከል እና የቤተ ክርስቲያናችሁን ደህንነት ከመጠበቅ በተጨማሪ ለዚህ ሕገ ወጥ አድራጎት ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግ ተቋማት እና ግለሰቦችን አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ የመከላከል ሥራችሁን እንድትወጡ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

8. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስምን ከፊትም ሆነ ከኃላ በመጨመር እና በመቀነስ በከፊልም ሆነ በሙሉ መጠቀም፤ ዓርማዋን፤ አድራሻዋን፤የአምልኮ እና የሥርዓት መፈጸሚያ የሆኑ ንዋያ ቅዱሳትንና አልባሳት እንዲሁም መጻሕፍት መገልገል የማይችሉ መሆኑ ታውቆ ይህንን ጉዳይ በየደረጃው ያሉ መንግሥታዊ አካላት እና የቤተ ክርስቲያኒቱ  የሥራ ኃላፊዎች ተከታትለው እንዲያስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን በተጨማሪም ይህን ውሳኔ ተላልፈው በሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች እና ተቋማት ላይ ተገቢውን ሕግ አግባብ ተከትሎ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለማት የሚያስፈጽም ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች በመመደብ ተገቢውን ሁሉ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

9. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ
ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
  
11. እነዚህ ግለሰቦች የፈጸሙት ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

12. ይኽ ሕገወጥ አደረጃጀት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የታሰበበት፤ በየጊዜው የነበሩ የፖለቲካ እና የመንግሥት ኃላፊዎች በመታገዝ ሥር የሰደደ ድብቅ አጀንዳ በሚያስፈጽሙ ግለሰቦች የተቀናበረ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቦ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞታል፡፡ በመሆኑም ሕገ ወጥ አደረጃጀትን ማምከን እና ቤተ ክርሰቲያንን ነፃ ማድረግ የሚቻለው ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት እና ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሲደረግ በመሆኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ ሊቃውንት፣ መላው ውሉደ ክህነት፣ ወጣቶች ሰንበት ትምሀርት ቤት አባላት፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች በሙሉ በመጾም፣ በመጸለይ፣ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮና መዋቅር በጠበቀ መልኩ  በመደራጀት አፍራሽ እና የጥፋት መረጃዎችን፣ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ለውሳኔ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደኅንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ በመንፈሳዊ ተጋድሎ መበርታትና የመጣብንን ፈተና በጽናት መታገል እንደሚገባ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 

13.  በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች እየተከሠተ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት የተፈጠረ አለመግባባት ካለፈው ስህተታችን በመማር ችግሩን ተቀራርቦ በውይይትና በእርቅ እንዲፈታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም አካላት የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

14.  እንደ ሀገር የገጠመንን የሰላም መደፍረስ በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለግ እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰላም ጉዳይ የሚሠሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተቋቁሞ ሥራው እንዲሠራ ወስኗል፡፡ 
  
በመጨረሻም እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

             እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
                ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. 
                     አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ ያልተቋረጠ የክህነት ቅብብሎሽ
፩) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፪) ቅዱስ ማርቆስ
፫) አናንዮስ
፬) መልዮስ
፭) ካርዳኖስ
፮) ፐሪሙስ
፯) ዮስጦስ
፰) ኦማንየስ
፱) ማርያኒስ
፲) ክላንድንያስ
፲፩) አግሪጳኖስ
፲፪) ዩልያኖስ
፲፫) ዲሜጥሮስ ፩ኛ (ባሕረ ሐሳብ የተገለጠለት)
፲፬) ኤራቅሊስ
፲፭) ዲዮናስዮስ
፲፮) ማክሲመስ
፲፯) ቴዎናስ
፲፰) ጴጥሮስ ፩ኛ (ተፍጻሜተ ሰማዕት)
፲፱) አኪላስ
፳) እለእስክንድሮስ ፩ኛ (የጉባኤ ኒቅያ አፈጉባኤ)
፳፩) አትናቴዎስ
፳፪) ጴጥሮስ ፪ኛ
፳፫) ጢሞቴዎስ ፩ኛ (የጉባኤ ቁስጥንጥንያ አፈጉባኤ)

፳፬) ቴዎፍሎስ
፳፭) ቅዱስ ቄርሎስ ፩ኛ (የጉባኤ ኤፌሶን አፈ ጉባኤ

፳፮) ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፩ኛ
፳፯) ጢሞቴዎስ ፪ኛ
፳፰) ጴጥሮስ ፫ኛ
፳፱) አትናቴዎስ ፪ኛ
፴) ዮሐንስ ፩ኛ
፴፩) ዮሐንስ ፪ኛ
፴፪) ዲዮስቆሮስ ፪ኛ
፴፫) ጢሞቴዎስ ፫ኛ
፴፬) ቴዎዶስዮስ ፩ኛ
፴፭) ጴጥሮስ ፬ኛ
፴፮) ድምያኖስ
፴፯) አንስታትዮስ
፴፰) እንድራኒቆስ
፴፱) ብንያሚ ፩ኛ
፵) አጋቶን
፵፩) ዮሐንስ ፫ኛ
፵፪) ይስሐቅ
፵፫) ስምዖን ፩ኛ
፵፬) እለእስክንድሮስ ፪ኛ
፵፭) ቆዝሞስ ፩ኛ
፵፮) ቴዎድሮስ ፩ኛ
፵፯) ሚካኤል ፩ኛ
፵፰) ሚናስ ፩ኛ
፵፱) ዮሐንስ ፬ኛ
፶) ማርቆስ ፪ኛ
፶፩) ያዕቆብ
፶፪) ስምዖን ፪ኛ
፶፫) ዮሴፍ ፩ኛ
፶፬) ሚካኤል ፪ኛ
፶፭) ቆዝሞስ ፪ኛ
፶፮) ሱንትዩ ፩ኛ
፶፯) ሚካኤል ፫ኛ
፶፰) ገብርኤል ፩ኛ
፶፱) ቆዝሞስ ፫ኛ
፷) መቃርዮስ ፩ኛ
፷፩) ቴዎፋኖስ
፷፪) ሚናስ ፪ኛ
፷፫) አብርሃም
፷፬) ፊላታዎስ
፷፭) ዘካርያስ
፷፮) ሱንትዩ ፪ኛ
፷፯) ክርስቶዶሉስ
፷፰) ቄርሎስ ፪ኛ
፷፱) ሚካኤል ፬ኛ
፸) መቃርዮስ ፪ኛ
፸፩) ገብርኤል ፪ኛ
፸፪) ሚካኤል ፬ኛ
፸፫) ዮሐንስ ፭ኛ
፸፬) ማርቆስ ፫ኛ
፸፭) ዮሐንስ ፮ኛ
፸፮) ቄርሎስ ፫ኛ
፸፯) አትናቴዎስ ፫ኛ
፸፰) ገብርኤል ፫ኛ
፸፱) ዮሐንስ ፯ኛ
፹) ቴዎዶስዮስ ፪ኛ
፹፩) ዮሐንስ ፰ኛ
፹፪) ዮሐንስ ፱ኛ
፹፫) ብንያሚ ፪ኛ
፹፬) ጴጥሮስ ፬ኛ
፹፭) ማርቆስ ፭ኛ
፹፮) ዮሐንስ ፲ኛ
፹፯) ገብርኤል ፬ኛ
፹፰) ማቴዎስ ፩ኛ
፹፱) ገብርኤል ፭ኛ
፺) ዮሐንስ ፲፩ኛ
፺፩) ማቴዎስ ፪ኛ
፺፪) ገብርኤል ፮ኛ
፺፫) ሚካኤል ፭ኛ
፺፬) ዮሐንስ ፲፪ኛ
፺፭) ዮሐንስ ፲፫ኛ
፺፮) ገብርኤል ፯ኛ
፺፯) ዮሐንስ ፲፬ኛ
፺፰) ገብርኤል ፰ኛ
፺፱) ማርቆስ ፭ኛ
፻) ዮሐንስ ፲፭ኛ
፻፩) ማቴዎስ ፫ኛ
፻፪) ማርቆስ ፮ኛ
፻፫) ማቴዎስ ፬ኛ
፻፬) ዮሐንስ ፲፮ኛ
፻፭) ጴጥሮስ ፭ኛ
፻፮) ዮሐንስ ፲፯ኛ
፻፯) ማርቆስ ፯ኛ
፻፰) ዮሐንስ ፲፰ኛ
፻፱) ማርቆስ ፰ኛ
፻፲) ጴጥሮስ ፮ኛ
፻፲፩) ቄርሎስ ፬ኛ
፻፲፪) ዲሜጥሮስ ፪ኛ
፻፲፫) ቄርሎስ ፭ኛ
፻፲፬) ዮሐንስ ፲፱ኛ
፻፲፭) መቃርዮስ ፫ኛ
፻፲፮) ዮሳብ ፪ኛ
፻፲፯) ቄርሎስ ፮ኛ
፻፲፰) አቡነ ባስልዮስ ዘኢትዮጵያ
፻፲፱) አቡነ ቴዎፍሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳) አቡነ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
፻፳፩) አቡነ መርቆሬዎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፪) አቡነ ጳውሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፫) አቡነ ማትያስ ዘኢትዮጵያ

የክህነት ምንጭ ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ እስከአሁኑ ፓትርያርካችን እስከ አቡነ ማትያስ ያለው የክህነት ቅብብሎሽ ከላይ ያለውን ይመስላል። የእያንዳንዱ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ጳጳስ ክህነት ቢቆጠር ነቁ እና የክህነቱ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በጉልበት ራሳቸውን የሾሙ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ የተሿሿሙ ሰዎች ክርስቶሳዊ የሆነው ክህነት የላቸውም። ይህም ማለት ቀድሰው ምሥጢራትን አይለውጡም። ጸጋ እግዚአብሔርን አያሰጡም። ስለዚህ ሕገወጥነትን አምርረን ልንቃወም ይገባናል።
                      
@ መ/ር በትረማርያም አበባው
2024/04/28 14:05:26
Back to Top
HTML Embed Code: