የማለዳ ማስታወሻ #157
.
ሔጄ ተመለስኩ። የሔድኩት ወደ 'ማይደሰስ፣ ወደ 'ማይታይ እና ወደ 'ማይጨበጥ ስሜታዊ ሁኔታ ነው። የማላውቀውን የራሴን ስብዕና ዐይቼ ራሴን ያደነቅኩበት፣ ራሴን የጠላሁበት ደግሞ "አገኘሁት" ብዬ የማስበውን ማንነቴን እንደ ጭስ የበተንኩበት ሁኔታ ውስጥ ነው ሔጄ የተመለስኩት።
.
መማር ከፈለግክ ከሕይወት የተሻለ መምህር የለም። "እንዲህ ዓይነት ሰው ነኝ!" ብለህ ስለ ራስህ እርግጠኛ የኾንክበት እምነትህ የሚናድበት ቀን ይመጣል። አሁን የምታውቀው ማንነትህን ያወቅከው እዚህ ስለኾንክ ብቻ ነው። የነገው ማንነትህ ሕይወት ነገ በምታደርስህ ቦታ እና ሁኔታ ላይ ይወሰ'ናል።
.
የዛሬው ማንነቴን ትናንት እንደ ነብይ ተንብያችሁ ብትነግሩኝ ኖሮ አላምናችሁም ነበር። "ፈጽሞ አላደርግም!" ያልኩትን አድርጌያለሁ፣ "ብሞት አልኾንም!" ስል የከረምኩትን ኾኜያለሁ። ከሕይወት ገጾች አይገመቴነቷ ይስበኛል።
.
"ማምለጫ" ብለህ የዘለቅከው በር ወህኒ ቤትህ ኾኖ ይገኛል፣ መሻገሪያ ያልከው "ጀልባ" መስጠሚያህ ይኾናል። ሕይወት የገባህ ቀን በበሩም በጀልባውም አትፈርድም። ያንተም ጥፋት አታደርገውም። ሕይወትን የምታይበት አንፃር(Angle) ያንተ ምርጫ አይደለም። ሕይወት ፐውዛ ያስቀመጠችህ ቦታ ነው ዕይታህን የሚመርጥልህ!
.
ይልቅ ስሕተትንና መዘዘኛ አጋጣሚን የሕይወት አንድ አካል አድርገህ ተቀብለህ ከሌላኛው ጫፍ ለመነሣት ትሞክራለህ። "ረዥም ዕድሜ እኖራለሁ!" ብለህ እያሰብክ ለውሳኔህ አትዘግይ...ማንም አይኖርልህም፣ ማንም አይሞትልህም....ታዲያ ለምን ሥርዓት፣ ሰዎች አልያም ሆድህ ይወስንልሃል?
(ማንምም አይወስንልህ!)
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih