የላቀው ክብር ማለት፦
ቀጥተኛው መንገድ ላይ መፅናት ነው!!




https://www.tg-me.com/hamdquante

     እንኳን ለ1447ኛው የሂጅራ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!!
  ከችግር እና ከመከራ ተላቀን ምኞታችን ሰምሮ ሐያታችን የሚያምርበት ዘመን አላህ ያድርግልን!!



📖{ثُمَّ يَأْتِى مِنۢ بَعْدِ ذَٰلِكَ عَامٌۭ فِيهِ يُغَاثُ ٱلنَّاسُ وَفِيهِ يَعْصِرُونَ}
{ከዚያም ከእነዚያ (የድርቅ ዓመታት) በኋላ ሰዎቹ በርሱ የሚዘነቡበት በርሱም (ወይንን) የሚጨምቁበት ዓመት ይመጣል፡፡}

       [ዩሱፍ:⁴⁹]



https://www.tg-me.com/hamdquante
⚫️
ሞትን መለማመድ!!


የማወጋችሁ ድርሰት ሳይሆን ትክክለኛ ታሪክ ነው
   አባት እና እናት በስተ እርጅና ሕይወታቸው ላይ ናቸው። ልጆቻቸው አድገው ተምረው በተለያየ መስክ የየራሳቸው ሕይወት መምራት ጀምረዋል። አባት ብዙ ለየት ያሉ ባህሪዎች ያሉት ሲሆን አንዱ አሁን የምነግራችሁ ነው......

  ሁሌ የቤተሰብ ጨዋታ ሲጀመር "ሞት እንለማመድ" ይላል። ቀሪው ቤተሰብም ይህ ጨዋታ ለምደውታልና ፍላጎቱን ያሟሉለታል። ምን ያደርጋሉ መሰላችሁ?....

  ከልጆቹ አንዱ "ዑመር" የሚባል ከሆነ "ዛሬ ዑመርን እንግደለው" ይላቸዋል። እነርሱም "እሺ" ብለው ተሰብስበው ይቀመጣሉ። "ዑመር ዘገየም ፈጠነ የሆነ ቀን መሞቱ አይቀርም። እናም ዛሬ ሁላችንም ዑመር ሞቷል ብለን እንመን። እሺ ሞተ። ከዝያ ምንድን ነው ምናደርገው? እንዴት ነው የምንሆነው?" እየተባባሉ በተለያየ ቀን ሁሉም ልጆቻቸው እየገደሉ ሞታቸውን ይለማመዱታል።

  ለአባት "እንዴት ይህንን ልታስብ ቻልክ?" ተብሎ ሲጠየቅ ምላሹ አጭር ነበር;
   "የሆነ ቀን መሞታቸው ስለ ማይቀር ቀድመውኝ ቢሞቱ በጊዜው እንዳልደናገጥና ሰብር እንዳላጣ ከአሁኑ ሞታቸውን እያመንኩ ራሴን አለማምዳለሁ።"


ከመልካም ቀደምቶቻችን........
    ቀብር ቆፍሮ, ለኽዱን አስተካክሎ, ገብቶ ይተኛበትና በሚሞት ጊዜ ሊሆነው ስለሚችለው ነገር የሚለማመድ፤
   ከፈን ገዝቶ ልብሶቹን በሚያስቀምጥበት ሳጥን ያስቀምጠውና በየቀኑ እያየው ሞቱን የሚጠባበቅ፤
   ባቀጣጠለው እሳት ላይ ጣቱን እያስገባ ሰውነቱን በእሳት እያስፈራራ ጀሀነምን የሚያስታውስ፤
   ሌላም ሌላም ዓይነት ዘዴ እየተጠቀሙ ሞት እና አኼራን የሚዘክሩ ብዙዎች ነበሩ።


አንተስ..........
   እንደው አንድ ቀን ለአፍታ በፀጥታ ቁጭ ብለህ ነፍስህን ስለ ሞትህ አውርተሃት ታቃለህ???

ሳትነግራት ከመጣ እኮ ያስደነግጣታል!!
  



https://www.tg-me.com/hamdquante

     የሙኸረም ጾም..........

አቡ ሁረይራ ባስተላለፈው ነብዩ እንዲህ ይላሉ፦
«أفضل الصيام بعد رمضان شهر الله المحرم، وأفضل الصلاة بعد الفريضة صلاة الليل»
«ከረመዷን በኋላ ከሁሉም በላጩ ጾም የአላህ ወር የሆነው የሙኸረም ጾም ነው፤ ከፈርድ ሰላቶች በኋላ በላጩ ሰላት የለይል ሰላት ነው።»






https://www.tg-me.com/hamdquante
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
⚫️ ሞትን መለማመድ!! የማወጋችሁ ድርሰት ሳይሆን ትክክለኛ ታሪክ ነው    አባት እና እናት በስተ እርጅና ሕይወታቸው ላይ ናቸው። ልጆቻቸው አድገው ተምረው በተለያየ መስክ የየራሳቸው ሕይወት መምራት ጀምረዋል። አባት ብዙ ለየት ያሉ ባህሪዎች ያሉት ሲሆን አንዱ አሁን የምነግራችሁ ነው......   ሁሌ የቤተሰብ ጨዋታ ሲጀመር "ሞት እንለማመድ" ይላል። ቀሪው ቤተሰብም ይህ ጨዋታ ለምደውታልና…
⚫️
     ጥበትን አስፍታ ድሎት አስረስታ ጥፍጥና የምትቆርጠዋ ..........ሞት!!

ነብዩﷺ በተረጋገጠው ሓዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
«أكثروا ذكر هاذم اللذات»
  «ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችዋ ሞት ማውሳትን አብዙ።»

ነብዩﷺ በዚህ ሓዲስ "ሞትን አውሱ" ብቻ ሳይሆን «አብዝታችሁ አውሱ» በማለት ይገፋፋሉ።

በሌላ ሓዲስ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋ ሲመክሩ፦
«أكثِروا ذِكْرَ هاذمِ اللَّذَّاتِ فما ذكَره عبدٌ قطُّ وهو في ضيقٍ إلَّا وسَّعه عليه ولا ذكَره وهو في سَعةٍ إلَّا ضيَّقه عليه»
  «ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችዋ ሞት ማውሳትን አብዙ። አንድም ሰው በመጣበብ በችግር ላይ ሆኖ አያስታውሰውም ቢያሰፋለት እንጂ፤ አንድም ሰው በምቾት ላይ ሆኖ አያስታውሰውም ቢያጣብበት እንጂ።»

  እሱን በማውሳት ምቾት ላይ ያለ ሰው ምቾቱን፥ መከራ ላይ ያለ ሰው መከራውን የሚረሳበት ነገር ቢኖር ሞት ነው።
እንዴት??....
  ምቾት ላይ ያለ ሰው ምቾቱን ሁሌም እንዲቀጥልለት ይፈልጋል። ከእሱ መቋረጥ አይፈልግም። አንዳንዴም አላህ ካላዘነለት ድንበር ወደ ማለፍ እና ወደ አመፅ ይገፋፋዋል; ግን ቆም ብሎ ሞትን ካስታወሰ: ይህንን ሁሉ ምቾት የሆነ ቀን እንደሚቋረጥ፥ በዚህ ምቾት ድንበር ካለፈም ከሞት በኋላ እንደሚጠየቅበት ይገነዘብና ሰብሰብ ይላል። በደስታ የሚፈነጥዘው ልቡን ሞትን በማሰብ ስለ አኼራው እያሰበ ይጣበባል።

  ችግር ላይ ያለ ሰው ከዚህ ችግር መውጣት እና መላቀቅ ይፈልጋል። በመሆኑም ቆም ብሎ ሞትን በሚያስብ ጊዜ; ካለበት ችግር ሞት እንደሚገላግለው ስለ ሚያውቅ እና በሚያሳልፈው ችግር ሰብር ካደረገ ከሞት በኋላ እንደሚመነዳበት ስለሚያውቅ ያለበትን መከራ በመርሳት ልቡ የአኼራው ምንዳ በመከጀል ሰፋ ትልለታለች።


⚫️ሞትን እንዴት ማስታወስ እንችላለን??.....
1ኛ, ስለ ሞት የሚገስፁ የቁርኣን እና የሓዲስ አንቀፆች በሚያልፉብን ጊዜ በእርጋታ ማስተንተን፤

2ኛ, ነብዩﷺ ባመላከቱት መልኩ ቀብርን በመዘየር፤

3ኛ, የሚረብሹ ከሆኑ ድምፆችም ይሁን ሁኔታዎች ርቆ በፀጥታ በተሞላ ስሜት ስለ ሞት, ጠፊ ስለሆነችዋ ዱንያ እና ዘውታሪ ስለሆነችዋ አኼራ ማስተንተን፤

4ኛ, ዱንያ ላይ በድሎትም ይሁን በስቃይ ኖረው ዛሬ ግን ከምድር ስር የተኙ ሰዎች በማስታወስ እና ሁኔታቸውን በማስተንተን፤
  እና የመሳሰሉ መንገዶች በመጠቀም ሁሌም ሞትን ከሁለቱ ዓይኖቻችን መሃል አኑረን መጠባበቅ ይኖርብናል።


ለሁላችንም የቤት ስራ.........
    ከላይ እንዳየነው ነብዩﷺ ሞትን አብዝተን እንድናስታውስ አዘውናል። ረሱልﷺ ናቸው ያዘዙት: እንደው አንድ ቀን እንኳ ነፍስያችን ሞታችንን አውስተንላት እናውቃለን???



🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር
ሰኔ 20/2017 E.C
https://www.tg-me.com/hamdquante

     ለጀነት ሰዎች..........
"ከዚህ ሕይወት የምትወጡበት አንድ ቀን ይመጣል"
ቢባሉ ያዝኑ ነበር;

   ለጀሀነም ሰዎች..........
"ከዚህ ስቃይ የምትድኑበት አንድ ቀን ይመጣል"
ቢባሉ ይደሰቱ ነበር።


ተስፋ.........
   የሕይወት ዋናው ቅመም ነው!!






https://www.tg-me.com/hamdquante

    "የሆነ ሰው በውሀ ላይ ሲራመድ፤ በአየር ላይ ሲከንፍ ብታዩት እንኳ;
  የሰውየውን ሀል በቁርኣን በሓዲስ እስከምትፈትሹት ድረስ እንዳትታለሉበት!!"

          /ኢማሙ ሻፊዒ/





https://www.tg-me.com/hamdquante

     አቡ ሁረይራ ባስተላለፈው ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦

«مَا مِنْ يَوْمٍ يُصبِحُ العِبادُ فِيهِ إِلَّا مَلَكَانِ يَنْزِلانِ، فَيَقُولُ أَحَدُهُمَا: اللَّهُمَّ أَعْطِ مُنْفِقًا خَلَفًا، وَيَقُولُ الآخَرُ: اللَّهُمَّ أَعْطِ مُمْسِكًا تَلَفًا»
  «ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መላኢካዎች የሚወርዱበት ቢሆን እንጂ;
አንደኛው:
   🤲አላህ ሆይ ለሚሰጥ ሰው ምትክ ስጠው ሲል
ሌላኛው:
  🤲አላህ ሆይ ለሚቋጥር ሰው መጥፊያ ስጠው ይላል።»






https://www.tg-me.com/hamdquante

"አላህን የሚፈራ እና ዱንያን ቸላ የሚል አንድም ሰው የለም;
በጥበብ ቢናገር እንጂ!!"

/ኢማሙ ማሊክ/




https://www.tg-me.com/hamdquante

    "እብሊስ መጥቶ........
“አላህ ስንቴ እየለመንከው ምንም እንዳልተቀበለህ አታይም?” ካለህ;
  “እኔ በዱዐ ጌታዬን እያመለኩኝ ነው” በለው!!"
     /ኢብኑ ጀውዝይ/




https://www.tg-me.com/hamdquante

    አስደማሚ የሆነ ታሪክ ይኖረናል


👇👇👇
https://www.tg-me.com/hamdquante
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
    አስደማሚ የሆነ ታሪክ ይኖረናል 👇👇👇 https://www.tg-me.com/hamdquante

አትገረሙም??.............

    አንድ ከ"አህለል_ከላም" የሆነ ተሟጋች ወደ ኢማሙ ሻፊዒ ለክርክር ይመጣል። የተለመደው ፍልስፍናቸው እያነሳ መናገር ጀመረ።     
  "አህለል_ከላም" ማለት ስለ አላህ የማይጠየቁ ጥያቄዎችን እያነሱ ራሳቸው ባክነው ሌላውም የሚያደክሙ ጠሞ አጥማሚዎች ናቸው።

  ይህ ሰው ስለ አላህ መፈላሰፍ ሲጀምር ኢማሙ ሻፊዒ አስቆሙትና "አንዲት ጥያቄ ልጠይቅህ" አሉት "እሺ ጠይቀኝ" አላቸው።

  "ሰማይ ላይ ያሉ ከዋክብት ብዛታቸው ታቃለህን?" አሉት "ኣይ አላውቅም" አላቸው።
ቀጠሉና "እሺ ከእነሱ ውስጥ አንዱን እንኳ መጠኑ፣ ከምን እንደተሰራ፣ በምን ወቅት እንደሚወጣ ታቃለህን?" አሉት "ኧረ አላውቅም" አላቸው።

  "ይገርማል!! በዓይኖችህ ስለምታያቸው ፍጡራን እንኳ ጠንቅቀህ አታውቅም፤ ስለ ፈጣሪያቸው ልትመራመር ይቃጣሃል¡¡" አሉት።

  ሼኹ ቀጠሉና ስለ ውዱእ የሆነች ጥያቄ ጠየቁት። ሰውየውም አራት ጊዜ ሞክሮ ተሳሳተ። "የምትገርም ሰው ነህ!! በቀን አምስት ጊዜ ስለሚያስፈልግህ ጉዳይ አታውቅም፤ በማይመለከትህ ጉዳይ ገብተህ ራስህን ታጨናንቃለህ¡¡" ብለው ገሰፁት።


  ሰውየውም አላህ ግሳፄያቸው ሰበብ አድርጎለት ተውበት አርጎ ወደ ሱና ተቀጣጨ። ከተውበቱ በኋላ "እኔ ማለት ከኢማሙ ሻፊዒ ኹሉቆች አንዱ ነኝ" ይል ነበር።


ይህ ሰው ማን እንደሆነ ታቃላችሁ?????
  ከእስልምና ከዋክብቶች አንዱ ሁኖ ለመቆጠር የበቃው ኢማሙ "ሙዘኒ" ነው። አላሁ አክበር!!





https://www.tg-me.com/hamdquante
🪑
የመጅሊስ ምርጫ እና ጣጣው.....

ትናንትና ኹጥባ ላይ ምን አለ መሰላችሁ;
"ምርጫው እንደ ሰላት እንደ ጾም ዋጂብ ነው, የማይመርጥ ተላላኪ ከሀዲ ነው" አለ።

ዛሬ ደሞ;
ፊታቸውን እንኳ ያልሸፈኑ ሴቶች የወንዶቹ መስጂድ ውስጥ ቁጭ ብለው ይመዘግባሉ። ግቢ እኮ አይደለም መስጂዱ ውስጥ¡¡




https://www.tg-me.com/hamdquante

    "ሰዎች 🥛የሚጠጣ ውሀ እንኳ እንዲያቀብሉህ ብትጠይቃቸው;
  በጠየካቸው ነገር ልክ እነርሱ ዘንድ የነበረህ ክብር ይቀንሳል!!"

     /ኢማም ኢብኑ ተይሚያ/





https://www.tg-me.com/hamdquante
🇸🇦ሐምዱ ቋንጤ🇵🇸
⚫️      ጥበትን አስፍታ ድሎት አስረስታ ጥፍጥና የምትቆርጠዋ ..........ሞት!! ነብዩﷺ በተረጋገጠው ሓዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦ «أكثروا ذكر هاذم اللذات»   «ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችዋ ሞት ማውሳትን አብዙ።» ነብዩﷺ በዚህ ሓዲስ "ሞትን አውሱ" ብቻ ሳይሆን «አብዝታችሁ አውሱ» በማለት ይገፋፋሉ። በሌላ ሓዲስ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋ ሲመክሩ፦ «أكثِروا ذِكْرَ هاذمِ اللَّذَّاتِ…
⚫️
    ሞት የማስታወስ ጥቅሞች........

  አንድ ሰው በዕለታዊ የሕይወት እንቅስቃሴው ውስጥ ሞትን ማስታወሱ የሚያስገኝለት በርካታ ዱንያዊና አኼራዊ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን; የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸው፦

1ኛ, ለተውበት መፍጠን!!
    አንድ ሰው ሞትን በሚያስታውስ ጊዜ ለሕይወቱ የተቀረው ጊዜ ቲንሽ መሆኑን በመገንዘብ ከወንጀል ርቆ ለተውበት ይፈጥናል።

2ኛ, የልብ ዕርካታ!!
   ሞትን የሚያስታውስ ሰው እቺ ጠፊ ለሆነችው ዱንያ የነበረው መስገብገብ ይተውና አላህ ቀድሮ የሰጠውን ነገር በመውደድ የልብ ዕርካታ ያገኛል።

3ኛ, ዒባዳ ላይ ነሻጣ ማግኘት!!
  ሞት ድንገት መጥቶ ከዱንያ እንደሚለየው የሚያስታውስ ሰው ሀሳብ ጭንቀቱ ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ በማድረግ አኼራ ላይ ሊጠቅመው የሚችል ነገር ለመስራት ጠንካራ ሞራል ይኖረዋል።

4ኛ, የሰዎችን ሐቅ መመለስ!!
  ሁሌም ሞት የሚያስታውስ ሰው ከሞት በኋላ በማንም መብት ላለመጠየቅ ለሁሉም ባለሐቅ ሐቁን ይመልሳል። በየትኛውም መልኩ የሌሎችን ሐቅ ተሸክሞ መሞት አይፈልግም።

5ኛ, ለዘላለማዊው አኼራ መዘጋጀት!!
  ሞት የሚያስታውስ የሆነ ሰው ሁሌም አኼራውን እያሰበ ለአኼራው ይጨነቃል ይሰነቃል ይዘጋጃል።

6ኛ, ከغፍላ መላቀቅ!!
   ሞትን የረሳ ሰው በغፍላ ውስጥ እንደሚኖረው ሁላ ሞትን የሚያስታውስ ሰው ከغፍላ ወጥቶ ሁሌም በሚጠቅመው ነገር ላይ ብቻ ያተኩራል።

7ኛ, ዱንያን ቸላ ማለት!!
  ሞቱን የሚያስታውስ ሰው ጠፊ የሆነችዋ ዱንያን ቸላ በማለት ዘውታሪ በሆነችዋ የአኼራ ስራ ላይ ይጠመዳል።

8ኛ, መልካም ስነምግባር መላበስ!!
  ሞትን ከዓይኖቹ መሃል አርጎ ሁሌም የሚያስታውሰው ሰው ሁሉም ነገር አላፊ ጠፊ መሆኑን ስለሚያውቅ ሁሉንም በመልካም የሚኗኗር የመልካም ስነምግባር ባለቤት ይሆናል።

9ኛ, ለማይቀረው ጉዞ መዘጋጀት!!
  የዱንያ ቆይታው ሲያበቃ ወደ አኼራ እንደሚሻገር የሚያስታውስ ሰው ለማይቀረው እና ለከባዱ ጉዞ ተዘጋጅቶ ይሰነቃል።

        👇
        👉ከዕቅዶችህ መሃል ሞት ጨምርበት!!




🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር
ሰኔ 22/2017 E.C
https://www.tg-me.com/hamdquante

     ቆንጆ ፋኢዳ.........

  "ሱረቱል በራእ ላይ بسم الله الرحم الرحيم “ወርዳለች ወይስ አልወረደችም?” በሚል ሰሓባዎች መሃል ምንም ልዩነት አልነበረም። ሰሓባዎች ላይ ጥያቄ የፈጠረው “ሱረቱል በራእ እና ሱረቱል አንፋል የተለያዩ ሁለት ሱራዎች ናቸው? ወይስ ሁለቱም እንደ አንድ ሱራ ነው የሚቆጠሩት?” የሚለው ነው የነበረው።
  እንጂማ ሱረቱል በራእ ላይ بسملة የወረደች ቢሆን ኖሮ ያለ ምንም ጥርጥር ትጠበቅና ቦታዋ ላይ ትሰፍር ነበር።"

    /ተፍሲር ኢብኑ ዑثይሚን/





https://www.tg-me.com/hamdquante
🤲اللهم غزة🤲

ሪያ እና ዓይነቶቹ!!

ሪያ ማለት፦
   አንድ ሰው ሰዎች ዓይተውት እንዲያወድሱት ብሎ የሚሰራው ዒባዳ ነው። በዚህ ዒባዳው አኼራ ላይ እጠቀምበታለሁ ብሎ የሚነይተው ነገር የለውም; ሙሉ ኒያው ሰዎች ዘንድ መታወቅ እና መወደስ ብቻ ነው።


የሪያ ዓይነቶች፦
   ከትልቁ ሽርክ የሚመደብ እና ከቲንሹ ሽርክ የሚመደብ ተብሎ ለሁለት ይከፈላል።


ከትልቁ ሽርክ የሚመደበው፦
  ሰውየው ዒባዳውን የሚሰራው መቶ በመቶ ሰዎች እንዲያዩለት ወይም እንዲሰሙለት፥ በዚህም እነርሱ ዘንድ ክብር እና ዕውቅና ለማግኘት ነይቶ ብቻ ሲሰራው ነው።

ከትንሹ ሽርክ የሚመደበው፦
   ዒባዳውን የሚሰራው ለአላህ ብሎ አኼራ ከጅሎ ነው, በዚህ ለአላህ ብሎ በሚሰራው ዒባዳ ላይ እግረ መንገድ የሰዎች ውዳሴ በመከጀል ሰዎች እንዲያዩት ይጥራል ያሳምራል። ይህ ከመጀመሪያው መለስ ይልና ከቲንሹ ሽርክ ይቆጠራል። ብዙኅኖች ያስቸገረው የዚህ ዓይነቱ ነው።


ከሁለቱ በተለየ መልኩ........
  አንድ ሰው ዒባዳ ላይ ሆኖ ሳለ ወደ ሪያ ሚገፋፋው ወስዋስ ቢመጣበት; እሱም ነፍሲያውን እየታገለ የሪያው ስሜት ከራሱ ካራቀ: ይህ ሰው ዒባዳው ላይ ምንም ዓይነት ክፍተትም ይሁን ችግር አይፈጥርበትም።
እንደውም ወስዋስን ከራሱ ለማራቅ በሚያደርገው ትግል "ሙጃሂድ" ተብሎ ይመነዳል። ከመሆኑም ጋ ምንም ዓይነት የሪያ ስሜት ሳይመጣበት ሳፊ በሆነ ኢኽላስ ዒባዳው የሚፈፅመው ግን ያለ ምንም ጥርጥር የተሻለና በላጭ ይሆናል።



በዚህ መልኩ..........
   ጥርት ያለ ሪያያ ትልቁ ሽርክ ነው፤
   ከኢኽላስ ጋ የተደባለቀ ሪያ ቲንሹ ሽርክ ነው፤
   ልብ ላይ ውል የሚል ሪያ ሆኖ ሰውየው ታግሎ ከመለሰው ምንም አይጎዳውም።
           /ኢብኑ ዑثይሚን/





https://www.tg-me.com/hamdquante

"ጫማህን አውልቅህ ትንኝን ስትገላት
አስበህ ታውቃለህ ልጅ እንደሚኖራት?"





https://www.tg-me.com/hamdquante
🤳
    በሞባይል ባንኪንግ የሆነ ዕቃ ከገዛህ በኋላ
  "ውድ ደንበኛችን ከነበሮት ሂሳብ ላይ ** ተቀንሷል"
የሚል መልእክት ይላክልሃል።


አስበው እስኪ.......
   ሁሌም የሆነ ወንጀል ስትሰራ "ከነበረህ ምንዳ ላይ **  ያህሉ ተቀንሷል"
የሚል መልእክት የሚላክልህ ቢሆን እንደው አንዲትን ወንጀል የመስራት ድፍረት ይኖርህ ነበር??


ነገሩ ከዚህ የከፋ ነው..........
   ሙሉ ሐያትህ የለፋህበትን ዒባዳ ያለ ጥንቃቄ በተዘፈቅክባቸው ወንጀሎች ሰበብ እየቦነነ ከወላጆችህም, ከልጆችህም, ከወዳጆችህም የምትሸሽበትን ቀን ፍራው!!






https://www.tg-me.com/hamdquante
2025/07/01 17:37:49
Back to Top
HTML Embed Code: