Telegram Web Link
#ሀዋሳን_ማን_ለዚህ_አበቃት| ቀደምቶቹ
#hawassa| By Jone Fikre Berhe
፡፧፡፧፡፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(መረጃው ከተለያዩ ሰዎች ያገኘው ነውና የጎደለውን በመሙላት ወይ በማረም ማሟላት ይቻላል።)
1. ራስ መንገሻ ስዩም ከተማዊ ቅርፅ በመስጠት፤
2. የሲዳሞ ክ/ሀገር አስተዳደር ፅ/ቤት፡- አሁን ሳውዝ ስታር የተሰራበት ቦታ የበፊቱ እርሻ ጣቢያ፡፡ እኛን ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅስ ሰዓት የነበረበት፡፡
3. የመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች ኦሲስ እና ፕላዛ (እኛ ብላዛር ጓሮ የምንለው)
4. የመጀመሪያው ያማረ ሆቴል (አሁን ህንፃ እየተሰራበት ያለ) የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ስፖርት ፅ/ቤት ከዚያም የመንግስት መድሃኒት ቤት ከዚያም ሃቄ ስፖርት የነበረው፡፡
5. የመጀመሪያዎቹ ልብስ ሰፊዎች (አቶ ቤተማሪያም፣ አቶ ድማ ሄይ፣ አቶ ደንቦባ፣ ምንዳዬ አካሉ (ነፍስ ይማር)፣ በኋላ ጌታቸው ቀነዓ፣ ሲሳይ ባህሩ
6. የመጀመሪያዎቹ ሻይና ብስኩት ቤት የጀመሩ፡- ፍቅሬ ሃሰና፣ በቀለ ሀሰና (የነ ዳዊት ዳላስ አባት) ኃይሉ እንግዳወርቅ በኋላም የመጀመሪያው ቡቲክ የከፈተ)
7. ፈረስ ጋሪን ወደ ሃዋሳ ያስገቡና የነዱ፡- ጋሪና የጋሪ እቃዎች ከአዲስ አበባ ይመጣ ነበር፣ አቶ ደበሽ አባሰንጋ፣ አቶ ከፋ ነጋሽ አረብ ሰፈር አካባ የሚኖሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋሪ በሃዋሳ ማምረት ጀምረዋል፣ ቀጥሎ ፒያሳ አካባ አቶ ሃብቴና ብርሃኑ ብርሃኑ ወልዴ፣ አቶ ወልዴ አሼቦ፣ ያለው አበበ፣ ዳንሴ ምትኩ፣ ይመር ሹሙ፣ አቶ ብርሃኑ
8. በሃዋሳ የመጀመሪያው የሴቶች ፀጉር ቤት አሁን አሚን ህንፃ ያለበት ወ/ሮ ወርቄና(የፒና ሆቴል ባለቤት) በሃዋሳ ታቦር አስተማሪ የነበረችው ወ/ሮ አሚና፣ አቶ ቱፋ ገመቹ፣ አቶ ሰለሞን አበጋዝ፣ አቶ ክንፈ ደንቢ
9. የመጀመሪያዎቹ የሆቴል ባለቤቶች፡- አቶ በቀለ ሞላ፣ አቶ ታረቀኝ ገብሬ(ሹፌሮች ሆቴል) አቶ አማረ ለማ (ያማረ ሆቴል) ቶታል፣ አቶ ኃይለ ጋሼ (ቶታል)፣ እንጆሪ ሆቴል (አቶ ታደሰ እንጆሪ)፣ መስከረም ሆቴል (አቶ ተሰማ) መናኸሪያ ሆቴል፣ ኮከብ ሆቴል፣ ገበሬዎች ሆቴል፣(አቶ አብረሃም) ጆሊ ባር፣ ምድረገነት ሆቴል፣ አንድነት ሆቴል፣ ነጋዴዎች ሆቴል፣ አቶ ድማሙ ሄይ)
10. የወንዶች ፀጉር ቤት አቶ አሰፋ፣ የ10 አለቃ አለሙ ተፈራ (የአፄ ኃይለስላሴ ፀጉር ከርካሚ የነበሩ)፣ አቶ ኤዴማ አላሮ፣ አቶ ተክሌ ጋጋ
11. ሙዚቃ ቤት፡- ሸገር ሙዚቃ ቤት፣ አዋሳ ሙዚቃ ቤት፣ ዙቤር ሙዚቃ ቤት፣ አዲስ ሙዚቃቤት፣ ቤርሙዳ ሙዚቃ ቤት
12. ኬክ ቤት፡- ፒና ኬክ ቤት(ወ/ሮ ወርቄ)፣ ሞሜንቶ (የእምነቴ ቤተሰቦች)
13. ቡቲክ፡- ኃይሉ እንግዳወርቅ፣ መሊ፣ ጀማል
14. ፖስተኛ፡- አቶ ሻንቆ
15. ግሮሰሪ፡- አቶ እስጢፋኖስ፣ አቶ አማረ አጎናፍር፣ አቶ ታደገ ታሪኩ
16. ምግብ ቤት (ወ/ሮ ማሚቴ እምሩ)
17. የመጀመሪያው ደላላ፡- አቶ ዳምጠው
18. ሳይክል ለመጀመሪያ ጊዜ ያስገቡ የሚያድሱና የሚያስነዱ፡አቶ ደለለኝ መኩሪያ፣ አቶ ረጋሳ ጩቃላ፣ አቶ ብሩ ማሞ፣ አቶ ተፈራ አለሙ፣ አቶ አሸብር አወቀ፣
19. ወፍጮ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ያስገቡ፡- አቶ ደንደና ቱፋ፣ አቶ ዘለቃው በለጠ፣ አቶ ሽኩሪ፣ አቶ ጌጡ
20. ሉካንዳ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የከፈቱ፡- አቶ ጩካላ፣ አቶ በረግ፣ አቶ ሽፈራው ሙሚቻ
21. የመጀመሪያዎቹ ከንቲባዎች፡-ባላምበራስ ዘርፉ ዳምጤ፣ አቶ ሙሉጌታ ኃይለስላሴ፣ አቶ ካሳሁን ተፈራ፣ (በሃዋሳ ታቦር መንገድና በአረብ ሰፈር መንገድ ላይ የመንገድ ዛፎችን ያስተከሉ ሰው ናቸው አብዛኛዎቹ ዛፎች በመንገድ ሰበብ የመጥረቢያ ራት ሆነዋል)ራስ መንገሻ ስዩም (ቀያሽ)
22. የመጀመሪያው ገበያ፡- አሁን ቼሜንታል አካባቢ (ጥቁር ውሃ)፣ አሁን ቃጫፋብሪካ አካባቢ(አጨቀቴ) ተብሎም ይጠራ ነበር፡፡ አረብ ሰፈር፣ ከዚያም አሁን ያማረ ሆቴል ፊት ለፊት መናፈሻ ጋ፣ ከዚያም ቶታል ሆቴል የአሁኑ አካባቢ፣ ከዚያም የአሁኑ ሲዳማ ባህል አዳራሽ፣ ከዚያም የአሁኑ ታደሰ እንጆሪ ፖሊስ ክበብ የነበረው አጠገብ፣ አሁን ያለበት ቦታ
23. የመጀመሪያዎቹ ፋብሪካዎች፡- ቃጫ ፋብሪካ፣ ዘይት መጭመቂያ(እርሻ ጣቢያ)፣ ጆጋርዲ ጣልያናዊ የስሚንቶ ውጤቶች ማምረቻ፣ አሁን ቼሜንታል
24. የትምህርት ተቋም፡- ታቦር ትምህርት ቤት (አንደኛ ደረጃ)፣ ቤተክህነት ት/ቤት፣ ከፍተኛ ህዝባዊ ኑሮ እድገት ማሰልጠኛ (የአሁኑ ግብርና ኮሌጅ)፣ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም (የአሁኑ ቲቲሲ)
25. ጅምላ ሸቀጥ ሱቅ፡-አረብ ሰፈር(1958)፣ ሱማሌ ሱቅ፣ መሃመድ ሱቅ፣ መንግስቱ ሱቅ
26. የመጀመሪያዎቹ የእምነት ተቋማት የመጀመሪያዎቹ፡- ገብርኤል (1953)፣ ሙስሊም በዚሁ ዓመት፣ ስላሴ ቤ/ክ፣ አድቬንቲስት፣ መካነ እየሱስ፣ ህይወት ብርሃን
27. የመጀመሪያዎቹ መስሪያ ቤቶች፡- የሃዋሳ ወረዳ ፍርድ ቤት(አሁን የሃዋሳ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያቤት ያለበት)
28. የመጀመሪያው ፎቅ፡-በፊት ፊልም ቤት፣ ቀጥሎም የእርዳታ ማስተባሪያ ቢሮ የነበረው፣ የሃዋሳ መስጂድ ጎን የሚገኘው የቀድሞው የቀይሽብር መግረፊያ የሚባለው
29. መጀመሪያዎቹ ፎቶ ቤቶች፡- ግርማ አብቼ(ፒያሳ)፣ በቀለ ወ/ሰንበት (ፒያሳ)፣ ማሞ ወልደሰንበት (ቤርሙዳ ሰፈር)፣
30. ጭፈራ ቤት፡-ዘነበች ሃሰን፣ ማሚቴ እምሩ፣ ስሪ ዶርስ፣ ነጋዴዎች ሆቴል በባንድ የታገዘ ጭፈራ ቤት የነበራቸው(ገበሬዎች ሆቴል)
31. የመጀመሪያዎቹ ጠጅ ቤቶች፡- አቶ ተሾመ በላይነህ፣ አቶ ውብሸት፣ አቶ አሸብር አወቀ (በኋላ ጋይንት ሆቴል) ሳይክል ማከራየትና ማስነዳት የጀመሩ፣ ወ/ሮ ምንትዋብ ግዛው፣ አቶ ታደሰ ገዳ፣ አቶ ተሰማ (ፒያሳ)
32. የመጀመሪያዎቹ አናፂዎች፡- አቶ ወርቁ ያኢ፣ አቶ ወልዴ (ዋርካ አካባ)፣ አቶ ኃለሚካኤል ዋንሰራ፣ ወልደመድህን ዳዲሶ (እነዚህ ሰዎች፡-ቤተ ክህነት፣ ታቦር ትምህርት ቤትን፣ የለኩ ልብስ ስፌት ማህበርን፣ አብዛኛዎቹን የሃዋሳ መኖሪያ ቤቶችን የሰሩ ናቸው፡፡
33. የመጀመሪያዎቹ ግንበኞች፡- አቶ ተክሌ ነጋሽ፣ አቶ ተሸመ መኮንን፣ አቶ እሸቱ አለሙ ፎሌ፣ አቶ ከበደ በሽር፣ አቶ ታፈሰ ተሰማ
ምንጭ፡- ቃል በቃል ጠይቄ ያጠናከርኩት ሲሆን እዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሱ ሰዎች በሕይወት የሌሉ ስለሚበዙበት ነገር ግን ሃዋሳን ሃዋሳ በማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች የህሊና ፀሎት አድርጋችሁ እንድታስቧቸው እያሳሰብኩ በህይወት ያሉትን ደግሞ በማመስገን ታሪኩን እንድታስተላልፉ ስል እጠይቃለሁ በዚህ አጋጣሚ መረጃውን ለሰጡኝ፡-
አቶ ተፈራ አለሙ
አቶ በላይ ወጋሶ
አቶ አለማየሁ አበበ
አቶ ወልዴ ባቢሶ
አቶ ሻላሞ ዶያሞን
እድሜያችሁን ያርዝምልኝ እላለሁ የጎደለውን ጨምሩ!
ምንጭ:-
Jonny Fikre Ethiopian
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
መስከረም 2016
#አይረሴው_መምህር| መምህር ፀጋዬ
#hawassa| እስኪ አመስግኑልን
       ሰለ እሳቸው የታቦር ት/ቤት ዛፎች ዛሬም ይመሰክሩላቸዋል! የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድሮች ይመሰክሩላቸዋል!! በተለይ ዩኒት ሊደር ሆነው ለእኛ በብዙ ደክመዋል! ዛሬ በሐዋሳ ትዝታ ዛሬም አስታውሰናቸዋል!!!! ትዝታችሁን አጋሩን እናክብራቸው።
   ስለ መምህር ፀጋዬ በርካቶች ከመሰከሩት መካከል የሚከተለውን አጋርተናል። ጠምሩበት

"በእውነት መነሳት ካለባቸው መምህሮቻችን መካከል  አንዱ እና ዋናው  መምህር ፀጋዬ ናቸው።እሳቸውን ከመምህርነታቸው እና አባትነታቸው በተጨማሪ ለሀዋሳ ከተማ እስፖርት እድገት ያበረከቱት አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ነው።"

  "ጋሽ ፀጋዬ ለስፖርቲ ሌሊት ወጥተው ሲሰሩ ውለው እቤታቸውን የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ እንደውም ሳስበው እንቅልፍም የሚተኙ አይመስለኝም፡፡ ምክራቸው፣ ለስፖርት በተለይ ለእግር ኳስ ያላቸውን ፍቅር በምን ልንለካው እንችላለን?"
    " ልጆቻቸውን አሳድገው ለወግ ለማዕረግ ያበቁበት መንገድ ግርም ይሉኛል! ጠዋት ከቤት ሲወጡ ብታይ አንተ በመኪና ወደ አንዱ የከተማው ጥግ ብትሄድ እርሳቸው እዛ ከልጆች ጋር ሀነው ኳስ ሲመለከቱ ታገኛለህ፡፡ "

     "የሚወደዉን ስራ በፍቅር የሚሰራና በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንደርሳቸው አይቼ አላውቅም፡፡ ጋሽ ፀግሽ ረዥም እድሜ ከጤና ጋር!"

የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
መልካም ስራ በትውልድ ይዘከራል!
#ተጫዋች_አምራቿ_ሐዋሳ| ከየት ወዴት?
#hawassa| በቼቼ ጳውሎስ
@ርዕሰ አንቀፅ "ልብ ያለው ልብ ይበል!
       የኢትዮጵያ የእግርኳስ ታሪክ ከረጢት ነች፤  በየትኛውም ዘመን የትውልድ ቅብብሎሿ ሳይቋረጥ ላለፉት በርካታ ዓመታት እንደ ሃገር የበርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማምረቻ የኢትዮጵያዋ ብራዚል ነበረች ብል አላጋነንኩም።

ለብሄራዊ ቡድን ጥሪ ሲደረግ ለግማሽ የቀረበው ቁጥር ከዚህችው ዕንቁ ከተማ ከሐዋሳ ነበር ጥሪ የሚደረግላቸው። ከዋናዋ የሃገሪቱ መዲና አዲስአበባና ከበርካታ የክፍለሃገር ከተሞች በተሻለ ተጫዋቾችዋን ስትቸርና በአፍሪቃ መድረክ አብሪ ኮከብ ሆነውላት ኢትዮጵያ በሃዋሳዊያን ተወድሳለች። ያለፉት ደማቅ ታሪክ ፅፈው አልፈዋል፥ ያሉትና የቀሩት በቻሉት ሁሉ ለክለብና ለሃገር ያላተውን ችረዋል።

በሀዋሳ ልጆች ያልደመቀና ያልተዋበ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ፈልገህ አታገኝም፤ ብቻ ግን ሀዋሳ ትውልድ ሳይነጥፍባት ኳሰኞችን ሳታርጥ ከውብ ማህፀንዋ ውብ እግርኳሰኞችዋን ለኢትዮጵያ ሳትሰስት ሰጥታለች።

የዛሬው የፅሁፌ ዋነኛ ነጥብ ግን የከተማዋ የእግርኳስ አሁናዊ ገፅታ ላይ ያለኝን ታላቅ ስጋት የሚገልፅ ነው።  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አራቱም የሃገሪቱ ማዕዘናት ለሚገኙ ክለቦች የሚጫወቱ ሃዋሳዊያን ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ከዓመታት በፊት ጀምሮ የጉዳት ሰለባ ሆነው ቀርተዋል። ሀዋሳ ከተማ ተወላጆችዋን ለብሄራዊ ቡድን የሚሆኑ ልጆችን ማስመረጥ የተሳናት ይመስላል። ከሃገር አልፎ ለአህጉርና ለዓለም ዓቀፍ ውድድሮች የጠበቅናቸው በርካቶች በጉዳት ሰበብ ካለ ዕድሜያቸው ተቀምጠዋል። የከተማው ተወካይ በሆነው በሀዋሳ ከነማ ዋናው ቡድን እንኳን ሳይቀር ቋሚ ተሰላፊ የሆኑ የሀዋሳ ልጆችን ማየት ተስኖናል። በርካታ ዕንቁ ልጆችዋ ካለምንም ግጭትና አደጋ ከእግርኳሱ ዓለም ሸሽተዋል፤ ያሉትም ፈታኝ ጊዜ እያሳለፉ ነው።

ለኢትዮጵያ በርካታ ውለታን የዋለችው ሀዋሳ ዛሬ ዛሬ ላይ በፕሪሚየርሊግ ደረጃ ሳይቀር በየክለቦቻቸው ቋሚ ተሰላፊ የመሆን ዕድላቸው መመናመን በከተማዋ ላይ አንዳች መንፈሳዊ አሰራር መኖሩን እንዳስብ አድርገውኛል። አሁን አሁን ላይ አዳማ (ናዝሬት) ለኢትዮጵያ እግርኳስ ዕድገት ከአሰልጣኝ እስከ ተጫዋች ድረስ በርካቶችን የምታፈራ ከተማ ሆናለች የቀደመችውን ሀዋሳዬን የሚያስታውስ የእግርኳስ ትውልድ ፈጥራለች። በርካታ ኳሰኞችዋ ለብሄራዊ ቡድን ጥሪ ተመራጮችም ጭምር ሆነዋል።

ሀዋሳ ለምን የእግርኳስ ትወልድዋ ተመናመነ?

ለሀዋሳዊያን እንቁ እግርኳሰኞች ከሌሎች በተለየ የጉዳት ሰለባ መሆን ምክንያቱ ምን ይሆን?

በኩራት የምንጠራቸው የአሁን ቀን የከተማችን ውድ ተጫዋቾችስ አሉን?

ይሄ ጉዳይ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የኢትዮጵያዋ ብራዚል የሆነችው ከተማችን ታዳጊዎች ዕጣፈንታ ምንድነው?

ሁላችሁም በየግላችሁ ከራሳችሁ ጋር አውሩበት ሀዋሳ እንደ ክለብ ሳይሆን እንደ ከተማ ዘግናኝ የተጫዋች ድርቅና የጉዳት መፈንጫ የሆኑ ልጆች የሚወለዱባት ከተማ ሆናለች ለኔ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል መፍትሄን የሚሻ ሳይሆን በመንፈሳዊ መነፅር የሚታይ ሆኖ ስላገኘሁት እጅግ አስፈርቶኛል።

ሌላው ሁሉ ቀርቶ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መንገድ ባለፉት ዓመታት የሞቱ ከተማዋ ያፈራቻቸው  እግርኳስ ተጫዋቾች ቁጥር ቀላል አይደለም። ከኮረም፥ከውቅሮ፥ ከጎድጓዳ በቀላሉ ያጣናቸው ወንድሞቻችን ጉዳይ በመንግስትና በውይይት የሚፈታ ጉዳይ አይደለም።

ነገር ግን አንዳች በከተማዋ ስፖርተኞች ላይ የተሰራ ክፉ አሰራር ከተማዋ የተጫዋች ድርቅ እንዲጎበኛትና ትወልድ እንዲመክንባት አድርጓታል።

" ልብ ያለው ልብ ይበል።"🙏🙏🙏

የትናንቷን የእግርኳስ ምድር ሀዋሳዬን አጥብቄ እናፍቃለሁ።
   የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
ህዳር 2016
2025/10/24 07:41:04
Back to Top
HTML Embed Code: