Telegram Web Link
የእግዚአብሔር ቃል በህይወት ያኖረናል
በወንድም ሰለሞን ዮሐንስ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ሚያዝያ 20 /2016 ዓ.ም የተካሄደው የእሁድ የጉባኤ የዝማሬ፣ የፀሎት ፣ የአምልኮ እና የቃል ጊዜ

በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት ወንድም ሰለሞን ዮሐንስ (ዕብ 4:12_13፤ ዘሁ 6:22_27፤ ዘዳ 8:2_4) የሚገኘውን   የእግዚአብሔር ቃል መሰረት በማድረግ "የእግዚአብሔር ቃል በህይወት ያኖረናል" በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት  ነጥቦች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

አስቀድመን የእግዚአብሔር ቃል ምንድነው? የሚለውን እንመልከት፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በትምህርት፣ በትዕዛዝ፣ በማስጠንቀቂያና በማበረታቻ መልክ ከእግዚአብሔር፣ በሰው አማካይነት ለሰው የተነገረ መለኮታዊ መልዕክት ነው፡፡ ‹‹ቃል›› በመሰረታዊ ቅርፁ የተነገረ ነው፡፡ ይኸ ጠባብ ፍቺ ቢሆንም እኛ መናገር ከምንፈልገው ጉዳይ አንፃር የቀረበ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል በባህርዩ፡-
የተናጋሪው የእግዚአብሔር የአምላክነቱ ልክ ነው፡፡ በቃሉ ፍቅር ቢገለጥ የእግዚአብሄር ፍቅር ነው፡፡ ፍርድ ቢገለጥ የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው፡፡ ሌላውም እንደዚሁ፡፡ በሌላ አንፃር የእግዚአብሔርን ስልጣን፣ ሃይልና ጥበብ ይገልፃል፡፡

ቃሉ፣ ተናጋሪው እንዲሆን የሚሻውን ያንኑ እንደታሰበው ያከናውናል፡፡ ‹‹ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ [እንደ ዝናቡ] ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል፤ የላክሁትንም ይፈፅማል›› (ኢሳ. 55፡11) ተብሎ እንደ ተፃፈ፡፡

የእግዚአብሔር ቃል ህያውና የሚሰራ ነው፡፡ ህይወት የሌለው ነገር አይደለም፤ የሚሰራውም ለዚህ ነው፡፡

ቃሉ ሲሰራ በሁለት በኩል እንደ ተሳለ ሰይፍ ይቆርጣል፡፡ በአንድ ወገን ለማይታዘዙና ህጉን ለሚተላለፉ የፅድቅ ፍርድ ይሰጣል፡፡ በሌላ በኩል ለሚታዘዙ ተስፋውን ይፈፅማል፡፡

ቃሉ ሲሰራ ተጨባጭ ውጤት አለው፡፡ የሚታይ ወይም መገንዘብ በሚቻል መልኩ ፍሬ አለው፡፡ ለምሳሌ፣ ‹‹ብርሃን ይሁን›› ካለ ብርሃን ይሆናል፡፡ ‹‹ኤፍታህ›› ካለም ይከፈታል፡፡ ኤርምያስ በተሰጠው የመንቀልና የመትከል የስልጣን ቃል መሰረት ህዝቦች ተነቅለዋል፡፡ መንግስታት ፈርሰዋል፡፡

ይህን መሰረት ከዘሁ. 6፡22-27 ና ከዘዳ. 8፡2-4 አንዳንድ ሃሳቦችን እንመልከት፡፡ የአሮን በረከት የተሰጠው ህዝቡ በሲና ምድረ በረሃ ያደረገውን የሁለት ዓመት ቆይታ አጠናቆ ረዥሙን የምድረ በዳ ጉዞ ለመጀመር ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት ነው፡፡ በዝግጅቱ መጨረሻ አሮን ባረካቸው፡፡

በምድረ በዳ በተጉዋዙባቸው ሰላሳ ስምንት ዓመታት የተሸከማቸው ይህ የበረከት ቃል ነበር፡፡ በምድረ በዳ ያበዛቸው፣ እርሻ ሳይኖር እንጀራ ያበላቸው፣ በሬ ሳይኖር ስጋ ያበላቸው፣ ልብሳቸው ሳያረጅ፣ ጫማቸው ሳያልቅ ለአርባ ዓመታት ያገለገለው፣ ‹‹እግዚአብሔር ይባርክህ›› በሚለው ቃል መሰረት ነበር፡፡ በሃሩር ንዳድ ያልነደዱት፣ የበለዓም ርግማን ያላገኛቸው ‹‹እግዚአብሄር ይጠብቅህ›› በሚለው የበረከት ቃል ነበር፡፡ ሌሎችም እንደዚሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይሰራል፤ በህይወትም ያኖራል፡፡

እናም በጉዞአቸው መጨረሻ፣ በበአል ሰጢም ተቀምጠው ሳሉ ሙሴ ብዙ ነገሮችን እንዲያስታውሱ ያደርጋቸው ነበር፡፡ በመጀመሪያ፣ የመጡበት መንገድ ምን እንደሚመስል፣ ቀጥሎም ለብዙ ዓመታት እንዴት እንደተመሩ ማለትም ምን እንደተደረገላቸው፣ እናም በዚያ ሁሉ ጎዳና የመራቸውን አምላካቸውን እንዲያስቡ ነገራቸው፡፡ እርሻ ሳይኖር እንጀራ የበሉት፣ ደካማ ህዝብ ሳሉ ጠላት የፈራቸው ስለነርሱ በተነገረው ‹‹መፈራቴን በፊትህ እሰዳለሁ››፤ ‹‹እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋል›› በሚለውና በመሳሰለው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን፣ ከዚህም የተነሳ ሰው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ በህይወት እንደሚኖር አስታወሳቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በህይወት ያኖራል፡፡

Follow Us
YouTube (https://is.gd/FGBCHawassaYoutube)
Facebook (https://facebook.com/FGBCHawassa)
Instagram (https://ig.me/FGBCHawassa)
Telegram (https://www.tg-me.com/hawassafullgospelch)

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ሚያዝያ  20/2016 ዓ.ም
የልጆች አገልግሎት ዘርፍ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የህፃናት ማሳደጊያን ጎበኙ

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን  የልጆች አገልግሎት ዘርፍ ሚያዝያ 20/2016ዓ.ም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤን በዓል ምክንየያት በማድረግ በጎ አድራጎት ከልጆች  ለልጆች በሚል ርዕስ ልጆች እንደ የእግዚአብሔርን ቃል ቃልን በተግባር በመኖር ማደግን እንዲለማመዱ በቁጥር ከ15 የሚበልጡ የልጆች ተወካዮች፣  የመምህራንና የአስተባባሪዎች ተወካዮች በጋራ በመሆን ርኆቦት የህፃት ማሳደጊያን ጎብኝተዋል::

በጉብኝት ወቅት  በአንድነት የእግዚአብሔር ቃል በመካፈል የጋራ ዝማሬ ተከናውኖ፣ ለልጆችና ለማሳደጊያው ማህበረሰብ ፀሎት   ተደርጓል ::

በመቀጠል   ልጆችና መምህራን ተዟዙረው የልጆችን ስሜት በመረዳትና በማነቃቃት ከፍ ያሉትን ለማዋራትና ለማጫወት ሞክረዋል:: እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ በራሳቸው በልጆች መዋጮ የታሸገ ወተትና የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል::

በመጨረሻ  በጉብኝት የተሳተፉ ልጆችና  የመምህራንና የአስተባባሪዎች ተወካዮች  በሙሉ በታላቅ ደስታ :ማዕድ አብረው የቆረሱ ሲሆን፣ በቀጣይነት ጊዜያቸውን  አመቻችተው በየደረሱበት የተጎዱ ልጆችን ለመርዳትና  ይህንንም ጅማሬ አጠናክረው ለመቀጠል ቃል በመግባት የዕለቱ ውሎ ተጠናቋል::

Follow Us
YouTube (https://is.gd/FGBCHawassaYoutube)
Facebook (https://facebook.com/FGBCHawassa)
Instagram (https://ig.me/FGBCHawassa)
Telegram (https://www.tg-me.com/hawassafullgospelch)

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ሚያዝያ  21/2016 ዓ.ም
የረድኤት አገልግሎት ዘርፍ ለ36 ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የረድኤት አገልግሎት ዘርፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለትና የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በቤተክርስትያኒቱ ድጋፍ ለሚደረግላቸው 38 ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ።

ሚያዝያ 22/2016ዓ.ም የቤተክርስትያኒቱ የመሪዎች ጉባኤ ሰብሳቢ መጋቢ ሰለሞን ጃቢር እና የቤተክርስትያኒቱ የረድኤት ዘርፍ አገልጋዮች በተገኙበት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 36 ቤተሰቦች ጫማ፣ ቦርሣ፣ ልብሰ እንዲሁም 25ኪሎ ግራም ፉርኖ ዱቄት ክፍፍል ተደርጓል።

ድጋፉን ያደረጉት በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን አስተባባሪነት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ፈቃደኛ ክርስትያን ወንድሞችና እህቶች መሆኑን የቤተክርስትያኒቱ የረድኤት አገልግሎት ዘርፍ አገልጋይ የሆኑት ወንድም ኢዩ አሰፋ ገልጸዋል።
የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስትያን የመሪዎች ጉባኤ ሰብሳቢ መጋቢ ሰለሞን ጃቢር ቤተክርስትያን የእግዚአብሔር ቃል በሚያዛት መሰረት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረጓን የምትቀጥል መሆኑን በመግለጽ የቤተክርስትያንን ጥሪ ሰምተው በፈቃደኝነት ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙትን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙትን ክርስትያን ወንድሞችና እህቶችን እግዚአብሔር ይባርካችሁ ብለዋል።

ድጋፉ የተደረገላቸው ቤተሰቦች የፍቅር ስጦታ ያደረጉላቸውን በውጭ ሀገርና በሀገር በውስጥ የሚኖሩ ክርስትያኖችን፣ እንዲሁም የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያንን እኛን እንደቤተሰባቸው፣ ልጆቻችንንም እንደ ልጆቻቸው ቆጥረው መልካም ነገር ስላደረጉልን እግዚአብሔር ይባርካቸው የሚል መልዕክትን አስተላልፈዋል።

Follow Us
YouTube ( https://is.gd/FGBCHawassaYoutube )
Facebook ( https://facebook.com/FGBCHawassa )
Instagram ( https://ig.me/FGBCHawassa )
Telegram ( https://www.tg-me.com/hawassafullgospelch )

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ሚያዝያ 23/2016 ዓ.ም
የውሃ ጥምቀት ስነስርዓት ተካሄደ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 23 /2016 ዓ.ም "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" (ማቴ 28፡19-20) በሚለው መሪ ቃል መሰረትጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደዋል፡፡
በነበረው የውሃ ጥምቀትስነስርዓት ብዙዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ሀሴት አድርገዋል፡፡ በዕለቱ ከሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ወንድ 11፣ ሴት 14 በድምሩ 25 ወንድሞችና አህቶች የውሃ ጥምቀት ወስደዋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል ጌታን ተቀብለው የውሃ ጥምቀት ወስደው ከእግዚአብሔር መንገድ ርቀው የነበሩ፣ አሁን ግን በንስሃ የተመለሱ ወንድ 4፣ ሴት 4 በድምሩ 8 ሰዎች በቤተክርስቲያኒቱ የሚሰጠውን የመሰረታዊ የክርስትና ትምህርት ተምረዋል።
በእለቱ የውሃ ጥምቀት የወሰዱት፣ እንዲሁም በንስሃ የተመለሱት ወገኖች ሁሉም ከቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ጋር ህብረት አድርገዋል። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን!!
Follow Us
YouTube:—
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
Telegram:—
https://www.tg-me.com/hawassafullgospelch
Facebook:—
https://facebook.com/FGBCHawassa
የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስ ነፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
ለጌታችን ፣ ለመድኃኒታችን ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል
እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!


የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን
Follow Us
YouTube (https://is.gd/FGBCHawassaYoutube)
Facebook (https://facebook.com/FGBCHawassa)
Instagram (https://ig.me/FGBCHawassa)
Telegram (https://www.tg-me.com/hawassafullgospelch)
የጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በዓል በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን!

📆 አርብ ሚያዚያ 25 2016 ዓ.ም
🕑 ከጥዋቱ 2:00 ጀምሮ

@hawassafullgospelch
2024/06/08 18:25:42
Back to Top
HTML Embed Code: