Telegram Web Link
የሻእባን መባቅያው ላይ ቆመን የረመዳን መግቢያን በጉጉት ስንጠብቅ... ጨረቃይቷ እንደ ፈገግታ ብቅ ብላ የራህመቱን ወር መዝለቅ ታበስረናለች።
:
ከሙዕሚኖች ልቦና ውስጥ ጥላቻና ቂምን ነቅላ ይቅርታን የምታነግስ ፡ የመኳረፍን ተራራ ንዳ የመከባበርና መዋደድን ድልድይ የምትገነባዋ!! ሁሉም ለይቅርታ ልቡን በሰፊው ከፍቶ ሁሉንም ይቅር ብያለሁ ፡ እኔም ሰው ነኝና በውልክፍክ አረማመዴ ያስቀየምኳቸው ሁሉ አውፍ ይበሉኝ!! ይላል..ረመዳን አንድ ጣቱን ሲያስገባ።
የይቅር ባይነት ሚዛናችን ሀቢባችን (ሰዐወ) ናቸው!

እነሆ ልባችንን ለይቅርታ በሰፊው ከፍተናል!! በህይወታችን ላይ እሾህ ሆናችሁ ማይፋቅ ጠባሳን ማይረሳ ህመምን፣ ማይሽር ቁስልን ያስታቀፋችሁን : ትንሽ ትልቁን ህመማችንን ትተን ለአሏህ ብለን ይቅር ብለናችኋል!!
ለምን አትሉንም??
ተፈቃሪያችን ﷺ እንዲህ ነበሩና !!

ለአሏህ ብለን
ይቅር ብለናል....

••ረ መ ዳ ን••
@heppymuslim29
ማታ ላይ ከመተኛቷ በፊት ስትኳካል አይተዋት
"ምንድነው በእንቅልፍ ሰዓት እንዲህ የምትቀባቢው?" አሏት።
"አስከሬን እያበጃጀሁ፤ ለገናዦቼ ሥራ እያቃለልኩ ነው " አለች አሉ አንዷ እብድ።

አስክሬን ነንና ዉዱእ አድርገን፣ በልቦናም ንፁህ ሆነን፣ አዝካሮችን አድርገን፣ የምድር ላይ የመጨረሻ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ።

@heppymuslim29
....ከጎናችን ባለው ሰው አይን ውስጥ ይሄ ረመዳን የመጨረሻው እንደሆነ ብንመለከት ምን እናደርግ ነበር? አልያም.... ይሄ ረመዳን የመጨረሻችን እንደሆነ እያየ ምንም ባይለን ምን ይሰማን ይሆን ? ብዬ አሰብኩ...

.....አለ አይደል?.... በሚለዋወጥ አላቂ አለም ውስጥ የማይለወጥ ተደጋጋሚ እኛነት። የመጣውን ስለመጣብን ብቻ መቀበል... የለመድነውን ዑደት መደጋገም... ሲሄድ በግድየለሽነት መሸኘት። ቆይ ከዚ በኋላ ባይመጣስ?.... ለአንዴ እንኳን "ረመዳን ስለደረሰ አውቄም ሆነ ሳላውቅ...." በሚል መልዕክት ፈንታ "....ያ አኺ ፊላህ... ይሄ ረመዳን የመጨረሻችን ይሁን አይሁን ስለማላውቅ በህይወታችን አሳልፈነው የማናውቀው አይነት ልዩ የዒባዳ ወር እንድናሳልፍ ልጠይቅህ ወደድኩ። አድርገነው የማናውቀው አይነት ልዩ ቃል እንገባባ። አደራህን ባሁኑ ለለይል ካልተነሳሁ ቀስቅሰኝ... ተራዊህ ላይም ካልተያየን ተደዋወለን እንተዋወስ... ቁርዓንን ደጋግሞ ከማኽተሙ እንለፍና እንማማረው... የመጨረሻችንም አይደል?... በቀን ውስጥ አላህን ባስታወስናቸው ሰዎች ቁጥር እንፎካከር... መጥፎ ቃል የወጣንም እንደሆን አሁን በምንገባባው ቃል ታስረን ሰደቃ እንስጥበት... እንደውም የተመደበች የሆነች ሰደቃን ያልሰጠንበት ቀን እንዳያልፍ.... የመጨረሻችንም አይደል? ምናልባት ከዚያ በላይ ረመዳኖችን እንድንኖር ተፅፎልን እንደሆንና ተኮራርፈን ቢሆን እንኳ... 'ያኔ ባሳልነፍነው 30 መልካም ቀናት ትዝታ' ስም ያለ ቴክስት አማላጅ አፉ እንባባላለን።" የሚል መልዕልት ቢደርሰኝ ተመኘሁ።

ያ ኡመተል ሀቢብ.... አላፊ የሆኑ ወዳጆቻቹንና... መጪዎቹን የሚቆጠሩ ቀናት አደራ...

@heppymuslim29
ወጣቱ ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሲያጣጥር እናት ታለቅሳለች። ልጁም "እማ የቂያማ እለት ሂሳብ ተሳሳቢዬ አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊያለሽ ? ብሎ ጠየቃት ። እናትም "ስለማዝንልህ ይቅር እልሀለው " አለችው ! እሱም እንዲህ አላት "ካንቺ በላይ ወደሚያዝንልኝ ጌታ እየሄድኩ ነው አታልቅሺ

@heppymuslim29
ተራዊሕ አምሽተን ስንገባና ደክመን ስንወድቅ ዘጠኝ እና አሥር ሰዓት አካባቢ ገላን ከፍራሽ ማላቀቅ ትልቅ ጉልበት ይጠይቃል። ለሱሑር እንደመነሳት የሚከብድ ነገር የለም። በመሆኑም ብዙዎቻችን ያለ ሱሑር መፆምን በወደድን። ግና ሱናዉን አስበንና በረካዉን ለማግኘት ብለን እየታገልን እንነሳለን። ዐይናችን ሳንከፍት የምንበላ ሁሉ አለን።

ከሱሑር በኋላ እስከ ሱብሒ ያለው ሰዓት አጭር ቢሆንም ለብዙዎቻችን ይረዝምብናል። ግና ከፊቱ ያለዉን የግዴታ ሶላት ሳይሰግዱ መተኛት ቁጭትን የሚያስከትል በመሆኑ እንቅልፋችንን እየታገልን በኢስቲግፋርና ቁርአን በመቅራት እንቆያለን ።

ገና ለሱብሒ ሶላት እንደቆምን ከሶላቱ በኋላ ያለው ጣፋጭ እንቅልፍ ይታወሰናል። ያ እንቅልፍ ዱንያ ላይ ካሉ ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ ቀዳሚው ሳይሆን አይቀርም። ግና ከሱብሒ በኋላ መተኛት አይመከርም ። ሰዓቱ አላህን የማውሳትና የዱዓ ሰዓት በመሆኑ ወደ አላህ መቅረብንና በርሱ ዘንድ መወደድን አስበልጠው ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ዚክርና ዱዓ እያደረጉ የሚቀመጡ ብርቱዎችም አሉ።

ኢማን ማለት ይህ ነው። የማይታየዉን የአላህ ቃልኪዳን እንደሚታይ አድርጎ ማመን። እኛ ከምንፈልገው በላይ አላህ የሚወደዉን ማስቀደም። ጀነት ዉድ ናት ። ነፍሲያን መጫንን ፣ ፍላጎትን መጨቆንን ትጠይቃለች። ጀነት ለነፍሲያ በሚከብዱ ነገሮች የተከበበች ናት። እንቅልፍ መቁረጥን፣ ድካምን መርታትን፣ ስንፍናን ማሸነፍን ፣ የምንወደዉን አላህ በሚወደው መተካትን ትሻለች።

አላህ ያበርታን።
@heppymuslim29
ከአጠገቤ የተቀመጠ ልጅ ነው። በግምት አስራ ሁለት / አስራ ሶስት አመት ይሆነዋል። የልጅ መዳፎቹን ዘርግቶ መለመን ይዞዋል። ጠበቅኩት። እንደ ልጅኛ ከማስበው በላይ ዱዐውን አርዝሞታል። ሲጨርስ ተጠግቼ ምን ብለህ ዱዐ አደረግክ? ብዬ ጠየቅኩት።
.
በልጅነት ጥርሶቹ ፈገግታውን እያካፈለኝ " ለኔ እና ለእናቴ የሚለፋን ሰው ጠብቀው።" እያልኩኝ ነበር አለኝ።
የልጁ አባት ይህንን ጊዜያዊ አለም ተሰናብተው ከሄዱ አመታት አልፈዋል። የቲም ነው።
ልጅ የህይወት ሽንቁራቸውን ለመሙላት ለሚጥር ሰው የዱዐ መዳፎቹን ዘርግቶ ይለምናል።
:

በረመዳን ላይ የቲሞችን እናስታውስ። እንዘይር። ከተትረፈረፈው ምግብ እናካፍል። መስጠት ውስጥ ሰላምን መሰጠት አለ። የነፍስ እርካታ ይገኛል። የቲሞችን መንከባከብ የሀቢበላህን ጉርብትና የሚያስገኝ ተግባር ነው።

@heppymuslim29
ወንጀል ሠርተህ ትፀፀታለህ፡፡ <ጌታዬ ሆይ ሁለተኛ አልመለሰበትም፡፡› ትላለህ፡፡ ተመልሰህ ያንኑ ወንጀል ትሠራለህ፡፡ ተፀፅተህ ጌታዬ ሆይ! አልመለስበትም፡፡ ትላለህ፡፡ ለሦስተኛ አራተኛ ጊዜም እንዲሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ተውባ ማድረጉ ይከብድሃል፡፡ ለምን ካልክ በራስህ ላይ እምነት ስላጣህ ነው፡፡ ዳግም ተመልሰህ ተውባ አድርጌያለሁ፡፡ ለማለት ታፍራለህ፡፡ አትፀናበትምና፡፡ በዚህ የተነሳ ባንተና በአላህ (ሱ.ወ) መካከል ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል፡፡ መመለሱም ይከብድሃል፡፡ ዳግመኛ ተውባን እንዳታስብ የሚያደርግ ባንተና በአላህ መካከል ግርዶ እስከመከሰት ይደርሳል፡፡

ነገር ግን አላህ ይወድሃልና እንድትመለስ ይፈልጋል፡፡ ተውባ ታደርግ ዘንድ ይህ መሰናክል እንዴት ይወገድ ይሆን? አዎን ባልተለመደ ሁኔታ ይወገድልሃል፡፡ ባልታሰበ መልኩ ግዙፍ በሆነ ነገር መሰናከሉን ያነሳልሃል፡፡ ይህም ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ በዚህም ስጦታ አላህ (ሱ.ወ) ወዳንተ ይወደዳል፡፡

ይህ ስጦታ ለይለቱል ቀድር ይባላል፡፡ ይህች ለሊት ይቅር የምትባልበት ሌሊት ናት፡፡ ያለፈ ወንጀልህ ሁሉ ይታበስልሃል፡፡ ስለሆነም ተውባ ለማድረግ ባትታደል እንኳ ይህን ስጦታ በመቀበል አዲስ ሕይወት ትጀምር ዘንድ በዚህች ሌሊት ወደሱ መምጣት ይኖርብሀል፡፡ በዒባዳ ወደሱ ትመጣለህ፡፡ በዚህ መልኩ አል-ዐፋው ወደ ተውባ ይመራሃል፡፡ ከዚያም በሌሊት አጋማሽ በራስህ ጊዜ እፍረት ይይዝህና በተውባ ወደ አላህ ለመመለስ ትወስናለህ፡፡ ባንተና በተውባ መካከል ያለው ግድግዳ ፈርሷልና፡፡ በዚህም የተነሳ ይህች ሌሊት ከተውባ ጋር አዲስ ጅማሮ ትሆንሃለች ማለት ነው።


ከቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍ
ሙሐመድ ሰዒድ (ABX) እንደተረጎመው

@heppymuslim29
የሆነ አካል ዱአ አድርጉልኝ ብሎ
ሲለን እሺታችን ከአንገት ብቻ መሆን የለበትም። ይህን ሲለን ለእኛ ተራ ነገር መስሎ ሊታየን ይችላል ነገር ግን ለዛ ሰው ነጃ የመውጫ , የመፈረጃ ወይንም የኸይር መንስኤ ሊሆነው ይችላልና የሚሰጠንን አማና ችላ ባለማለትና የጠየቀንን ቀላል የሆነ ጥያቄ በመወጣት ሀላፊነታችንን እንወጣ ባይ ነኝ። እኔንም በዱዓቹ አትርሱኝ !!

@heppymuslim29
የሁሉን ዓመት ዒድ በደሰታ ስሜት ዉሰጥ ሆነህ አትደርስም መቸስ። አንዳንዱን በህመም፣ አንዳንዱን በገፍላ፣ አንዳንዱ በሐዘን፣ አንዳንዱን በችግር ዉስጥ ሆነህ... ልታሳልፈው ትችላለህ።
ሁሉ ዒዴ ዒድ ካለመሰለ አትበል። በሁሉም ሁኔታህ ዉስጥ አላህን አመስግን።

በሁሉም ሁኔታ ዉስጥ ላላችሁ ኡመተ ሙሐመድ እንኳን አደረሳችሁ።
ዒዱኩም ሰዒድ ወሙባረክ

عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عم وأنتم بخير🤍
@heppymuslim29
ሰሞኑን በሪያድ ከተማ የተከሰተው የመኪና አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊቴ ተጋጭተው ነበር። አምቡላንስ አየሁ። ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ። አንድ ወጣት ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየሁ፡፡ ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል። አካላቱ ተቆራርጧል። እግሩም ጭምር ተቆርጧል። እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ።

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል
"መሞት አልፈልግም። በጣም ፈርቻለሁ እሳት ነው 'ምገባው እኮ" ይለዋል። እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔ 'ኮ አልሰግድም ነበር። ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም። ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ። ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል።

ሰዎችም ተሰበሰቡ። እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ። በጣምም ፈርቻለሁ፡፡ በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል። የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ። ጩኸቱም ቀጠለ። ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ። ሊያድኑት ግን አልቻሉም።

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሃዳ በል! ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል። ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም። ሱብሃነላህ በጣም ፈርቶ ነበር። ነገር ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ሸሃዳን ምላሱ ለማለት እምቢ ማለቷ ነው። ዚያም አልተንቀሳቀሰም ሰውነቱም ደርቆ ቀረ።

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ። ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት። ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም። ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም። ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት። ዘጋቢውም ይለናል " በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ። እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው። ሰላታችሁን ግን ጠብቁ። በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡ ዛሬውኑ መስገድ ጀምሩ። የመጨረሻ ቀናችን መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም። እኔም ከዚህ ክስተት በኋላ መተኛት አልቻልኩም። እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር። ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...”። እሰግዳለሁ፣ወላሂ ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ፣መሞት ግን አልፈልግም...ባለቀ ሰዓት ከንቱ ልፍለፋ ብቻ።”

@heppymuslim29
አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል። አንድ ቀን የግቢው ባለቤት ግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል። ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ስር ይቆምና ሰው መኖር አለ መኖሩን ቅኝት ይጀምራል። ወደ ፊት፣ወደ ኋላ፣ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ። ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደ ታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች። ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ ሲያይ ከቤቱ ባለቤት ጋር ተፋጠጠ። ባለ ቤቱም “ይህን ያደረግኩት ለምን እንደ ሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰው እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ 'ላይም ማዬት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።


ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን የፈጠረን አላህ ያየኛል ብለን ማሰብ አለብን። "የትም ብትሆን አላህን ፍራ" ማለት ይሄ ነው!!

@heppymuslim29

:
ቁና ቁና እየተነፈስ የተናደደ ፊቱ ቀልቶ እግሩን እያማታ ቶሎ ቶሎ ይራመዳል ።
ልጄ የሚል ድምፅ የሰማ መስሎት ሲዞር ድቅቅ ያሉ ሽማግሌ በተለማማጭ አይነት ስሜት አይን አይኑን እያዩ እጃቸውን ዘረጉ፤
.....ምን ልስጦት አባባ ያው ባዶ ኪስ ነኝ ያለሁት ባዶ እያለ ኪሱን ገልብጦ አሳያቸው፤
..በሁኔታው ቅር አልተሰኙም."ልጄ አመስግን በአላህ እዝነት ተስፋ አይቆረጥም ባይገባህ ነው እንጂ አንተኮ ኪሱ ባዶ የሆነ ሱሪ አለህ ፡አንተ ያለህ የሌላቸው ብዙ አሉና ባለህ አልሀምዱሊላህ በል..ስታመሰግን የምታመሰግንበት ስታማርር ደግሞ ምታማርርበት ነው ሚሰጥህ "ብለው ማዝገማቸውን ቀጠሉ ።

... "ኪሱ ባዶ የሆነ ሱሪ አለህ.." የአዛውንቱ ንግግር ጆሮ ላይ አስተጋባ ። ""አልሀምዱሊላህ"ይቺ ቃል ልቡ ውስጥ ሲደጋገም ተሰማው።!
:

" #ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም ነበር" ሚለው ንግግር እንዴት ትዝ አለኝ!

@heppymuslim29
በሰርጓ ቀን አንዷ የMakeUp ባለሞያ እቤቷ አምጥታ በጥንቃቄ MakeUp ተሰራች። በጣም ለውበቷ በመጨነቅ በዝግጅቱም ላይ ልዩ ለመሆን ፈልጋ ነበር። ነገር ግን ከዛ ሁሉ የጥንቃቄ ሥራ በኋላ ልክ ቀጠሮው ሲደርስ አንድ ነገር ረስታ ነበር። MakeUp ከመሰራቷ በፊት ውዱእ ማድረግ። ውሃው ወደ ፊቷ እንዲደርስ MakeUpuን ማንሳት ነበረባት። የዝግጅቱ ግዜው ደረሰ፤ በአዲስ ድጋሚ ለመቀባባት ጊዜ አይበቃትም። አንዳንድ ከሷ ጋር የነበሩ ቤተሰቦቿና የ(MakeUp) ባለሞያዎች ‹‹አሁን አትስገጂ.. ዝግጅቱ ካለቀ በኋላ ቀዷእ ታደርጊያለሽ›› አሏት። ነገርግን እሷ አሏህን ስለምትፈራ እነሱን ትታ ፊቷ ላይ የነበረውን በሙሉ በውሃው አንስታ ውዱእ አደረገች። ሶላቷንም መስገድ ጀመረች፤ ነገርግን በጣም ቆየች... ቤተሰቦቿ እሷን መፈለግ ጀመሩ፤ ለካ እሷ ሱጁድ ላይ እያለች ሞታለች...!

አሏህን እንፍራ...ሶላትን አንተዉ....

@heppymuslim29
ቁርጥ እርሣቸዉን የምትመስል ቆንጆ ናት፣ ዉብ ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት እርሣቸው ጋር መጡ፤ ብዙ የተከበሩና ትላልቅ ሰዎች …

አንዲት ዐሊን የምትወድ የአንሷር ሴት ዐሊ ዘንድ ሄዳ
“ፋጢማን ብዙ ሰው እንደጠየቃት ታውቃለህ ግን?” አለችው፡፡
“አዎን” አላት፡፡
“አንተሰ ለምን ሄደህ አትጠይቅም፤ ለምን ዳሩልኝ አትላቸዉም፣ ትወዳት የለ?” አለችው፡፡
አንገቱን አቀረቀረ
“ድሃ ነኝ ምን አለኝና? በምንድነው የማገባት?” አላት፣
“ዝምብለህ ሂድና ጠይቅ፤ መልካም ነገር ልትሰማ ትችላለህ አብሽር፡፡” ብላ አሳመነችው፡፡

ሄደ፡፡ ፈራቸው፤ እርሣቸው ፊት ተቀምጦ መናገር ከበደው፡፡ እናም ዝም አለ፡፡
“ምነው ዐሊ ምን ሆነህ ነው? ምንድነው ያመጣህ ጉዳይ?” አሉት፤ አከታትለው ጠየቁት፡፡
ዐሊ አሁንም ዝም አለ፡፡
“ምናልባት ፋጢማን እንድሰጥህ ለመጠየቅ መጥተህ እንዳይሆን፡፡” አሉት፡፡
አዎን በሚል ሀሳብ ራሱን ነቀነቀ፤
“ታዲያ ጥሎሽ ይኖርሃልን?” አሉት፡፡
“ምንም የለኝም” አላቸው፡፡
“የሆነ ጋሻ እንዳለህ አስታውሳለሁ፡፡” አሉት፡፡
“አዎን አለኝ፣ ግን እሱ ምን ያደርጋል፣ ምን ዋጋ ያወጣል?” አላቸው፡፡
“ይጠቅማል ሽጠዉና ...፡፡” አሉት፡፡

ቤት ገዙላቸው፤ ጋብቻው ተፈፀመ፡፡

ዐሊ እንዲህ ይላል
'ከዚያ በኋላ ፋጢማን እጅግ ወደድኳት፡፡ አንድም ቀን በስሟ ጠርቻት አላውቅም፤ “ የአላህ መልዕክተኛ ልጅ ሆይ” ነበር የምላት፡፡
ልክ እሷን ሳይ ሀሳብና ጭንቀቴ ሁሉ ይወገዳል፣ ልቤ እረፍት ይሰማዋል፣ አንድም ቀን አስቆጥቻት አላውቅም፣ አንድም ቀን አላስለቀስኳትም፣ አንድም ቀን አስቆጥታኝ፣ አንድም ቀን አስቸግራኝ አታውቅም፡፡ በአላህ አምላለለሁ አንድም ቀን ጀርባዬን ሰጥታችት አላውቅም፤ ሁሌም እጆቿን እንደሳምኳት …   

ፋጢማ ከአባቷ ከአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) ህልፈት ከስድስት ወር በኋላ ተከተለቻቸው፡፡ በሞተችም ጊዜ ባለቤቷ ዐሊ አጠባት፣ ከፈናትም፣  ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎም

“ፋጢማዬ እኔ ዐሊ ነኝ፡፡” አላት፡፡  

@heppymuslim29
አንድ ሰው ከአንድ መልካም ሰው ጋር ተቀምጦ
ሳላ በረካ የሚባለው ነገር የለም ሲል ሀሳብ አነሳ...!

መልካሙ ሰውም:_ ውሻና በግ  ተመልክተሀል ወይ አለው...?

ሰውየውም:- አዎ አለ!

መልካሙ ሰውም:-  የትኛው ብዙ ይወልዳል ሲል ጠየቀው..?

ሰውየው:- ውሾች ሰባት ይወልዳሉ በጎች እስከ ሶስት ይወልዳሉ በማለት መለሰ!

መልካሙ ሰውም:-   በዙሪያህ ብትመለከት ከሁለቱ የቱ ብዙ ነው ሲል ጠየቀው...?

ሰውየውም:- በጎቹ ብዙ ሁነው እንመለከታለን አለ ...

መልካሙ ሰውም:-  የሚታረደው በጎች ናቸው  መቀነስ የነበረባቸው እነሱ ነበሩ አይደል?

ሰውየውም:- አዎ አለ

መልካሙ ሰውም:- እንግዲህ   በረካ ማለት ይህ ነው ሲል መለሰለት !

ሰውየውም እንዴት ታዲያ ከውሾቹ በጎቹ በረካን ተሰጣቸው ሲል ጠየቀው..?

መልካሙ ሰውም :-በጎች ከለሊት መጀመሪያ ላይ ተኝተው ከፈጅር በፊት ስለሚነሱ ነው ...ውሾች ደሞ ከለሊት መጀመሪያ ጀምረው ይጮሁና ፈጅር ሲደርስ ይተኛሉ የእዝነቱ ጊዜ ያልፍቸዋል በረካም ከነሱ ላይ ይነሳል !


ለሊቱን በማይረባ ነገር ስናነጋው የለይል ረህመት የፈጅር በረካ እንዳያልፈን አደራ!!

@heppymuslim29
«She is ቆንጆ ናት... አፍላ .... 20 አመቷ ነው።
ጎረምሶች ሲያዩዋት አይናቸው ይጎለጎላል። ጎልማሶች አይተው ይመኛታል። ወንዶች ይከጅሏታል። ሴቶች በቅናት እንደ ሽንኩርት ይልጧታል።

🧢  አንድ ቀን እንዲህ ስል ጠየቅኳት።
<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን መስፈርት እንዲያሟላ ትፈልጊያለሽ? >>
🧢በፍጥነት መለሰችልኝ
የተማረ መሆን አለበት፤ ማስተርስ ያለው ይመረጣል። ከተቻለ የግል ቢዝነስ የሚሰራ፤ ካልሆነ ግን አሪፍ ደሞዝ ሊኖረው ግድ ነው። መኖሪያ ቤቱ G+2 ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ከG+1 በታች ግን አልፈልግም።
🧢መኪና በጣም ነው የምወደው። አሪፍ መኪኖች ቢኖሩት አሪፍ ካልሆነም ከተጋባን በኋላ እኔ እንዲገዛ አደርገዋለሁ። ሙድ የገባው ቢሆን ደስ
ይለኛል። ሁሌ ግን የሚቅም መሆን የለበትም። ጨዋታ የሚያውቅ ሁሌ የሚያስቀኝ!!!
🧢 ቁመቱ በጣም እንዲረዝም አልፈልግም። እኔ አጠር ስለምል በጣም እንዳይበልጠኝ። ደረቱ ሰፋ ያለ ሆኖ ቦርጭ የሚባል እንዲኖረው አልፈልግም።
🧢ጸጉሩ ፍሪዝ ቢሆን ደስ ይለኛል፤ ድሬድ ቢሆን ደግሞ ነፍስ ነው። አይኑ የሚያምር፤ መልኩ ጸይም መሆን አለበት በጣም ቀይ ወይም በጣም ጥቁር
ወንድ አልወድም። አለባበሱ ዘናጭ መሆን አለበት። የሚወደኝ፤የሚንከባከበኝ፤ ሮማንቲክ የሆነ፤ በሳምንት ቢያንስ ሁለቴ የሻማ እራት ያለበት ሆቴል የሚጋብዘኝ፤ ፤.ከበዓላት እና  ቀን በተጨማሪ ስጦታ እያመጣ ስርፕራይዝ የሚያደርገኝ፤ ፍቅር የሚያውቅ፤ በተለያየ ቁልምጫ ስም የሚጠራኝ እና ታማኝ ከእኔ ውጪአንዲት ሴት የማያይ ...
🧢 >>ይበቃል አልኳት እንደማታቆም ስለገባኝ። እንዲህ አይነት ወንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀርቶ በዩኒቨርሱ ውስጥ እንኳን አይገኝም አልኩ በውስጤ። ለሷ ግን አልነገርኳትም።


ከ5አመት በኋላ ሳገኛት 25 አመቷ ነበር። አላገባችም። ዩኒቨርስቲ ጨርሳ ስራ ይዛለች። አሁንም ታምራለች እንደድሮው ግን የሰው ሁሉ አይን ማረፊያ አይደለችም። መልሼ ያንኑ ጥያቄ ጠየቅኳት።

🧢<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>> የማፈቅረው ሰው መሆን አለበት፤ ፍቅር ከሌለ ላገባው አልችልም።
ከማልወደው ሰው ጋር አንድ ቀን ላድር አልችልም። ታማኝ እንዲሆን እፈልጋለሁ። እንዲያከብረኝ እፈልጋለሁ። ጥሩ ስራ ቢኖረው፤ ማንበብ
የሚወድና በሃሳብ የምንግባባ ቢሆን ደስ ይለኛል። ቆንጆና ሃብታም ከሆነ ጥሩ ነው፤ ካልሆነም ግን አብረን ሰርተን መለወጥ እንችላለን። ዋናው መግባባት ነው። በተረፈ ቤተሰቡን የሚወድ እና የማይዋሽ መሆን አለበት። ወንዱ ሁሉ የማይታመን ሆነብን እኮ። ዋናው የሚታመን ከሆነ ሌላው ችግር የለውም>>

ጊዜው ይሮጣል!!! ከ5አመት በኋላ ስንገናኝ አላገባችም። 30 አመት እያለፋት ነበር። ደግሜ ያንኑ ጥያቄ ጠይቅኳት።

<<ማግባት የምትፈልጊው ባል ምን አይነት ነገሮች ማሟላት አለበት?>> ትንሽ አሰብ አደረገኝና
<<የምግባባው ሰው ከሆነ ሌላው ችግር የለውም>> አለችኝ መልኩ፤ ጸጉሩ፤ ሃብቱ፤ እውቀቱስ አልኳት።
<<ወንድ ልጅ ደግሞ መልክ ምን ያደርግለታል? ከቺምፕ (ቺምፓንዚ) መለስ ካለ ሌላው ችግር የለውም>> አለች እየሳቀች።

🧢ከ5 አመት በኋላ ሳገኛት አግብታ ሁለት ልጆች ወልዳ ነበር።ባሏ አጭር፤ ጥቁር፤ መላጣ፤ የከባዳ መኪና ሾፌር አይነት ቦርጭ ያለው፤ሱሪውን ቦርጩ መሃከል ላይ የሚታጠቅ፤ ሁልጊዜ መላጣውን የሚያልበው  ነገር ነው።

<<እንዴት ነው ትወጂዋለሽ>> አልኳት

<<ምን ማለትህ ነው ትዳር አይደል?>>

<<ማለቴ ድሮ የነገርሽኝ አይነት ሰው አይደለም ብዬ ነው?>>

<<ያኔማ አየር ላይ ነበርኩ፤ እድሜ መስታወት ነው፤ ብዙ ያስተምራል፤ አሁን ተምረን ልብ ገዝተን ነው>> አለች ተከዝ ብላ።

<<በትዳርሽ ደስተኛ ነሽ?>> አልኳት እያዘንኩ
<<ደስታ አንጻራዊ ነው፤ በልጆቼ ደስ ይለኛል፤ ትዳሬን አከብራለሁ። በተረፈ ግን እየኖርኩ ነው>> አለች ፈገግ ብላ። በዛች ቅጽበታዊ ፈገግታ ውስጥ
የጊዜን ኃይለኝነት አየሁ። በስተመጨረሻም የተረዳሁት ነገር ሴት ልጅ የተጋነነ መስፈርቷ ጠላቷ እየሆነ ነው።»

@heppymuslim29
« እንደው ግርም የሚል ነገር ነው። ያቺን የመሰለች ዓሊም እንዴት ብላ ያን ጃሂል እንዳገባች የሚደንቅ ነው! አላቸው ነገሩ ቢያብከነክነው።
ረጋ ብለው ካዳመጡት በኋላ
« ነፍሱን ካመለከ ይልቅ ስለነፍሱ ያላወቀ ይበልጥ መልካም ለመሆን ይቀርባል « አሉትና ዝም አሉ። ንግግራቸውን እንደሰማ ሀፍረትም ንዴትም ተቀላቅለውበት ተለጎመ። »

@heppymuslim29
አሥሩ የዙል-ሒጃ ቀናት፡፡
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ፡፡

ዛሬ ዙል-ቂዕዳ 29ኛ ቀን ላይ ነው ያለነው፡፡ ነገ የሚገባው ወር ዙልሂጃ ይባላል ‼️

- ዙል-ሒጃ እጅግ የተከበረ ወር ነው፡፡
- ጦርነት በውስጥ ከተከለከለባቸው ከአራቱ የተከበሩ ወራት ውስጥም አንዱ ናት፡፡
- ከወሩም የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡
- ቀናቶቹ የዙል-ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ። የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡
- ከነኚህ ቀናት ውስጥ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ የሐጅ ሥራዎች ይከናወናሉ።
- እነኚህ ቀናት ክቡር መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡
- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም የዱንያ ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡
- የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡
- ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳ መበርታት ይገባል፡፡
- በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ተወዳጅ የመሆናቸውን ያህል በውስጣቸው የሚሠራ ኃጢኣትም ጥፋቱ ክቡድ ነው፡፡
- እነ ዐብደላህ ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡
- በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡
- በነኚህ ቀናት ውስጥ ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ይወደዳል፡፡

- በዐረፋ ቀን ዱዓና ዚክር ማብዛት ይመረጣል፡፡ በተለይ ላ ኢላህ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … የሚለዉን፡፡
- በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ የዒባዳ ዓይነቶች ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡

- ደጋጎች እነኚህን ሦስት አሥርት ልዩ ጊዜያቶች በእጅጉ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡ የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣ የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣ የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡

ያስታውሱ ቀናቱ ነገ ይጀምራሉ ‼️
@heppymuslim29
ሐጀተል ወዳእ
(የመሰናበቻው ሐጅ)
.
.

በወርሀ ዙልሒጃ ከሚነሱ እውነታዎች አንዱ የሆነው የኢስላም አምስተኛው ማእዘን ሐጅ ነው። በነብዩላህ ኢብራሂም አለይሒሰላም እና በልጃቸው ኢስማኢል አማካኝነት በተገነባው ካእባ ዙሪያ የሚደረግ አምልኮ! የቆዳ ቀለም፣ ፆታ፣ ጎሳ፣ ብሔር፣ የሰውነት ገፅታ ሳይለያያቸው አቤቱ ጌታችን የሚሉበት የእኩልነት ማሳያ ኢባዳ!

ወቅቱ አስረኛው አመተ ሒጅራ ወርሀ ዙልቃኢዳ ሐያ ስድስተኛው ቀን ቅዳሜ ነበር። ረሱሉ ሰለላሁ አለንሒ ወሰለም በይፋ ለሐጅ መነሳታቸውን ካወጁ በኋላ የመዲና ነዋሪዎች (የቻሉት በሙሉ) ከረሱሉ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር በመጣመር ስንቃቸውን ቋጥረውና ለጉዞ ተዘገጃጅተው ወደ መካ ጉዞ ጀመሩ። አቡበከር አስሲዲቅ እየመሩ በዘጠነኛው የሒጅሪያ አመት ወደ መካ ካቀኑ በኋላ ቀጣዩ የጉዞ ቅፍለት መሆኑ ነው። እኚህ መቶ ሺህ የሚደርሱ አስሐቦች ገላቸውን ተጣጥበውና ሐርመው (ኢህራም አድርገው) ጉዞ ተጀመረ።

ረሱሉ ሰለላሁ አለይሒወሰለም ውድ ግመላቸው የሆነችው ቀስዋህ ላይ ከወጡ ጀምሮ መዲና በተልቢያ ተናወጠች።

<<ለበይከላሁመ ለበይክ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ ኢነል ሐምዳህ ወንኒእመተህ ለከወልሙልክ ላሸሪከለክ>>
<<አላህ ሆይ! (ታዛዥ ሆኜ መጥቻለሁ) አቤት። አንተ ተጋሪ የለሕም አቤት ምስጋናና ፀጋ ያንተ ነው። ንግስናም ያንተ ነው። ተጋሪ የለህም።" ሲሉ በአንድ ድምፅ ያስተጋባሉ።

የመጀመሪያው የጉዞ ማረፊያ አል አሪጅ ሆነ። ቀጣይ አል አብዋእ፣ አስፋን፣ ዚጡዋህ በቅደም ተከተል የሰፈሩባቸው ስፍራቸው ናቸው። ዚጡዋህ ሲደርሱ ዙልሒጃህ አራተኛው ቀን ነበር። ገላቸውን ተጣጥበው በሰሜን የመካ መግቢያ ወደ ካእባ አቀኑ።

ከነብይነታቸው በፊት ወደቦታው እንዲመልሱ የተመረጡለትን ሐጀር አል አስወድን ስመው ወደ ጠዋፍ ስነስርአት አመሩ። የመጀመሪያዎቹ ሶስት ዙሮች በፍጥነት ቀጣዮቹን አራት ዙሮች ደግሞ እየተራመዱ ካእባን ዞሩ። ከዚህ በኋላ መቃሙ ኢብራሒም ላይ ቆመው የበቀራህን መቶ ሐያ አምስተኛ አያ (አንቀፅ) አነበቡ።
<<ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ)፣ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፤ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎችና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃልኪዳን ያዝን፡፡” [አል-በቀራህ፡ 125]

ከዚያም ከመቃሙ ኢብራሒም ትይዩ ሑለት ረከአ ሰላትን ሰግደው ለሁለተኛ ጊዜ ሐጀር አል አስወድን ሳሙት። ሶፋና መርዋ ጋር የሔዱት ከዚህ በኋላ ነበር። ሰፋ ተራራ አጠገብ ሲደርሱ የሚቀጥለውን የቁርአን አንቀፅ አነበቡ።

<<ሰፋ እና መርዋህ ከአላህ ትእዛዝ መፈፀሚያ ምልክቶች ውስጥ ናቸው። ቤቱን (ከእባን) በሐጅ ወይም በኡምራህ ስራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ መሀከል በመመላለሱ በርሱ ላይ ሐጢአት የለበትም። መልካምንም ስራ በፈቃደኝነት የሰራ ሰው አላህ ይመነዳዋል። አላህ አመስጋኝ አዋቂ ነውና።>>
[አል በቀራህ:158]

በሰፋና መርዋ መሐል ሰዕይ ካደረጉ በኋላ መስዋእት ያመጡ ሲቀሩ ከኢህራማቸው እንዲፈቱ አዘዙ። መስዋእት ያላመጡት ፀጉራቸውን በማሳጠር ኡምራ ብቻ እንዲያደርጉ ሲታዘዙ ቀሪዎቹ በኢህራማቸው ቆዩ። ረሱሉ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለምና ባልደረቦቻቸው መካ ውስጥ ከእሑድ ጀምሮ አራት ቀናትን ቆይተው ሐሙስ ጠዋት ሚና ሰፈሩ። በማግስቱም ከዚህ በፊት ቁረይሾን ከሌላው ተነጥለው ከሚያርፉበት መእሸር አል ሐረምና ሙዝደሊፋ በተቃራኒ ከአረፋህ ተራራ በደቡብ በኩል ባለው ነሚራህ የተሰኘው ቦታ ላይ ቁባ የሚመስል ድንኳን አስተክለው አረፉ።

ነብያችን ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም ፀሐይ ወደ ምእራብ ስትገሰግስ ወደ ኡረናህ ሸለቆ አመሩና ከ120 ሺህ ለሚልቀው የሐጅ ታዳሚ ኹጥባ ማድረግ ጀመሩ።

<<ሰዎች ሆይ ንግግሬን አድምጡ። ምናልባት ከዚህ አመት በኋላ በዚህ ቦታ ላይ ዳግም ላንገናኝ እንችላለን። በዚህ በሀገራችሁ በዚህ ወራችሁ የዛሬው ቀን ክቡር እንደሆነ ሁሉ ደማችሁና ሐብታችሁ የተከበረና የማይደፈር ነው። የመሐይምነት ዘመን የደም ብቀላ ውድቅ ሆኗል። መጀመሪያ ውድቅ የሚደረገው የኢብን ረቢአ ኢብን አል ሐሪስ ደም ነው። እርሱ በበኑ ሰዕድ ጎሳ ውስጥ የገባ ሲሆን በሁዘይል ጎሳ ተገድሏል። የቅድመ ኢስላም አራጣ ውድቅ ተደርጓል። መጀመሪያ ውድቅ የተደረገው የዐባስ ኢብኑ አብዱልሙጠሊብ አራጣ ነው።

★በሴቶች ጉዳይ አላህን ፍሩ። የወሰዳችኋቸው በአላህ አደራ ሲሆን ብልቶቻችሁንም ሐላል ያደረጋችሁት በአላህ ቃል ነው። እናንተ በነርሱ ላይ የምትጠሉትን ሰው በፍራሻችሁ ላይ እንዳያስቀምጡ የማድረግ መብት አላችሁ። ይህን ከጣሱ የማይጎዳ ምት ምቷቸው። እነርሱ በእናንተ ላይ ያላቸው መብት ቀለባቸውንና አልባሳታቸውን ልታቀርቡላቸው ነው።

በሚገባ ከያዛችሁት የማትጠምሙበትን ነገር ትቼላችኋለሁ። የአላህን መፅሐፍ! ስለኔ ብትጠየቁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ?>> ሲሉ ንግግራቸውን በጥያቄ አሳረጉ።
ሰሐቦችም <<መልእክቱን በሚገባ ማድረስዎትንና እኛንም ከልብ መምከርዎን እንመሰክራለን።>> አሉ። ረሱላችን አለይሒሰላምም እጃቸውን ከፍ አድርገው ወደ ህዝቦቻቸው እየተመለከቱ <<አላህ ሆይ ምስክሬ ሁን፣ አላህ ሆይ ምስክሬ ሁን፣ አላህ ሆይ ምስክሬ ሁን>> በማለት ተናገሩ።

ንግግራቸውን ሲቋጩ የሚከተለው የቁርአን አያ ወረደ። <<ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ።ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሐይማኖት በኩል ወደድኩ።>> [አል-ማኢዳህ:3]

ቢላል አዛን አድርጎ ነብያችን ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም እና ባልደረቦቻቸው የዙህርን ሁለት ረከአ ሰላት ሰገዱ። ከዚያም ቢላል ሌላ ኢቃም አድርጎ የአስርን ሁለት ረከአ ሰገዱ። ፀሐይ ከገባች በኋላ ወደሙዝደሊፋ በማቅናት በሁለት ኢቃም የመግሪብንና የኢሻን ሰላት ሰግደው ተኙ። ከሱብሒ ስግደት በኋላ ወደ መእሸረል ሐረም ጋለቡ። ወደቂብላ ዞረው ዱአ አደረጉ። ለፀጋው አመሰገኑ።

ከዚህ በኋላ የነበረው ጀምረተል ኩብራ (የጠጠር ውርወራ) ነበር። በእያንዳንዱ ጠጠር ተክቢራ እያደረጉ ሰባቱንም ጠጠር ወረወሩ። የእርድ ስርአቱ ቀጠለ። ስልሳ ሶስቱን ረሱላችን ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም ሲያርዱ ሰላሳ ሰባቱን ሰይዱና አሊይ ረዲየላሁ አንሁ አርደው ለሚቀርቧቸው ሰዎች አከፋፈሉ።

ጠዋፈል ኢፋዳን(የመጨረሻ ጠዋፍ) ለመፈፀም ሲሉ ወደመካ ተመለሱ። በዚያው 'ለት ወደሚና ተመልሰው ካደሩ በኋላ ማግስቱን ጀመራት ላይ ጠጠር ጣሉ። በዚህ መልኩ ለተከታታይ ሶስት የዙልሒጃ ቀናት ጠጠር እየወረወሩ ከቆዩ በኋላ ወደ መዲና ጉዞ ጀመሩ። ጁሕፋ አቅራቢያ ሲደርሱ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣
<<ሰዎች ሆይ እኔ ሰው ነኝ። ምናልባትም የጌታዬ መልእክተኛ(መለከል መውት) ወደኔ ይመጣና መልስ እሰጥ ይሆናል። በመካከላችሁ ሁለት ከባድ ነገሮችን ትቻለሁ። የመጀመሪያው የአላህ መፅሀፍ ነው። ሁለተኛው ደሞ የኔ ቤተሰቦች(አህሉል በይት) ናቸው። የእኔን ቤተሰብ በተመለከተ አላህን እንድትፈሩ እጠይቃችኋለሁ።>>

የመዲና ድባብ ከሩቅ በታያቸውም ጊዜ እንዲህ አሉ። << ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። ብቸኛ ነው። አጋርም የለውም። ንግስና የርሱ ነው። ምስጋና የሚገባውም ለርሱ ነው። እሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። ንስሐ ገብተን ለአላህ ተገዢዎች፣ ሰጋጆችና አመስጋኞች ሆነን ተመልሰናል። አላህ ቃሉን አረጋገጠ። ባሪያውን ረዳ። ብቻውንም አህዛብን ድል ነሳ።>>

ይህ ነበር የረሱሉ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም የመጨረሻ ሐጅ፣ ለኡማው ፈር የቀደዱለት ከጃሒሊያ በኋላ የነበረ የመጀመሪያው ሐጅ🕋

@heppymuslim29
🔻ተክቢራ🔻


በነዚህ አስር ቀናቶች ከሚፈፀሙ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ተክቢራ ነው። ዙል ሂጃ ከገባበት ሰአት ጀምሮ እስከ ዙልሂጃ አስራ ሶስተኛው ቀን ድርስ ተክቢራ ማለት የተወደደ ተግባር ነው። ስንተኛ፣ ስንነሳ፣ ስራ ላይ ስንሆን በማንኛውም ሰአት ወንዶች ድምፃችን ከፍ ሴቶች ዝቅ በማድረግ ተክቢራ ልንል ይገባል።

الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
@heppymuslim29
2025/10/15 20:19:02
Back to Top
HTML Embed Code: