Telegram Web Link
Channel photo updated
👉🏾# ሥርዓት_ ዘሰሞነ_ ህማማት


ሥርዓት_ዘሰሙነ_ሕማማት ( ከሰኞ እስከ ዓርብ )
 
✍️ሰሙነ ህማማት ማለት :- "ሰመነ፣ ማለት ሳምንት አደረገ ማለት ነው " ይሄውም ከእለተ ሆሳዕና ሰርክ፣ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ እና ቀናት" የሚያመለክት ነው ፡፡

ሀመ - ማለት "ታመመ" ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዳያቢሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ፅዋተ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፣ "የሰሙነ ህማማት እለታት የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው" ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት፣ ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ አምላካቸውን የሚማፀኑበት፣ ጠዋት ማታ አምላካቸውን ደጅ የሚጠኑበት ፥ ኃጢያታቸውን በቤተክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት፣ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው ፡፡ 

መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፣ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጠን አይፈጽሙም፣ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት፣ አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሠመረላቸውም፣ ምክራቸው የተፈፀመው ረቡዕ ነው፣ ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ “እንስቀለው፣ እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር" ይህንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፣ "መስቀልም አንሳለምም" ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡

ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ “እኔ የምስመው እርሱ ነውና ያዙት” ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው፣ ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት አይደለም፣ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፤  የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፣ "ሔዋንን ሰላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት" የዲያቢሎስ እና የይሁዳ ሰላምታ ሰይጣናዊ ነው፣ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብ በሰሙነ ህማማት ሰላምታ ልውውጥ የለም፣ ዛሬ እየተስተዋለ ያለው ይኸው ሰላምታ ያለመለዋወጥ ሁኔታ ሥርወ መሠረቱ ይህ ነው፣ ከጥንት ጀምሮ እዚህ ትውልድ ላይ ደርሷል።

በህማማት ሳምንት "ሥርዓተ ፍትሀት አይደረግም"፣ ይኸውም ይህ ሳምንት "ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት፣ ከጨለማ ወደ ብርሀን የተጓዝንበት" የመሸጋገሪያ ወራት ምሳሌ በመሆኑ ነው፣
በእለተ ምፅአት መላእክት የመለከትን ድምፅ እንደሚያሰሙ፤ የዳግም ምፅአትን እለት በማሰብ ምዕመናን ጥሪውን ሰምተው፣ ከዚያም አስቀድመው የበአሉ ታዳሚዎች መሆናቸውን ለማጠየቅ "በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭሉን እያቃጨለ ምዕመናኑን ያሳስባል"

በዚህ የህማማት ሳምንት የስግደት የፀሎትና የፆም ስርዓታችን እንደሚከተለው ነው።

"ስግደት"
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ፣ 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል፣ ይህም ክርስቶስ ስለ እኛ በደልና ኃጢአት በሰው እጅ ተይዞ የቀበለውን መከራና ስቃይ ለማሰብ ነው፣ ክርስቶስ ለእኛ ፍቅሩን አንዴ ሞቶ ገልፆልናል፣ እኛ ግን ስለ በደላችን፣ በፍርድ ሰዓት በግራ እንዳንቆም አብዝተን ንስሐ በመግባት ሥጋችንን እናደክማለን።

"ጸሎት"
በሰሙነ ህማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ፣ እኒህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት ፣ 3 ሰዓት ፣ 6 ሰዓት ፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት፣ 3 ሰዓት፣ 6 ሰዓት፣ 9 ሰዓት፣ 11 ሰዓት ናቸው፣ በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር "መዝሙረ ዳዊትና፣ ግብረ ሕማማት፣ ድርሳነ ማህያዊ አብዝተው ይጸለያሉ" ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚደረግ የጸሎት ሥርዓት ሲሆን ምዕመናን ተገኝተው ፀሎቱን ተካፋይ ይሆናሉ፣ "የግል ጸሎታቸውም ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ከውዳሴ ማርያምና ከውዳሴ አምላክ ፣ ከሰይፈ ሥላሴና፣ ሰይፈ መለኮት" ሲሆን፤ "መልክዓ መልክእና ድርሳናት እንዲሁም ተአምራት በህማማት ሳምንት ባሉ ቀናት ውስጥ አይጸለዩም

ይልቁንም ከቅዱሳን መጻሕፍት የጌታችን የአምላካችንን መከራውንና ድካሙን የሚያስታውሱ "ከትንቢተ ኢሳይያስ፣ ከትንቢተ ኤርሚያስ፣ ከመዝሙረ ዳዊት ፣ ግብረ ህማማት" በየሰዓቱ ይነበባል፡፡

       "ጾም"
በሰሙነ ህማማት "ብዙ አዝማደ መባልዕት አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም" ይልቁንስ በመራብ፣ በመጠማት፣ በመስገድ፣ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የአምላካችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውን ህማሙን ግርፋቱን ድካሙን በማሰብ ይዋላል። በዚህም "ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም" ይኸውም ቆሎ፣ ዳቦ፣ ውኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

በሰሞነ ህማማት የሚጸለዩና የማይጸለዩ የጸሎት መጽሐፍት አሉ

  "በሰሞነ ሕማማት የማይደገሙ የማይጸለዩ የጸሎት መጽሐፍት" :-

1.ድርሳናት
2.ገድላት
3.መልክአ መልክእዎች

"የሚጸለዩት ደግሞ:-"

1. ውዳሴ ማርያም፣
2.መዝሙረ ዳዊት በብዛት ከወትሮ በተለየ ቢያንስ የየዕለቱን ሙሉዉን፣
3. ሰይፈ መለኮት፣ ሰይፈ ሥላሴ፣ ውዳሴ አምላክ
4. ድርሳነ ማኀየዊ የጌታችን ሕማማትና እንግልቱ ያደረጋቸው ተዓምራትና፣ ዐርኬ መልከአ ማኀየዊ አንድ ላይ የየዕለቱ አለው፣
5.ላሓ ማርያም የእመቤታችን ለቅሶ ሐዘን

እነዚህ የጸሎት መጽሐፍቶቹ ያለን ሰዎች በርትተን እንጸልይባቸው፣ የጌታችንንም የእመቤታችንን ስቃይ እንግልት ሐዘን እንካፈል፣ በረከት እናግኝ ለአገራችንና ለዓለም ሰላም ለቤተክርስቲያናችን ፍቅር፣ አንድነት ተግተን እንጸልይ"
@haymanotanednat
@haymanotanednat
            " መልካም ሰሞነ ሕማማት "
#ሐሙስ

#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ ፳፮፥፳፮-፳፱/26:26-29 በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳/22:8 የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥፲፭/15:15 የነጻነት ሐሙስ ይባላል።
እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
     አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ 
     ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር
     በፍስሐ ወበሰላም:: አሜን፡፡
@haymanotanednat
@haymanotanednat
፡- ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጀና የጸሎት ሐመስ እለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብጽ ተሰደው በሚነጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜያልቦካው ሊጥ እያጋገሩ ቂጣ መብላት ንፎሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓልይታሰባል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሰረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን እንዲሁም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውሃ የሚያስጠማ በመሆኑየጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ስርዓት በእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያ አብዛኛዎቹን የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻስላላቸው ስርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡
@haymanotanednat
@haymanotanednat
#የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ

ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡

#የስቅለት_ዓርብ ይባላል
የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል።  (ማቴ 27፡35)

#መልካሙ_ዓርብ ይባላል
ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦
1. ፀሐይ ጨልማለች
2. ጨረቃ ደም ሆናለች
3. ከዋክብት ረግፈዋል
4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች)
6. መቃብሮች ተከፍተዋል
7. ሙታን ተነስተዋል

በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
@haymanotanednat
@haymanotanednat
Channel photo updated
ክርስቲያኖች ሁላችሁ ኑ ድንግልን እናጽናናት በልጇ ሰቃይ ሆድ ብሷታልና


ድንግል ማርያም የልጅዋን ልብስ እንኳ ይዛ የማልቀስ እድል አልነበራትም።

ምክንያቱም ልብሱን ለአራት (4) ቀደው ተካፍለውታል በቀሚሱም ላይ ዕጣ ተጣጥለዋል

ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንዱ ልጅዋ መከራ ሲጸናበት እያየች መጽናናት አልቻለችምና

የእናቱ ኃዘን የተሰማችሁ የደረሰባትን ግፍና ኃዘን እያሰባችሁ አልቅሱ።

             ልብሱን ገፈፉት

በወንጌል የምናውቃቸው ጌታችን የለበሳቸው ልብሶች አራት (4) ሲሆኑ ሦስቱ ከዕለተ ዓርብ በኃላ የለበሳቸው ናቸው።

የመጀመሪያው ከመያዙ በፊት ልብሶት የነበረው የራሱ ልብስ ነው።

2ኛ. ሄሮድስ ለመዘበት ያለበሰው የጌጥ ልብስ ነው

3ኛ. ወታደሮቹ ያለበሱት ቀይ ልብስ (ከለሜዳ) ነው

4ኛ. ከትንሣኤው በኃላ ሲገለጥ የለበሰው ነጭ ልብስ ነው
ሚስጥረ እለተ አርብ ( ስቅለት )





13ቱ ህማማተ መስቀል
➊ እራሱን በዘንግ ተመታ ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው
እራሱን መቱት ።《ማቴ 27÷30》
➋ በጥፊ ተመታ ፦ በጥፊም ይመቱት ነበር።《የሀ 19÷4》

➌ ምራቅ ተፉበት ፦ ተፉበትም መቃውንም ይዘው እራሱን
መቱት።《 ማቴ 27÷30》
➍ የሾክ አክሊል ጎንጉነው በእራሱላይ አቀዳጁት 《ማቴ.27፥29 》

➎ መራራ ሀሞት አጠጡት ፦ በሀሞት የተደባለቀ የወይን
ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም ።《ማቴ 27÷34 》

➏ ጀርባውን መገረፉ ፦ በዚያን ጊዜም ጲላጦስ እየሱስን ይዞ
ገረፈው ። 《ዩሀ 19÷1》

➐ ጎኑን በጦር መውጋት፦ ነገር ግን ከጭፈራዎቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው ወድያውም ደምና ውሃ ወጣ።《የሀ 19÷34 》

➑ ወደ ኃላ መታሰሩ ፦ የሾለቃውና ጭፍሮቹ የአይሁድም ሌሎችም እየሱስን ይዘው አሰሩት። 《ዩሀ.18÷12 》

➒ ሳዶር
➓ አላዶር
➊➊ ዳናት
➊➋ አዴራ
➊➌ ሮዳስ

5ቱ #ቅንዋተ #መስቀል ችንክሮች ሳዶር ፣ አላዶር ፣ ዳናት ፣ አዴራ እና ሮዳስ ይባላሉ።
#ሳዶር ፦ ማለት ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
#አላዶር፦ ማለት ግራ እጁ የተቸነከረበት
#ዳናት ፦ ማለት እግሮቹ የተቸነከረበት
#አዴራ ፦ ማለት ደረቱን የተቸነከረበት
#ሮዳስ ፦ ማለት ከወገቡ (እብርቱ) አጣብቆ እንዲይዝ
የተቸነከረበት
መከራን ታገሰ

በህይዋንና በሙታን ላይ የሚፈርድ እርሱን እንደበደለኛ
ተፈረደበት
አለምን ሁሉ በቅፅበት የፈጠረ እርሱ በስጋው ሞተ በመለኮት ህያው ሆነ
📖
ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ ከ6-9 ስአት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር ቃላት
ኤሉሄ ኤሉሄ ለማስበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ) ማቴ 27÷46
እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ።
ሉቃ.23÷43
አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃ 23÷43
አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው። ሉቃ.23÷34
እናትህ እንኃት እንሆ ልጅሽ:: ዩሀ 19÷26-27
ተጠማሁ። ዩሀ 19÷28
ተፈፀመ። ዩሀ 19÷30

#ጌታችን_መድኃኒታችን_እየሱስ_ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
የተፈፀሙ 7ቱ ታአምራት
1⃣ ፅሀይ ጨለመች
2⃣ ጨረቃ ደም ለበሰች
3⃣ ከዋከብት ብርሃናቸውን ነሱ
4⃣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከሁለት ተከፈለ
5⃣ አለቶች ተሰነጣጠቁ
6⃣ መቃብራን ተከፈቱ
7⃣ የሞቱት ተነሱ
ክብርና ምስጋና አምልኮት ውዳሴ ስግደት ዝማሪ ይድረሰ ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለእየሱስ_ክርስቶስ

🌿❤️ አቤቱ አምላካችን ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ
አስበን አሜን ፫
 @haymanotanednat
@haymanotanednat
Channel photo updated
" እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የብርሃን ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ሀይል ወሥልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን- አግአዞ ለአዳም፤
ሰላም- እምይዜሰ፤
ኮነ - ፍስሐ ወሰላም
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዐለም።
       ተነስቷል በዚህ የለም።
ክርስቶስ በታላቅ ሀይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ፤
ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤
ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ
@haymanotanednat
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያል የልደት በዓል በሰላም፡አደረሰን አደረሳችሁ ።

ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ ፣ ልቦናዬ በጎነ ነገርን አወጣ ፣ ልቦናዬ በጎ ነገርን አወጣ !

እኔስ የማሪያምን ክብር እናገራለሁ :: በማብዛት አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ።

እኔስ የድንግልን ውዳሴ እናገራለሁ መዘንጋት ባለበት ቃል በማስረዘም አይደለም በማሳጠር ነው እንጂ።

ድንግል ሆይ በኃጢያት ፍትወት የተፀነሽ አይደለሽም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ ።

ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚገዝፍ እንደ ዕብራዊያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም በንፅሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ ።

ድንግል ሆይ ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለሽም ከሠማይ ሠማያት የበሠለ ሠማያዊ ኀብስትን ነው እንጂ ።

ድንግል ሆይ ካንቺ አስቀድሞ ከአንቺ በኃላም እንዳሉ ሴቶች እድፍ የምታውቂ አይደለሽም በንፅሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ ።

ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሠማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ ። እንደተነገረ ካሕናትና የካሕናት አለቆች አመሠገኑሽ እንጂ ።

ድንግል ሆይ ለዬሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም ንፁሕ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ ።

እንዲሁም ስለሆነ እርሱ ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር አብ ንፅሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መለአኩን ወደ አንቺ ላከ መንፈስ ቅዱስም በላይሽ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ እንጂ ። እመቤቴ አንቺን የሚመስልሽ ማንም ምንም የለም እኛም እንወድሻለን እናገንሻለንም ።

ሊቁ አባ ህርያቆስ ኤጲስ ቆጶስ ዘሀገረ ብህሳን [ ቅዳሴ ማርያም ]
@haymanotanednat
@haymanotanednat
🕊  💖       💖   🕊

[ " ል ደ ታ ለ ማ ር ያ ም " ]

▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬
                    
" አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም  "

🕊

" በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ :- ያለ አንቺ ከአንቺ በቀር እንደምን ያለ ፈውስ እንደምን ያለ ይቅርታ ተደረገ ? አንቺ ሳትወለጂ : ከመወለድሽ አስቀድሞ እንደምን ያለ መድኃኒት : እንደምን ያለ ረድኤት ተደረገ ? አቤል በቃየል በግፍ ተገደለ : ደሙ ማንንም ማነን አላዳነም:: የማሕፀንሽ ፍሬ የክርስቶስ ደም ግን አዳምንና ልጆቹን አዳናቸው::

ሰይጣንም የአንቺን ምስጋና ወሬ ሲሰማ በብስጭት ጥርሱን ያፏጫል የምስጋናሽ ወሬ በእርሱ ዘንድ መራጃ ነውና እራሱን ይቆርጠዋል፡፡ ከስምሽ አጠራር የተነሣ መብረቅ በኃይል ሲጮህ እንደ ሰማ ሁሉ ይደነግጣል፡፡

አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ፈጽሞ ዕረፍት አላገኘም፡፡ ባንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው፡፡ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣል አንቺን ይጠላል፡፡"

[  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  ]

@haymanotanednat
@haymanotanednat
🕊   እንኳን አደረሳችሁ   🕊

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

    ☎️   +251977338586       🇪🇹
    ☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇


https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹
2024/05/15 00:03:29
Back to Top
HTML Embed Code: