Telegram Web Link
አንድ ቀን ወደ ወዘመክር ቤተ መፃህፍ እየሔድኩ ሳለሁ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግንብ ስር የተቀመጡ የሽበት ዘውድ የደፉ አንድ አዛውንት ቀልቤን ሳቡኝ።ሰወች እንዲመዘኑ ሚዛናቸውን እየጠቆሙ በአክብሮት ሲጣሩ ሳይ ትህትናቸው ጠርቶኝ በፈገግታ ተጠግቻቸው ሚዛኑ ላይ ወጣሁ....

እንዴት አረፈዱ አባባ??

እግዚአብሔር ይመስገን አንበሳዬ

ከላይ ወደታች ጥቁር ነጥብ ያልቀላቀለ ነጭ ሽበታቸውን አየሁት የአባትነት ሞገስ አላቸው። የሚዛናቸው ሰሌዳ ላይ ክብደቴን ለማወቅ ካተኮሩ በኋላ በፈገግታ ከንፈራቸውን ለቀቅ እያደረጉ ወደላይ ሲያዩኝ በብቸኝነት የቆመችው አንዷ ጥርሳቸው ተገለጠች...
  
ከጤና ጋ ይበቃል"እግዚአብሔር ከዋናው ሚዛን አያጉድልህ"(ከልባቸው እንደሆን ያስታውቃል

አሜን  ብዬ ደስ እያለኝ 5ብር ሰጠኋቸው። እስክርቃቸው ግን ምርቃታቸው እየተደጋገመ ይሰማኛል።"እግዚአብሔር ከዋናው ሚዛን አያጉድልህ"

  የአባባ ምርቃት ብቀበለውም አባታዊ ትእዛዝም እንዳለው የተረዳሁት ግን ቆይቼ ነበር።ብዙወቻችን ስጋዊ አቋማችንን እና ኪሏችንን ለማወቅ በየጊዜው በ5ብር እንመዘናለን።በጣም የሚያሳዝነው ግን ዋናውን መንፈሳዊ አቋማችንን እና ክብደታችንን በእግዚአብሔር ፊት በነፃ ከተመዘንን ዘመናት ተቆጥረዋል።

የሚገርማችሁ ደሞ መንገድ ላይ ተመዘኑ እያሉ እንደሚጣሩት ህፃናት እና አዛውንት ቤተክርስትያንም ካህናቶቿን አሰማርታ የየእለት ልመናዋ ተመዘኑ(ንሰሐ ግቡ) ነው።ከስተን ከሆነ በእግዚአብሔር ቃል እንድንወፍር፤አንሰን ከሆነ በስጋ ወደሙ ከፍ እንድንል፤ቀለን ከሆነ በንሰሀ እንድንከብድ፤ዛሬም ሚዛኑ ሰው እየጠበቀ ነው። ዛሬም ሚዛኑ ባዶ ነው።በአለም ሚዛን ከብደን ይሆናል ወፍረን ይሆናል..በመንፈሳዊው ሚዛንስ ኪሏችን ምን ያህል ይሆን??ገለባ ብንሆንስ??ከሲታ ብንሆንስ??አናሳ ኮስማና ብንሆንስ???ሚዛኑ ላይ እንውጣ እራሳችንን እንፈትሽ ለአካላችን ክብደት እንደምንጨነቀው ለነብስ ክብደታችን ለአፍታ እናስብ ለጡንቻችን ቅርፅ እንደምናስበው ስለ ህይወታችን መንፈሳዊ ቅርፅ እናስብ።ሲመስለኝ ከስተናል ቅርፃችን ጠፍቷል መንምነናል በሰው ፊት እንመር እንጂ በእግዚአብሔር ፊት ተራቁተናል....

ነገ ዛሬ ሳንል እራሳችንን ካህናት ጋር  እናስመዝን!!
 
   “ቴቄል ማለት፥በሚዛን ተመዘንህ፥ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው።”ዳን5፥27 ቀልሎ ከመገኘት ይሰውረን!!
  "እግዚአብሔር ከዋናው ሚዛኑ አያጉድለን"
+++ ጸልየህ ልታደርገው ትችላለህ? +++

ማልዶ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ ወደ ሥራ የሚሄድ አንድ መንፈሳዊ ሰው በጉዞው ከሌላ መንገደኛ ሰው ጋር ይገናኛል። ጥቂት እንደ ተጨዋወቱ ይህ በመንገድ ያገኘው ሰው ከደረት ኪሱ የሲጋራ ፓኮ በማውጣት አንዱን መዝዞ እንዲወስድ ይጋብዘዋል። ያም መንፈሳዊ ሰው "አይ ይቅርብኝ" ሲል እምቢታውን ገለጸ። ባለ ሲጋራውም "ኃጢአት ነው ብለህ ስላሰብህ ነው እምቢ ያልከኝ? ማጨስ እኮ ከአስጨናቂዋ ሕይወት ፋታ ለመውሰድና ራስን ዘና ለማድረግ ይረዳል። ግድ የለህም አንዱን ሞክር" እያለ ሊያግባባው ጣረ።  በመጨረሻም መንፈሳዊው ሰው "ግድ የለም ለእኔ ይቅርብኝ። ባይሆን አንተ ይጠቅመኛል ካልህ በቃ ሲጋራውን ከመለኮስህ በፊት አንድ "አባታችን ሆይ" ጸልይና ጀምር" አለው። በዚህ ጊዜ ያ መንገደኛ ደንግጦ እንዲህ ሲል መለሰ "ጸሎት ጸልዬማ እንዴት እንዲህ አደርጋለሁ?!"

በጸሎት ልትጀምር የማትችላቸው ማናቸውም ነገሮች ለአንተ መልካም አይደሉም። በልብህ ኃጢአት እንድታደርግ የሚገፉፉህ ክፉ ሐሳብ ሲመጣ "ይህን ጸልዬ ማድረግ እችላለሁ?" ብለህ ራስህን ጠይቅ። ከጸሎት ጋር የማይጣጣም ከመሰለህ እርሱ ኃጢአት ነውና ተወው። ጸልዮ የሚዘሙት፣ ጸልዮ የሚሰርቅ፣ ጸልዮ ባልንጀራውን የሚሳደብ፣ ጸልዮ በወንድሙ ላይ ክፉ የሚያደርግ ማን ነው?
*☞#ካህኑ ለምን በእጁ ያሳልመናል?*
የካህኑን እጅ መሳለም፦ አንዳንድ ሰዎች ካህኑ ለምን በእጁ
ያሳልመናል ይላሉ።ነገርግን ሚስጢሩ ይሄ ነው የካህኑ እጅ እኮእሳታዊያን የሆኑ መላዕክት መንካት የማይቻላቸውን ቅዱስሥጋውን ክቡር ደሙን የዳሰሰበት ነው። በቅዳሴ ላይ ቅዱስሥጋውን መንካት የሚችለው ዋናው ካህን ብቻ ነው ፤ ሁለተኛውካህን እንኳን መንካት አይችልም። ቅዱስ ሥጋውን ክቡርደሙን የዳሰሰበት ስለሆነም ካህኑ በእጁ ያሳልመናል እኛም
የተቀደሰውን የጌታ ስጋና ደም የተዳሰሰበት እጅ እየተሳለምን
የቅዳሴው በረከትና የአምላካችን ምህረት በእኛ ላይ እንዲሆን
አሜን አሜን እንላለን።ድንቅ መለኮታዊ ሚስጢር ማለት
እንዲህ ነው..አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስ ፦ ዲያቆኑ ይህን
በሚልበት ጊዜ ንፍቁ ካህን ማሕፈዱን ከጻሕሉ ላይ ያነሳል ፤
ይህም የጌታ መልአክ የመቃብሩን ድንጋይ የማንከባለሉ ምሳሌ
ነው። ከዚህ በኋላ ጌታችን በምሴተ ሐሙስ ሕብስቱን
እንደያዘው ዋናው ካህንም ሕብስቱን ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ፤
ይህም የጌታ ትንሣኤ ምሳሌ ነው።
እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ፦ በእግዚኦታ ላይ ካህኑ ሕብሥቱን
ይበልጥ ከፍ አድርጎ ይይዘዋል ይህም የዕርገቱ ምሳሌ ነው።
ከካህኑ ጋር ሆነን 41 ግዜ እግዚኦ መሐርነ ክርስቶስ እንላለን ፤
ይህም አርባው እግዚኦታ አይሁድ ጌታችንን 40 ግዜ
እንገርፋለን ብለው እያዛቡ ብዙ ግዜ የመግረፋቸው ምሳሌ
ሲሆን በመጨረሻ ካህኑ ብቻውን የሚላት እግዚኦታ ደግሞ
የአዳምና የሔዋን የንስሃ ምሳሌ ነው። 12 ግዜ እግዚኦ
መሐርነ ክርስቶስ ስንል ደግሞ ስለስምህ ብለህ ይቅር በለን
ስንል ነው።“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” የሚለውን
እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12 ይሆናልና!!እንዲሁም 12ግዜ
በእንተእግዚትነ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ ስነንል ደግሞ
ስለእናትህ ብለን ማረን ማለታችን ሲሆን*ቅድስት ድንግል
ማርያም*የሚለውን እያንዳንዱን ፊደል ስንቆጥር 12
ይሆናልና ነው
ወንጌል፦ የመጀመሪያው መልዕክት ሲነበብ ዲያቆኑ ፊቱን ወደ
ምዕራብ አዙሮ ያነባል; ሁለተኛው ዲያቆን ፊቱን ወደ ሰሜን
አዙሮ ያነባል; ንፍቅ ካህን ወደ ደቡብ ዙሮ የሐዋርያት ሥራን
ሲያነብ ዋናው ካህን ደግሞ ወደ ምሥራቅ ዙሮ ወንጌልን
ያነባል ፤ ይህም ግሩም የሆነ ምሳሌ አለው፦ አንድም ወንጌል
በአራቱም አቅጣጫ መሰበኩን ለመግለጽ ነው; አንድም ገነትን
የሚያጠጡ 4 ወንዞች አሉ; ኤፍራጠስ ጤግሮስ ጊዮን [ዓባይ]
እና ፊሶን ናቸው።
ገነትን አጠጥተው ለምለም እንደሚያደርጓት ጌታችን የተጠማ
ቢኖር የህይወትን ውሃ በነፃ ይጠጣና ይርካ እንዳለው ወንጌሉም
እንዲሁ ያለመልማል ሲሉ ነው።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ
ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች
ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለች!!

❀ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❀
❀ወለወላዲቱ ድንግል❀
❀ወለመስቀሉ ክቡር❀
2025/10/23 05:04:24
Back to Top
HTML Embed Code: