የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለቋሚ ሲኖዶስ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀሩ!
በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ቋሚ ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ጋር ዛሬ ጥር 25/2014 ዓ.ም ሊያከናውነው የነበረው ውይይት ከንቲባዋ በጠየቁት የውይይት ቦታ ለውጥ ምክንያት ሳይደረግ ቀርቷል።
ቋሚ ሲኖዶሱ መንበረ ፓትርያርክ ውስጥ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ውይይቱን ለማድረግ እየተጠባበቀ የነበረ ቢሆንም ከንቲባዋ ቦታው ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ይቀየር በማለታቸው ምክንያት ውይይቱን ለማድረግ እንዳልተቻለ ታውቋል።
ከ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር የሚኖራቸውን ውይይት ወደ መንበረ ፓትርያርክ በመመጣት ሲያከናውኑ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን የዛሬው የከንቲባዋ ድርጊት ሊቃነ ጳጳሳትን ያሳዘነ ደርጊት ሆኗል።
ምንም እንኳን ከንቲባዋ በውይይቱ ላይ ባይገኙም ቋሚ ሲኖዶሱ ግን ስብሰባውን እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን እኛም ጉዳዩን እየተከታተልን አስፈላጊውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

🌿❤️ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-
1. #ሲጸልይ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡
2. #ሲያመሰግን ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡
3.#ሲመጸውት ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡
4. #ቅዱሳት #መጻሕፍትን #ሲያነብ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡
እግዚአብሔር የተግባር ሰዎች ያድርገን!!

#ሐምሌ_5
#ቅዱስ_ጳውሎስና_ቅዱስ_ጴጥሮስ
ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።
በዚህች ዕለት ስለክርስቶስ የተገፋ፣ ስለክርስቶስ የተወገረ፣ ስለክርስቶስ የተሰደደ፣ ስለክርስቶስ የታሰረ፣ ስለክርስቶስ ከአለም ሃሳብና መሻቷ የተለየ፣ ስለክርስቶስ ራሱን የለየ፣ ስለክርስቶስ ምእመናን ያነፀ፣ ስለክርስቶስ መልካምን መልእክት የፃፈ #ቅዱስ_ጳውሎስ ሰማዕት ሆነ። ነገር ግን በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ነው፤ የፅድቅን አክሊል ተቀበለ ከክርስቶስ ጋር መኖርን እንደናፈቀ አገኛት፤ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን ማህበር ተቀላቀለ ከመላእክት ምስጋና ተጋራ በስጋ ህይወቱ ከእውቀት ከፍሎ እንዳወቀ በሰማያዊው ኑሮ በእጅጉ የበለጠ እውቀትን ተቸረ። በማይጠወልግ፣ በማይደርቅ፣ በማይዝል፣ ፍሬያማም በሆነ ክርስቶስ ግንድነት ላይ ቅርንጫፍ ሆኖ ተሰርቷልና በስጋ ኑሮው በድካም ዝለት ጠውልጎ እንደነበረ የሚጠወልግ አይደለም፤ በማስተማር ብዛት ጉሮሮው እንደደረቀ አሁን የሚደርቅ አይደለም፤ በብርቱ ክንድ ላይ በምቾት አለና የሚዝልም አይደለም፤ ክፉወች ሮማውያን ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ። አይሁድም እፎይ ጳውሎስ ሞተ አሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ግን የናፈቀው ክርስቶስ ጋር ሊኖር ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት ሄደ፤ ራሱን ህያው መስዋእት አድርጎ በክርስቶስ ፊት እንደ ንፁህ መገበሪያ ስንዴ ተፈጨ፤ አይሁድ በጳውሎስ መሞት ድል ያደረጉ ይመስላቸዋል ነገር ግን የፅድቅን አክሊል በራሱ ላይ አድርጎ ከፀሃይ ይልቅ እያበራ በሰማይ ሆኖ ቅዱስ ጳውሎስ አለ በማይደርቅ ግንድ ላይ የተተከለ ቅዱስ ጳውሎስ ፍሬ በሙላት የያዘ የለመለመ ቅርንጫፍ ሆኖ አለ በቅድስና በተዋበ የክርስቶስ አካል መካከል መልካም ብልት ሆኖ አለ፡፡
አይሁድ ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ በሰይፍ አንገቱን ቆርጠው በስጋ ገድለውታልና አላዋቂ አይሁድ ከሮማውያን ጋር አብረው ጳውሎስን ገደልን አሉ፤ እርሱ ግን ከአፈር በተበጀ ስጋ ሞት ቢሞት በእግዚአብሔር እስትንፋስ ስለተሰጠች ነፍስ ህያው ነው፡፡
ዳግመኛም በብርሃኑ ብርሃንን በጨውነቱ መጣፈጥን በመድሃኒቱ መፈወስን የሰጣቸው ተወዳጅ የሐዋርያት አለቃ #ቅዱስ_ጴጥሮስን አይሁድ ቁልቁል ሊሰቅሉት ወደ ሮም አደባባይ ከወዳጁ ከጳውሎስ ጋር አጣደፉት፤ ጴጥሮስ ግን በትምህርቱ ብርሃን ጨለማቸውን ገፍፎላቸው፣ በእምነት መድሃኒት ሙታናቸውን አንስቶላቸው፣ ጎባጣቸውን አንቅቶላቸው አንካሳወቻቸውን አፅንቶላቸው ክፉ ጠላት ዲያብሎስንም አባርሮላቸው ነበር አይሁድ ግን ከወዳጃቸው ጴጥሮስ ይልቅ ጠላቶቻቸውን ሮማውያን ጋር አብረው አንድም ከወዳጃቸው ከክርስቶስ ይልቅ ከጠላታቸው ዲያቢሎስ ጋር አብረው ቅዱስ ጴጥሮስን እንደጌታውና መምህሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሊሰቅሉት ወደሮም አደባባይ አፋጠኑት። የማይጠፋውን ፋና ሊያጠፉ የማይደበዝዘውን ብርሃን ሊያደበዝዙ የማይሞት የክርስቶስን ልጅ ሊገድሉ በገሃነም ደጆች የማትናወጥ ክርስትናን ሊያናውጡ አይሁዳውያን የክርስቲያኖች ዋና ያሉትን ቅዱስ ጴጥሮስን በብዙ ስቃይ አንገላቱት፤ ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የስጋ ሞቱ ዕረፍቱ እንደሆነ እጅግ አስቀድሞ አውቆ ነበር የአይሁድ ማሰቃየት ወደ ክርስቶስ የፀጋ ግምጃ ቤት እንደሚያደርሰው አውቆ ነበር የአይሁድ መጨከን ወደ ክርስቶስ አማናዊ ፍቅር እንደሚመራው አውቆ ነበር፤ “ገደልንህ” አሉት። እርሱ ግን “ወደ ዘለዓለማዊ ህይወት ክርስቶስ ገፋችሁኝ” አላቸው። “ክርስቲያኖችን ጨረስን” አሉት እርሱ ግን “የእኛ ሞት የክርስቲያኖች ዘር ነው” አላቸው፤ “አንተ ርጉም” አሉት እርሱ ግን “የክርስቶስ ምህረት በእናንተ ላይ ይሁን” ሲል በፍቅር ፀለየላቸው፡፡
እነሆ አባቶቻችን እነሆ ዋኖቻችን በክፋት በአንዳች እንኳን የሚከሰሱበት ምክንያት አልተገኘም በቀማኝነትም ማንም እነሱን ሊከስ የሚችል የለም ነገር ግን የሚሰድቧቸውን መረቁ ለሚያሳድዷቸው ፀለዩ ለተራቡት ምግብን ለተጠሙት መጠጥን አቀበሉ ድሆችን ተንከባከቡ ድውዮችን ፈወሱ የጨለማን ክፋት በፍቅር ብርሃን አረከሱ የዲያብሎስን ጭካኔ በክርስቶስ ርህራሄ ሰበሩ፡፡ እነሆ አባቶቻችን አስቀድመው ክርስቶስን አይተው ነበርና ክርስቶስን በትምህርቱ በተአምራቱ በሞቱም መሰሉት፡፡
እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስና ለቅዱስ ጳውሎስ አመታዊ መታሰቢያ እለት አደረሰን፡፡ በረከታቸው ይደርብን። አሜን!!

የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
“እንተ በአማን ንጹሕ ዝናም” የተባለ፣ የነፍሳትን ጥም ያበረደ የሕይወት ዝናም፣ የሕይወት ጠል፣ የሕይወት ውሃ ክርስቶስን ቋጥረሽ (በድንግልና ፀንሰሽ፣ በድንግልና ወልደሽ) የታየሽልን እውነተኛ ደመና አንቺ ነሽ፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም፡- “ንዑ እንከ ከመ ናልዕላ ለዛቲ ደመና ብርሃን እንተ ጾረቶ ለማየ ዝናም ንጹሕ" "ንጹሑን የዝናም ውሃ የተሸከመችውን የብርሃን ደመና ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት” ብሎ ጋብዞናል /አርጋኖን ዘሠሉስ ፮፡፪7። ስትወልጂው ማኅተመ ድንግልናሽ አለመለወጡ፤ አካላዊ ቃል ሰው ሲኾን አምላክነቱ ላለመለወጡ፣ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባዪ መኖርሽም ልጅሽ አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው) ሲባል ለመኖሩ ምሳሌ ነውና አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢያድርብሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ቢለብስ፤ አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት (ማለትም ከሩካቤ፣ ከዘር፣ ድንግልናን ከመለወጥ) ቢከለክልሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ቢከልልሽ ለዘላለሙ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን /ሃይ.አበ.፻፲፡፳፱/። እርሱም ሰው ኾኖ ከኃጢአት አንድም ከኃጢአታችን ፍዳ አዳነን።
ደስ ያለህ ባለ ምሥራች ገብርኤል ሆይ! ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነግረኸናልና ላንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ አንድም “ወነዋ ተወልደ ፍስሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኩሉ ዓለም" "እነሆ ለሕዝቡ ኹሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ” ብለህ /ሉቃ.፪፡፲/የጌታን ልደት ለኖሎት (ለእረኞች) ነገርኻቸዋልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ “እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ይሆናልና ደስ ይበልሽ” ብለህ /ሉቃ.፩፡፴/ ለእመቤታችን ነግረኻታልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም

በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የደንግል ማርያምን ፅንሰቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተደላ እንደሚሆን ነገረው፡፡
ይህ ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ፤ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበረ፤ የእስኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና፡፡
እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር፡፡ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሄር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ፡፡
የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሲጸልይና ሲማድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ፡፡ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷም ድኅነት የሚሆንባን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች፡፡
በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚህች ቀን የከበረች ቅድስት ሐና ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ፀነሰች።
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው። ይህ እንዴት ነው ቢሉ፦
#መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ ተጽፎአልና።
#ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል፣ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7፥14)
#ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።
#አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።
#አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው። "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።
እመቤታችን ሱባኤያችንን የሐዋርያት ሱባኤ ታድርግልን፣ ካህናትና ምዕመናን እንደ ዕጣን ከእሳት ተጨምረው በሰማዕትነት መዓዛ ያስጀመሩትን ሱባኤ የሰላምና ከበረከታቸው የምንሣተፍበት ያድርግልን። የሀገራችንን ፍጹም ኀዘንዋን፣ የቤተ ክርስቲያንንም ልቅሶዋን በምልጃዋ ትስማልን።
#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?
ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል
ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል
ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና
ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም
ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና
ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው
ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው

‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)
በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)
በዚህችም ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡
ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደእርሱ መጡ፡፡ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው፤ ‹‹አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን? ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።››
በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሳበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።
እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።
የጌታችን ጌትነቱን የሚገለጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው፤ እርሱንም ስሙት። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ። ስለ እርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነብያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ምንጭ:መጽሐፈ ስንክሳር
እንኳን አደረሳችሁ!

"መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡
"እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡
ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"

#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_ኪዳነ_ምሕረት
፩/ ነግሥ ( ለኲልያቲክሙ )
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡
ዚቅ፦
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፨ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፨ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፨ ለሕይወት ዘለዓለም ፨ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፨ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
፪/ ነግሥ ( እምጌቴሴማኒ ፈለሰት )
እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤
እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን፤
ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡
ዚቅ፦
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፨ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፨ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡
፫/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ኪዳነ ምሕረት )
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡
ዚቅ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፨ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፨
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፨ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፨ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።
ወረብ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ
ወዓሊ።
፬/ ለዝክረ ስምኪ ( መልክአ ማርያም )
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡
ዚቅ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፨ ወልድኪ ይጼውዓኪ፨
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡
ወረብ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት፤
ወልድኪ ወልድኪ ይጼውዓኪ ውስተ ሕይወት ወምንግሥተ ክብር።
፭/ ለእስትንፋስኪ ( መልክአ ማርያም )
ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፥
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡
ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፨ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፨ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡
ወረብ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል መዓዛ አፉሃ ታንሶሱ፡፡
፮/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ፍልሰታ )
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤
ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤
ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡
ዚቅ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ማኅደረ መለኮት ፨እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት ፨ እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡
ወረብ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማኅደረ መለኮት ጽርሕ ንጽሕት።
+++++ አንገርጋሪ +++++
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፥
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡
ወረብ ዘአመላለስ፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ወይቤላ ሠዓለም፡፡
+++++ ዘሰንበት +++++
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን፤ መዓዛ ዕፍረትኪ እምኩሉ አፈው፤ እትፌሳህ ወእትኃሰይ ብኪ ነፍቅር አጥባተኪ እምወይን፤ ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኩለንታኪ ሰናይት አንተ እምንሴየ፤ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ፃዒ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት፡፡
💠💠💠 መልካም በዓል💠💠💠

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ በረከት
ጷጉሜን ፬ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
-በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
-ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
-የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
-በሕመም ምክንት በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
-እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵውያት በሙሉ!
የዓመታትና የአዝማናት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለአዲሱ ዓመት ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ !!
“ወዓመቲከኒ ለትውልደ ትውልድ፤ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው” (መዝ. ፻፩፥፳፬)፡፡
ይህንን ቃለ እግዚአብሔር የተናገረው እግዚአብሔር በቅብዕ ቅዱስ አማካኝነት ሀብተ ትንቢት ወመዝሙር ያሳደረበት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው፤ የቃሉ መሠረተ ሐሳብም ዓመታት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆናቸውን፣ እንደዚሁም የተሰጡት ለሰው ልጆች መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ በእርግጥም ዓመታት ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጡ ሀብቶች ናቸው፤ ዓመታት፣ ወራት፣ ዕለታት፣ ቀናት፣ ሰዓታት የሚያስፈልጉት ለሰው ልጅ እንጂ ለእግዚአብሔርና በመንፈሳዊ ዓለም ለሚገኙ ፍጡራን አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው በደካማው ዓለም የሚኖር ደካማ ፍጡር ስለሆነ ለኑሮው ጊዜያት የግድ ያስፈልጉታል፤ በመንፈሳዊ ዓለም የሚገኙ ፍጡራን ግን፣ ድካም የሌለባቸው ትጉሃን ስለሆኑ፣ ዓመትም ቀንም ሰዓትም ወዘተ አያስፈልጋቸውም፤ የሰዓት መለኪያ ብርሃንም የላቸውም፤ ምክንያቱም ያሉበት ዓለም ሁሌም ብርሃን እንጂ ጨለማ ስለማይፈራረቀው፣ እንደዚሁም ተለዋዋጭ አየርም ሆነ ዕድሜ ስለሌላቸው ማለት ነው፤ ለሰው ግን የጊዜ መለኪያ የሚሆኑ ብርሃናትና አዝማናት ወዘተ የተመደቡለት ስለሆነ፣ በእነሱ እየተመራ ጊዜያትን ይለካል፤ ዓመታትን ወራትንና ቀናትን ወዘተ ይቈጥራል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡-
ዓመታት ከእግዚአብሔር ለእኛ የተሰጡን ያለምክንያት አይደለም፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ክብርም ጥቅምም አለውና ልናከብረውና ልንጠቀምበት እንጂ፤ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ጊዜ ትልቁና ቀዳሚው የሥራ መሣሪያ ነው፡፡ እህልን ዘርተን የዓመት ምግባችንን የምናገኘው ወርኃ ክረምት ስለተሰጠን ነው፤ ይህ ወቅት ባይኖር ኖሮ የእርሻ ሥራ ሠርተን ራሳችንን መመገብ እንደማንችል የምንስተው አይሆንም፡፡ ከዚህ አንጻር ዓመታትንና ወቅቶችን እንደ አመቺነታቸው እየተጠቀምን ልንሠራባቸው እግዚአብሔር አመቻችቶ ሰጥቶናል ማለት ነው፤ ስለዚህ በብሂለ አበው “ጊዜ ሳለ ሩጥ ….” እንደሚባለው ሁሉንም በጊዜው ጊዜ መሥራትና ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሰውም ሆነ ጊዜ ለሥራ የተፈጠሩበት ምክንያት መክበርም መዳንም ማግኘትም ማደግም መልማትም በሥራና በሥራ ብቻ የሚገኝ ከመሆኑ የተነሣ እንደሆነ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ “ብላዕ በሐፈ ገጽከ፤ በፊትህ ላብ እንጀራህን ብላ” የሚለው አምላካዊ ትእዛዝም ይህንን ይገልጻል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ያለመታከት ሠርተን ራሳችንን በራሳችን የምናስተዳድርባት በሀብትና በጊዜ የተዋበች ምድር አስረክቦናል፤ ምድሪቱንም ለእኛ በሚመች አኳኋን አበጅተን እንድንጠቀምባት የሚያስችል አእምሮና ጉልበትም ከጤና ጋር ሰጥቶናል፤ ሐቁ ይህ ከሆነ ታድያ ለምንድን ነው በምድራችን ስጋትና ጭንቀት፤ ረኃብና እርዛት፣ የሀብት እጥረትና የእርስ በርስ ግጭት በስፋት የሚታየው የሚለውን ጥያቄ ሰው ሁሉ በጥልቀት ሊያጤነው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ምድር አሁንም ለፍጡራን የሚበቃ የተትረፈረፈ ሀብት ያለጥርጥር አላት፣ የአጠቃቀም ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሀብት የሌለው የምድር አካባቢ ፈጽሞ የለም፡፡ ይህም ከሆነ ሁሉም ወደ ሥራና ሥራ ብቻ ተሠማርቶ ጥረቱን ከቀጠለ የሚያጣው ነገር የለም ማለት ነው፣ ሰው ጤና ዕውቀትና ሰላም ካለው ሀብታም ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከተሟሉለት ሌላው ሁሉ እግዚአብሔር ከሰጠው ምድር ሠርቶ የሚያገኘው ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ግን ነገሩ ሁሉ ጨለማ ይሆንበታል፤ አካላዊና አእምሮአዊ ጤናውም ይደፈርስና ሳያጣ ያጣ ወደ መሆን ይቀየራል፡፡ ዛሬ በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን እየተከሠተ ያለው ሐቅ ይኸው ነው፡፡
ይህ የሰላም እጦት በሀገራችን በኢትዮጵያ በርከት ላሉ ዓመታት እየተደጋገመ በመከሠቱ፣ በዚህ ጠንቅ ሕዝባችን ሳያጣ ያጣ ሆኖአል፤ ኢትዮጵያን በመሰለች ለምና ምድራዊት ገነት ተቀምጠን፣ በዓለም ውስጥ የድህነት ተምሳሌት ሆነን መገኘታችን፣ የሁላችንም ኅሊና ሊኰረኲረው ይገባል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት
በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሁሉ በአጽንዖት የምንመክረው ዓቢይ ምክር በግጭት ችግሮቻችንን መፍታት በፍጹም አንችልም፤ በመራራቅም ማደግ አንችልም፤ በተለያየን ቊጥር ድህነታችንን ከማስቀጠልና ደካሞች ከመሆን በቀር የምናገኘው አንዳች ፋይዳ የለም፤ እውነቱ ይህ ከሆነ ከገባንበት ያላስፈላጊ ግጭት በፍጥነት ወጥተን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ወደሚያስችል ወደ ምክክርና ውይይት እንግባ፤ አዲሱ ዓመት እውነተኛ አዲስ ዓመት ሊሆን የሚችለው ይህንን ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡ አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጉም የለም፡፡ ስለሆነም አዲሱን ዓመት አዲስ የሆነ የሰላምና የዕርቅ የስምምነትና የአንድነት የይቅርታና የምሕረት የፍትሕና የእኩልነት መርሕ አንግበን ፍጹም ሰላምን ለማንገሥ በቊርጥ ማሰብና መነሣሣት አለብን፣ ይህንንም ለማሳካት በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ ጠረጴዛ ተገናኝተን ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር እንድንፈታ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም
አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የበረከት የዕድገት የሃይማኖትና የልማት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና በብሩህ ተስፋ እንድንቀበለው መልእክታችንን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡
እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዓመት ያድርግልን !
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን !!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፡፡

ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃችሁ ሃይማኖታችሁ የቀና የተወደዳችሁ ምእመናን ሆይ ልዑል እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል። በይቅርታው ገናናነት በጎ የሆኑትን ሁሉ ስለሰጠን የልዕልናውን ምስጋና ጨምረን እጅግ ልናበዛ ይገባናል። እስከዚህች ዕለትና ሰዓት አድርሶናልና።
ዳግመኛም ከበደላችንና ከክፉ ሥራዎቻችን ወደ ንስሐ እስከምንመለስ በእኛ ላይ ይታገሥ ዘንድ ከእኛ አስቀድሞ ብዙዎች አሕዛብን እንዳጠፋቸው ስለ ክፉ ሥራችን እንዳያጠፋን እግዚአብሔርን እንለምነው። እንግዲህም ከታካችነታችን ነቅተን ከወደቅንበት እንነሣ ስለ አለፈው በደላችንና ስለ ብዙ ኃጢአታችን በፊቱ ልናለቅስ ወደርሱም ልንጮህ ይገባናል።
በሕይወታችን ዘመን ሁሉ ከጠላችን ሰይጣን ወጥመድ ጠብቆ በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ በነፍስ በሥጋም ጤነኞች እንደሆን በቀናች ሃይማኖትና በበጎ ሥራ ሁሉ ጸንተን ደስ እንዳለን እንደ ዛሬው ለመጪው ዓመት ያደርሰን ዘንድ እንለምነው።
ከእኛም በሞት የተለዩትን በበጎ ዕረፍት እንዲያሳርፍልን፣ በሀገራችንም ጽጋን በረከትን ይሰጥ ዘንድ፣ የተራቡም እንዲጠግቡ የምድራችንን ፍሬ ይባርክ ዘንድ፣ በሽተኞች ይፈወሱ ዘንድ፣ ሽማግሎዎችና አሮጊቶች፣ የሙት ልጆችም ይጠበቁ ዘንድ ለሀገራችንና ለዓለሙ ሁሉ ሰላም ይሁን አሜን!
መጽሐፈ ስንክሳር

#መቁጠርያ_በቤተክርስቲያን (Prayer Ropes)
በተለያዩ መናፍቃን ዘንድ እንደ ባዕድ ነገር ነው የሚታየው የሚገርመው ለዚህ ንግግራቸው ምክንያት እንኳ ማስቀመጥ አይችሉም። አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ ይጠቀሙበታል። መቁጠርያን ለፀሎት ስለተጠቀሙ መክሰስ አይገባም። ቅዱስ ጳውሎስ በ 1ኛ ተሰ 5፥18 ላይ "ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ..." በማለት እንዳስተማረን አብዝቶ መጸለይ ያስፈልጋል። የጸሎት ተቃዋሚም ጠላት ሰይጣን ነው፡፡ ጌታም "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ" ማቴ 26:41 ብሏል፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም ፀሎትን አብዝተን እንድናደርግ መፅሀፍ ቅዱስ ይመክራልና
#እኛ_ኦርቶዶክሳውያን_መቁጠርያን_የምንጠቀመው
#1ኛ በትኩረትና በተመስጦ ሆነን ለመፀለይ
#2ኛ ይዘነው በመጓዝ ፀሎትን መፀለይ እንድናስታውስ
#3ኛ እንዳንፀልይ ከሚያግዱን ክፉ መንፈሶች ለማሸነፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙባቸው መቁጠርያዎች ባለ 41 መቁጠርያ (Beads) (በውስጡ 41 ድብልብሎችን) እና ባለ 64 መቁጠርያ (በውስጡ 64 ድብልብሎችን) ናቸው
41_የመሆኑ_ምስጢር_የጌታችንና_የመድሃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን_41_ግርፋት_ቁስል_ለማሰብ_ሲሆን
#64_የመሆኑ_ምስጢር_ደግሞ_የእናታችን_የእመቤታችን_በምድር_ላይ_የኖረችበት_እድሜ_ለማሰብ_ነው
አንዳንድ ቀሳውስትና መነኮሳት 150,300 ወይም ከዛም በላይ ድብልብሎች በመቁጠርያ ውስጥ
ይጠቀማሉ። ባለ 41 መቁጠርያ ላይ በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች አሉ።እነርሱም፦
👉 1ኛ ጌታ በመዋዕለ ስጋው እንድንፀልይ ያስተማረን ፀሎትን እና የቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ።
ይህም፦ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ
መንግስትህ ትምጣ... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልዓኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ...(12 ጊዜ)
👉 2ኛ አቤቱ ማረን! (41 ጊዜ)
👉 3ኛ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ
ማረን! (41 ጊዜ)
👉 4ኛ ኪርያላይሶን(41 ጊዜ)
👉 5ኛ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት ፣አዴራ፣
ሮዳስ (41 ጊዜ)
👉 6ኛ. ኦ! አምላክ(41 ጊዜ)
👉 7ኛ .ኦ! ክርስቶስ (41 ጊዜ)
👉 8ኛ ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም
ብለህ ከመአቱ አድነን፣ሰውረን
ምህረትንም ላክልን (ማረን)41 ጊዜ)
👉 9ኛ አቤቱ አምላካችን መድሃኒታችን ሆይ ስማን! (41 ጊዜ)
👉 10. ኤሎሄ (አምላኬ) (41 ጊዜ)
👉 11. ወዮልኝ! ወዮልኝ!ወዮልኝ!አምላኬ ሆይ እየኝ (ተመልከተኝ)
👉 12.አቤቱ እንደ ምህረትህ
እንጂ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን! (12 ጊዜ)
👉 13. አቤቱ በመንግስትህ አስበን! (12 ጊዜ)
👉 14. እመቤቴ ሆይ (7 ጊዜ) ከዚህ በላይ የተጠቀሱት 14ቱ በፀሎት ጊዜ በመቁጠርያው በመደጋገም የሚፀለዩ ናቸው። እኚህ የተለመዱ ስርዓት ወጥቶላቸው በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች ሲሆኑ ከዚህ በላይም የራስን የግል መሻት(ጨምሮ) ጨምሮ መፀለይ ይቻላል።ባለ ስልሳ አራቱን ( 64) መቁጠርያ ስንጠቀም ደግሞ 41 ጊዜ ተደጋግመው የሚፀለዩትን 64 ጊዜ ማድረግ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ 12 እና 7 የነበሩት እንደዛው ሆነው ይቀራሉ።

እሾህ #የሌለባት_ጽጌ_ሬዳ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ጊዜው የአበባና የፍሬ ጊዜ ነው ቤተክርስቲያንም ዘመነ ጽጌ ወርሃ ጽጌ ብላ ስለ ጽጌያት ታስተምራለች:: #ከመስከረም 26 እስከ #ህዳር 6 ቀን ያሉት ተከታታይ 40 ቀናት ናቸው ስለ ጽጌ ወይም ስለ አበባ የምታስተምረው ትምህርት ይህ እኛ የምናውቀውን በአፈር፣ በውኃና በፀሐይ ብርሃን አማካኝነት የሚያድገውን የእጽዋት አይነት ብቻ የሚመለከት አይደለም። ከዛ ይልቅ አማናዊት አበባ ስለምትባል ስለ ድንግል ማርያም በዚህ ወቅት በምልዐት ታስተምራለች ትሰብካለች:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እውነተኛ አበባ ነች።
እንደ ሳይንሱ ገለጻ አንድ እጽዋት እጽዋት ለመሰኘት ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን ሊያሞላ ይገባል ይላል። እነርሱም እውነተኛ ሥር እውነተኛ ግንድ እውነተኛ ቅርንጫፍ ናቸው ። እነዚህ እጽዋት በሥሮቻቸው አማካኝነት ከአፈር ውስጥ ውኃና ሚኒራልን በመውሰድ ከቅርንጫፍቻቸው ካሉ ቅጠሎች ደግሞ የፀሐይ ብርሃን በማምጣት በግንዶቻቸው አጓጓዠነት በመጠቀም ፖቶሰቴንስስ በተባለ ሂደት ምግቦቻቸውን ማዘጋጀት ይችላሉ ።እውነተኛ ሥር ግንድና ቅርንጫፍ የሌላቸውን አረንጓዴ ተክሎች ግን አልጋይ እና ፈንጋይ እየተባሉ ይጠራሉ እውነተኛ ሥር ግንድና ቅርንጫፍ የላቸውምና ምግባቸውን ማዘጋጀት አይችሉም ስለዚህ እጽዋት ተብለው አይጠሩም ::
#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ታዲያ ከእውነተኛም እውነተኛ የሆነች ( እጸ ሕይወት) እውነተኛ የሕይወት አበባ ነች መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች እውነተኛ የወይን ግንድ አብቃይ ቅርንጫፎቿም በሰማያተ የሚገኑ አረገ ወይን ነች:: (ሥር) መዝ 86÷1 (ግንድ)ኢሳ11÷1 (ቅርንጫፍ)ዮሐ 15÷5 ።
የሕይወት መብል መጠጥ የሆነ ክርስቶስን የወለደችልን ድንግል ማርያም እውነተኛ ሥር ግንድና ቅጠል ያላት እውነተኛ አበባ መሆኖን አሰረግጦ መናገር የተገባ ነው። ለምን ቢሉ
አንዳንድ ዲያቢሎስ ያደረባቸው ደፋር ሴቶች በዘመኑ ብኖር እኔም ክርስቶስን እወልደው ነበር ብለው የድንግልን ክብር ከእራሳቸው ክብር ጋር በትቢት ባልተገባ የሚያስተካክሉ ልካቸውን ማሳወቅ ስለሚገባ ነው በእስራኤል ያሉ ሴቶች ደግሞ ዛሬ ድረስ ክርስቶስ አልተወለደም ወደፊት ከአንዳችን ይወለዳል ብለው በድፍረት በከንቱ ይጠባበቃሉ በእውነት ግን እነዚህ ሴቶች እንኳን የሕይወት መብልና መጠጥ የሆነውን ክርስቶስን ሊወልዱ ቀርቶ ሊወልዱት የሚችሉትል ተራ ሰው እንኳ በአግባቡ ስለመመገባቸው እርግጠኞች አይደሉም ስለዚህም ምግባቸውን እንኳን ማዘጋጀት እንደ ማይችሉ አልጋይና ፋንጋይ ናቸው ማለት ይቻላል። እውነተኞች አይደሉምና ።
#እርሷ_እመቤታችን እንኳን ስለራሷ በትንቢት የተጻፈውን ባነበበች ጊዜ ከዚህች ቅድስት ሴት ከዘመኗ ደርሼ ውኃ ቀድቼ እንጨት ፈልጬ ገረዷ ሆኜ ባገለገልኳት ብላ በትህትና ገረድነትን ተመኘች እንጂ እኔ በሆኩ አላለችም ጊዜው ደርሶም መላእኩ ገብርኤል መጥቶ አምላክን ለመውለድ በተገባ ተገኝተሻል ብሎ የመውለዷን ዜና ሲያበሥራት እንኳ ይህ እንዴት ይሆንልኛል እኔ #የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለችሁ እንጂ ከወነማ ከመጣህማ ብላ በኩራት ሆና አልተናገረችሁም .....ይህ እንዴት ያለህ ትህትና ነው? የአምላክ እናቱ ነሽ እየተባሉ እራስን ገረድ ማለት! ሊቁም ይህ ትህትና ቢገርመው ልዕልናዋን ከትህትናዋ አስማምቶ " #በትህትና_የተናገርሽ ተራራ ሆይ " ብሎ ጠራት::
እውነተኛይቱ አበባ ግን አስቀድማ ዓለም ሳይፈጠር በተዘክሮተ ፈጣሪ ዋላም ዓለም ከተፈጠረ በኃላ በነቢያት ትንቢት በሐዋርያት ስብከት በደቂቀ አዳም ልብ የነበረች፣ ያለችና ፣የምትኖር የማደርቅና የማጠወልግ እንቡጥ አበባ ነች።
#አበባ የዓይን ማረፊያ የልብ ተስፋ የአፍንጫ መዐዛ ነው እመቤታችንም አስቀድማ ለእናት ለአባትዋ በኃላም ለደቂቀ አዳም ሁሉ የዓይን ማረፊያ የልብ ተስፋ የነፍስ መዐዛ ነች " #ከዕሴይ_ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ " እንዳለ ሊቁ #ውዳሴ_ማርያም ዘእሁድ ኢሳ11÷1
#አበባ መድኃኒትን ያስገኛል እውነተኛይቱ አበባ እመቤታችንም መዳኒ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን አስገኝታለች እስለዚህ " እሙ ለመዳኒት" የመዳኒት እናት ትባላለችና አባባ ነች ሉቃ 2÷10-11
አበባ ንብቦችን ይስባል ማርን ያሰራል እውነተኛይቱ አበባ እመቤታችንም ወልድ ክርስቶስን ስባለች ማር የሆነች የወንጌል ሕግን አሰርታለች። ማር ጥዑም ነው ክርስቶስና ወንጌልም ጥዑማን ናቸው አንድም ማር መድኃኒት ነው ክርስቶስ እና ወንጌልም መድኃኒት ናቸው::"ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል" መዝ 86(87)÷2
"ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና" መዝ 44(45)÷10-11
አበባ ምግበ ሥጋን ያስገኛል (ለምሳሌ አበባ ጎመን የመሰሉ ተክሎች ወዘተ...) እውነተኛይቱ አባ እመቤታችንም ምግበ ሥጋወነፍስ የሆነ ክርቶስን አስገኝታለች ዮሐ 6÷56 ማቴ 26÷26
"በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ " እንዳሉ ሊቃውንት ድንግል ሆይ በምንና በማን እንመስልሻለን ክብርሽን የሚገልጥ ነገር አጣን ብለን በተደሞ ዝም እንበል እንጂ እመቤታችንንስ አበባ ብቻ የሚገልጣት ሆኖ አይደለም።
እንዴት? ቢሉ አበባ ከምድር ተገኝቶ በምድር ይቀራል አበባይቱ እመቤታች ግን ከምድር ብትገኝም ቅሉ የማትደርቅ የማትጠወልግ ምድራዊት ወ ሰማያዊት የሆነች ለምለም አበባ ነች።
አበባ ይልቁኑ ጽጌ ሬዳ በእህሾ የተከበበ ነው ። አበባይቱ እመቤታችን ግን የጥንተ አብሶ እሾህ ያልከበባት ንፁህ ጽጌ ሬዳ ናት። ወርቅ ከመሬት ከጭቃ ይገኛል ነገር ግን ጭቃ አይደለም እመቤታችንም ከምድር የተገኘች ሆና ሳለ ግን ምድራዊ በደል ያላቆሸሻት እሾህ አልባ የወርቅ አበባ ነች ለይቶ ቀድሷታልና “ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።” መዝ45(46)፥4
አበባ መድኃኒት ቢያስገኝ ከጊዜያዊ ሕመም የሚያድን ጊዜያዊ መድኃኒት ነው የሚያስገኘው አበባይቱ እመቤታችን ግን አንዴ ከተበላ አንዴ ከተጠጣ ዳግመኛ የማያስፈልገውን ዘላለማዊ ፍቱን መድኃኒትን ያስገኘች ሕያው አበባ ነች።
አንድ ንጥል አበባ ዘሩን የሚተካው ወንዴና ሴቴ የተባሉ ክፍሎቹን በመጠቀም ነው የወንዴው ብናኝ ጊዜውን ጠብቆ እራሱን ሲያበን ማጣበቅ የሚችለው የሴቴ ክፍል ብናኙን ይቀበልና ሌሎች አበቦችን ማፍራት ይጀምራል ። ይህ ሂደት ኢ ተሻጋሪ(እዛው በዛው) የማፍራት ሂደት ይባላል ። በሌላ በኩል ደግሞ የአንዱ ንጥል አበባ የወንዴ ብናኝ በንቦች ፣በወፎች፣ እንዲሁም በሰዎች ንኪኪ ወይም በንፋስ ሽውታ አማካኝነት በኖ ከራሱ የሴቴ ብናኝ ተቀባይ ውጪ ተሻግሮ በሌላ አበባ የሴቴ ክፍል ላይ በመጣበቅ የሚያፈራበትም መንገድ አለ ይህም ተሻጋሪ የአረባብ ዘዴ በመባል ይታወቃል ።
አበባ እንዲ ባለ መልክ ሲያብብ አማናዊቷ አበባ እመቤታችን ግን ያለ ዘርዐ ብዕሲ ያለ ወንድ ዘር ) በ ግብረ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ጸንሳ መውለድ ችላለች ስለዚህ በእጅጉ ከአበባዎች ሁሉ ትበልጣለች አልን።
"ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች #አንቺ_እንደ_እርሷ_ነሽ #ውዳሴ_ማርያም_ዘእሁድ
.......ይቆየን ............

+++ "እኔ" ብቻ +++
ዕውቁ ሩስያዊው የልብ ወለድ ደራሲ ዶስቶየቩስኪ "Brothers Karamazov" በተሰኘው ድርሰቱ ስለ አንዲት ምናባዊት ንፉግ ሴት ታሪክ እንዲህ ይተርካል። በአንድ ዘመን በግብርና ሥራ እየተዳደረች የምትኖር ክፉ ሴት ነበረች። ታዲያ በሕይወት እያለች አንድ በጎ ነገር እንኳ ሳትሠራ ይህን ዓለም በሞት ተሰናበተች። ነፍሷም በወጣች ጊዜ ወዲያው አጋንንት እየተናጠቁ ይዘዋት ሄደው ወደ እሳት ባሕር ወረወሯት። ጠባቂ መልአኳም ይህን ባየ ጊዜ ከፈጣሪ ፊት ቆሞ የሚያዘክርላት ጥቂት በጎ ሥራ ሠርታ እንደ ሆነ ለማስታወስ ሞከረ። ወዲያውም "አንድ ጊዜ ከማሳዋ ላይ አንድ ራስ ሽንኩርት ነቅላ ለአንዲት ነዳይ መስጠቷን" ለአምላኩ አሳሰበላት። እግዚአብሔርም "በል ያን ሽኝኩርት ውሰድና ወደ እርሷ ሂድ። እርሱን ይዛ መውጣት ከቻለች ወደ ገነት ታስገባታለህ። ካልሆነ ግን እዚያው ሲኦል ትቀራለች" አለው።
መልአኩም እንደ ተባለው ሴቲቱ የሽንኩርቱን ራስ እንድትይዝ አድርጎ በጥንቃቄ ወደ ውጭ ይስባት ጀመር። ነገር ግን ሌሎች በዚያ የእሳት ባሕር ውስጥ የነበሩ ኃጥአን ስትወጣ ሲመለከቱ አብረዋት ለመውጣት እርሷ ላይ ተንጠላጠሉ። ያቺ ጨካኝ ሴት ግን ክፉኛ በመወራጨት ከላይዋ ላይ እያራገፈቻቸው "እኔ ነው እየሳበኝ ያለው እናንተን አይደለም። ይህ ሽንኩርት የእኔ ነው። የእናንተ አይደለም።" አለች። ይህን እየተናገረች ሳለም የያዘችው የሽንኩርቱ ጫፍ ተበጥሶ ወደ እሳቱ ተመልሳ ገባች። መልአኩም በሁኔታው እያዘነ ከእርሷ ተለይቶ ሄደ።
ያን የሽንኩርት ጫፍ የበጠሰው ምን ይመስላችኋል? እርሷ ላይ የተንጠለጠሉት ነፍሳት ወይስ የእርሷ ጭካኔ እና ንፋግነት?
ይህ የዶስቶቩስኪ ምናባዊ ትርክት በዚህ ዘመን ያለነውን የእያንዳንዳችንን ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል። ከመጠን በላይ ለራስ በመጨነቅና የራስን ምቾት ብቻ መፈለግ የእኛ ጊዜ መለያ ጠባይ ሆኗል። በንግግራችን ውስጥ "እኔ" "ለእኔ" "የእኔ" የሚሉት ቃላት እየረቡ "እኛ" የሚለው ቃል እየሳሳ መጥቷል። በብዙዎች የሚመለክ በየቤቱ የቆመ የዘመኑ አዲስ ጣዖት ቢኖር "እኔ"ነት (ራስ) ነው።
ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትኩረት ማዕከል ለመሆን የማይቆፍሩት ጉድጓድ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በተገኙበት ሁሉ ስለ እነርሱ እንዲወራ ይፈልጋሉ። ለቀብር እንኳን ሄደው ለሞተው ሰው ከሚሰጠው ትኩረት አንጻር በዚያች ቅጽበት ያን አስከሬን ቢሆኑ አይጠሉም። ስማቸውን በየሰው አፍ ለማስገባትና መነጋገሪያ ለመሆን የትኛውንም ዓይነት ዋጋ ይከፍላሉ። ይህን ጊዜ "ራስን መውደድ" በሽታ ይሆናል። በራስ ዓለም ውስጥ እንደ መጥፋት፣ ራስን በራስ እንደመዋጥ ያለ ሊታከም የሚገባው ጽኑ ደዌ!
ሁልጊዜ በስግብግብነት እና ለእኔ ብቻ በማለት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች መንፈሳቸው የተሰበረ ይሆናል። የገዙት አያስደስታቸውም፣ የሰበሰቡት አያረካቸውም። በሕይወታቸው ውስጥ ያስወጡት መልካም ነገር ስላለ መቼም የውስጥ ዕረፍት አያገኙም። ያ ከሕይወታቸው ያስወጡት መልካም ነገር ምንድር ነው? "ብቻ ያለ መሆን" መልካምነት ነዋ!
"ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም" ዘፍ 2፥18
በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ግለኝነትና "ለእኔ ብቻ" ማለት ፈጽሞ የተወገዘ ነው። ምድር ላይ ባለችው ቤተ ክርስቲያን በኅብረት መንፈስ ካልኖርህ "በሰማያት ወደ ተጻፉት የበኩራት ማኅበር" ልትገባ አትችልም።(ዕብ 12፥23) በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ቆመው የሚያመሰግኑት ሱራፌል ክንፎቻቸው እርስ በርስ የተያያዘ ነው። ይህንንም አንድ ሊቅ ሲተረጉም በአምላክ ዙፋን ፊት ለመቆምና ከእነዚህ አመስጋኝ መላእክት ጋር አብሮ ለመቆጠር ሰዎች በአንዲት ኅብረት ሊኖሩ እንደሚገባቸው ያሳያል ሲል ተርጉሞታል። ክርስትና ራስን ማዕከል የማድረግ ሳይሆን ሌሎችን የማገልገልና ስለ ብዙዎችም በፍቅር መሥዋዕት የመሆን ሕይወት ነው።

በወላይታ ዞን በቀበሌያቸው ውስጥ ብቻቸውን ኦርቶዶክስ ሆነው ለጸኑት እናት የታነጸው ህንጻ መቅደስ ነገ ህዳር 04 ይመረቃል።
በወላይታ ሀገረስብከት ዳሞት ወይዴ ወረዳ አንካ ሻሻራ ቀበሌ ብቸኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሆነው ለዘመናት ብቻቸውን በቀበሌው ውስጥ ኖረዋል።
በማሳቸው ውስጥ ሣር ጎጆ ቀልሰው ዘውትር ሰንበት በእዚያ እልፍኝ የቅድስት አርሴማን ሥዕለ አድኖ ይዘው ስርዓተ አምልኮ ይፈጽሙ ነበር።
በአሁኑ ወቅት 60 ተጨማሪ አባወራ እና እማወራ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በአካባቢው አግኝተዋል። እኚህ እናት በማሳቸው ላይ በሰጡት ስፍራ የቅድስት አርሴማ ህንጻ መቅደስ ሙሉ በሙሉ ታንጾ ነገ ህዳር 04 ይመረቃል ሲል ወላይታ ዲቻ ታይምስ ዘግበዋል።