Telegram Web Link
#አድኑኝ! መኖር ፈልጋለሁ እባካችሁ ወገኖቼ
#hawassa| በአስቸኳይ 560000 ካላገኘች 😭
"ወገኖቼ_በገንዘብ_ምክንያት_መሞት_የለብኝም"
በለጋ እድሜዋ በልብ ህመም ምክንያት ቤቷ በስቃይ ስትማቅ ወላጆች የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲጨነቁ ማየት በእውነት ልብ ይሰብራል። አስቸኳይ ህክምና ካላገኘች ሁለተኛው ቫልቭ ስራ ያቆማል። ልብ ስራ ካቆመ ምን ማለት እንደሆነ ይገባናል።
የዛሬ 11 ዓመት ገና በጨቅላ እድሜዋ በትምህርት ላይ እንዳለች ነበር የልብ ህመም እንዳለባት የተረዳችው። ችግሩ የልብ የደም ቱቦ መጥበብ (Redo Mitral Valve) ሲሆን በወቅቱ በሙሉወንጌል ኮምፓሽን ድጋፍ ወደ ህንድ ተወስዳ በቀዶ ጥገና ሰው ሰራሽ ቫልቭ ተገጥሞላት ወደ መደበኛ ጤናዋ ተመለሰች።
ነገር ግን ያ የተገጠመላት ቫልቭ ከእድሜዋ (የአካል እድገት ጋር) አስፈላጊውን የደም ዝውውር ለማድረግ የማይችል በመሆኑ አንዱ ቫልቭ ስራ ማቆሙን ሁለተኛውም ሊያቆም ጥቂት ጊዜ እንዳላት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሐኪሞች አሳወቁ። ህክምናውን በጥቁር አንበሳ ማድረግ የሚቻል ቢሆንም የግድ 600 ወረፋ መጠበቅ ግድ ይላታል። በዚህ መሐል ህይወቷ አደጋውስጥ እንደሆነ ያሰዱት ሐኪሞቹ አቅም ካለ ወደ ግል ተቋም አፋጣኝ የቀዶ ጥገና እና የነበረው ቫልቭ እንዲቀየር አሳሰቡ።
ለቃል ቤተሰቦቿም ያላቸውን ሁሉ ለልጃቸው ህክምና ያዋሉ ቢሆንም ይህንን ቀዶ ጥገና ለማስደረግ በግል የህክምና ተቋሙ የወጣውን ተመን ለመክፈል አቅሙ እንደሌላቸው ያውቃሉ። በአካል ባገኘኋቸው ወቅት ልጃቸውን በገንዘብ ምክንያት ሊያጧት እንደተቃረቡ በማሰብ በከፍተኛ ጭንቀት ተወጥረው ይገኛሉ።
ወጣት ፍሬወይኒ "ጤነኛ ሆና እንደእኩዮቿ የቤተሰብ ብሎም ለሀገር አለኝታ መሆን ህልም እንዳላት ስትገልፅ የቤተሰቦቿን ጭንቀት ማየቱ የከበደ ህመም ከማስተናገድ የላቀ ህመም ሆኖባታል።
በአሁኑ ሰዓት ፍሬወይኒ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን በህመሙ ምክንያት አቋርጣለች። ህልሟ ተስፋዋ ወደ መጨለም እንደተቃረበ ሁኔታዋ ያሳብቃል። ለመንቀሳቀስም ሆነ ተፈጥሯዊ ግብሮቿን ለመፈፀም የሰው ድጋፍ ግድ ብሏታል። ይሁን እንጅ ተስፋዋ አልከሰመም። የጤናዋ ሁኔታ በህክምና የሚድን ሆኖ በገንዘብ ችግር ለሞት የተቃረበን የኢትዮጵያ ደግ ህዝብ ከጎኗ ሊሆን እንደሚችል ታምናለች። ጤናዬን እንዳገኝ፣ ህልሜን እንዳሳካ ከኔ አልፌ ለሌሎች ወገኖቼ አለኝታ እሆን ዘንድ እርዱኝ ስትል በተማፅኖ ፊታችን ቀርባለች።
560000 ብር ህይወቷን ይታደጋል። ከተባበርን ደግሞ ነገ ያለመችውን ስታሳካ የምንኮራባት እናደርጋታለን።

"TO WHOM IT MAY CONCERN

FREIWOT TESFAYE came to Efouzeir cardiac center and she needs open heart surgery for Redo Mitral Valve Replacement. The total cost for the surgery is:

560,000Birr (Five sixty Twenty Thousand Birr only).

The center will perform the surgery when the total payment is made. This letter was written upon her request."
ህክምናዋንና ለበርካታ አመታት ወላጇቿ ያደረጉላትን ማስረጃ አያይዘናል። በገንዘብ ባንችል እንኳ በመደወል እናፅናናት።
ውድ ኢትዮጵያውያን አነሰ በዛ ሳንል በመደገፍ ህይወቷን እንታደግ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን።
የወላጆቿን ስልክና የባንክ አካውንት ከስር አስቀምጠናል።
CBE-1000187280595 /0930958512 ( 0912184652 እናት ሁሌ ጌታቸው CBE- 1000252939818 አባት ጌታቸው ወጋሳ አየለ)
#እናመሰግናለን!| ዶ/ር ዘነበ መኮንን
#hawassa #Alphacare
በብቁ የህክምና ሙያው የምናውቀው ዶ/ር ዘነበ #የአልፋኬር መካከለኛ ክሊኒክ ባለቤት ማህበረሰብን ከሙያው በተጨማሪ በበጎ አድራጎት ስራ ሁሌም ቀድሞ ይገኛል። አሁን ደግሞ ለወጣት ፍሬህይወት ህክምና በሚደረገው የድጋፍ ጥሪ እኔም የበኩሌን በማለት አንድ ሺህ ብር ለግሷል። ደጋግ ልቦች ፈጣሪ ብድራቱን ይክፈልልን። እናመሰግናለን።
በነገራችን ላይ በእናቶችና ህፃናት እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ ህክምና ለማግኘት ከፈለጋችሁ መምቦ ወደ ሪፈራል በሚወስደው መንገድ በስተግራ ከኮሜሳ ህንፃ ጎን አልፋኬር መካከለኛ ክሊኒክ ዶ/ር ዘነበን ያገኙታል።
መልካምነት ይከፍላል!
#እንኳን_ደስ_አላችሁ| ፍሬ ታክማለች
#hawassa
እህታችንን ፍሬ በዛሬው እለት ከ5 ሰዓት በላይ የፈጀውን የልብ ቀዶ ጥገና (የቫልቭ ለውጥ) ተደርጎላት ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ እሷም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አባቷ አቶ ጌታቸው በደስታ ውስጥ ሆነው ምስጋናቸውን በስልክ ነግረውኛል። ክበሩልን።
ውድ ቤተሰቦች ለበጎነት ሁሌም ቀና የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን የእህታችንን አትርፉኝ ጥሪ ተቀብላችሁ በሐሳብ፣ በገንዘብና ደግሞም በማህበራዊ ሚዲያ ተረባርባችሁ የተጠየቀውን 560,000 በማዋጣት ህይወት ስለታደጋችሁ ፈጣሪ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ 😍
ቤተሰቦቿም ከቃል በላይ የሆነ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አድርሱልን ብለዋል።
ሐምሌ 7/2015 ዓ.ም
2025/10/27 05:06:46
Back to Top
HTML Embed Code: