ጥሩ እና መጥፎ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ውስብስብ ናት፣የማትፈታ ትብታብ፤
የመባዘን መዝገብ፣የድባቴ ኪታብ።
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ልክ እንደ ወንዝ ናት!
እንባችን እንጂ አይመለስም ትናንት።
ካገኘነው በላይ ያጣነው 'ሚገደን፣
ከማለሙ ቀድመን መታመሙን ለምደን!
.
ጥሩው ነገር. . .
ለመፍጠር የኛን ቀን. . .
ታግለን!
ተፋልመን!
አልያም ተናንቀን. . .
እንደ ዐፄ በጉልበት ወይ ደሞ በሰላም፤
ሁሉም ነገር ያልፋል. . .
ብንወድም ብንጠላም!
.
ጥሩው ነገር. . .
የማለዳ ተስፋችንን፣ቢበላውም ጤዛ፤
በሕላዌ መስክ ላይ. . .
ምን ትግል ቢበዛ፣
እኛም ልክ እንደ ሕይወት
አይደለንም ዋዛ!
.
@huluezih
@huluezih
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ውስብስብ ናት፣የማትፈታ ትብታብ፤
የመባዘን መዝገብ፣የድባቴ ኪታብ።
.
መጥፎው ነገር. . .
ሕይወት ልክ እንደ ወንዝ ናት!
እንባችን እንጂ አይመለስም ትናንት።
ካገኘነው በላይ ያጣነው 'ሚገደን፣
ከማለሙ ቀድመን መታመሙን ለምደን!
.
ጥሩው ነገር. . .
ለመፍጠር የኛን ቀን. . .
ታግለን!
ተፋልመን!
አልያም ተናንቀን. . .
እንደ ዐፄ በጉልበት ወይ ደሞ በሰላም፤
ሁሉም ነገር ያልፋል. . .
ብንወድም ብንጠላም!
.
ጥሩው ነገር. . .
የማለዳ ተስፋችንን፣ቢበላውም ጤዛ፤
በሕላዌ መስክ ላይ. . .
ምን ትግል ቢበዛ፣
እኛም ልክ እንደ ሕይወት
አይደለንም ዋዛ!
.
@huluezih
@huluezih
"የሴቶች ቦታ ኩሽና ነው!"
.
ይኽ የተፈፀመው በሐገረ ጀርመን ነው። እየተካሔደ የነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ በሴት ዳኛ እየተመራ ነበር። በጨዋታው መሐል በተፈፀመ የጨዋታ ሕግ-ጥሰት (Foul) እንስቷ ዳኛ ከሪም ዴሚርባይ ለተባለ ቱርካዊ ተጫዋች ቀይ ካርድ በመሥጠት ከሜዳ እንዲወጣ ትዕዛዝ ታስተላልፋለች። በውሳኔው የተበሳጨው ተጫዋች ውሳኔውን በጸጋ ከመቀበል ይልቅ ወደ ዳኛዋ ተጠግቶ "አንቺ ኩሽና ውስጥ ነው መኾን የነበረብሽ፣ቦታሽ እዚህ አይደለም!" ሲል ተደመጠ።
.
ከጨዋታው በኋላ ለፊፋ የከሰሰችው ዳኛዋ ጉዳይዋ በፍጥነት ትኩረት ተሠጥቶት ተጫዋች ለቅጣት ተዳረገ። ጉዳዩ እዚህ ጋር አያበቃም። በተጫዋቹ ላይ ከተላለፉት ቅጣቶች መካከል "ተጫዋቹ በጀርመን የታዳጊ ሴቶች ሊግ ዳኛ ኾኖ አምስት ጨዋታዎችን እንዲመራ" የሚል ይገኝበት ነበር። በውሳኔው መሠረት በመጀመሪያ የዳኝነት ቅጣቱ ላይ ካፖርቱን፣ ቡትስ ጫማውን በማድረግ ጨዋታ ሊመራ ሳይኾን ፊልም የሚሠራ ተዋናይ በመምሰል ጨዋታውን መምራት ጀመረ። በጨዋታውም ለ8 ሴት ታዳጊ ተጫዋቾች ስምንት ቀይ ካርዶችን ሠጥቷል።ከጨዋታው በኋላ "ለምን ይኽን አደረግክ?" ተብሎ ሲጠየቅ "ምክንያቱም ሴቶች ኳስ ሜዳ ሳይኾን ኩሽና ነው ቦታቸው!" የሚል ለቅጣት የዳረገውን ንግግር መድገሙ አነጋጋሪ ጉዳይ ኾኗል! 😏

ከልጅነት አንዲት ገጽ
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰደብኩት ስድብ ‹‹ከብት›› የሚል ነበር፡፡የሰውነት ማጎልመሻ መምህር ነበር የሰደበኝ፡፡ በወቅቱ ምንም አልመሰለኝም ነበር፡፡እየዋለ እያደር ግን ይነደኝ ጀመር፡፡ ስድቡ አይደለም. . .ግልጽ አለመኾኑ እንጂ፡፡ ‹‹ከብት ሲል ምን ማለቱ ነው? ብዙ ዓይነት ከብት አለ…የትኛውን ነው ሊለኝ የፈለገው? በሬ ነው? በግ ነው? ላም ነው? የጋማ ነው ወይስ ያልጋማ ነው?››
ለዚህ ስድብ ያበቃው. . .ሰውነታችንን እንዴት እንደምናጎለምስ ለማስተማር እየሞከረ ሳለ ከጓደኞቼ ጋር ስሳሳቅ በማየቱ ጓደኞቼ ፊት ሊያሸማቅቀኝ አስቦ ‹‹በዚያ በበጋ!›› የሚለውን መዝሙር እንድዘምር አዘዘኝ፡፡እኔም አሻፈረኝ አልኩት፡፡
.
በመሠረቱ በዚያ በበጋ የሚባለውን መዝሙር አሁንም ድረስ አልወደውም፡፡ አለመውደድ ብቻ ሳይኾን ይኽ መዝሙር የእኛን ትውልድ ያሰናከለና ዛሬም ድረስ ከመዝሙርነት የዘለለ ተልዕኮ እንዳለው አምናለሁ፡፡
.
ከሥር መሠረቱ ላስረዳ!
በእኛ ዘመን አንድ ተማሪ አዕምሮው ለትምህርት ዝግጁ መኾን አለመኾኑ ሳይጣራ ነው ወደ ትምህርት ቤት የምንላከው፡፡የቀኝ እጅህ በጭንቅላትህ ዞሮ ግራ ጆሮህን ከነካ አለቀ! ማምኮ ደብተርህን ይዘህ፣ የዳርማር ቆዳ ጫማህን ተጫምተህ፣ ከአባትህ ሱሪ በተረፈ ጨርቅ ዩኒፎርም ተሰፍቶልህ ወደ ትምህርት ቤት ትሔዳለህ፡፡ እኔ ተፈጥሮ እጄ አጭር ስለነበረ በዘጠኝ ዓመቴ ነው ትምህርት የጀመርኩት፡፡እጅህ ረጅም ከኾነ ደሞ በአራት ዓመትህም ተማሪ ቤት ከመግባት የሚያድንህ ምድራዊ ኃይል የለም!
.
የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ቤት ስሔድ አባቴ ነበር ያደረሰኝ፡፡ ለራሱ ካስሰፋው ሱሪ በተረፈው ጨርቅ ዩኒፎርም ስላሰፋልኝ የዚያን ቀን አንድ ዓይነት ነበር አለባበሳችን፡፡ በዚህ ምክንያት የኾነ ባዕድ ስሜት እየተሰማኝ ነበር፡፡ የኾነ አለ አይደል. . .አባቴን ትምህርት ቤት የማደርሰው ዓይነት ስሜት፡፡
የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜዬ ላይ አንዲት መምህርት ገብታ ‹‹በዚያ በበጋ›› የሚለውን መዝሙር ታዘምረን ጀመር፡፡ ግጥሙን ታስታውሳላችሁ?
‹‹በዚያ በበጋ፤በዚያ በበጋ
እጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ!››
.
ጥያቄ አይኾንባችሁም?! አንድ ተማሪ በልጅነቱ ዕውቀትን ፍለጋ በሔደበት ትምህርት ቤት ‹‹ዕጮኛ ጠፍቶ ፍለጋ!›› የሚባለውን መዝሙር መማሩ ወደ ብልጽግና የምናደርገውን ጉዞ አያደናቅፍም ወይ?. . .አያሳስብም?
.
‹‹መሸበትና ሰው ቤት ገባ፣
ልጅቷን ዐያት፣ተከናንባ
ወደዳት! ወደዳት! ይዟት ጠፋ በለሊቱ. . .
ከዚህ ግጥም መረዳት ያለባችሁ የመጀመሪያው ነገር የእኛ ዘመን ልጆች እንደምንከናነብ ነው፡፡ ወላጆቻችን ብርድ እንዳይመታን የማያለብሱን ነገር አልነበረም፡፡ አጋነንክ አትበሉኝና አንድ ክረምት ላይ ብርድ እንዳይመታኝ እናቴ ጋቢ፣ብሉኮ፣ የአባቴን ጃኬትና የእሷን ፎጣ ደራርባ ብርድ እንዳይመታኝ ስትሞክር ሙቀት መታኝ! ከሰሚ ሰሚ የሰማሁት ነው!
.
እና የበዚያ በበጋ አስቀያሚው ነገር ጠያቂ ትውልድ እንዳይፈጠር ማድረጉ ይመስለኛል፡፡ ተከናንባ ዐይቶ የወደዳትን ልጅ ይዟት ጠፋ፣ ከዚያ ዓባይ ደርሰው ለመሻገር ሲጥሩ እሱ ምንም ሳይኾን እሷ ሠጠመች፡፡እሱ አልቅሶ እንደተመለሰ ነው ታሪኩ የሚነግረን፡፡
.
ብዙ መሠረታዊ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ መዝሙር ነው፡፡ ለምሳሌ ልጅቷን ይዟት የጠፋው በበጋ ነው፡፡አባይ ደግሞ በበጋ አይሞላም፡፡ክረምት ቢኾን መስመጧ ያሳምነኝ ነበር፡፡ ‹‹በቃ ሞተች አዘነላት!›› በሚል ምክንያት እንዴት ከሕግ ሊያመልጥ ቻለ? ይኼ መዝሙር በፍትሕ ተስፋ እንድቆርጥ ያደረገኝ ያኔ ነው፡፡ ገድሏት አባይ በረሃ ላይ ቀብሯትስ ቢኾን? ይኼ መዝሙር ሊነግረን የፈለገው ነገር. . .ሲመስለኝ ‹‹እዚህ ሐገር ውስጥ የሚገደል ሰው ገዳዩ ተጣርቶ ለሕግ ስለማይቀርብ ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ፖለቲካ ውስጥ ላለመግባት መሞከር እንዳለባቸው ነው!››
.
ያ ሰውነቱ ያልጎለመሰ ሰውነት ማጎልመሻ መምህር ይኼን ዘምር ሲለኝ አልዘምርም ብዬ ነው እንግዲህ ‹‹ከብት!›› የተባልኩት፡፡ አድጌ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ወጥቼ እንኳ አንድ ቀን ያን መምህር አግኝቼ ‹‹ከብት! አይደለሁም!›› ብዬ ‹‹የከብትን ዘርፈ ብዙ የሌማት ትሩፋቶች›› ለማስረዳት ዕድሉን ባገኝ ብዬ እመኝ ነበር፡፡ ደስ የሚለው ነገር ምኞት ብቻ ኾኖ አልቀረም፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ መምህርነቱን ትቶ በሌላ የሥራ ዘርፍ ተሠማርቶ አገኘሁት፡፡ አዲሱ ሥራ ምን ቢኾን ጥሩ ነው? ወተት አከፋፋይ! በስተመጨረሻም የከብት ጠቃሚነት ገብቶታል ማለት ነው! ይኼ….ከብት!

ስለ መጽሐፉ እና ስለ 53,500 ብር
.
ከዓመት በፊት አንድ ባለኃብት "መድረኮች ላይ የምታቀርባቸውን ጽሑፎች እወዳቸዋለሁ! ለምን ሰብሰብ አድርገህ አታሳትማቸውም?" ሲለኝ ካነሣኸው አይቀር ብዬ "ተሰብስበው በባለሙያ ሳይቀር ተገምግመው አልቀዋል፤ አንዳንድ ጥቃቅን ጉዳዮችን ብቻ ማስተካከል እንጂ ለህትመት ዝግጁ ናቸው...ከፋይናንስ ውጪ" አልኩት። እሱም "ያልካቸውን ጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ጨራርስና ለህትመቱ መፍትሔ አናጣም...ስትጨርስ አሳውቀኝ!" ብሎ ተስፋ ሠጥቶኝ ተለያየን። ከዚያ በኋላ በስልክም በአካልም በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተን እየጨረስኩ መኾኔን አውግተን ስጨርስ እንድነግረውና ወደ ህትመት የሚገባበትን ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባበት ነግሮኛል።
.
በመጨረሻ መጽሐፉ እኔ በቂ በምለው ደረጃ አለቀ። ማለቁን ሳሳውቀው "እሺ! በጣም ጥሩ! መልሼ እደውልልሃለሁ!" ብሎ ንግግራችን ተጠናቀቀ። ከዚያ በኋላ ግን እንደ ወትሮው ስልክ ማንሳት፣ቴክስት መመለስና ራሱም ሳይደውል ጊዜያት አለፉ። እኔም የሰውዬው ሁኔታ እየከነከነኝ በራሴ ወይም በሌላ መንገድ የማሳትምበትን መንገድ ማሰብ ጀመርኩ። በኾነ አጋጣሚ ታዲያ ባለኃብቱ ጋር በቅርበት የሚሠራ አንድ ሰው አገኘሁ። በወሬ ወሬ መሐል ስለ ባለኃብቱ ድንገተኛ የሐሳብ መቀዛቀዝ አነሣሁ። ይኽው ሰው ስለ ጉዳዩ ባለኃብቱ አጫውቶት እንደነበረና
ባለኃብቱ መጽሐፍ ለማንበብ የሚኾን ጊዜ ስለሌለው መጽሐፉን ቢያሳትም የሚመጣበት "መዘዝ" መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በእኔ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን እንደጠየቀና እንዳማከረ ነገረኝ።
እኔም መጽሐፌን ስለምተማመንበት፣ እሱም ቢያሳትመው ኩራትና ውለታ እንጂ ችግር ውስጥ የሚያስገባው አለመኾኑን መመስከር የሚችሉ ሥራውን ያነበቡና የገመገሙ ባለሙያዎችን ሳይቀር ለማገናኘት ፍቃደኛ መኾኔን ነገሬው ጨዋታችን ተቋጨ።
.
በሥራና በኑሮ ውጥረት ሳላስበው ጊዜው እንደ ንፋስ ሽው ብሎ አልፎ ከባለኃብቱ ቅርብ ሰው ጋር ዳግም በአካል ተገናኘን። እኔም ባገኘኋትን ትንሽ ቅጽበት ባለፈው ስላወጋነው የመጽሐፌ ጉዳይ በጨረፍታ አነሣሁበት። ባለኃብቱ እኔን የሚያውቁኝንና እሱ የሚያምናቸውን በመሐል ያሉ ሰዎችን "ላሳትምለት ወይስ ይቅርብኝ?" ብሎ እንዳማከረ ሰማሁ። እነዚህ በእኔና እሱ መሐል ያሉ "ታማኝ" ሰዎቹም ያላነበቡትንና ሐሳቡ እንኳ ስለምን መኾኑን በውል ሳያውቁ "ይቅርብህ!" ብለው ጥርጣሬ እንደዘሩበት ነገረኝ። ከአራት በላይ በደንብ የማያውቁኝ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች አንብበው የሚታረመውን አርመው የወደዱት ጽሑፍ በሚያውቁኝና መጽሐፌን ባላነበቡት ሰዎች ምክንያት መሰናከሉ ልቤን ሰብሮኝ ዶሴው ተዘጋ።
.
ከዚህ ሁነት በኋላ በወዳጆች ምክርና እገዛ
መድረክ አዘጋጅቼ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ በቅድመ-ክፍያ በመሸጥ ህትመቱን ማሳካት ነበር ቀጣዩ መንገድ። ኾኖም በአካልም ኾነ በቅርበት ከማውቃቸው ሰዎች ይልቅ ጥቂት በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚያውቁኝ ሰዎች መጽሐፌን አምነው ቀድመው ገዝተውኛል። ባለብኝ የመጠየቅ ኀፍረትና የመሸማቀቅ ባሕሪ ገፍቼ ብዙ ባለመጠየቄ እስካሁን 53,500 ብር ላይ ለመቆም ተገድጃለሁ። ጥሬ ግሬ ራሴ ለመሙላት ባስብም በፍጥነትና በጥራት ወደ ህትመት መድረስ አዳጋች ኾኗል። በየቀኑ የሚጨምረው የወረቀት ንረት አንዱ መሰናክል ቢኾንም በየቀኑ የሚሻሻሉ ታሪኮችና የሐሳብ ብስለቶች ትንሽ ተስፋዬን ባለበት ያቆዩታል። አሁንም ብዙ ነገር ውስጥ እየገባሁ ለዚህ መጽሐፍ መታተም እየታተርኩ ነው...ቀድመው አምነው ለገዙኝ በአካል ለማያውቁኝ ሰዎች ክብሬ ከፍተኛ ነው። ለመዘግየቱ ይቅርታ እጠይቃለሁ።በዙሪያዬ ያሉ ግማሹን ብር በብድርም ኾነ በሌላ መንገድ መሙላት የሚችል ዘመድ፣ወዳጅ ወይም ሌላ ባለኃብት ሳይኾን በአካል ሳያውቁኝ እንደገዙኝና እንዳመኑብኝ ዓይነት ቀናዎች ጋር በአጋጣሚም ኾነ በስሌት ስላልተገጣጠምኩ፣ የራሴም ሁሉም ቦታ የመግባትና የመመላለስ ስብዕና ስላልታደልኩ ከማሳካት ይልቅ ለመዘግየት ቅርብ ኾኛለሁ።
.
አዘለም ተሸከመም አንዳንዴ ከጋዜጠኝነትና ከሥነ-ጽሑፍ ሥራዎቼ እየወጣሁ በሌላ ሙያዎች ውስጥ ለዚህ መጽሐፍ መፍትሔ እየፈለግኩ ነው። ከይቅርታችሁ በኋላ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ።