👉 በነዚህ ውድ ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀሙ ታላላቅ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ተክቢራ ነው። አላህ በቁርአኑ መልእክተኛው በሀዲሳቸው ተክቢራ በማለት ላይ ከመጠቆምና ከማመላከት ውጪ ይህን ተክቢራ ይበል በሚል የመጣ የተክቢራ አይነት የለም። ስለዚህ አንድ ሰው በየትኛውም አላህ ማላቂያ ተክቢራ ማድረግ ይችላል። ነገር ግን ከቀደምት የዲን ሊቃውንቶች ከሰለፎቻችን የተገኙ የተክቢራ አይነቶች አሉ። እነሱን መጠቀም ግን የተሻለ ይሆናል። ከነዚህ ተክቢራዎች መካከል፦
①) አንደኛ
«الله أكبر، الله أكبر، لاإله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر ، ولله الحمد»
♦️ኡመር፣ አልይ፣ ኢብኑ መስኡድ፣ አቡሀኒፋ፣ ሰውርይ፣ ኢስሀቅ፣ ኢብኑ ተይምያ፣ ኢብኑ ረጀብ ሸኽ አልባንይና ኢብኑ ኡሰይሚን ይህንን መርጠዋል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
②) ሁለተኛ
«الله أكبر كبيرًا، الله أكبر كبيرًا، الله أكبر وأجل، الله أكبر ولله الحمد»
♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። ኢብኑ አቢሸይባ መርጦታል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
③) ሶሰተኛ
«الله أكبر كبيرًا، والحمد لله كثيرًا، وسبحان الله بكرة وأصيلا»
♦️ኢማሙ ሻፍእይና ኢማሙ ነወውይ መርጠውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
④) አራተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله، والله أكبر، ولله الحمد»
♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
⑤) አምስተኛ
«لا إله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد".»
♦️ኡመርና ኢብኑ መስኡድ ብለውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
⑥) ስድስተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر»
♦️ከኢብኑ አባስ፣ ከኢማሙ ማሊክና ሻፍእይ ተወስቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
⑦) ሰባተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر كبيرًا ".*»
♦️ከሱፍያን ተወርቷል። ኢብኑ ሀጀር መርጦታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ*
⑧) ስምንተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد، الله أكبر وأجل، الله أكبر على ما هدانا»
♦️ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል።
➡️ በተገኘ አጋጣሚ እየቀያየርን በሆነ ጊዜ አንዱ በሌላ ጊዜ ሌላውን መጠቀም እንችላለን።
@heppymuslim29

ሐጀር ወንድ ልጅን በሰላም ተገላግላ የአራስነት ጊዜዋን በቅጡ ሳትጨርስ የነቢዩላህ ኢብራሂም የመጀመርያ ሚስት ሳራ የቅናት መንፈስ አደረባት። አዲሱን ልጅ ከነሚስቱ ራቅ ወዳለ በረሀ ጥሏቸው እንዲመጣ አዘዘችው።
ኢብራሂም ሐጀርንና ኢስማዒልን ይዞ በረሀውን እየሰነጣጠቀ ጉዞ ማድረግ ጀመረ። ከዕልህ አስጨራሽ አድካሚ ጉዞ በኋላ ከምድረ በዳው የዐረብያ ምድር ምንም የሚላስ የሚቀመስ ከሌለበት ተራራ ስር የያዘውን ስንቅ አስቀምጦላቻው ወደ መጣበት ሊመለስ እግሩን አነሳ። "ውሀ እንኳ በሌለበት በዚህ በረሀ ትተከን ለመሄድ ስትነሳ በራስህ ወይስ አላህ አዞህ?" በማለት ጠየቀች ሐጀር።"ከአላህ ታዝዤ" አላትና ዱዓ አድርጎ ወደመጣበት ተመለሰ
ሐጀር ኩርምት ብላ ከበረሐው መሀል ከተመች። አየሩ በጣም ሞቀታማ መሬቱም በንዳዱ ግሏል። የያዘችውም ውሀ አልቆ ጥም አቃጥሏታል። ወደ ሆዷ ያስገባችው ፈሳሽ ባለመኖሩ በአንቀልባዋ የታቀፈችው ልጇ ከጋቷ የወተት ጠብታ ጠፍቶ ረሀቡን መቋቋም አቅቶት እያመረረ ይጮኻል። እናት በጀርባዋ እያዘለች ሌላ ጊዜም በደረቷ እያቀፈች ለቅሶውን እያባበለች በሐዘን ተከዘች።
ልጇን ከድንኳኑ አስተኝታ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሯሯጥ ሰፋ እና መርዋ በተባሉ ተራራዎች ጫፍ ወደሚገኝ ሸለቆ መሐል ደረሰች። ውሀ ፍለጋ በተስፋ እየሮጠች ወደ ሰፋ ተራራ ወጣች ግና አላገኘችም። ወደ ሸለቆው ወርዳ መርዋ ተራራን እየሮጠች ወጣች እርጥበት እንኳ የለም። ከሰፋ ወደ መርዋ ተራራ ለ7 ግዜ ውሀ ፍለጋ በሩጫ እየተመላለሰች ድካሟን መቋቋም በማትችለው ሁኔታ ላይ ደረሰች። ጉሮሮዋ ደረቀ። ውሀ ፍለጋ ዳገት መውጣት ተሳናት። ልጇን ወዳስቀመጠችበት ቦታ አቀናች።
ህፃኑ እያለቀሰ ሲፈራገጥ በእግሩ መሬቱን ሲጭር ከመሬቱ ውሀ ፈልቆ ተመለከተች። ውሀውን ጠጥታ ልጇን አጥብታ ለአላህ ምስጋናዋን አደረሰች።
በውሀ ጥም ተቃጥለው ያንን በረሀ የሚያቋርጡ ነጋዴዎች በድንገት ምንጩን ተመለከቱና ከውሀው በክፍያ ታስጎነጫቸው ዘንድ ለመኗት። ከውሀው ፈቅዳላቸው በምትኩ ተምር ተቀበለቻቸው።
በውሀ ችግር የሚታወቀው የዐረብያ ምድር በሀጀር ምክንያት በፈለቀው የውሀ ምንጭ ወሬው ተጥለቀለቀ። የተለያዩ የዐረብ ነገዶች ከሀጀር አቅራቢያ እየሰፈሩ ቤታቸውን ቀለሱ። አካባቢውንም ገነቡ።
የማወጋችሁ ስለመካ ነው

Copy!!
አረፋህ ሊመን አረፈህ!
ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።
ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!
ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ
ጠዋት
ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!
ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአን፣ተህሊል፣ተህሚድ በአጠቃላይ በዚክር ማሳለፍ(አዝካረ ሰባህ ሳይረሳ)
ፀሀይ ስትወጣ የፀሃይ መውጣትን ሰላት እዛው ከመስገጃችን ሳንነሳ በመከወን ከረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሀጅ የማድረግን ምንዳ እንጎናጸፍ
ለቀን ኢባዳ ያግዘናል ብለን ካሰብን መጠነኛ እኝቅልፍ እንተኛ። ስንነሳ በትንሹ 4 ረክኣ ሰላተ ዱሃ እንስገድ!
ከሰአት
ከዝሁር ሰላት በኋላ ቁርዐናችንን እንቀራለን። የአረፋ ኹጥባ(ከመስጂደ ነሚራህ የሚተላለፈውን) መልእክት በጥብቅ መከታተል
ልባችንን ሊያረጥብ የሚችል መፅሐፍ ወይም ቪድዮ እንመልከት
ከአስር ቀጥሎ እንዲሁ በቁርአን እና በዚክር መግሪብ 1 ሰአት አቅራቢያ እስኪቀረው ማሰለፍ!
የእለቱ ወሳኝ ሰአት ይህ ነው።
የተሰበረ የሚጠገንበት፤ የታመመ የሚፈወስበት፤ ተስፋ የቆረጠ ተስፋው ነፍስ ሚዘራበት ድንቅ ሰአት!
ዱኣ!!! ዱኣ ብቻ!
በዚህ ቀን ከእሳት ነፃ አለመባል ኪሳራ ነው።
"አረፋ ተራራ ላይ መቆም ያልቻለ
አላህ ያሳወቀው ድንበር ላይ ይቁም
ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ያልቻለ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ይደር...ያቀርበዋልና!
ሚና ላይ እርዱን መከወን ያልቻለ
ምኞቱን ይረድ! ከፍ ይላልና።
ወደ ቤቱ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለ
ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ይከጅል!" ኢብኑ ረጀብ

9ኛው ቀን /ዐረፋ
ከሐጅ ቀናት ሁሉ ትልቁ እና ዋናው ነው። "የዐረፋ ቀን" በመባልም ይታወቃል። በዚህ ቀን ሐጃጆች በተከበረው የዐረፋ ኮረብታ ላይ በመቆየት ዱዓእ ሲያደርጉ ይውላሉ። ዐረፋ ላይ ላልተገኘ ሑጃጅ ላልሆነ ሰው በፆም መዋል ይወደዳል።
ቀኑ ታላቅ ቀን ነው። ቀኑን መፆምም ትልቅ ምንዳ አለው። " ከአላህ ዘንድ የሁለት ዓመት ኃጢአትን ያሰርዛል ብዬ አስባለሁ ።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛﷺ
ዙል-ሂጃ 9 የነገው ቅዳሜ ነውና ዕለቱን
በፆም፣በዚክርና መልካም በተባሉ ስራዎች
እናጅበው።

አስላሙ አሌይኩም ያጀመዓ
አንድ Giveaway ለቤተሰቦች አዘገጅተናል ስጦታውም የአንድ ዓመትወንጀላችሁን እና የወደፊት የአንድ ዓመት ወንጀልን ነገን በፆም ከሰለፍን የምናገኘው ስጦታ ነው በመቀጣል ሱቢህን ዛሬን ሰግደን ሊነገጋ አከባቢ ላይ ሁለት ረካ ብቻ ከሰገድን ተናፋቅውን መካ መዲና ሄዳን ሀጅ እንደደረግን ይቆጣረል እና ከዚህ የበለጠ ስጦታ አለ ወይ🙄🎁
አንድ Giveaway ለቤተሰቦች አዘገጅተናል ስጦታውም የአንድ ዓመት
ይህን👇👇👇👇👇ዱዐ
: لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيئ قدير
በጣም አብዝተህ በለው ምክንያቱም የዐረፋ ቀን ከሚባሉ ዱዐዎች ሁሉ የሚበልጥ ዱዐ ነውና
በዱአቹ አትርሱኝ

በአላህ መንገድ ሲታገል ከርሞ ወደ ኮርዶቫ ሲዘልቅ ዕለቱ ዒድ አል አድሀ ጠዋት ነበር። ሙጃሂዶቹ በፈረሶቻቸው ጀርባ ላይ ተፈናጠዋል። በድካም የሚንጠፈጠፈውን ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠራረጉ አቧራና ደም ባጨማለቀው ልብሳቸው ወደ ኢድ መስገጃው ሜዳ በማቅናት ላይ ሳሉ እድሜዋ የገፋች አዛውንት ከሡልጣን መንሱር ፊት ቆማ የፈረሱን ልጓም ይዛ ከመንገዱ በማስተጓጎል እንዲህ ያለችው:-
"በዛሬው የዒድ ቀን ከእኔ በቀር ሁሉም ሙስሊሞች ደስተኞች ናቸው"
ሐጂብ መንሱር ንግግሯን ሲሰማ ደነገጠ "ለምን?" ሲልም ጠየቀ።
ዕንባ ባቀረረው ዓይኗ እየተመለከተችው እንዲህ አለችው "በረባህ ምሽግ ከመስቀል ጦረኞች ጋር ሲፋለም የተማረከ አንድ ፍሬ ሙጃሂድ ልጅ አለኝ እሱ በጠላት እስር ቤት ውስጥ ሆኖ እንዴት መደሰት ይቻለኛል?"
ሐጂብ ንግግሯን ሲሰማ ፊቱን ወደሠራዊቱ አዞረ። የፈረሱን ልጓም አጥብቆ ያዘና በጂሃድ ሜዳ የአፈር ትቢያውን ገና ላላራገፈው ሙጃሂድ፣ ከድካም ጀርባውን ላላሳረፈው ሠራዊት "ከፈረሳችሁ ላይ እንዳትወርዱ" በማለት ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የፈረሱን ልጓም እየጎተተ ጀርባው ላይ እንደተፈናጠጠ ወደ ረባህ ምሽግ ሰራዊቱን ይዞ ገሰገሰ። የአሮጊቷን ልጅ ጨምሮ ሙስሊም እስረኞችን አስፈትቶ ከተማዋን በድል ከፍቶ ተመለሰ።
ዒዱኩም ሙባረክ

"አንቺ ልጅ ወዴት ነው ጥድፊያው?"
"እማ መድረሣ ነውዋ!"
"በዛሬ ቀን? እቤት ያሉት እንግዳስ ነይ ጊቢ አሁን....." እናት ተቆጣች።
"ምንድነው ምትጨቃጨቁት? እቤት ሰው ተቀምጦ የለ ኧረ አደብ ያዙ ሴቶች" አባት ፊቱን አጨፈገገ።
"ታዲያ ልጅህን ቅጣ እንጂ እንደ አሮጊት ተሸፋፍና መድረሣ መድረሣ ስትል"...
"ዝም ስንልሽ ጭራሽ ባሰብሽ አይደል እንደውም ከዛሬ ጀምሮ አትሄጅም ለወትሮም ለእውቀት ሣይሆን ስራ ላለመስራት ነበር... እንደውም ሂጂ ከእንግዶቹ ፊት ቡና ቁይላቸው!!"
"የፈለጋችሁትን ብላችሁ ብታዙኝም ከጌታዬ መንገድ ግን ልታርቁኝ አትችሉም" እንደ ሁል ቀኗ አባሽ ያጣው እንቧዋን እየጠረገች መንገዷን ቀጠለች.....
.
.
.
.
ይገርማል! ልጆች ወደ እውነተኛው መንገድ በመሄድ ላይ ሣሉ ወላጆች እንቅፋት ሲሆኑባቸው። እንደው እንኳን ከመጥፎ መንገድ አርቀው ፤ ቀጥተኛው መንገድ መምራቱን ባይችሉ፤ በልጆቻቸው ቀናው መንገድን ቢመሩ ምነኛ ያማረ ቤተሰብ ይኖር ነበር።

ለአንድ ጥበበኛ "እገሌ እኮ መብረር ይችላል" አሉት። "ምኑ ይገርማል ታዲያ ከርሱ ያነሱት እን ዝንብ እና ትንኝ ሁሉ ይበሩ የለም እንዴ!" በማለት አጣጣለባቸው። "እንትና እኮ ውሃ ላይ መሄድ ይችላል ።" አሉት። " ምኑ ይገርማል ታዲያ ቁራጭ ጣውላም ባህር ውሃ ላይ ቢጥሉት አይሰጥምም ውሃ ላይ ይሄዳል እኮ" አላቸው።
.
"እንግዲያውስ ባንቱ እይታ ገራሚው ነገር ምንድነው? " አሏቸው። " እጅግ አስደናቂው ነገር ሰዎች የያዙትን ዓላማና መርህ ሳይለቁና ሳይስቱ በከባድ ፈተናዎች መሃል ከሰዎች ጋር መኖር ፣ አለመዋሸት፣ አለመስረቅ፣ አለማታለል፣ እምነት ለጣሉብህ መታመን ፣ የተማመኑብህን አለማሳፈር፣ ሰዎችን በየትኛውም መልኩ ቀልባቸውን አለመስበር....
እጅግ አስደናቂው ነገር ይህ ነው !!!

በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ ሶማሊያዊት ሙስሊም ሴት እርዳታን ለማግኘት ወደ አንድ ድርጅት ደወለች። አምላክ የለም በሚለው እምነቱ የሚታወቀው ሰው የስልኩን እጀታ አነሳና አዳመጣት። ፋጡማ ቤቷ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩን በመንገር ለችግሯ መፍትሄ እርዳታ ያደርግላት ዘንድ ተማፅና ቁጥሯን እና አድራሻዋን ሰጥታ ስልኩን ዘጋችው።
ምግብና ሌሎች እርዳታዎች ተዘጋጅተው ወደ አድራሻዋ እንዲያደርስ ለግል ጸሃፊው መመሪያ ሰጠ። እንዲህም አለ፡- "የእርዳታውን ምንጭ ከጠየቀችሽ ከሸይጣን የተሰጣት ስጦታ መሆኑን ንገርያት" በማለት ሴትየዋ ላይ እየተሳለቀ አዘዛት።
ፀሐፊዋ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ሸክፋ ወደ ሴትየዋ ቤት አቀናች። ምስኪኗ ሴት በደስታ እያነባች የተላከላትን ተቀብላ ወደ ውስጥ ለመግባት በመራመድ ላይ ሳለች ጸሃፊዋ "የዚህን እርዳታ ምንጭ ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊምን?" ስትል ጠየቀቻት። ይህች ማንበብና መጻፍ የማትችል ሙስሊሟ ፋጡማ የሰጠችው ምላሽ እምነት አልባውን ዶ/ር ቲሞሲ ቬንተርን አስተሳሰብ ቀይራ እስልምናን እንዲቀበል አደረገው ስሙንም ዐብዱልሀኪም ሙራድ ብሎ እንዲሰይም አስገደደው። ምላሿ ይህ ነበር፡-
"ለማወቅ አልፈልግም ማንነቱም ግድ አይሰጠኝም። ጌታዬ አላህ አንድን ነገር ከፈለገ ሰይጣኖች እንኳ ቢሆኑ ይታዘዙታልና"

~«ለምንድን ነው እስካሁን ያላገባሽው? ምንድን ነው እንደ ዘልዛላ ሴት የምተሆኚው ሴት ልጅ ከደረሰች የግድ ማግባት አለባት። ለምን በእድሜሽ ትቀልጃለሽ! ትዳር ይዘሽ ለምን አትሰበሰቢም?» አላት።
እሷም፦―ልክ ነህ እኮ ግን እይ እነዛ ታናናሽ ወንድምና እህቶቼ ናቸው። ልጅነታቸው ብዙ የሚያስቦርቃቸው አየሀቸዋ ሲጫወቱ። እንደምታየን በኑሯችን ደከም ብለን ነው የምንኖረው። አየሀት ይህቺ ቤት ተከራይተን ነው የምንኖርባት። ወላጆቼ ጤና ከራቃቸው ሰንበትበት ብለዋል። እነዚህ ነፍሶች ሁሉ እገዛዬ ያሻቸዋል። ስለነሱ መኖር ነው እያኖረኝ ያለው። ስለኔ መኖር ብጀምር ምን የሚሆኑ ይመስልሀል? ግዴለም ማወቅ አይቻልህም! የተቸገሩ ቤተሰብ ያላትን ሴት እስከነ ቤተሰቧ የሚቀበል ስንቱ ነው? ተወው እሱንም! እሺ የሆነው ይሁን ብሎ ያገባኝ በኋላ ላይ ቤተሰቦቼን አይናችሁ ላፈር ቢል ምንድን ይወጠኛል? የባል ሀቅ ባለመወጣት ልከሰስ ወይስ የወላጆችን ሀቅ በማጉደል ልቀጣ?..እውነት ነው ትዳር ያስፈልገኛል! ቤተሰቦቼስ መኖር አያስፈልጋቸውም? ወንድምና እህቶቼስ ተስፋቸውን ማጣት አለባቸው? በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ ሴትነቴ ትዳር የሚቀበል ይመስልሀል?
«ግን አኮ…»
" ግዴለህም እኔን ሆነህ ኖረህ ስለማታውቅ አትረዳኝም "
ከራሳቸው ደስታ በላይ የቤተሰቦቻቸውን ደስታ ባስቀደሙ ላይ የ አላህ ሰላም እና እዝነት በ እነሱ ላይ ይሁን!

ታላቁን ኢብኑ ሲሪንን ታውቃላችሁ አይደል?
ሙሉ ሀብቱን ባጣ ጊዜ ሰዎች «ከባድ ኪሳራ ነው የደረሰብህ!» አሉት።
«ይህ ከ40 ዓመት ጀምሮ ቅጣቱን ስጠብቅለት የኖርኩት የሠራሁት ወንጀል ዉጤት ነው።» አላቸው።
«ምንድን ነበር የሠራኸው ወንጀል?» አሉት።
« አንድን ሰዉዬ "አንተ ድሃ!" በማለት አሸማቀቅኩት። ይኸው ዛሬ ከአርባ ዓመት በኋላ እኔም ድሃ ሆንኩ። » ብሎ መለሰላቸው።
በሆነ ነገር ሰዎችን አታሸማቅቁም ወይም አታነዉሩም ያ ነገር የደረሰባችሁ ቢሆን እንጂ።
ተጠንቀቁ! አትመፃደቁ! እሺ።

ምርጧ ፋጢማ የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ቆንጆዋ ልጅ፤ በመልክም፣ በፀባይም በአካሄድም ጭምር ቁርጥ አባቷን ትመስል ነበር ይባላል፡፡ ትህትናዋና ደግነቷ በዝቶ ይወራላታል፡፡ ለአጎታቸው ልጅ ለደጉ ዐሊ ረ.ዐ. በእጃቸው የዳሯት ተወዳጇ ፋጤ ከርሣቸው ወደ አኺራ መሸጋገር በኋላ ምድር ላይ የቆየችው ለስድስት ወራት ብቻ ነበር፡፡ ከርሣቸው ልጆች መካከልም ወደኋላ የቀረችው እሷ ብቻ ነበረች፡፡
ነቢዩ ﷺ ልጃቸው ፋጢማን አብዝተው ይወዷታል፤ እንደ አባት ቅርባቸው፣ እንደ ልጅ ሚስጢረኛቸው ነበረች፡፡ በልዩ ሁኔታ ያዩዋታል፣ ተነስተው ሁሉ ይቀበሏታል፣ ከጎናቸው አስቀምጠው ያወጓታል፤ እርሷም እጅግ እጅግ ትወዳቸው ነበር፡፡ ሊሞቱ አካባቢ ጭምር በቅርቡ ወደኛ ትመጪያለሽ ብለው በጆሮዋ ሹክ ብለዉላታል፡፡ እርሷም ሳቀችም አለቀሰችም፡፡ ሳቋ ወደርሣቸው በቅርቡ የምትሄድ በመሆኗ መደሠቷን፤ እንባዋ ደግሞ እርሣቸው ተለይተዋት ሊሄዱ በመሆናቸው ማዘኗ ነበር፡፡
በበኩሌ ፋጢማ እነዚያን ከርሣቸው ተለይታ የቆየችባቸዉን ወራት እንዴት አሳልፋ ይሆን የሚለዉን ነገር ሳስብ ጭንቅ ይለኛል፡፡ ኢማም ዘሀቢ ሁኔታ “ፋጢማ ከርሣቸው መለየት በኋላ በቁሟ እየሟሟች አለቀች፡፡” በማለት ይገልፁታል፡፡
አንዳንድ ሰው ዱንያን ለቆ ከጎናችን ተነጥሎ ሲሄድ ብቻዉን የሚሄድ አይምሠላችሁ፡፡ ሩሓችን ይዞ የሚሄድ አለ፤ ቀልባችንን ይዞ የሚሄድ አለ፤ ጉልበታችንን፣ ተስፋችንን፣ ብርሃናችንን፣ ደስታችንን ይዞ የሚሄድ አለ፡፡የአንዳንድን ሰው ሐዘን በመፅናናት አይሻገሩትም፡፡ እያደር ይቆረቁራል፡፡
የአንዳንድ ሰዉን ቦታ ማንም ምንም አይሞላዉም፡፡ ነቢዩ የዕቁብ አሥራ አንድ ልጆች ነበሯቸው ግና ስለ ዩሱፍ እንዳዘኑ እንደተከዙ ዐይናቸው ጠፍቷል!!

«የ እዝነት ጥግ……»
መልዕክተኛው ኑህ ለበርካታ ምዕተ ዓመታት የሰበኩት ሕዝብ ጥሪያቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም። ተስፋቸው ሟሸሸ። በመጨረሻም መቅሰፍት ወርዶ ዓለም እንድትጠፋ ከጌታቸው ጋር መከሩ። መቅሰፍቱ ሊወርድ 40 ዓመት ሲቀረውም ኻሊቅ አንድ ውሳኔ አሳለፈ።በምድር ላይ ያሉ ሴቶች ኹሉ ማህፀናቸው እንዲደርቅ ሆነ።ፅንስ መቋጠር ሳይችሉ 40 ዓመት ሙሉ ቆዩ።መቅሰፍቱም ወርዶ ዓለም ድምጥማጧ ጠፋ። (ጥቂት አማኞች ሲቀሩ) በጊዜው ግን ዓለም ላይ ህፃን ሚባል አልነበረም ሁሉም ከ40 ዓመት በላይ ነበር።
ከሚያጠፋቸው ህዝቦች ላይ እንኳን እዝነቱ አልተለየም!

አንዲት እናት ለሴት ልጇ ፦ ስትራመጂ እግርሽ የት ላይ እንደሚያርፍ እያስተዋልሽ ተራመጂ።" ስትል መከረቻት።
ልጅቷም "ማማ አንቺም ስትራመጂ ጥንቃቄ አድርጊ! እኔ ያንቺን እርምጃ ነው የምከተለው።" ብላ መለሰችላት።
እራስሽን አስተካክይ ልጆችሽ አንችን አርዓያ አድርገው ይከተሉሻልና።
@heppymuslim29
ልጅቷም "ማማ አንቺም ስትራመጂ ጥንቃቄ አድርጊ! እኔ ያንቺን እርምጃ ነው የምከተለው።" ብላ መለሰችላት።
እራስሽን አስተካክይ ልጆችሽ አንችን አርዓያ አድርገው ይከተሉሻልና።
@heppymuslim29
መለኩል መውት የሱለይማን ኢብኑ ዳውድ ዐለይሂሰላም በውብ ሰው ገፅታ እየመጣ የሚዘይራቸው የቅርብ ወዳጅ ነበር
ታድያ በአንዱ ቀን ሱለይማን አለይሂሰላም ከሹማምንታቸው ጋር ተሰብስበው ሳሉ ለመዘየር ጎራ ብሎ ይወጣል። ከሹማምንቶቹም አንዱ አንተ የአላህ ነብይ ሆይ አሁን የመጣው ሰው ማን ነው? ብሎ ይጠይቃቸዋል። ለምን ጠየከኝ ? ቢሉት" የሚያስፈራ አስተያየት ሲያየኝ ነበረና ነው...እንደው ማንነቱን ባውቅ" አለ።
ሱለይማንም እንግዳው መለከል መውት መሆኑን ሲነግሩት በፍርሀት እየተርበተበተ በአላህ ይሁንብህ ንፋስን እዘዛትና ራቅ ወዳለ ወደ ህንድ ሀገር ርቄ መኖርን እሻለሁ አለው። "ለመሆኑ በመራቅህ የአላህን ቀደር የምትቀይር መሰለህን? ቢሉትም መለከል መውትን ያየሁበት አካባቢ መኖርን አልሻምና ህንድ እንድሄድ በጌታዬ እጠይቅሀለሁ ብሎ ተማፀነ።
ሱለይማንም ፈቅደውለት ከህንድ ሀገር ይዘልቃል።
•°•በነገው ዕለት መለከል መውት ወደ ሱለይማን ይመጣና ኸበሩን ይነግራቸው ጀመር
•°•"ያ ሱለይማን ትላንት አንተ ጋር ስመጣ በህንድ ሀገር ሩሁን እንዳወጣው የታዘዝኩት ሰው ካንተው ጋር ሳየው ተገርሜ ሳማትር ነበር። ግና ወደ ህንድ የጌታዬን ትዕዛዝ ለመፈፀም ስጓዝ እዛው እየጠበቀኝ አገኘሁት!!"
سبحان الحي الذي لا يموت

የአሥራ ሰባት ዓመት ወጣቱ ሶሓባ ሓሪሣ አንድ ቀን ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ዛሬ ትክክለኛ ሙዕሚን / አማኝ/ ሆኞ አደርኩኝ ’ አላቸው፡፡
ታላቁ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘ እንዴት ባክህ ያ ሓሪሣ ! እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ ?’ በማለት ጠየቁት ፡፡ ወጣቱም ሁኔታዉን ሲያብራራ እንዲህ አለ ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ለሊቱን የአላህ ዐርሽ ቀርቦ የታየኝ መሰለኝ፡፡ የጀነት ሰዎች በጀነት ኒዕማዎች ( ፀጋና ድሎቶች ) ሲደሰቱ፤ የጀሀነም ሰዎች ደግሞ ከጀሀነም አሰቃቂ ቅጣት ሲጯጯሁና ሲያለቅሱ እሪታቸዉን ሲያቀልጡ የታየኝ መሠለኝ፡፡ እናም በዚህን ጊዜ አንድ ነገር ወሰንኩኝ፡፡ ለሊቱን በቂያም ( በሰላትና በዱዓዕ በመቆም ) ቀኑን ደግሞ በሲያም (በፆም) ማሣለፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ። ’
ነቢያችንም ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘ሓሪሣ ሆይ ! ለሌሎች ሰዎች ያልታየ ነገር በርግጥ ታይቶሃል፡፡ ሌሎች ሰዎች ያልተረዱትንም ነገር ተረድተሃል፡፡ በዚሁ አቋምህ እንድትፀናና እንድትዘወትር እመክርሃለሁ ፡፡ ’ አሉት
ሓሪሣ ለራሱና ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይህ ወሰለም በገባው ቃል ላይ ረግቶ የዱንያ ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከእውነተኛና ጠንካራ የአላህ ባሪያዎች መካከልም ሆነ፡፡ በበድር ዘመቻ ጊዜ ሙስሊሞች ትንሹን ቁጥራቸዉን ከመጥፋት ለማዳን ብለው ከመካ ሙሽሪኮች ጋር ፍልሚያ ሲገጥሙ ሓሪሣ ገና በአሥራ ስምንት አመቱ የጦርነቱ ተካፋይ ለመሆን ቻለ። በፍልሚያው ላይ እያለም ከየት እንደተላከች ያልታወቀች አንዲት ቀስት እየበረረች መጥታ ሓሪሣ አንገት ሥር ተሰነቀረች፡፡ ሓሪሣም በዚሁ ሸሂድ ሆነ ። የሰማእትነትን ክብር ተጎናፀፈ፡፡”
የበድር ጦርነት በሙስሊሞች የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡ የልጇን ሰማእትነት የሰማችው የሓሪሣ እናት ከፍልሚያዉ ማብቂያ በኋላ ወደ ነቢዩ እየገሰገሰች መጣችና ‘ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! ልጄ የት ነዉ ያለው?! ’ ስትል አስጨንቃ ያዘቻቸው፡፡ ‘ ያ ረሱለላህ ! የት እንደሆነ ይንገሩኝ የጀነት እንደሆነ ልደሰት የጀሀነምም ከሆነ መርዶዬን ልስማ ! ’ አለቻቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ሰላላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሓሪሣ እናት ሁኔታ በመገረም ‘ የሓሪሣ እናት ሆይ ምን ነካሽ? ምነው ምን አገኘሽ? በጤና አይደለሽም እንዴ ! ’ ካሏት በኋላ ‘ የሓሪሣ እናት ሆይ ! ሓሪሣ ያገኘው ጀነት ብቻ አይደለም ጀነቶችን እንጂ፡፡ ሓሪሣ ያገኘው ከጀነት በደረጃ ትልቅ የሆነዉን ጀነት አል-ፊርደዉስን ነው፡፡ ’ አሏት ።
ሸይኽ ኻሊድ አር-ራሺድ እንደተረኩት

ታላቁ ሌባ በሚል ስያሜው ድፍን ሃገር የሚያውቀው አንድ ሌባ ነበር። ታዲያ ታላቁ ሌባ የሌብነት ተግባሩን ሊፈፅም አንድ ቤት በር ላይ ደርሷል፣ አዩኝ አላዩኝ በሚል ዙሪያ ገባውን አማተረና ማንም እንዳላየው ሲያረጋግጥ ወደ ዛ ቤት ዝው ብሎ ገባ። ዳሩ ቤቱ ኦና ነው። ሚዘረፍ አንጡር ሃብት ይቅርና ሚላስ ሚቀመስ ያለበት እንኳን አይመስልም።
«ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል » እንዲሉ ሌባው ላመል ልሸው የምወጣው ባገኝ ብሎ ቤቱን ሲመነቃቅር የቤቱ ማዕዘን አቅራቢያ ሆነው ሲሰግዱ የነበሩት የቤቱ ባለቤት ሶላታቸውን ሲጨርሱ ሌባው የሚሰረቅ አንዳች ነገር አጥቶ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲሰናዳ ያዩታል። በእድሉ ያዘነው ሌባ ለመውጣት ወደ በሩ ሲያመራ። «ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ አንዴ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርድና አስር ሀሰናት (ምንዳ)ይዘህ ውጣ»የሚልን ድምፅ ሰማ። ሌባው ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ ሲዞር አንድ ግርማ ሞገስ የተላበሱ ሰው ያያል። የቤቱ ጌታ ናቸው። ይህ ክስተት ለታላቁ ሌባ ፍፁም እንግዳ ነው። ሊሰርቅ የመጣንና እጅ ከፍንጅ የተያዘን ሌባ ጠፍረው ወደ ህግ በሚገትሩበት አሊያም እዛው ቀጥቅጠው አፈር ድሜ በሚያስግጡበት ሀገር። ባዶ እጅህን ከምትወጣ ይልቅ እንዲህ ያለ መልካም ስራ ስራና ሰዋብ(ምንዳ) ይዘህ ሂድ» የሚልን ሰው ማግኘት የሰራቂውን ልብ ሰረቀው። በንግግራቸው የተማረከው ሌባም በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ ካጠገባቸው ተቀመጠ። የቤቱ ባለቤት ታላቁ ታቢኢን ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረዲየሏሁዓንሁ ናቸው።
እንደሚታወቀው « ማሊክ ኢብኑ ዲናር» ደግሞ የሀገሩ ታላቅ አሊም ናቸው። ከዚያም ሌባው ኢማም ሆይ! ምከሩኝ? አላቸው። እሳቸውም በዛች ንግግር አንዴ ልቡን ሰርቀውታልና ምርኮኛቸውን ይመክሩት ያዙ።
በዚህ መካከል የሶላት ወቅት ደረሰና ኢማሙ ሌባው ጋር ሆነው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የቤቱን በር ሲከፍቱ ኢማሙን አጅበው ወደ መስጊድ ሊሄዱ የተዘጋጁት ጎረቤቶቻቸው ነበርና አይናቸው ጉድን አስተዋለ « የሀገራችን ታላቅ አሊም ከሀገራችን ታላቅ ሌባ ጋር! » ሲል አንደበታቸው ገለፀው። ኢማሙም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው « ሊሰርቀን ሲመጣ ሰረቅነው! » ታዲያ ያ ታላቅ ሌባ ከኢማሙ ስር በመክረም ታላቅ ደረሳቸው ለመሆን በቃ።