Telegram Web Link
በየአመቱ አንድ አንድ ህመሞች
ልባችንን ያረጥቡብናል

ዛሬ የሆኑ በሚመስል ሁኔታ የሞጣው፣
የዒዱ፣የሂጃባችን ከፍ ሲል ደግሞ የመስጂዶቻችን አለፍ ሲል ደግሞ የወንድሞቻችን ህይወት እያሳጣን ነው‼️

@heppymuslim29
ነብዩ ካለፉ በኃላ ቢላልን አዛን በል ሲሉት አሽሃዱ አነ ሙሐመደን ረሱለላህ ጋር ሲደርስ ተናነቀው ! ጉልበቱ ከዳው! የመልዕክተኛው ከመካከላቸው መጉደል ሮሮ'ውን አባሰው። ዛሬም በቢላል ሀገር በእንባ የታጀበ አዛን ተሰማ ! አሁን ግን ሁኔታው ሌላ ነው ። ፈላህ'ን ፈልገው ወደ ጌታቸው ቤት የመጡት አማኞች ላይ ታሪክ የማይረሳው በደል ተፈፀመ! አዛኑም ተጣራ! ሙዓዚኑም አሽሃዱ አነ ሙሐመደን ረሱለላህ ጋር ሲደርስ ሲቃ ተናናቀው ! በእርግጥ ጌታችን በደለኞች የሚሰሩትን ግፍ ዘንጊ አይደለም ! 💔

ለታሪክ ይቀመጥ!
25/09/2015

@heppymuslim29
የፀጉር አስተካካዩ እና የሙስሊሙ ውይይት

አንድ ፀጉር አስተካካይ የአንድ ሙስሊምን ፀጉር እየቆረጠ ሳለ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “እኔ በአምላክ መኖር አላምንም”።

ሙስሊሙም፦ "ለምን አታምንም?"

ፀጉር አስተካካዩ፦ “በዓለም ላይ ብዙ መከራና ትርምስ አለ። አምላክ (አላህ) ቢኖር ኖሮ ይህ ሁሉ ውዥንብር አይኖርም ነበር።"

ሙስሊሙ፡- “እኔም ፀጉር አስተካካዮች አሉ ብዬ አላምንም።"

ፀጉር አስተካካዩ ግራ በመጋባት “ምን ማለትህ ነው?” ሲል ጠየቀ።

ሙስሊሙ፦ ውጭ ወዳሉት ሰዎች እያመለከተ “እነዚህን ሰዎች ታያቸዋለህ? ፀጉራቸው የተንጨባረረ ነው።" አለው።
ፀጉር አስተካካዩ፦ “አዎ” አለ።

ሙስሊሙ፦ "ፀጉር አስተካካዮች ቢኖሩ ኖሮ ረጅምና የተመሰቃቀለ ፀጉር ያላቸው ሰዎች አይኖሩም ነበር።" አለው

ፀጉር አስተካካዩ፦ “እኛ (ፀጉር አስተካካዮች) አለን ነገር ግን ሰዎቹ ወደ እኛ አይመጡም!” አለ።

ሙስሊሙ፡፦ “በትክክል! አላህ አለ፣ ነገር ግን ሰዎች ምሪት ለማግኘት ወደ አላህ አይመለሱም። ለዚህም ነው በአለም ላይ ብዙ ችግሮች ያሉት።"

ድንቅ ምሳሌ፦ ፀጉራቸው የተንጨባረሩ ሰዎች አሉ ማለት ፀጉር አስተካካዮች የሉም ማለት አይደለም። ፀጉራቸው የተንጨባረሩ ሰዎች ፀጉራቸው እንዲስተካከልላቸው ከፈለጉ ፀጉር አስተካካዮች ዘንድ መሄድ ይኖርባቸዋል። መከራና ችግር በምድሪቱ ላይ በዛ ማለት አምላክ የለም ማለት አይደለም። አላህ አለ ነገር ግን ሰዎች ፍትህን በደል እንዲቆም የሚሹ ከሆነ ወደ አላህ መመለስ አለባቸው።

@heppymuslim29
ኹዘይማ ለችግረኞች ብቻ ሳይሆን መካከለኛ ገቢ ላላቸው የሀገሬው ሰው ሳይቀር ገንዘብ የሚለግስ ፍፁም ለጋ ስ ሰው ነው። (በዐብዲል መሊክ ኢብን መርዋን ዘመን)

ዱንያ ነች'ና ግዜ ዞረበት። ሀብታሙ እና ለጋሱ ኹዘይማ ተመልሶ ተመፅዋች ሆነ። ያኔ በሀብት ዘመኑ ይለግሳቸው የነበሩ ሰዎች ከአንድ ወር በላይ ሊመፀውቱት አልቻሉም።

ችግር ቸነፈሩ ሲበረታበት የሰው አይን ከሚገርፈኝ ብሎ በሩን በላዩ ጠርቅሞ ከሚስቱ ጋ የረሀብ ሞትን ይጠባበቁ ጀመር።

በግዜው የክፍለ ግዛቱ መሪ ዒክሪማ ይሰኛል። ይህ መሪ ኹዘይማን ያውቀው ነበር'ና የት እንደጠፋ ከዙርያው ያሉትን ሰዎች ጠየቀ።

‹‹ኹዘይማ ደኸየ እኮ! ዱንያ ዞረችበት'ና የእለት ጉርሱን እንኳ አጥቶ በሩን በላዩ ዘጋ›› ብለው መለሱለት።

‹‹ኹዘይማ ደኸየ! ያ ለጋስ ለሱ ሚለግሰውን እስኪያጣ ድረስ ደኸየ! ያ ሲለግስ ድህነትን እማይፈራው ኹዘይማ ደኸየ!›› ብሎ እጅግ አዘነ።

ያን ቀን መሽቶ ፀሀይ ጠለቀች። ይህ ዒክሪማ የተሰኘው መሪ ምሽትን ተገን አድርጎ ማንም እንዳያየው ፊቱን ተሸፋፍኖ በድቅድቅ ጨለማ ወደ ኹዘይማ ቤት አቀና።

የኹዘይማ በር ተንኳኳ።

‹‹ማን ነው?›› ኹዘይማ ጠየቀ።
‹‹እንግዳ ነኝ›› ዒክሪማ መለሰ።
እንግዳ በር ላይ ማቆም ነውር መሆኑን የተረዳው ኹዘይማ በሩን ወድያው ሲከፍት ዒክሪማ በከረጢት የተሸከመውን 4,000 ዲናር አራገፈለት።

‹‹ከየት ነው?›› ሲል ኹዘይማ የገንዘቡን ምንጭ ጠየቀ።
‹‹ከአላህ ካዝና ነው›› ብሎ መለሰለት ዒክሪማ።
‹‹ታድያ አንተ ማን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ኹዘይማ።
‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝ ነኝ›› ዒክሪማ መለሰ።
‹‹በአላህ ይሁንብህ ማን ነህ?›› ኹዘይማ በጉጉት ጠየቀ።

ዒክሪማም፦‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝ ነኝ›› ብሎ ትቶት ተሰወረ።

‹‹ይህ ተከናናቢ ያመጣልንን ስጦታ እንይ እስቲ ኩራዝ ለኩሺ›› አለ ኹዘይማ ሚስቱን።
‹‹ኩራዛችን ከተበላሸ ስንት ዘመኑ!›› ብላ መለ ሰችለት።

ኹዘይማም ከረጢቱን እየነካካ ለማየት እንደጓጓም ጎህ ቀደደ። ወጋገኑ መታየት ሲጀምር ከረጢቱን ሲከፍተው 4,000 ዲናር ተመለከተ።(1,000 ዲናር 4,5 ኪሎ ግራም ወርቅ ነው)

ኹዘይማ ከጨለማው ህይወቱ ተገላግሎ እዳዎቹን በሙሉ ከፋፍሎ የድሮውን የድሎት ኑሮ እንደ አዲስ ማጣጣም ጀመረ።

ያን ሌሊት ዒክሪማ ለኹዘይማ ገንዘቡን ሰጥቶ ሲመለስ ሚስቱ፦‹‹ሁለተኛ ሚስትህ ጋ ሄደህ ነው አይደል?›› ብላ ወቀሰችው።

‹‹ወላሂ አይደለም›› አላት።
‹‹ታድያ በዚህ ሌሊት የት ሄደህ ነው ከሞቀ አልጋህ?›› አለችው።
‹‹ላንቺ አልያም ለሌላ ሰው ምነግረው ጉዳይ ቢሆን ለምን በሌሊት ተከናንቤ እወጣለሁ?›› አላት።

ያን ማታ ሚስት ባሏ የወጣበትን ለማወቅ ወጥራ ያዘችው። ባልም ውትወታው ከአቅሙ በላይ ሲሆን ሚስጥሩን እንድትደብቅ ለምኗት ሁሉንም ነገራት።

ወራት ተቆጠሩ። ከእለታት አንድ ቀን ኹዘይማ የጠቅላይ ግዛቱን ንጉስ ለመዘየር ንጉስ ዐብዲል መሊክ ዘንድ ተጓዘ።

ንጉሱም ትልቅ አቀባበል ካደረገለት በኋላ ለምን እንደጠፋ ጠየቀው። ኹዘይማም የደረሰበትን ቸነፈር እና በመጨረሻም ስለ ‹‹የለጋሶች ስሜት ጠባቂ›› የገጠመውን ፀጋ ተረከለት።

ንጉስ ተደነቀ፦‹‹ማንነው የለጋሶችን ስሜት ጠጋኝ?›› ብሎ በጉጉት ጠየቀ።
ኹዘይማም፦‹‹አላውቀውም ሊነግረኝም አልፈቀደም›› አለው።
‹‹አይ ምን ነበር አውቀኸው በሆነ?›› ብሎ ንጉስ ተፀፀተ።

በመጨረሻም ንጉስ ዐብዱል መሊክ ለኹዘይማ ገንዘብ እንዲጫንለት እና መሪ ዒክሪማ ከስልጣን ተወግዶ የክፍለ ግዛቱ መሪ ኹዘይማ እንዲሆን ደብዳቤ አስይዞ ላከው።

ኹዘይማም ከንጉሱ የተቸረውን የሹመት ደብዳቤ ይዞ ወደ ትውልድ ሀገሩ በመምጣት ለዒክሪማ አስነበበው።

ዒክሪማም፦‹‹ሁሉም ለመልካም ነው›› ብሎ ስልጣኑን አስረከበ።
ኹዘይማም፦‹‹ከመውጣትህ በፊት ሂሳብ እንደራረግ›› ብሎ ሂሳብ ሲያሰራው ከግምጃ ቤት 4,000 ዲናር ጎድሎ አገኘ።

‹‹4,000 ዲናር የት አለ›› ኹዘይማ ጠየቀ።
‹‹የለኝም›› ዒክሪማ መለሰ።
‹‹ስለዚህ ክፈል›› አለው ኹዘይማ።
‹‹ምንም የለኝም›› አለ ዒክሪማ።
‹‹ወይ ክፈል ወይ ታሰር!›› ብሎ ኹዘይማ ወሰነበት።

ትናንት መሪ ሳለ ውለታ የዋለው ዒክሪማ እጅ እግሩ ተጠፍሮ ለእስር ተዳርገ። የፊት ገፅታው ተቀየረ ተኮራመተ።

ይህን የዒክሪማ ሚስት ስትሰማ ወደ አዲስ ተሿሚው ኹዘይማ ዘንድ ሂዳ፦‹‹የለጋሶች ስሜት ጠባቂን ውለታ በዚህ ልክ ልትመልስ አይገባም ነበር ›› አለችው።

ኹዘይማ ደነገጠ፦‹‹ዒክሪማ ነበር እንዴ ስሜቴን ተደብቆ የጠገነው!›› እያለ በለቅሶ ወደ እስር ቤት ሩጫ ጀመረ።

ኹዘይማ እስር ቤት ገብቶ እያለቀሰ የ ዒክሪማን ሰንሰለት ይፈታለት ጀመር፡፡
ዒክሪማም፦‹‹ምን ተፈጠረ? ለምንድነው ምትፈታኝ?›› ብሎ ጠየቀው።
‹‹ውለታህ እና ልግስናህ አንገቴን አስደፋኝ፤ ትዕግስትህ እና ሚስጥረኛነትህ ረታኝ›› ብሎ ኹዘይማ ለቅሶውን ቀጠለ።

በክብርም ቤቱ ወስዶ ተንከባከበው። ከቀናት በኋላም ኩዘይማ ይህን ድንቅ ሰው ለጠቅላይ ግዛቱ ገዥ ሊያሳይ ይዞት ሄደ።

ንጉሱ ኹዘይማን ሲመለከት፦‹‹ኹዘይማ አዲስ ተሿሚ ሁነህ ሳለ ወደዚህ ለምን መጣህ?›› ብሎ ጠየቀ።
‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝን እኮ ይዤልህ መጣሁ›› ብሎ መለሰለት።

ንጉስ ደነገጠ፦‹‹ዋ! ጥፋቴ አንተን ነበር ከስልጣን ያባረርኩህ! ዋ! ትዕግስትህ እና ጨዋነትህ ዋ የኔ ክስረት! ›› ብሎ ተ ፀፀተ። 10,000 ዲናርም ሰጥቶት ግዛቷን ሁለቱም በትብብር እንዲያስተዳድሩ ወስነላቸው።

ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ በፍቅር እና በመከባበር ግዛቷን መሯት።


@heppymuslim29
የሐጅ ናፍቆት

የሆነው በ2017 የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ነው። አንድ የቱርክ ቡድን ለፊልም ቀረፃ ሥራ የሚጠቀምባት ድሮን በርራ ሄዳ ዐብደላህ በተባለ በዚህ የጋና ድሃ ገበሬ እግር ሥር ትወድቃለች። ድሮኑን ፍለጋ የተሠማራው ቡድን በሠላም ከዐብደላህ እጅ ገብታ ያገኛታል።

ዐብደላህ በየዋህነትና በቅንነት አንዱን ጠጋ ብሎ ጠየቀ። "መካ ሄጄ ሐጅ የማደርግባት ከዚህች ከፍ ያለች ድሮን ይኖራችሁ ይሆን?" አለው።

ዐብደላህ እንደዋዛ የተናገራትን ቃል ቸሩ አምላክ አላህ (ሱ.ወ.) መዘገበለት። አስፈፃሚ ባሮቹንም ላከለት።
በ2018 ም በቱርክ መንግሥት ወጭ ዐብደላህ ሐጅ አደረገ። እንኳን ደስ ያለው።

የአላህ ቤት ናፍቆት አያስተኛም እኮ ወዳጆቼ!
@heppymuslim29
በሀብቱ የሚታወቀዉ ቱጃር ሰዉዬ በሀጅ ወቅት አረፋ ተራራ ላይ በአከባቢያቸዉ ዝቅተኛ የኖሮ ደረጃ ኖሮት ቆሎ እየሸጠ የሚተዳደርን ሰዉ ያገኘዋል።

በጣም ተደነቀ። በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ከስክሶ ለሀጅ የሄደዉ ባለሀብት የደሀዉን ሰዉዬ በቦታዉ መገኘት አስገርሞታል። ወደ'ሱ ጠጋ በማለት ሰላምታ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩም ሰላምታዉን መለሰለት።

"እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልክ?" በማለት ጥያቄ አቀረበለት። ቆሎ ሻጩ ትንሽ ግራ ተጋባ። አረፋ ተራራ ላይ ለሌላ ጉዳይ እንዳልመጣሁ እያወቀ ሳለ እንዴት ጠየቀኝ ሲል አሰበ።

"ያዉ ... ለሐጅ ስነ ስርአት ነዋ አመጣጤ"

"ገባኝ ግን ያዉ... በየትኛዉ አቅምህ እዚህ ልትመጣ ቻልክ?.. ማለቴ ቆሎ ቸርቻሪ ሆነህ ሳለ ገንዘቡን ከየት አመጣሃዉ?" በማለት ጠየቀዉ።

ቆሎ ሻጩም በተረጋጋ መንፈስ መለሰለት።

"እኔ ቆሎ ሻጭ ብሆንም ጌታዬ ግን ቆሎ ሻጭ አይደለም! እዚህ ቦታ ላይ ሆኜ እሱን እንድለምነዉና እንድገዛዉ ስለፈለገ ጌታዬ እንድመጣ ፈቀደ። ይኼዉ ነዉ...."

...

ኢላሂ! ለኛም ሀጅን ወፍቀን! ሁሌም ካንተ ከጃይ ነንና!

@heppymuslim29
ኡመር ኢብን አል-ኸጣብ አላህ መልካም ስራዉን ይውደድለትና እንዲህ ሲል ይናገራል አንድ ሰው ስለሚስቱ ስሞታ ሊያቀርብ ወደ እኔ ቤት መጣ ልክ በር (የዑመር) ደጃፉ ላይ ሲደርስ የዑመር ባለቤት ዑመርን በቁጣ ስትናገረው እና ስትወቅሰው ይሰማል ይሄን ባየ ጊዜ ዑመርም እንደኔው ችግር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ላይ ስለሆነ ሰሞታዬን ባቀርብ ምንም ሊረዳኝ አይችልም ብሎ በማሰብ ዞሮ መመልስ ይጀምራል ይህን ጊዜ ዑመር ሰውዬውን ያዩትና ይጠሩታል ለምንድን ነበር የመጣህ ብለው ይጠይቁታል

🍃ሰውዬውም ሲመልስ አይ የመጣሁበት ጉዳይ እንኳን በሚስቴ ላይ ስሞታ ላቀርብ ነበር ነገር ግን በር ደጃፍ ላይ ስደርስ እርስዎም እንደ እኔ ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ላይ ሁነው ስመለከት ተመለስኩኝ ዑመርም ለሰውዬው እንዲህ አሉት ሚስቴ በኔ ላይ የተወሰነ መብት አላት ስለዚህም ነው በቁጣ ስትናገረኝ ና ድንበር ስታልፍ ዝም ያልካት እርሷ አይደለች እንዴ ምግብ አብስላ የምታበላኝ አልባሳቶቼን የምታጥብልኝና ልጆቼን የምትንከባክብልኝ ይህን በማድረጓም ከብዙ ድካምና የገንዘብ ወጪ አድናኛለች ታድያ እሷን መታገስ እና መቻል የለብኝም ??

ከዚህም በላይ የህሊና ደስታንና እረፍት ትሰጠኛለች ይህን ሁሉ መልካም እየዋለችልኝ እሷን ከማስከፋትና ማስቀየም እንድቆጠብ አድርጎኛል ስለዚህ እሷ ድንበር ብታልፍብኝም የእርሷን መልካም ነገሮችን በማሰብ እንድታገስ እና እንድችል ያደርገኛል::

@heppymuslim29
ኹዘይማ ለችግረኞች ብቻ ሳይሆን መካከለኛ ገቢ ላላቸው የሀገሬው ሰው ሳይቀር ገንዘብ የሚለግስ ፍፁም ለጋስ ሰው ነው። (በዐብዲል መሊክ ኢብን መርዋን ዘመን)

ዱንያ ነች'ና ግዜ ዞረበት። ሀብታሙ እና ለጋሱ ኹዘይማ ተመልሶ ተመፅዋች ሆነ። ያኔ በሀብት ዘመኑ ይለግሳቸው የነበሩ ሰዎች ከአንድ ወር በላይ ሊመፀውቱት አልቻሉም።

ችግር ቸነፈሩ ሲበረታበት የሰው አይን ከሚገርፈኝ ብሎ በሩን በላዩ ጠርቅሞ ከሚስቱ ጋ የረሀብ ሞትን ይጠባበቁ ጀመር።

በግዜው የክፍለ ግዛቱ መሪ ዒክሪማ ይሰኛል። ይህ መሪ ኹዘይማን ያውቀው ነበር'ና የት እንደጠፋ ከዙርያው ያሉትን ሰዎች ጠየቀ።

‹‹ኹዘይማ ደኸየ እኮ! ዱንያ ዞረችበት'ና የእለት ጉርሱን እንኳ አጥቶ በሩን በላዩ ዘጋ›› ብለው መለሱለት።

‹‹ኹዘይማ ደኸየ! ያ ለጋስ ለሱ ሚለግሰውን እስኪያጣ ድረስ ደኸየ! ያ ሲለግስ ድህነትን እማይፈራው ኹዘይማ ደኸየ!›› ብሎ እጅግ አዘነ።

ያን ቀን መሽቶ ፀሀይ ጠለቀች። ይህ ዒክሪማ የተሰኘው መሪ ምሽትን ተገን አድርጎ ማንም እንዳያየው ፊቱን ተሸፋፍኖ በድቅድቅ ጨለማ ወደ ኹዘይማ ቤት አቀና።

የኹዘይማ በር ተንኳኳ።

‹‹ማን ነው?›› ኹዘይማ ጠየቀ።
‹‹እንግዳ ነኝ›› ዒክሪማ መለሰ።
እንግዳ በር ላይ ማቆም ነውር መሆኑን የተረዳው ኹዘይማ በሩን ወድያው ሲከፍት ዒክሪማ በከረጢት የተሸከመውን 4,000 ዲናር አራገፈለት።

‹‹ከየት ነው?›› ሲል ኹዘይማ የገንዘቡን ምንጭ ጠየቀ።
‹‹ከአላህ ካዝና ነው›› ብሎ መለሰለት ዒክሪማ።
‹‹ታድያ አንተ ማን ነህ?›› ብሎ ጠየቀ ኹዘይማ።
‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝ ነኝ›› ዒክሪማ መለሰ።
‹‹በአላህ ይሁንብህ ማን ነህ?›› ኹዘይማ በጉጉት ጠየቀ።

ዒክሪማም፦‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝ ነኝ›› ብሎ ትቶት ተሰወረ።

‹‹ይህ ተከናናቢ ያመጣልንን ስጦታ እንይ እስቲ ኩራዝ ለኩሺ›› አለ ኹዘይማ ሚስቱን።
‹‹ኩራዛችን ከተበላሸ ስንት ዘመኑ!›› ብላ መለ ሰችለት።

ኹዘይማም ከረጢቱን እየነካካ ለማየት እንደጓጓም ጎህ ቀደደ። ወጋገኑ መታየት ሲጀምር ከረጢቱን ሲከፍተው 4,000 ዲናር ተመለከተ።(1,000 ዲናር 4,5 ኪሎ ግራም ወርቅ ነው)

ኹዘይማ ከጨለማው ህይወቱ ተገላግሎ እዳዎቹን በሙሉ ከፋፍሎ የድሮውን የድሎት ኑሮ እንደ አዲስ ማጣጣም ጀመረ።

ያን ሌሊት ዒክሪማ ለኹዘይማ ገንዘቡን ሰጥቶ ሲመለስ ሚስቱ፦‹‹ሁለተኛ ሚስትህ ጋ ሄደህ ነው አይደል?›› ብላ ወቀሰችው።

‹‹ወላሂ አይደለም›› አላት።
‹‹ታድያ በዚህ ሌሊት የት ሄደህ ነው ከሞቀ አልጋህ?›› አለችው።
‹‹ላንቺ አልያም ለሌላ ሰው ምነግረው ጉዳይ ቢሆን ለምን በሌሊት ተከናንቤ እወጣለሁ?›› አላት።

ያን ማታ ሚስት ባሏ የወጣበትን ለማወቅ ወጥራ ያዘችው። ባልም ውትወታው ከአቅሙ በላይ ሲሆን ሚስጥሩን እንድትደብቅ ለምኗት ሁሉንም ነገራት።

ወራት ተቆጠሩ። ከእለታት አንድ ቀን ኹዘይማ የጠቅላይ ግዛቱን ንጉስ ለመዘየር ንጉስ ዐብዲል መሊክ ዘንድ ተጓዘ።

ንጉሱም ትልቅ አቀባበል ካደረገለት በኋላ ለምን እንደጠፋ ጠየቀው። ኹዘይማም የደረሰበትን ቸነፈር እና በመጨረሻም ስለ ‹‹የለጋሶች ስሜት ጠባቂ›› የገጠመውን ፀጋ ተረከለት።

ንጉስ ተደነቀ፦‹‹ማንነው የለጋሶችን ስሜት ጠጋኝ?›› ብሎ በጉጉት ጠየቀ።
ኹዘይማም፦‹‹አላውቀውም ሊነግረኝም አልፈቀደም›› አለው።
‹‹አይ ምን ነበር አውቀኸው በሆነ?›› ብሎ ንጉስ ተፀፀተ።

በመጨረሻም ንጉስ ዐብዱል መሊክ ለኹዘይማ ገንዘብ እንዲጫንለት እና መሪ ዒክሪማ ከስልጣን ተወግዶ የክፍለ ግዛቱ መሪ ኹዘይማ እንዲሆን ደብዳቤ አስይዞ ላከው።

ኹዘይማም ከንጉሱ የተቸረውን የሹመት ደብዳቤ ይዞ ወደ ትውልድ ሀገሩ በመምጣት ለዒክሪማ አስነበበው።

ዒክሪማም፦‹‹ሁሉም ለመልካም ነው›› ብሎ ስልጣኑን አስረከበ።
ኹዘይማም፦‹‹ከመውጣትህ በፊት ሂሳብ እንደራረግ›› ብሎ ሂሳብ ሲያሰራው ከግምጃ ቤት 4,000 ዲናር ጎድሎ አገኘ።

‹‹4,000 ዲናር የት አለ›› ኹዘይማ ጠየቀ።
‹‹የለኝም›› ዒክሪማ መለሰ።
‹‹ስለዚህ ክፈል›› አለው ኹዘይማ።
‹‹ምንም የለኝም›› አለ ዒክሪማ።
‹‹ወይ ክፈል ወይ ታሰር!›› ብሎ ኹዘይማ ወሰነበት።

ትናንት መሪ ሳለ ውለታ የዋለው ዒክሪማ እጅ እግሩ ተጠፍሮ ለእስር ተዳርገ። የፊት ገፅታው ተቀየረ ተኮራመተ።

ይህን የዒክሪማ ሚስት ስትሰማ ወደ አዲስ ተሿሚው ኹዘይማ ዘንድ ሂዳ፦‹‹የለጋሶች ስሜት ጠባቂን ውለታ በዚህ ልክ ልትመልስ አይገባም ነበር ›› አለችው።

ኹዘይማ ደነገጠ፦‹‹ዒክሪማ ነበር እንዴ ስሜቴን ተደብቆ የጠገነው!›› እያለ በለቅሶ ወደ እስር ቤት ሩጫ ጀመረ።

ኹዘይማ እስር ቤት ገብቶ እያለቀሰ የ ዒክሪማን ሰንሰለት ይፈታለት ጀመር፡፡
ዒክሪማም፦‹‹ምን ተፈጠረ? ለምንድነው ምትፈታኝ?›› ብሎ ጠየቀው።
‹‹ውለታህ እና ልግስናህ አንገቴን አስደፋኝ፤ ትዕግስትህ እና ሚስጥረኛነትህ ረታኝ›› ብሎ ኹዘይማ ለቅሶውን ቀጠለ።

በክብርም ቤቱ ወስዶ ተንከባከበው። ከቀናት በኋላም ኩዘይማ ይህን ድንቅ ሰው ለጠቅላይ ግዛቱ ገዥ ሊያሳይ ይዞት ሄደ።

ንጉሱ ኹዘይማን ሲመለከት፦‹‹ኹዘይማ አዲስ ተሿሚ ሁነህ ሳለ ወደዚህ ለምን መጣህ?›› ብሎ ጠየቀ።
‹‹የለጋሶች ስሜት ጠጋኝን እኮ ይዤልህ መጣሁ›› ብሎ መለሰለት።

ንጉስ ደነገጠ፦‹‹ዋ! ጥፋቴ አንተን ነበር ከስልጣን ያባረርኩህ! ዋ! ትዕግስትህ እና ጨዋነትህ ዋ የኔ ክስረት! ›› ብሎ ተ ፀፀተ። 10,000 ዲናርም ሰጥቶት ግዛቷን ሁለቱም በትብብር እንዲያስተዳድሩ ወስነላቸው።

ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ በፍቅር እና በመከባበር ግዛቷን መሯት። ይባላል

@heppymuslim29
ዙ-ኑን አልመስሪ ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በረሃ ላይ እየተጓዙ ነበር። ጀንበሯ ተራዋን ለጽልመት እየለቀቀች መሸትሸት ሲል ከአንድ የፈራረሰ ጥንታዊ ቤት ለይሉን ለማሳለፍ መሸጉ። እንደገቡ መጀመርያ በተመለከቱት ነገር የሁላቸውም ቀልብ ደነገጠ። እየተጣደፉ ሄዱና ቀርበው ተመለከቱት። በጣምም ተደሰቱ። ማሰሮው በወርቅና ልዩ ልዩ እንቁዎች የተሞላ ነበር። ድንገት ባገኙት ሀብት አማካኝነት ሀሴት አደረጉ። ከማሰሮው በላይ ደግሞ "አላህ" የሚል ፅሑፍ ያለበት ሰሌዳ ተቀምጧል። ሰዎቹ እንቁና ወርቁን መከፋፈል ሲጀምሩ ዙ-ኑን እንዲህ አሉ

"የፍቅሬ ስም የተከተበበትን ሰሌዳ ስጡኝ" ስሜታቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፤ አለቀሱ። በስስት እያዩት፣ በፍቅር እየዳበሱት፣ በክብር እያላቁት ቆዩ። ቅንጣት ታህል ወርቅ አልያ የከበረ ዲንጋይ ሳይሹ ወዱዱን አላህን እንዳቀፉ በህልማቸው እንዲህ ተባሉ

"ሌሎች ውድ የሆነላቸውን ወርቅና ጌጥ በመሰብሰብ ሲዋከቡ አንተ በእኔ ስም ተብቃቃህ። ሐቂቃ የማወቅንና ጥበብ የማርቀቅን በራፎች ከፍተንልሃል"

ለዚህም ነው "አላህን ያጣ ምን አገኘ፤ አላህን ያገኘ ምን አጣ" የሚባለው

@heppymuslim29
ባል ወደ ቤት ሲገባ ሚስቱ የአልጋውን ጫፍ ተደግፋ ተንሰቅስቃ እያነባች አገኛት። ደነገጠ ስታለቅስ ሲያያት ሆዱ ተላወሰ። ያፈቅራት ነበርና ሐዘኗ አሳዘነው። አቅፎ ደግፎ ግንባሯን እየሳመ ለምን እንደምታለቅስ ጠየቀ።
"ከቤታችን ፊት ለፊት የሚገኘው ዛፍ ላይ ያሉት ወፎች ዘወትር ልብሴን ስቀይር ፀጉሬን ያዩብኛል። ይህም አላህን ማመፅ እንዳይሆንብኝ ብዬ እፈራለሁ ለዚህ ነው የማለቅሰው" ብላ መለሰችለት።

   ባል በንጽሕናዋና አላህን በመፍራቷ ተደንቆ በዓይኖቿ መካከል ሳማትና መጥረቢያውን አውጥቶ ከቤታቸው ደጃፍ ላይ የበቀለውን ዛፍ ቆረጠ።

ከሳምንቱ መጨረሻ በአንደኛው ቀን ስራ አድክሞት ያለ ወትሮው ወደቤቱ አቀና። ሌላ ጊዜ ከሚገባበት ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ቤት ተመለሰ። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሚስቱ በሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ተኝታ አገኛት። አልጋው ላይ እሱ የገዛውን አንሶላ ከሌላ ወንድ ጋር ለብሳ ተመለከታት።

የሚያስፈልገውን እቃ ሻንጣው ውስጥ ሸክፎ ምንም ሳይናገር የትውልድ ቀየውን ለቆ ወጣ።

   ራቅ ወዳለ ሥፍራ ተጓዘ። መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ ከአንድ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከተ። ለምን እንደተሰበሰቡ ሲጠይቃቸው የንጉሱ ግምጃ ቤት ተዘርፎ ሌባው አለመገኘቱን ነገሩት።

በዚህ መሐል በእግሮቹ ጣት ጫፍ በቀስታ የሚራመድ ሰው ተመለከተ። ስለማንነቱም ጠየቀ "የከተማው ሸይኽ ነው ጉንዳን ረግጦ አላህ ዘንድ እንዳይጠየቅ በዝግታ ይጓዛል ከአላህ ፍራቻ ብዛት የጉንዳኖችን ህይወት ላለመቅጠፍ በመስጋት በቀስታ ይራመዳል" ብለው መለሱለት።

ወደ ንጉሡ ውሰዱኝ አለ። ወሰዱት። ለንጉሱም የአንተን ግምጃ ቤት የዘረፈው በጣቶቹ የሚራመደው ሸይኽ ነው። እሱ ሆኖ ካልተገኘ ፍርዴ ሞት ይሁን አለ። ንጉሱ ተገረመ በተቅዋው የሚታወቀው ሸይኽ እንዴት ሊዘርፈኝ ይችላል ሲል ራሱን ጠየቀ።

ወታደሮቹ ሸይኹን አምጥተው ከንጉሱ ፊት አቀረቡት። ምርመራው ተጀመረ ሸይኹ መስረቁን አምኖ ተቀበለ። መዝረፉም ተረጋገጠ።

ንጉሱም ወደ ሰውየው ዞሮ ሌባው እሱ መሆኑን እንዴት አወቅክ ሲል ጠየቀው
ሰውየውም፡-
    "አላህን እንፈራለን ብለው ራሳቸውን የሚያጋንኑ ሰዎችን ከተመለከትክ ወንጀላቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እወቁ" ሲል መለሰለትና በሩን ከፍቶ ከቤተ መንግስቱ ግቢ ወጣ።

@happymuslim29
ኢስሓቅ ኢብኑ ዐባድ አልበስሪ ይባላሉ። በአንድ ወቅት ተኝተው ሳለ በህልማቸው የሆነ አካል መጥቶ "ችግረኛውን እርዳ!" አላቸው።

ከእንቅልፋቸው ተነስተው በጎረቤት የተቸገረ ካለ ቢጠይቁ "አናውቅም" የሚል ምላሽ አገኙ ተመልሰው ተኙ።

አሁንም ለሁለተኛ፣ ከዚያም ለሶስተኛ ጊዜ መጥቶ "ችግረኛውን ሳትረዳ ትተኛለህ?" አላቸው።

ተነሱ 300 ዲርሃም ያዙ። በቅሏቸው ላይ ሆነው ወደ መስጂድ ወጡ። ሲደርሱ ሶላት የሚሰግድ ሰው አለ። ማጠናቀቁን ሲገምቱ ተጠጉና "አንተ የአላህ ባሪያ! ምነው በዚህ ሰዓት? በዚህ ቦታ? ምን አወ።ጣህ?!" አሉት።

ሰውየው:– "እኔ ወረቴ መቶ ዲርሃም የሆንኩ ሰው ነበርኩ። ግን ጠፋብኝ። ከዚያም የ200 ዲርሃም እዳ ተጫነኝ" አለ።

ዲርሃሞቹን አውጥተው "ይሄው እነዚህ 300 ዲርሃሞች ናቸው። ውሰድ" አሉት። ወሰደ።

ከዚያም "ታውቀኛለህ?" አሉት።
"አላውቅህም" አለ።
"እኔ ኢስሓቅ #ኢብኑ_ዐባድ ነኝ። ችግር ከገጠመህ ከኔ ዘንድ ና" ብለው ቤታቸው የሚገኝበትን አካባቢ ነገሩት።ሰውየው በዚህም ጊዜ እንዲህ አለ:–
"አላህ ይዘንልህ ችግር ከገጠመኝ አንተን ከቤትህ አውጥቶ እኔ ዘንድ ወዳመጣህ ጌታ ነው የምሸሸው"።

@heppymuslim29
...ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላል፡- በስራ ከተማ ገባሁ ...አንድ ቀን ሰዎች በታላቁ መስጂድ ከዙሁር ሶላት  ጀምረው እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ተሰብስበው አሏህን ሲለምኑ ተመለከትኩ .... "ምን አጋጠማችሁ  ?"  አልኳቸው።

እነሱም "ሰማይ ውሃ ከማውረድ ተቆጠበ፣ ወንዞቹም ደረቁ፣አሏህ ዝናብ እንዲያወርድልን ዱኣ እያደረግን ነው" አሉ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፡- "ከዛም ሁሉም ወደ ቤታቸው ሄዱ፤ ለሀገሪቷ እንግዳ ስለነበርኩ በመስጅድ ውስጥ ተቀምጬ ቆዬሁ። በዚህ  ሰኣት አንድ ጥቁር፣ አፍንጫው አጭር፣ ሆዱ የገፋ ፣ ከድህነቱ የተነሳ በአንድ ቁራጭ ልብስ  እፍረተ ገላውን የሸፈነ፣ ሌላኛውን ጫንቃው ላይ ያደረገ ሰውዬ ወደ መስጅድ ገብቶ ሁለት ረከዓ ሰገደ፤ ከዛም በመስጅዱ ውስጥ ሰው መኖሩን ለማረጋገጥ ግራ ቀኝ ዞረ... እኔ ያለሁበት ቦታ ትንሽ የተደበቀ ስለነበር ሳያዬኝ ቀርቶ ሰው የለም በማለት ወደ ቂብላ ዞሮ እጆቹን በማንሳት፡- "አሏህ ሆይ! ባሮችህን ስርኣት ለማስያዝ ዝናብ እንዳይወርድ አግደሃል፤ በባሮችህ ኃጢኣት ላይ ታጋሽና ይቅር ባይ የሆንከው ጌታ ሆይ!  ባሮችህን ውሃ ታጠጣቸው ዘንድ እማፅንሃለሁ!" አለ።

እጆቹን ከማውረዱ ሰማዩ ጨለመ፣ ደመናም ከየቦታው መጦ ከደመነ በኃላ ዝናቡ ዘነበ። ሰውዬው በጣም ስላስደነቀኝ ከመስጅድ ወጥቶ ወደ ቤቱ ሲሄደ ተከተልኩት... የተወሰነ ከተጓዘ በኃላ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፤ ቤቱን በማግስቱ ለማግኘት ብዬ በሩ ላይ በጭቃ ምልክት አደረኩና ተመለስኩ።

በማግስቱ ፀሀይ ስትወጣ መንገዶቹን ተከትዬ ምልክት ያደረኩበትን ቤት ደረስኩ፤ ቤቱ የባሪያ መሸጫ ቤት ነበር ። የባሪያ ነጋዴውን "ባሪያ መግዛት እፈልጋለሁ" አልኩት። ነጋዴውም  ረዢምና አጭር የተለያዩ ባሪያዎችን አሳዬኝ... የፈለኩትን ስላላገኘሁ "ከነዚህ ውጪ ሌላ አለህ?" አልኩት።

ባሪያ ነጋዴው፡- "ከነዚህ ውጭ የሚሸጥ ምንም የለኝም" አለ።
ማሊክ፦"ተስፋ ቆርጬ ከባሪያዎች ቤት ውጭ ተቀምጬ ባለሁበት ሰኣት ከበሩ አቅራቢያ ከእንጨት የተሰራ ጎጆ  አየሁና..በዚህ ጎጆ ውስጥ ሰው አለ ወይ? " አልኩ።

ባሪያዎቹ " አንተ ባርያ መግዛት ነው የምትፈልገው በዚህ ውስጥ ያለው ባሪያ ግን ላንተ የሚገባ ባሪያ አይደለም አይመጥንህም" አሉ።

ማሊክ ፦"ላየው ፈልጋለሁ ይውጣ ብያቸው  ባሪያው ከጎጆው ሲወጣ  ያ! ትላንት በመስጅድ ውስጥ ሲሰግድ ያዩሁት ሰውዬ ነበር" አለ።

ማሊክ ለባሪያ ነጋዴው "ልገዛው እፈልጋለሁ" አለ።
ነጋዴው፦ " ይህ ባሪያ ለምንም ነገር ስለማይሆን ከሸጥኩልህ በኃላ ምናልባት አታሎ ነው የሸጠልኝ ብለህ ስሜን  ታጠፋ  ይሆናል!" አለ።
ማሊክ፦"እንዳሰብከው አይደለም ልገዛው ስለፈለኩ ነው" አለ....ነጋዴውም በርካሽ ዋጋ ሸጠለት ።

ማሊክ እንዲህ ይላል ፦ ይህን ባሪያ ወደ ቤቴ ወስጄው የተወሰነ ከተቀመጠ በኃላ አንገቱን ቀና አደረገና ጌታዬ ሆይ! ጥንካሬን ከፈለግክ ከኔ የሚበረታ አለ፣ ዝናን ከፈለክ ከኔ የበለጠ ቆንጆ አለ፣ ለስራ ከሆነ ደግሞ ከኔ የበለጠ አዋቂ  አለና ለምን ገዛኸኝ?" አለ።

ማሊክ፦ "ትላንት የበስራ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ ባጋጠማቸው ድርቅ ምክንያት በመስጅድ ውስጥ ከዙሁር ሶላት እስከ ዒሻእ ሶላት በኃላ ድረስ ዱኣ ሲያደርጉ ቆይተዋል...
ነገር ግን ልምናቸው ተቀባይት አላገኘም ነበር። አንተ ግን መስጅድ ገብተህ እጆችህን አንስተህ አሏህን በለመንክ ሰኣት ልመናህ ተቀባይነትን አግኝቶ ዝናብ ወረደ” አለው።

አገልጋዩ፡-" ምናልባት ሌላ ይሆናል! ምንስ  አሳወቀህ ምናልባት ያየኸው ሌላ ሰው ሊሆን ይችላል” አለ።

ማሊክ፦"ይልቁንስ! አንተ ነህ" አልኩት፤ አገልጋዩም፡- "አውቀኸኛል?"አለ፤
ማሊክ፦"አዎ!" አለ፤
አገልጋዩ ፡- "እርግጠኛ ነህ? " አለ፤
ማሊክ "አዎ!"አለ።

ማሊክ እንዲህ ይላል፦ "በአሏህ እምላለሁ! ከዛ በኋላ ወደኔ አልተመለከተም፤ ወዲያውኑ ለአሏህ ሱጁድ ወረደ...ስግደቱንም አራዘመ፤ ወደሱ በደንብ ስቀርብ፦ «የሚስጢሩ ባለቤት ሆይ! ሚስጥሩ ተጋለጠ፣ ይህ ሚስጢር ተስፋፍቶ ህይወትን መቋቋም አልችልም።» ሲል ሰማሁ ... ብዙም ሳይቆይ ነፍሱ ከሱ ተለይታ ይችን ዓለም ተሰናበተ።"

@heppymuslim29
ዲኔ ላይ ደህና ነኝ፡፡ መልክ አለኝ ባይባልም አልከፋም፡፡ በባህሪዬ ጥሩ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤተሰብ ሳልርቅ ነው ያደግኩት፡፡ የልጅነት ጊዜዬ አልፎ ወጣትነት መጣ፡፡ እንደማንኛዋም ሴት ትዳር አሰብኩ፡፡ ግና በማላውቀው ምክንያት ድርሻዬ ዘገየብኝ፡፡ ለጋብቻ የሚጠይቀኝ ጠፋ፡፡ ከኔ በኋላ የተወለዱ የቤተሰብም፣ የዘመድም፣ የሰፈርም ልጆች አንድ በአንድ አገቡ፡፡ ወለዱ፡፡ ልጆቻቸዉም አደጉ፡፡ ሳላስበው 34 ዓመት ሆነኝ፡፡ ዕድሜዬን ሳስታውሰው ደነገጥኩ፡፡ ብቻዬን ቆሜ የቀረሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተሠማኝ፡፡
፨፨፨
የሆነ ጊዜ ከቅርብ ዘመድ የሆነ አንድ ወጣት ለጋብቻ ጠየቀኝ፡፡ ፈቃደኝነቴን ገለጽኩ፡፡ ሁለት ዓመት ይበልጠኛል፡፡ ዲኑም ፀባዩም ቆንጆ ነው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ከሀሳቤ የተገላገልኩ መሰለኝ፡፡ ቤተሰብም ደስ አለው፡፡
.
ኒካሕ ለማሰር ተዘጋጀን፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን ለመጨረስ ብሎ መታወቂያዬን ይዞ ሄደ፡፡
.
.ከሁለት ቀን በኋላ ስልክ ተደወለልኝ፡፡ እናቱ ነበረች፡፡ እንደምትፈልገኝ ነገረችኝ፡፡ ምን ይሆን ብዬ እየበረርኩ ሄደኩኝ፡፡ ቤታቸው ገባሁ፡፡ ጥቂት ካወራን በኋላ መታወቂያዬን እያሳየችኝ እዚህ ላይ የተጠቀሰው የትውልድ ቀኔ ትክክል ስለመሆኑ ጠየቀችኝ፡፡ አዎን ትክክል ነው አልኳት፡ እንግዲያዉስ አንች አርባ ተጠግተሸል መውለድ አትችይም፡፡ አለችኝ፡፡ 34 ዓመቴ እኮ ነው እንዴት አልችልም አልኳት፡፡ አይ … አንች ሰላሳ አልፎሻል እኔ ደግሞ ልጅ አይደለም ገና የልጅ ልጅ ማየት እፈልጋለሁ አለች፡፡ ጋብቻው እንዲሰረዝ ሞገተች፡፡ ልጇንም አሳመነች ለቤተሰቤ ምን እንደምላቸው እያሰላሰልኩ ተስፋ ቆርጬ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡
፨፨
ቀናት አለፉ፡፡ ድፍን ስድስት ወራትን በሐዘን አሳለፍኩ፡፡ ረጃጅም ቀንና ሌሊቶችን  ስብሰለሰል ከረምኩ፡፡ በር በሩን ባይ  እኔን ብሎ የሚመጣ ለኔ የተፃፈ ባል ጠፋ፡፡ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት፣ አጥንት ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ፡፡አባቴ ሁኔታዬን ይከታተላል፡፡ ስለኔ አብዝቶ ተጨነቀ፡፡ በመጨረሻም ከወንድሜ ጋር ለዑምራ እንድሄድ መከረኝ፡፡ ሂጂና በተከበረው የአላህ ቤት አጠገብ ብሶትሽን ተናገሪ፤ የዉስጥሽን የዉስጥ አዋቂ ለሆነ ጌታ ተንፍሺ አለኝ፡፡ 
ዑምራ ሄድኩኝ፡፡ የአላህ ቤት ከዕባ ፊት ቁጭ ብዬ ረጅም ዱዓ አደረግኩ፡፡ ለርሱ የዉስጥ ስሜቴን ሁሉ አንሾካሸኩ፡፡ አለቀስኩ፤ ፈረጄን ያቀርብልኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡
፨፨
የሆነ ቀን ሱንና ከሰገድኩ በኋላ ጥቂት ቁጭ አልኩ፡፡ ከኋላዬ አንዲት ሴት ባማረ ድምጽ ቁርኣንን ታነባለች፡፡ “የአላህ ችሮታ ብዙ ነው፡፡” የሚል ትርጉም ያለዉን የቁርኣን አንቀጽ ስታነብ ቀልቤ በተለየ መልኩ ወደዚያ ተሳበ፡፡ በቁርኣን ዉስጥ የዚህ ዓይነት አንቀጽ ስለመኖሩ ገረመኝ፡፡ አላህ በችሮታው ያስበኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡ሴትዮዋ አየችኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ፡፡ ሁኔታዬን ነገርኳት፡፡ አብሽሪ አለችኝ “ አብሽሪ አላህም ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ ኢንሻአላህ ደስም ይልሻል፡፡” አለችኝ፡፡
፨፨
ዑምራውን አጠናቅቄ ተመለስኩ፡፡ ድንገት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬንና ባሏን በዐይሮፕላን ማረፊያው  አገኘኋቸው፡፡ የባሏን ጓደኛ ለመቀበል እየጠበቁ ነበር፡፡ ሰላምታ አቅርቤላቸው ትንሽ እንዳወጋን ጓደኛቸው ደረሰና ተሰነባበትን፡፡ ወዲያው አባቴ ደርሶ ተቀበለኝ፡፡
፨፨ 
ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ አሁን ከበፊቱ በተሻለ ልቤ በመጠኑ ሰክኗል፡፡ ዱዓዬን አላቋረጥኩም፡፡
የሆነ ቀን ያች ጓደኛዬ ደወለችልኝ፡፡ ያን ቀን ያየኝ የባሏ ጓደኛ ለትዳር እንዳሰበኝ ነገረችኝ፡፡ በአንድ ቀን እይታ እንዴት ሊሆን ይችላል ብዬ ተገረምኩ፡፡ ግና ለአላህ ምን ይሳነዋል!!፡፡
በእውነቱ የማይታሰብ ነገር ሆነብኝ፤ ማመን አቃተኝ፡፡ እሱ ግን የምሩን ነበር፡፡ ስለኔ ሁሉን ነገር ከጓደኛዬ ከሰማ በኋላ አላንገራገረም፡፡ ወደ ቤተሰቦቼ ሽማግሌ ላከ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ተስፋዬ ለመለመ፡፡ ወዜ ተመለሰ፡፡ ስሜቴ ታደሰ፡፡
፨፨
በመጨረሻም አገባሁ፡፡ ጥሩ አፍቃሪ፣ መልካምና ደጋፊ፣ አዛኝና አሳቢ ባል … አላህ ሠጠኝ፡፡ ለኔም ለወላጆቹም ጥሩ ሰው ነበር፡፡
.
ካገባሁ ቀናት ሄዱ፣ ሁለትና ሦስት ወራት ተተኩ፡፡ ሌላ ሀሳብ አስጨነቀኝ፡፡ የእርግዝና ምልክት ናፈቀኝ፡፡ ግና እስካሁን ምንም አላስተዋልኩም፡፡ ሲበዛ አሳሰበኝ፡፡ እንቅልፍ አጣሁ፡፡
.
መመርመር እንደምፈልግ ለባሌ ነገርኩት፡፡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድን፡፡ ጥቂት ቆይተን ለዉጤቱ ተጠራን፡፡ ልቤ መምታቱን ጨመረ፡፡ ገና እንደገባሁ “መዳም መብሩክ!” አለችኝ ሀኪሟ፡፡
አርግዤ ነበር፡፡ ሱብሐነላህ!፡፡ ለዚህ ብስራት ነበር እንዴ አላህ እዚህ ድረስ ያመጣኝ አልኩ፡፡
.
የእርግዝና ጊዜዬ ሰላማዊ ነበር፡፡ ግና የዕድሜዬ መግፋት መጠነኛ ተጽእኖ ነበረው፡፡ ሆዴ እያደገ ሲመጣ ሰዉነቴ ከበደኝ፡፡ እንደምንም የድካሙ ወራት አለፈ፡፡ የምጡ ቀን ደረሰ፡፡ በቀዶ ጥገና ነበር የወለድኩት፡፡ ከተሠጠኝ ሰመመን ስነቃ ቤተሰቦቼና ባለቤቴ ዙርያዬ ተሰብስበዋል፡፡ ይስቃሉ፣ ይጫወታሉ፡፡ “ምን ወለድኩ?” አልኳቸው ያለሁበትን ሁኔታ እያስታወስኩ፡፡
.
የተመካከሩ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ላይ ሆነው ነበር ሰርፕራይዝ ያደረጉኝ “ወንድ እና ሴት!” አሉኝ፡፡ መንታ!!፡፡ የኔን መንቃት ሲጠብቅ የነበረው ባሌ በደስታ ተፍነከነከ፡፡ እኔንም ሀሴት የምሆነውን አሳጣኝ፡፡ ብችል ተነስቼ በዘለልኩ፡፡ ቁስሌ ገና እርጥብ ነው፡፡ ሱጁድም ራቀኝ፡፡ በተኛሁበት እንባዬ በሁለቱም ጉንጮቼ በኩል ዝምብሎ ሲፈስ ይታወቀኛል፡፡ በትኩስ እንባ ፊቴ ታጠበ፡፡ ምስጋናዬን ያወጣሁበት ቃል እሱ ነበር፡፡ 
ያቺ “አላህ ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ ኢንሻአላህ ደስ ይልሻል፡፡” ያለችኝ ሴት ትዝ አለችኝ፡፡
፨፨፨
“ወለሰውፈ ዩዕጢከ ረቡከ ፈተርዷ” የሚለዉን የቁርኣን አንቀጽ አስታወስኩ፡፡ ስለ አላህ አስብኩና በሀሳብ ርቄ ሄድኩ፡፡ የሱ ሥራ አብዝቶ ገረመኝ፡፡ እኛ ተስፋ እንቆርጣለን እንጂ እሱ ያዘጋጀልን ነገር አለ፡፡ እኛው ሁለት ልብ ሆነን ተቸገርን እንጂ በርግጠኝነት በአንድ ሆነን ልብ ይሠጠናል ብለን ብንለምነው ይሠጠናል፡፡ 
እኛው እንቸኩላለን እንጂ እሱ ለሁሉም ነገር መላና መፍትሄ አለው፤ ለሁሉም ነገር ምክንያትና ጊዜ አለው፡፡ ለአላህ ዉሳኔ መታገስና ፈረጃዉን መጠበቅ ትልቅ ዒባዳ ነው፡፡

እንኳን እኛ ነቢዩ ዘከርያም በልጅ እጦት ተፈትነዋል፡፡ “ጌታዬ ሆይ ብቻዬን አትተወኝ፡፡ …” ሲሉ ነበር ዱዓ ያደረጉት፡፡
ኢንሻአላህ ፈጣሪሽ ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ አንቺም አንድ ቀን ደስ ይልሻል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
“ቂሰሱን ሚነል ዋቂዕ” ከተሠኘ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡

@heppymuslim29
ንጉሡ ሁልጊዜ አዲስ ዓመት ሲመጣ እስረኞችን የመጎብኘት ባህል ነበረው። የተለወጡትንም ማለትም የታረሙ እስረኞችንም በምህረት የመፍታት ተግባር ያከናውናል።
በአንድ የዘመን መለወጫም እስረኞችን ሲጎበኝ ይህ ሆነ?

አንዱ እስረኛ "ንጉሥ ሆይ እኔ ፍፁም ጨዋ ነኝ በሀሰት ሰርቀሃል ብለው ነው ያሰሩኝ። ምህረትህ ይገባኛል"አለ...

ሌላኛው ደሞ"ንጉሥ ሆይ እኔ ደበደብኩት እንጂ አልገደልኩትም። ንፁህ ሰው ነኝ ምህረትህ ይገባኛል " አለ...

ሌላም እስረኛ "ንጉሥ ሆይ እኔ ጫፏን አልነኳኋትም ሳምኳት እንጂ ደፈረኝ ያለችው የሀሰት ቃል ነው እባክህ ፍታኝ" አለ...
አንድ እስረኛ ግን "ንጉሥ ሆይ እኔ እንኳ የሚገባኝን ነው ያገኘሁት የወንድሜን እምነት ማጉደል አይገባኝም ነበር" አለ።
ንጉሡም በሉ ይህንን እስረኛ ፍቱት አለ። ጥፋተኛ መሆኑን በማመኑም የንጉሱን ምህረት አገኘ።
***
ስህተትን አምኖ መቀበል ‼️

@heppymuslim29
ዳዕዋው ሴቶች በሴቶች ነው። የተሰጣትም ርዕስ ስለ ሰደቃ። በቁርአንና በሐዲስ እያዋዛች የተሰበሰቡትን ሴቶች ቀል አርጥባ እንደጨረሰች ታዳሚዎቹ ያላቸውን መስጠት ጀመሩ።
የገጠማትን ክስተት ከአንደበቷ እንስማው

"አንዲት ሴት ወደተቀመጥኩበት መጣችና የለበሰችውን የአንገት ጌጥ አውልቃ ልትሰጠኝ እጇን ዘረጋች። ዙርያው በአልማዝ የተጌጠና በዳይመንድ ያሸበረቀ ውድ ስለነበር ለመቀበል አንገራገርኩ። እርሷ ግን ውብ ጌጧን እንድቀበላት አስገደደችኝ"

ለየቲሞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለመሸፈን የሰበሰብነውን ጌጣጌጥ ይዘን ወደ መሸጫ ሱቁ አመራን። ሽያጩን የምንፈፅምለት የመስጂዱ ጀመዓ ስለነበር ዋጋ ተስማምተን አልማዙን ከወርቁን ለመነጣጠል ይፈለቅቀው ጀመር። በውስጡ የተጠቀለለ ነገር አገኘ። በአረበኛ ቃላቶች የተፃፈ ወረቀት ላይ ሲህር የተሰራበት ፀጉሯ ተጠቅልሏል። ምን ጉድ ነው ብለው እየተዓጀብን አስቤዛና አልባሳቱን ለየቲሞች አከፋፍለን ተመለስን።

ከሳምንት በኋላ ይህን ጌጥ ሰደቃ የሰጠችን ሴት አጠያይቃ ወደቢሮዬ ዘለቀች ሰላምታን ከተለዋወጥን በኋላ ስለራሷ እንዲህ በማለት መናገር ጀመረች
"በአላህ እምላለሁ ከባለቤቴ ጋር በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ከተኛን አስራ ስድስት ዓመታትን አሳልፈናል። የቤተሰባችን ፍቅርና ሰላም ተናግቶ የስቃይ ህይወት መኖር ከጀመርን ድፍን አስራ ስድስት አመታት ተቆጥረዋል። ይህንን ጌጥ ሰደቃ ከሰጠሁ በኋላ ግን ቤተሰባችን በአንድ ማዕድ ተሰብስቦ በፍቅር እራታችንን ተመገብን። ከባለቤቴም ጋር በደስታ አንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ተኛን ጌጡን በጣም ከምንዋደድ ጓደኞቼ የተሰጠኝ ስጦታ ነበር" አለችኝና ስቅስቅ ብላ አነባች።

የገዛ ጓደኞቿ ሲህር አሰርተው እሷንም ቤተሰቧንም ሲያናጉት እንደኖሩ በሰደቃዋ ሰበብም አላህ ሊፈውሳት እንደፈለገ ተረዳሁ። በእርግጥም ውድ ዋጋ ያወጣ ነበር።
"ጠላትህን አንድ ጊዜ ወዳጅህን ደግሞ መቶ ጊዜ ተጠንቀቀው" የሚለው አባባል በአይምሮዬ አቃጨለ" በማለት ገጠመኟን ትቋጫለች።

@heppymuslim29
አንድ ቀን አመሻሹ ላይ እናት የአብራኳን ክፋዮች በማስጠናት ላይ ተጠምዳለች። አጠገባቸው ተቀምጣ የተማሩትን ታስረዳለች። ታላላቆቿን ከማስጠናት እንዳታዘናጋት ለትንሽዬዋ ልጇ የስዕል ደብተር ሰጥታታለች።

በግቢያቸው ውስጥ ከዋናው መኖርያ ቤት ወጣ ብሎ ለብቻ ተገልሎ በተሰራው ክፍል ውስጥ አብረዋቸው ለሚኖሩት ለባለቤቷ አባት እራት እንዳልሰጠቻቸው በድንገት ታወሳት።

ፍጥን ብላ ተነሳች። ምግብ አዘጋጅታ በሳሀን አድርጋ ወሰደችላቸው። ሌላ የሚፈልጉት ነገር ካለ እንዲጠሯት ነግራ ወደልጆቿ ተመለሰች። ህፃኗ በተሰጣት ደብተር ላይ
ባማረ ውብ ገፅታ የተንቆጠቆጠ ግቢ ከነቤት ዲዛይኑ በእርሳስ መሳሏን ስትመለከት "ውዴ ምን እየሳልሽ ነው?" በማለት ጠየቀች።

ጥርስ በሌለበት ምድረበዳ ምላሷ ጉበት የሚመስለው "ቱክ ቱክ" እያለ ቃል ለማምረት በሚባትል አንደበቷ
"አድጌ ለወግ ማዕረግ ስበቃ የምኖርበትን ቤት ዲዛይን እየሳልኩ ነው" በማለት መለሰች።
"መኝታ ክፍልሽ የታል"
ህጻኗ እያንዳንዱን ክፍል አሳየቻት። ይህ መኝታ ቤት ይህ ደግሞ ወጥ ቤታችን ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ እንግዶችን እንቀበልበታለን እያለች የቤቱን ክፍሎች ዘረዘረች።

ከሳለችው ግቢ ውስጥ አንድ ገለልተኛ ክፍልን እናት አስተዋለች። "ይህ ክፍል ከቤቱ ውጭ ከሌሎቹ ክፍሎች ለምን ተነጠለ...?" አለች።

"ያንቺ ክፍል ነዋ። እማ እንደ ቅድመ አያቴ እንደ አባዬ አባት እዚህ ክፍል አኖርሻለሁ"

እናት ልጇ የተናገረችውን ማመን አቃታት። ደነገጠች። በህይወቴ መጨረሻ ቀሪ ዘመኔን የልጅ ልጆቼን ድምጽ ሳልሰማ በአራት ግድግዳዎች መካከል ብቻዬን ላሳልፍ? በማለት በትዝብት ራሷን ጠየቀች።

እየተጣደፈች ከቤት ወጣች። እጅግ ውብ እና ያሸበረቀው የእንግዶች ማረፊያ ክፍል ውስጥ ያለውን እቃ አወጣች። በግቢው ውስጥ ለብቻው ተገልሎ የሚኖረውን የባሏን አባት ወደዚህ ክፍል አዘዋወረች።

ባል ከስራ ሲመለስ ባየው ነገር እየተገረመ
"ደግሞ ምን ተገኘ?" በማለት ጠየቀ።
ሚስት እንባዋን እየዘረገፈች መለሰች፡- "እኔና አንተ አላህ እድሜ ከሰጠን ስናረጅ የምናርፍበት ክፍል ነው" አለች።

ባል ምን ለማለት እንደፈለገች ተረዳ። አባቱን በፀፀት አይኑ ሲመለከት ፈገግ እያሉ ግንባራቸውን ነቀነቁለት።

ህፃኗ እየሆነ ያለውን ስትመለከት እንደመሳቅ አለች። ከላይ ያለው ጥርሷ ከአካባቢው የለም። ደብተሯን አንስታ የተገለለውን ክፍል ከቤቱ ዲዛይን ላይ እያስወገደች ዳግም ፈገግ አለች።

"እንዳበደርከው ይከፈልሀል" ማለት ይህ ነው።

@heppymuslim29
አንዲት ሴት በአንድ ቁጭብሎ በሚጽፍ የአካል ጉዳተኛ አጠገብ አለፈች፤ ልጅ እግር ነው፡፡ ዝምብሎ ማለፉ ከበዳትና “ምን እየሠራህ ነው?” አለችው፡፡
“ጀነትን እየሳልኩ እና ክፍሎቿን እያበጃጀሁ ነው” አላት፡፡
ፈገግ አለች፡፡ እንዴት ልትረዳው እንደምትችልም አሰበች፡፡
“በቃ አንዱን የጀነት ክፍል ሽጥልኝ፡፡”
“እሺ”
“ዋጋው ስንት ነው?”
“ሀያ ሪያል ብቻ፡፡”
ብሩን ሠጥታው፤ ቁራጩን ክፍል ወስዳ ባደረገችው ነገር ዉስጧን ደስ እያላት ወደቤቷ ሄደች፡፡
ሌሊት ላይ ጀነት የገባች በሚመስል መልኩ ህልም አየች፤ በዚያች ቅጽበትም ቀን ላይ የሠራችዉን መልካም አስታወሠች፡፡
“ጀነት ገዛሁኝ!” አለች በልቧ፡፡ አሸቀች፡፡ በሐሴት ፈነደቀች፡፡
ጠዋት ላይ ከአካል ጉዳተኛው ጋር ስለገጠማት ነገርና ስለህልሟ ጉዳይ ታሪክ ለባሏ ነገረችው፡፡
እሱም ለኸይር ነገር ለመሽቀዳደም አስቦ ፈጠን ብሎ ልጁ ወዳለበት ሄደ፡፡
አሁንም ልጁ ቦታው ላይ ቁጭብሎ ስዕሉን እየሳለ አገኘው፡፡
“አንድ የጀነት ክፍል ፈልጌ ነበር፤ ዋጋው ስንት ነው?” አለው፡፡
“አይሸጥም” አለው ልጁ፡፡
“እንዴ ትናንት ባለቤቴ እኮ በዚህ በኩል ስታልፍ አንዱን ጀነት ክፍል በሀያ ሪያል ሽጠህለታል፡፡” አለው፡፡
“አዎ ግና ባለቤትህ እኮ ጀነትን በሀያ ብር ልትገዛ አስባ አልነበረም፤ ባይሆን ይህንን ልጅ በምን ላግዘው እንዴትስ ልርዳው ብላ ተጨንቃ ነው፤ ወንድሜ ጀነት ዉድ ናት፤ ዋጋዋ አይተመንም፡፡” አለው፡፡ ሰዉየው እያጉረመረመ ወደኋላ ተመለሰ፡፡

ስትጨርሱ በነቢያችሁ ላይ ሶለዋት አዉርዱ
@heppymuslim29
እንዴት ሰለምክ? በማለት ነበር ጋጤዘኛው የጠየቀው። አይኑን ሰበር አንገቱን አጠፍ አድርጎ አቀረቀረና ንግግሩን ጀመረ
 "የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1993 ከዕለታት በአንዱ ቀን ከባለቤቴ ጋር ለመዝናናት ራቅ ብለን ተጓዝን። ዛፍ ቅጠሉን ጋራ ሸንተረሩን እያቆራረጥን አንድ መንደር ስንደርስ መሽቶ ነበርና መመለሻው መንገድ ጠፍቶን እየኳተንን በርሀብ ነደድን። ከአላፊ አግዳሚዎቹ አንዱን የሚበላ ነገር የምናገኝበትን ደህና ሆቴል እንዲጠቁመን ጠጋ ብለን ጠየቅን። አለባበሳችንን ተመለከተና እንግዳ መሆናችንን አስተዋለ"ደህና ሆቴል የለም። ምግብ ቤትም ቢሆን በዚህ ሰዓት ዝግ ነው። ወደ ከተማ ለመመለስ ደግሞ መሽቷል። ሰዓቱ የጅብ ነው። ባይሆን ወደ እኔ ቤት እንሂድና ራታችሁን በልታችሁ ታርፋላችሁ። ጠዋት ሲነጋ መንገዱን አሳያችኋለው" አለን።

ወደ ቤቱ ወሰደን። አንዲት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ አስገባን። ጨለማ ነው። ትንሽዬዋ ጠረጴዛ ላይ ያለው ፋኖስ ይንቀለቀላል። አምስት ሕጻናትና ሁለት አዛውንቶችን ከአንድ ጥግ ተቀምጠዋል። ግርግዳ ማገሩን እያየን ቀለል ያለ መጠነኛ እራት አቀረበልን። በልተን ስንጨርስ "አንተና ሚስትህ እዚህ አልጋ ላይ በነፃነት እረፉ። እኔና ቤተሰቤ ሌላ ክፍል ውስጥ እንተኛለን" በማለት ተሰናበተን።

ለሊቱን በበቂ ሁኔታ ተኛን። ማለዳ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ነቃን። ላደረገልን መልካም ነገር ልናመሰግነው ከተኛንበት ክፍል ለባብሰን ወጣን። ሌላ ክፍል ግን አላገኘንም። አይኔን ወርውሬ ስመለከት ሰውየው አንዲት ዛፍ ላይ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ ቤተሰቦቹ ተጎዝጉዘዋል። ህፃናቶቹም ኩርምት ብለው ሽፋሽፍቶቻቸውን ከድነዋል።

ባለቤቴ በሁኔታው አለቀሰችች። በዚያ ቀዝቃዛ አየር እንዴት ለማያውቁት ሰው ውጪ ማደርን ምርጫቸው ያደርጋሉ። እስልምና ለእንግዳ ያለው ቦታ ገረመን።  "ይህ የምናየው እስልምና ከምንሰማው ፍፁም ይለያል" ተባባልን። ወደሰውየው እየተንጠራራሁ እስልምናን እንዴት ማወቅ እችላለሁ በማለት ጠየቅኩት።
"የቁርአን ትርጉምና  አንዳንድ መፅሐፎችን ገዝተህ አንብብ" አለኝ የዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተጋድሞ ቁልቁል እየተመለከተኝ።

ወደ ሀገሬ እንደተመለስኩ ስለ እስልምና ለማወቅ በርካታ መፅሐፍትን ሸማመትኩ። ለተከታታይ ሁለት ወራት በጥሞና ተቀምጬ አነበብኩ። ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን በእውነት መሰከርኩ። እኔን ምክንያት አርጎ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ። አሁን በሀገረ ሩማንያ እስላማዊ ማዕከል እየገነባሁ ነው።  እስልምናን በአለም ላይ ለማስፋፋት ኢንሻ አላህ እተጋለሁ።

ወዳጆቼ በመልካም ስነ ምግባር ዳዕዋ ማድረግ ይሉሀል ይህ ነው።
@heppymuslim29
የዙሁር ሰላት ወቅት ከመድረሱ በፊት አንዲት አሮጊት
ውዱዕ ስታደርግ ተመለከትኩኝና አዛን አለ እንዴ
ብዬ ጠየኳቸው ...
እሳቸውም "እኔ ወደ ጌታዬ ሳይጠራኝ ነው ምሄደው"
ብለው መለሱልኝ...ይላሉ ይብኑል ጀውዚ ረሂመሁሙላህ

ሁሌም አዛን ከማለቱ በፊት ለሰላት እንዘጋጅ!
የስኬታችን መሰረቱ እሱ ነውና ሰላትን ስናስተካክል
ስኬታችን ያምራል!😊

@heppymuslim29
አንድ ጓደኛዬ እየነገረኝ እህቴ ከ ባሏ ጋር በጣም የከረረ ጸብ ይጣሉ እና መፋታት ይወስናሉ፤ ብዙ ተለምና እምቢ አለች ቤተሰብም ከ ጉዳዩ ክብደት አንጻር ምንም ሊጫናት አልፈለገም እና ውሳኔዋን አክብሮ ተቀብሏል። ቤቱን ትታ እኛ ጋር ስለገባች ሽማግሌዎች እቤት እየተመላለሱ ቢያስጨንቋትም ምንም ሀሳቧን ሊያስቀይሯት አልቻሉም፤ ሁሉም ተስፋ ቆረጠ እንደሚፋቱ እርግጠኛ ሆንን። ከዛም እነዛ የማይሰለቹ ሽማግሌዎች ድጋሜ መጡ የተለመደ ወሬያቸውን እያወሩ  በመኃል በመካከላቹ ለነበረው ጥሩ ጊዜ ስትዪ ይቅር በዪው አሏት እሷም ያጠፋው ጥፋት ያን ሁሉ ገደል ይከታል አለቻቸው ድንገት ባሏ " የ አባትሽ ለቅሶ ጊዜም ያደረኩት?" አላት ዝም አለች ሁሉም መልሷን እየጠበቀ ነበር ዝምታዋ ሲረዝም ጨነቃቸው መልሺልኝ ዝም አትበይ ሲላት ይቅር ብዬካለው አለችው። በጣም ተገረምኩ በ ደስታ ተነስቶ አቀፋት ሽማግሌዎቹም ዱዓ አድርገውላቸው ሄዱ አለችኝ  በጣም ገረመኝ ሰዎች ዘንድም አላህ ዘንድም እንደዚህ ሽማግሌ የሚሆኑን ስራዎች ሊኖሩን ይገባል ባል ምን እንዳደረገላት ከ ሁለቱ ውጪ ማንም አያውቅም ግን ምንም ይሁን ከዚ ቀን አውጥቶታል።

@heppymuslim29
2024/05/21 13:51:06
Back to Top
HTML Embed Code: