#የቅዳሜ_እንግዳ| ከወደቄራ
ጋዜጠኛ ለማ ብርሃኑ ( ለሚሾ ) ይባላል። ሐዋሳ ቄራ ሠፈር ተወልዶ፣ ሐይቅ ዳር ቃለህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብሎም በ አዳሬ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ጊዜውን ያጠናቀቀው።
በኋላም አዲስ አበባ በማቅናት የሚወደውን የኪነጥበብ ሙያ ሕልሙን ከግብ ለማድረስ በ ተፈሪ መኮንን የቴአትር ጥበባት -ቴአትር ተምሯል። በስራ አለምም በደቡብ ኤፍኤም እና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 97.7፣ በሗላ ደግሞ አዲስ ቴቪ እና በዛሚ ኤፍኤም የስራ ብቃቱን ካሳየባቸው ተቋማት ይጠቀሳሉ።
ጋዜጠኛ ለማ ከጋዜጠኝነት ሙያው ጎን ለጎን music vidieo directing ም የተዋጣለት ስራዎችን እንደሰራ ደረሰን መረጃ ሠረዳት ችለናል። ለሚሾ በወጣትነት ጠንክሮ መስራት፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መማርና እራስን ማሳደግ፣ በሙያው ራሱንና ህዝብን በታማኝነት ማገልገል ባህል መሆን እንዳለበት ያምናል። አመለ ሸጋና ብዙም መናገር የማይወድ ቁጥብ ሰው ወዳድ እንደሆነ የሰፈርና የስራ አጋሮቹ ይመሰክራሉ።
በአሁኑ ሰዓት ደግሞ በ ፌዴራል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋዜጠኝነት እያገለገለገለ የሚገኝ ሲሆን ታውቀው ከሚወራላቸው ሳይሆን ሳይታወቁ ከሚታትሩ ጉኑ ያለ ታዳጊ ጋዜጠኛ በመሆኑ በቅዳሜ እንግዳችን አቀረብነው።
ውድ ቤተሰቦች ስለወጣቱ ቀሪውን አክሉበት እያልን ሰላምጨጤናውን ተመኝተን ተሰናበትን! ለማ ባለህበት ሰላምህ ይብዛ! ከዚህም በላይ እንጠብቃለን።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ነሐሴ 13/2014

#ተምሳሌት| በትዳር 50 አመታት
#hawassa
ሞቢል ሰፈር፥ ማህበራዊነት እና ቡና እየተጠራሩ በደስታ ደስታን በሐዘን የማፅናናትን አኩሪ መስተጋብር ካልደበዘዘባቸው ሰፈሮች አንዱ ነው። ከዚህ ሰፈር ደግሞ ፈጣሪ ያጣመረውን ማንም አያለያየውም እንዲሉ በትዳር ተጣምረውና በልጆች ተባርከው ለ50 አመታት በትዳር ውስጥ የሚኖርና ያለን ፈተናዎች በፅናት፣ በብልሐትና በመቻቻል አልፈው ለዛሬ የበቁ ጥንዶችን ለተምሳሌትነት ይዘን ቀርበናል።
ዛሬ ዛሬ ተጠናንተው፣ ተመራርጠው ወደውና ፈቅደው አቅደው ለመጋባት የወሰኑ፤ ሰርግ በቅንጡ ስርዓት አከናውነው ሲያበቁ፤ ገና ፍርማቸው ሳይደርቅና የድግሱ አውድ ሳይበርድ ለፍች የሚሯሯጡ በበዙበት ዘመን፤ ያኔ ልጅህን ለልጄ፣ ተብሎ በወላጅ ምርጫና ፍቃድ በሚጣመዱበት ዘመን በእውነተኛ ፍቅር ለትዳር የበቁ፤ ለ50 ዓመታት በፍቅር ፀንተው እንዲህ አምረው ስናያቸው ምንኛ ያስደስታል!
ትዳር ከባድ ነው፣ ብለው እያሰቡ ለሚያፈገፍጉት ደግሞ የዛሬው የሞቢል ሰፈሮቹ ጥንዶች ጥሩ ማሳያ ይሆናሉ። በትዳር ያለንም በረባ ባረባ አለመግባባት ቢኖርም ጉዳዩን በሰከነ አዕምሮ ፈትቶ በፎቅር መኖር እንደሚቻል ያስተምረናል።
አቶ ጥበቡ ሰለሞን እና ወሮ አሰገደች አበራ ያለጥርጥር በርካታ አለመግባባቶችን፣ መኮራረፎችን እንዲሁም ሌሎች ችግሮች ሳይገጥማቸው ለዛሬ አልደረሱም! ነገር ግን መሰናክሎችን ተጋፍጠው፣ ጉዳዩን ተወያይተው፣ ጥፋትን ይቅር ተባብለው ነው ለዚህ ክብር የበቁት። በትዳር ዘመናቸው አራት ሴትና አንድ ወንድ ልጆችን ወልደው፣ አሳድገው ለቁም ነገር አብቅተዋል። (ሃና ጥበቡ፣ ትዕግስት ጥበቡ፣ ዶ/ር ሰናይት ጥበቡ፣ ጤናአዳም ጥበቡ፣ ዶ/ር አዳነ ጥበቡ)
አሁንም ቀሪ ዘመናቸው የደስታ እንዲሆን፣ እድሜና ጤና ሰጥቶ እንዲያቆይልን እየተመኘን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ወደድን።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ነሐሴ 18/2014

#ዘኪ_ኢንጂነሪንግ| ዘኪዎስ ጎአ
#hawassa
ዘኪ_ኢንጂነሪንግ በአቶ ዘኪወስ ጉአ መስራችነት የተቋቋመና #በፈጠራ_ስራና #ተኪ_ምርት በ2000 ዓ.ም በ500 ብር መነሻ ካፒታል የመበየጃ ማሽኞችን በመግዛት በቄርጥራጭ ብረቶችና ላሜራዎች የተጀመረው ስራ በአሁኑ ግዜ #ከውጭ_የሚገቡ ማሽኖችን #በሀገር_ዉስጥ በማምረት በርካታ የውጭ ምንዛሬን እያዳነ የሚገኝና ካፒታሉን ወደ 25 ሚሊዮን ማሳደግ የቻለ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡
ዘኪ በር፣ መስኮትና ወንበሮችን በመስራት የጀመረውን ስራ በማሳደግ ፈጠራ ስራዎች ላይ በማተኮር በአሁኑ ግዜ 18 የሚሆኑ ማሽኖችን በውጭ ስታንዳርድ በጥራት በማምረት ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ከሚያመርታቸው ማሽኖች መካከልም የዳቦ ማቡኪያ፣ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን፣ የቡና መቆሊያና መፍጫ ማሽን፣ የሽንኩርት መፍጫ፣ የዳጣ መፍጫና የተለያዩ የወፍጮ ማሽኖች ይገኙበታል፡፡
እነዚህን የፈጠራ ስራዎች በተለይም የዳቦ ማቡኪያና መጋገሪያ ማሽንን በሀገር ዉስጥ ገበያ ከማቅረብም ባሻገር ወደተለያየ የአፍሪካ ሀገራት ለመላክ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በሚቀጥለው ህዳር ወር ወደ#ኬኒያ፣ #ጅቡቲና #ደቡብ_አፍሪካ ምርቶቹን ለመላክ ስምምነት ለማድረግ ቀጠሮ ይዟል፡፡ ይህ ስምምነት እንደ ሀገራችን ላሉና በርካታ ምርቶችን ከውጭ ስታስገባ ለቆየች ሀገር ትልቅ እድል ነው፡፡
ዘኪ የሚያመርታቸው ማሽኖች #በውጭ_ስታንዳርድ እየተመረቱ ቢሆንም ለገበያ ሲቀርቡ ግን ከውጭ ከሚገቡት ማሽኖች እስከ 80 በመቶ ቅናሽ የተደረገባቸው ናቸው፡፡ ከውጭ የሚገቡ የዳቦ መጋገሪያና ማቡኪያ ማሽኖች እስከ 1 ሚሊዮን ብር እንደሚያወጡ የሚገልጸው #ዘኪ ድርጅታቸው ደረጃቸውን የጠበቁና #ከውጭ_ከሚገቡት ማሽኖች ተመሳሳይ የሆኑ ማሽኖችን እስከ 280 ሺ ብር ብቻ ለገበያ እያቀረበ ይገኛል፡፡
እነዚህም ማሽኖች የኤሌክትሪክ_አጠቃቀማቸውን ቀላል በማድረግ ከውጭ ከሚገቡ ማሽኖች ተመራጭ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን የሚገልጸው ዘኪ ለምርታቸውም ዋስትና በመስጠትና ማሽኖቹም ችግር ሲገጥማቸው በቀላሉ መስተካከል እንዲችሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
ዘኪ_ኢንጂነሪንግ የሚያመርታቸው ማሽኖች #ከውጭ_ከሚገቡ ምርቶች የ75 በመቶ ቅናሽ ያላቸውና ከአንድ ኪሎ እስከ 25 ኪሎ መቁላት የሚችሉ የቡና መቁሊያና መፍጫ ማሽኖችን እንዲሁም በኤሌክትሪክና በዲናሞ የሚሰሩ የተለያዩ መጠን ያላቸውን የወፍጮ ማሽኖችን #በጥራት እያመረቱ ይገኛሉ፡፡
ለሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ምርቱን እያቀረበና ተጠቃሚዎችን እያሳደገ የሚገኘው ዘኪ 620 ካሬ ላይ ባረፈ ቦታ ላይ ስራዎቹን እያከናወነ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት 16 ቋሚ ሰራተኞቹን ቀጥሮ እያሰራ ይገኛል፡፡ የፈጠራ ስራ የባለቤትነት መብት ጋር በተያያዘ ችግሮች እንዳሉበት የሚያነሳው ዘኪ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማትም እገዛ እንዲደርጉለት ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ራዕዩ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በሙሉ በማስቀረት በሀገር ውስጥ በማምረት ወደውጭ መላክ እንደሆነ የሚገልጸው ዘኪ ይህንንም ለማድረግ ሙሉ እምነት እንዳለውና በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች ኢንዱስትሪውን ማስፋፋት እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡
ዘኪ_ኢንጂነሪንግ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማ ቢሮ በመክፈት ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡
ውድ የሐዋሳ ትዝታ ቤተሰቦች ስለ ዘኪዎስ ያገኘነውን መረጃ ስናጋራችሁ ከጥቂት ተነስቶ ትልቅ የመሆን ስኬትን ልንማርበት የሚገባ ታታሪ የፈጠራ ሰው በመሆኑ ነው። እናንተም ስለ ዘኪ ብርታት እንድታበረታቱት ስንል እነሆ ብለናል።
@EED
#ዘኪ_ኢንጂነሪንግ
አድራሻ፡ ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ
ስልክ፡ +251 940 26 26 26/ +251 911 38 12 66
ኢሜል፡ [email protected]
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ነሐሴ /2014

#ለመልካምነታችሁ| እናመሰግናለን!
#hawassa| 229,724 እይታ /view
መልካምነት ቸበራክቷል! እናመሰግናችኋለን! #ምክር #ሐሳብ #አስተያየታችሁ ለዛሬ አድርሶናል። የማህበራዊ ሚዲያን ገፅታ በርካቶች ለመልካም ስራ እንዲያውሉ አግዛችኋል። ከምንም በላይ በፍቅር ማደጋችሁን በቅን ልቦና፣ በመረዳዳትና በማበረታታት የተገለጣችሁ ውድ የሐዋሳ ትዝታ ቤተሰቦች እናመሰግናችኋለን❤❤❤
ደግሞ በዚህ አዲስ አመት ከናንተ ጋር በመልካምነት ደምቀን እንደምንገኝ አንጠራጠርም። ደብተርና ብዕር፣ ያገለገሉ አልባሳት እንዲሁም በጎዳና ያሉትን ለእንቁጣጣሽ መመገብ ዋና ዋና ተግባራቶቻችን በናንተ እውን ይሆናል።
የፊታችን አርብ ከናንተው ያሰባሰብናቸውን አልባሳት የምናከፋፍል ይሆናል። አሁንም ባሉበት መጥተን እንቀበላለን። የደብተርና ብዕር የማሰባሰብ ስራው እየተከናወነ ነው። ምገባው ቀኑን ይጠብቃል!

#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል| ማይንድ
#አዲስ_አመትን| በተነቃቃ አዕምሮ
#hawassa|ፒያሳ_ሌዊ| በነፃ
ማይንድ የሥራ አመራር አማካሪና ስልጠና አገልግሎት :-የሁለት ዶክትሬት ባለቤት በሆኑት በዶ/ር #ሳምሶን_ታደሰ የሚመራው ማይንድ- #የስኬታማነት_ምስጢር" በሚል ርዕስ ማንኛውም ማህበረሰብ #በነፃ የሚሳተፍበትና አዲሱን ዓመት በተነቃቃ አዕምሮ መቀበል እንዲችል ለማድረግ ነሐሴ 29/2014 ዓ.ም በአይነቱ ልዩ የሆነ ኤቨንት አዘጋጅቷል!
በመሆኑም በዚህ ዕለት ከላይ በተጠቀሰው ርዕስ አጭር ስልጠና ይሰጣል፤ ለማህበረሰቡ አርኢያ የሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት በተቋማችን #ሽልማትና #እውቅና ይሠጣል፣ በተጨማሪም የተለያዩ አጫጭር መዝናኛዎች ይቀርባሉ፡፡ ስለሆነም እርሶም/ድርጅትዎ የዕለቱ የክብር እንግዳችን እንደሆኑበአክብሮት ተጋብዘዋል።
#ስለ_ተቋሙ
ማይንድ የሥራ አመራር አማካሪና ስልጠና አገልግሎት ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛና አለምአቀፍ ኩባንያዎችንና መሥሪያቤቶችን የማማከርና ውጤታማ ለማድረግ በቂ አቅም ያለው አማካሪ ተቋም ነው፡፡
☞ ለአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፤ ለፋብሪካዎች፤ ለትምህርት ተቋማት፤ ለንግድ ተቋማት፤ ለመንግስታዊ ላልሆኑ (NGO) መሥሪያቤቶችና ለሌሎችም በቂ የማማከር አገልግሎት በመስጠት፤ የተሳለጠ አሰራርና የስኬታቸው አጋር በመሆን ይሰራል።
አገልግሎቶቹም:-
☞ በማህበራዊ ሕይወት- ለግለሰቦችና ለማህበራት የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን!
☞ የማንኛውንም ድርጅቶች ከፍተኛ አስተዳደራዊ መደቦችን በኮንትራት ወስደን በማዘመን ማስተዳደር፤
☞ የየትኛውንም ድርጅቶች አስተዳደራዊና የሰው ሀብት መመሪያዎችን ማዘጋጀት- ስለመመሪያዎቹም ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ይሰጣል
► የሰራተኖችን የሥራ መዘርዘር እናዘጋጃለን በሀገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛው የግለሰቦችን የሕይወት ምሕንድስና life Engineering/ በሚል ርዕስ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት ብዙዎችን ውጤታማ ያደረገ በመሆኑ ማይንድ ተመራጭ የሥኬት መንገድ አሳይቷል፡፡
ውድ ቤተሰቦች የሰራ በሚመሰገንበትና በሚሸለምበት በዚ ልዩ መድረክ አዲስ አመትን በተነቃቃ አዕምሮ እንቀበለው ዘንድ ተገኝተን ከስልጠናው እውቀትን፤ ከመርሐግብሩ እርካታን ታገኙ ዘንድ እንድትሳተፉ ጋብዘናል።
አድራሻ፡-ሐዋሳ ከተማ (ፒያሳ) አዋሽ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 19
ስ.ቁ. +251-912 819 547
+251-994 105 252
e-mail: [email protected] [email protected]
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ነሐሴ 27/2014

☞ የየትኛውንም ድርጅቶች አስተዳደራዊና ስራዎች ይሰራል።

#መቶ_ሺህ_ለመቶ_አረጋውያን!
ዛሬ ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ስራ እያዋሉ ካሉ ወኔድም እህቶቻችን ጋር በመሆን ከለጋስ ወገኖቻችን የተሰበሰበውን 100,000 ብር ለመቶ አረጋውያን ከከተማችን ካሉ ክፍለ ከተሞች ለተወጣጡ አረጋውያንና ድጋፍ ለሚያሻቸው መቶ ግለሰቦች ተበርክቷል።
መልካምነት ይከፍላል! ለሰጭው የአባቶቻችን እና እናቶቻችን የልብ ምርቃት ይደርባቸው እያልን እኛንም ለዚህ አኩሪ ተግባራችሁ ስላሳተፋችሁ ክበሩ እንላለን።
ቀጣይ የአዲስ አመት ፕሮግራም ይቀጥላል። አዲሱ አመት የሰላም የፍቅርና የጤና እንዲሆን እንመኛለን።

#እናመሰግናለን
ፍቅሩ ፊሊጶስ ተማሪዎች በደብተርና ብዕር መወደድ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ሊለዩ አይገባም በማለት ቃል የገባውን 10 ደርዘን ደብተር አስረክቦናል እናመሰግናለን። ስጦታውን ከተለያዩ ክ/ከተሞች ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ መግዛት ለሚቸገሩ ተማሪዎች አርብ መስከረም 6 የምንሰጥ በመሆኑ #ቃል_የገባችሁ #ማገዝ_የምትፈልጉ እስከ መስከረም 5 እየጠበቅን ነው።
#አንድ ደብተር ትልቅ ዋጋ አለውና አነሰ ሳንል ቻሌንጁን እንቀላቀል።

#እናመሰግናለን!| ሰጭ ልብ ይኑርህ
#hawassa
እትዬ ገነትና ልጆችዎ እንዱና ሔርሜላ የለጋስነት ማሳያዎቼ እግዜር ያክብርልን። ስለዚህ ቤተሰብ ስራ ወዳድነት፣ ታታሪነትና ስኬት በሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። ሰው ከሰራ የትም እንደሚደርስ ያስተምሩናል። አሁን ግን ከስጦታው ባሻገር የሰጭነትን ጠአም ጠንቅቃ የተረዳች ግልፅና ለፋተኛዋ ትንሿ ሔርሜላ ልንገራችሁ።
ሔርሜላ የሙዝ ንግድ ስራ የጀመረችው ከእናቷ ጋር በመሆን ነበር። በኋላ ወደ ሙዝ አከፋፋይነት ስራዋን አሰፋችው። ".. እኔ ያየሁትን ፈተና ሌሎች እንዲያዩ አልፈልግም!" የሚል ጠንካራ አቋም አላት።
ለዚህም በየወቅቱ ሰርታ ካገኘችው (ልብ በሉ ከተረፋት አደለም!) አቅም ላጡ ህፃናትና አዛውንቶች በማገዝ ከፈገግታቸው ደስታን ከሰጭነት እርካታን ታጣጥማለች። ሔርሜላ ይህን ሐሳቧን ለወንድሟ ስታካፍል እንዱም ሊያበረታትና ሊያግዛት እናታቸውም እድሜና ጤና ከሰጠን በቀጣይነት ሊደግፉ አበረታተዋታል።
ለመስጠት ሰጭ ልብ እንጅ የናጠጠ ሐብት ብቻውን አይሰራም። ሙዝ ነግዳ ካገኘችው እንዲሁም በወንድሟ አጋዥነት ለተማሪዎች 10 ደርዘን ደብተርና አንድ ፓክ ብዕር ለማበርከት ችለዋል።
የሐዋሳ ትዝታ ሰጭና ቅን ልቦችን በማሳየት ሌሎች እንዲነቃቁ ሲል ሰጭዎችን የፎቶ ማስረጃ ይጠይቃል። ሔርሜላም ሆነች ወንድሟ ለፎቶ አልፈቀዱም ነበር። ነገር ግን የሐዋሳ ትዝታ ለሌሎች ማበረታቻ ይሆናል በሚል በልመና ፈቅደውልኛል።
አንድ ነገር አስባለሁ። ሰዎች ሲለግሱ ማሳየት የማይፈልጉት "ልታይ ልታይ አይነት ስሜት" እንዳይፈጥርና "ግራ ሲሰጥ ቀኝ አይይ..." ከሚል መንፈሳዊ አስተምሮ የመነጨም ሊሆን ይችላል። በዚህ በሐዋሳ ትዝታ የሚደግፉን በሙሉ ማለት ይቻላል ፎቶ መነሳትና መታየት አይፈልጉም! ነገር ግን የነሱ እዚ መቅረብ ሌላ ሰጭ ልቦችን ለመፍጠር አይነተኛ ሚና እንዳለው በማስረዳት እንለጥፋለን። እርስዎን ያየ ጓደኛዎ፣ ቤተሰብዎ፣ ወዳጅ ዘመድዎ አነሰ በዛ ሳይል መሳተፍ እንደሚቻል ይረዳል።
ለሐዋሳ ትዝታ አንድ ሳንቲ የሰጠም አንድ ቢሊየን እኩል ክብር አለን! ምክንያቱም ሰጭ ልብን ማብዛት እንጅ የስጦታ መጠንን አይደለም።
እባካችሁ አመስግኑልኝ፣ ሔርሜላንም ሆነ ቤተሰቧን አበርቱልን።

#እናመሰግናለን| ሰጭ ልብ ይስጠን
@hawassa
መቅደስ ተሰማ ይመለከተኛል ስትል ተማሪዎች በደብተርና ብዕር መወደድ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ሊለዩ አይገባም በማለት በሉቃስ (#ሉ_ፕሮሞሽን) በኩል ደብተር ለግሳለች። እናመሰግናለን። ስጦታውን ከተለያዩ ክ/ከተሞች ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ መግዛት ለሚቸገሩ ተማሪዎች ቅዳሜ መስከረም 7 የምንሰጥ በመሆኑ #ቃል_የገባችሁ #ማገዝ_የምትፈልጉ እስከ መስከረም 6 እየጠበቅን ነው። የስጦታ ቦታው ከ2/04 (ሚሊኒየም ቀበሌ) ከጠዋቱ 3 ሰዓት በመሆኑ የቻላችሁ ብቅ በሉ።
#አንድ ደብተር ትልቅ ዋጋ አለውና አነሰ ሳንል ቻሌንጁን እንቀላቀል።
....ይቀጥላል... ሰጭዎችን ማመስገንም ስጦታው አካል ነው።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
መስከረም 4/2014

አዋሳ...! "ዱቄት በጣሳ፥ ብር በአካፋ"
እሳቸው የዘመን ዋርካ... የታሪክ ድርሳን ናቸው። ትናንትን እንደዛሬ የሚያስታውሱ የዕድሜ ባለጸጋ የብዙሐን እናት ናቸው። "እስቲ የነበረ ያውራ እስቲ ያየ ይናገር"... እንዲባል፥ እሳቸው በሀዋሳ ከተማ ምስረታ ውስጥ ባለድርሻ ከነበሩት መካከል አንዱ ናቸው።
ምንም እንኳ የተፈጥሮና የጊዜ ህግ ሆኖ የከተማዋ መስራቾች በሞትና በተለያዩ ምክንያቶች መለየታቸው እሙን ቢሆንም፥ የዛሬዋ እንግዳችን ወ/ሮ ሰንበት ተስፋዬ ግን ዘመናትን የኋሊት ተሻግረው ብዙ ያጫውቱናል።
ማስታወቂያ ልክ እንደዛሬው ሳይዘምን ነገር ግን ግነት ታክሎበት ቅስቀሳ ይሰራበት እንደነበር የሚገባን የሀዋሳ ከተማ መስራቾች እንዴት ወደዚህ ስፍራ አንደመጡ ስትሰሙ ነው።
የዚህ ነገር እማኝ ደግሞ እናታችን ወ/ሮ ሰንበት ናቸው። ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ እንዲል ወደ ሀዋሳ እንዲሰፍሩ ከተላኩት ወታደሮች አብዛኞቹ“አዋሳ ዱቄት በጣሳ፤ ገንዘብ በአካፋ” የሚለውን ማስታወቂያ በ1952 ዓ.ም ሰምተው የመጡ መሆኑን ባለታሪካችን አጫውተውናል።
ይባል እንጂ ሁሉም ነገር ግን.. ውሸት ነው ብሩም፣ ዱቄቱም አልነበረም ሲሉ ያስታውሳሉ። ምንም እንኳ የሰሙትን አምነው እንደተባለው ወደ ሀዋሳ ቢመጡም÷ የጠበቃቸው ነገር ቢኖር ኑሮን አንድ ብሎ ከዜሮ መጀመር ነው።
ዕድሜ ለቀደሙት የሲዳማ ነዋሪዎች ምስጋን ይግባቸውና ከተማዋ ጫካ በነበረችበት ወቅት እነርሱ የእርሻ ማሳ እና ከብቶች ስለነበራቸው በጥሩ ሁኔታ ተቀብለውን ወተት፣ ቆጮ፣ ቂጣ፣ እንቁላል ከቤታቸው እያመጡ ለ2 ዓመታት በእንግድነት አስተናግደውናል ይላሉ ወ/ሮ ሰንበት ተስፋዬ።
ወ/ሮ ሰንበት ተስፋዬ ተወልደው ያደጉት መቀሌ አብርሀ አፅባ(ወሮ አፅባ) ነው። በ15 ዓመታቸው ለ1 ወታደር ተድረው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ይናገራሉ። ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ብዙም ሳይቆዩ ወታደሮችን የሚመለከት አንድ ስብሰባ መጠራታቸውን ያስታውሳሉ።
ይኸውም “አዋሳ ዱቄት በጣሳ ገንዘብ በአካፋ” የሚል ሰው በአዲስ አበባ መንደር ጥሩንባ በመንፋት እየዞረ ማስታወቂያ መልዕክት ይናገር ነበር፡፡ የማስታወቂያ መልዕክቱን የሰማ ወታደር ሰአቱን ሳያዛንፍ ወደተጠራው አዳራሽ ጉዳዩን ለማጣራት ተሰበሰበ፡፡
ውይይቱን የሚመራው አካል አዋሳ ስለምትባል ሀገር ልብ አንጠልጠይ ትረካ መልክ ጥሩ አድርጎ ነገራቸው፡፡ ዱቄት በጣሳ እንደሚገዛ እና ገንዘብ በአካፋ እንደሚዛቅ አሳመናቸው፡፡ መድረክ ያዥ በሚገባ መልኩ እንዳሳመናቸው ሲረዳ መሄድ የምትፈልጉ? ሲባል ሁሉም“ወጥቶ አደር” እጁን አወጣ፤ በአንድ ሀሳብ መሔድ እንደሚፈልጉ እዚያው አዳራሹ ውስጥ ተስማሙ፡፡
ከሰሙት አንፃር ከሚስቶቿቸውም ሆነ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መመካከር እንዳለባቸው ዘነጉት፡፡ ከስምምነቱ በኃላ በመጋቢት ወር1952 ዓ.ም ባሎቻቸው ብቻ ድንኳናቸውን ሸክፈው ወደ አዋሳ መጡ። ከዚያም ከሶስት ወራት ቆይታ በኃላ ሚስቶቻቸው ሲመጡ ዱቄቱም የለም... ብሩም የለም።
ይልቁንስ ወደፊት ሰርተው ካመጡት እንጂ.. የአሁኑ ከተማችን ጫካ ነበረች ወፍጮ፣ ውሀ፣ ቤት፣ መብራት አይታሰብም። ባሎቻቸው ቀድመው የተከሉት ድንኳን እንጂ ቤት አልነበረም። ፍራሽና ጋቢም አልያዙም ምክንያቱም ከሰሙት ወሬ ጋር ሲነጻጸር ሌሎች ቁሳቁሶችን መሸከም ተገቢ እንዳልሆነ አስበው ነው።
ግን ያሰቡት ቀረና ያላሰቡት ሲሆን ድንኳን ውስጥ መሬት ላይ ማደርና መዋል ሆነ። ታዲያ የዚህን ጊዜ ነው እንደእግዜር መልእክተኛ የሲዳማ ህዝብ የደረሱላቸው።
በመግቢያዬ ላይ ያሰፈርኩት የወ/ሮ ሰንበት ተስፋዬ ንግግር፤ እድሜ ለሲዳማ ህዝብ ከተማዋ ጫካ በነበረችበት ወቅት እነርሱ የእርሻ ማሳ እና ከብቶች ስለነበራቸው በጥሩ ሁኔታ ተቀብለውን ወተት፣ ቆጮ፣ እንቁላልና ፍም ውስጥ የበሰለ የሚጣፍጥ ቂጣ ያመጡልናል፤ እኛም ከያዝነው ስንቅ ሽሮና በርበሬ እናካፍላቸው ነበር።
ከዚያም ልብ ለልብ በደንብ ስንግባባ የምትወልድ ላም ሰጥተውን ወተቱን እንድንጠቀምና ጥጃዋን ደግሞ መልሰን እየሰጠናቸው ለ2 ዓመታት በእንግድነት ተቀብለውን እስክንቋቋም በብዙ አግዘውናል፡፡
በዚህ ሂደት መንግስት ቤት ሰራልን ይላሉ ወ/ሮ ሰንበት። እነርሱ ቤት በተሰራላቸው በዓመቱ ከሐረር፣ ከውቅሮ፣ ከኮረም እንደመጡ ገልፀው ኑሮአቸው የምር እንደሆነ ሲረዱ ቀድሞ ሆሆሆሆ...! ብሎ የመጣው ወገን አሁን ማጉረምረም ጀመረ።
ምክንያቱም በዚያች አዳራሽ የተነገረው ትርክት ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነባቸው። ከዚያም ለመንግስት አቤት ለማለት መከሩና ከመካከላቸው ያሉበትን ሁኔታ ለመንግስት የሚያስረዳ ሰው ወደ አዲስ አበባ ልከው እንደነበር ያስታውሳሉ።
የመብራት፣ የውሀና የመንገድ ጥያቄ እስከሚመለስላቸው መንግስት ኃላ መልሶ ቢወስድባቸውም ለጊዜው በተሰጣቸው የእርሻ ቦታ በቆሎና የተለያዩ አትክልቶችን በመትከል ነበር የሚኖሩት።
ታዲያ የደረሰው በቆሎ ወፍጮ ቤት ወስዶ ለማስፈጨት የማይታሰብ ስለሆነ በቆሎውን በውሀ ዘፍዝፈው ለንቅጠው ወይም በሙቀጫ ወቅጠው ቂጣና እንጀራ ጋግረው ይመገቡታል። ከዚያ ባለፈ ውሀ በጀርባቸው ተሸክመው ከወንዝ እንደሚያመጡ ነግረውናል፡፡ ጊዜ ጊዜን እየወለደ ከሰሙት በተቃራኒ መኖር የግድ ማለት ሲጀምር፥ ያልተመቻቸ ሁኔታ ብሎ ነገር እየቀረ፥ የኋላ ኋላ እየተጠናከሩና እየበዙ መምጣታቸውን ያስታውሳሉ።
ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ እንደ አዲስ አበባ፣ ሀረር፣ ውቅሩ፣ ኮረም እና ከተለያዩ ክፍለ ሃገራት የተሰባሰቡ ለሀገር ዋጋ የከፈሉ እንዲሁም በአዋሳ እንዲከትሙ ምክንያት መሆኑን ባለታሪካችን አጫውተውናል፡፡
ወዲያው እድራቸውን በማጠናከር አንድ ሰው እክል ሲገጥመው ሁሉም 50 ሳንቲም እንዲዋጣ ተደርጎ ሀገሩ ደርሶ ይመለስ ነበር አቤት ያለው መተሳሰብ… አቤት ፍቅር…፡፡
በወቅቱ የነበረው አንድ መንገድ ከአዲስ አበባ ይርጋዓለም የሚያስኬደው ብቻ ነበር፡፡ አንድ ሰው ወደ አዲስ አበባ መሔድ ቢፈልግ10 ሳንቲም መክፈል ነው ሚጠበቅበት ይላሉ ወ/ሮ ሰንበት በትዝታ ወደኋላ ትክዝዝዝዝ እያሉ፡፡
በዚህ መኃል ነበር ጃንሆይ፣ ራስ መንገሻ ስዩም እና ሌሎች ሰዎች ሆነው በቀድሞ ወይን ቤት ከታቦር ተራራ አጠገብ ቆመው ቀ/ሀ/ስ እያሉ በእጃቸው እየጠቆሙ መንገድ ሲያስመትሩ ትዝ ይለኝ ነበር ይላሉ፡፡
ዛሬ አብዛኛዎቹ በሞት አጥተናቸዋል ብዙም ቢለፉም ሳያርፉ አልፈዋል፡፡
እኔ ግን መድሐኒአለም ክብሩ ይስፋ አለም አየሁ፣ ብርሃን አየሁ ባለቤቴ በህይወት ባይኖርም ልጆቼ በተድላ አኑረውኛል18 የልጅ ልጅ አይቻለሁ ሲሉ በትዝታ ወደኋላ መለስ እያሉ ለሀገራችን ሠላምን ተመኝተዋል፡፡
እኛም ለ404 የሀገር አርበኛ ቤተሰቦች ለሞቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እየተመኘን በሕይወት ያሉትን እድሜ ከጤና ጋር እንዲሰጣቸው ተመኘን፡፡