"ጽሑፍ ምን ያደርጋል?"😭
.
ከስምንት ዓመታት በላይ ከእኔ ጋር የቆየው ላፕቶፔ እስትንፋሱ ተቋረጠ። የስምንት ዓመታት ታሪኬ ብቻ አይደለም የወደመው። እንደ ሌሎች ደራሲያንና ጸሐፊያን በእስክርቢቶ ለመጻፍ ልምድም ዐውድም ስለሚጎድለኝ የወደፊት ጸሑፊቼም በአግባቡ የሚወለዱ፣ ቢወለዱም ስሜት አልባ ሚኾኑ ይመስለኛል።
.
"ሰው እንዴት በዚህ ልክ ከቁስ ጋር ረቂቅ የኾነ ትስስር ሊኖረው ይችላል?" እላለሁ ከኮምፒዩተሬ ጋር ያለኝን ቁርኝት ሳስተውል። ስለእኔ ከኮምፒዩተሬ በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀኝ ያለ አይመስለኝም። ሐዘኔን፣ደስታዬን፣ ግራ መጋባቴን ሁሉ ከትቤበታለሁ። ተዝናንቼበታለሁ፣ ተጽናንቼበታለሁ. . .ደሞ አሻግሬ የሰዎችን ቁስል አክኬበታለሁ። ከቤተሰቤ አንዱን ያጣሁ ያክል ጠዝጥዞኛል።
.
በአምላኬና በኮምፒዩተሬ እገዛ ሁለት መጽሐፎችን ጽፌበት ለህትመት አብቅቻለሁ። መድረኮች ላይ የቀረቡ ሁሉም ጽሑፎቼ በዚህ እስትንፋሱ በተቋረጠው ላፕቶፔ በኩል ያለፉ ናቸው። ሦስተኛ መጽሐፌ 95% (ዘጠና አምስት በመቶው) የሚኾነው አልቆ ነበር. . .ግን ዱኒያ ውስጥ ያሉ ሁሉ የጊዜ ገደብ አላቸውና ላፕቶፔም የጊዜ ገደቡን ጥሶ አልፏል። አሁን ላይ ብዙም በስልክ ዘለግ ያለ ነገር የመጻፍ ልምዱ ስለሌለኝ ከጽሑፍ ራቅ ብያለሁ. . .የዚህም ቅሬታና ልዝብ ተስፋ መቁረጥ "ጽሑፍ ምን ያደርጋል?" እያስባለኝ ነው። ግን ሁሉም ለበጎ አይደል? በጎውን አያዘግየው😔
R.I.P dear😭

የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሳሞግስ ቀልብ የምሰልብ፤
ስተች ነውር የምገልብ፤
ከአባት አያቶቼ ሽለላ የተዋስኩ፤
በሰልፍና እንቅልፍ ዘመኔን የጨረስኩ !
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
በማሳ መሐል ኾኜ በረሃብ የተቀጣሁ፣
ዓለም ላይ ለመድረስ. . .
ትራንስፖርት ያጣሁ!
በታሪክ መሥሪያ ዕድሜ፣
ታሪክ 'ምተረጉም፤
የማያስኬድ መንገድ
ለሰው የምጠቁም!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ)
.
ግፍ እና ጡር አምላኬን ያስረሣኝ፤
ፀበል ሙሉ ሐገር፣ልቤን ያላነፃኝ!
አርሼ ዘርቼ መሶቤ የከዳኝ፤
ከአረር ጥይት ይልቅ በጀት የሚጎዳኝ!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
ቅሬታና ምሬቴን ከእልባት ለማድረስ
በጠረጴዛ ዙሪያ አድፍጬ ምቧቀስ
ጉልበተኛ ሲነካኝ. . .
"ልብ አድርጉልኝ!" እያልኩ ሁሉን የምታገስ!
የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!
.
@huluezih
@huluezih
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሳሞግስ ቀልብ የምሰልብ፤
ስተች ነውር የምገልብ፤
ከአባት አያቶቼ ሽለላ የተዋስኩ፤
በሰልፍና እንቅልፍ ዘመኔን የጨረስኩ !
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
በማሳ መሐል ኾኜ በረሃብ የተቀጣሁ፣
ዓለም ላይ ለመድረስ. . .
ትራንስፖርት ያጣሁ!
በታሪክ መሥሪያ ዕድሜ፣
ታሪክ 'ምተረጉም፤
የማያስኬድ መንገድ
ለሰው የምጠቁም!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ)
.
ግፍ እና ጡር አምላኬን ያስረሣኝ፤
ፀበል ሙሉ ሐገር፣ልቤን ያላነፃኝ!
አርሼ ዘርቼ መሶቤ የከዳኝ፤
ከአረር ጥይት ይልቅ በጀት የሚጎዳኝ!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
ቅሬታና ምሬቴን ከእልባት ለማድረስ
በጠረጴዛ ዙሪያ አድፍጬ ምቧቀስ
ጉልበተኛ ሲነካኝ. . .
"ልብ አድርጉልኝ!" እያልኩ ሁሉን የምታገስ!
የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!
.
@huluezih
@huluezih
አንቺ የሌለሽበት አራተኛው ረመዳን😢
.
ጊዜው አይታክተው፣መጋለቡን አይተው፤ እኔም በተዛነፈው የሕይወት መንገድ፣ በተስፋ ባንኜ አንድ ስንዝር አልራመድ፤ አለሁ በቆምኩበት፤ አለሽ ባልኖርሽበት!
.
ሰውነቴ ውስጥ ደሜ እስካለ ድረስ በእያንዳንዷ ጠብታ ውስጥ የማያረጅ፣ የጊዜ ኃያል ቁር የማያፈዝዘው፣የማያደበዝዘው ዘላለማዊ ትዝታሽ፣ ጠረንሽ፣ ሣቅሽ፣ ምክርሽ፣ በአቅመ ቢስነት ዘመኔ በጡትሽ በኩል የመጠጥኩት ደግሞም የማጌጥበት የእናትነት ማርዳ አለ። ሰውነቴ ውስጥ ነፍሴ እስካለ ኖረሽ ባየሻቸው የምላቸው ተራ ቀኖች አሉ። ተራ ቀን ውስጥ ከተራነት የሚያወጣኝ የአለኝታ ጎህ፣ ከተርቲበኛነት የሚያላቅቅ ውድ ቅርስ አንቺ ውስጥ አኑሬያለሁና።
.
እንድደርስ የፈለግሺው ቦታ ላይ ልደርስ አንድ ሐሙስ ሲቀርሽ፣ አንድ ረቡዕ የጎደለሽ፣ ሁለገብ ኾነሽ በሕይወቴ እያንዳንዱ ጽንፍ ውስጥ የገባሽ፣ መንገዴን ለማቅለል ከእቶን እሳት የተባሽ፣ እኔን ለማቅናት ዘላለም የሚያጥርሽ፣ ያልጠረጠርሺው ነገር. . ."የትም መድረስ አይከብደኝም፣ ጎኔ ቆመሽ መቻሌን ቀድመሽ ካመንሽ!"
.
የረመዳን ወጋገኖች ያላንቺ ምሉዕ አያደርጉም።ያላንቺ ግን በትዝታ፣ በናፍቆት በፀፀት ያልፋሉ እንደ ጉም።
.
ከመራቅሽ አራራቅሽ! ከዙሪያ-ገቡ ቅኝት የውስጥ ውስጥ ጭርታው! ሰዎች መሐል ያለ ኦናነት! ከጭብጨባው ከአድናቆቱ፣ ስኬት ውስጥ የመሸገ ትርጉም አልባነት ልብ ይሰረስራል። የማይታይ ቀለም አልባ ገመድ አካሔድን ያስራል። እንዲህም ቀን ይቆጠራል፣ እንዲህም ዘመን ይበርራል። የትናንት ሞገደኛ ሣቆቻችን፣ የትናንት ሌሊት የማይበግራቸው ውይይቶቻችን ዛሬ ጥቁር ለምድ ለብሰው ብቅ ብለዋል። ጉልበቴ ልሟል፣ ሕሊናዬ ግን ባጣሽ ቀን. . .ባጣሽ ቦታ ላይ ሐውልት ኾኖ ቆሟል። ዘመን ግን እንዲህም ይቆጠራል፣ ጊዜ ግን ዛሬም ይበርራል። አንድ. . .ሁለት. . . ሦስት. . . እነሆ በሌለሽበት አራተኛው ውድ እንግዳ መጥቷል. . .
.
ረመዳን ሙባረክ ለሁላችንም!

የማለዳ ማስታወሻ #149
.
እጅ ለእጅ ተያይዘን ቁልቁለት የወረድነው፣ ልብ አሙቅ ቃላት እየተለዋወጥን ጋራ የወጣነው፤ አንዳችን ለአንዳችን በክፉ ቀን መደበቂያ፣ በብሩህ ቀን መድመቂያ የኾንነው. . . እዚህ ደርሰን እንደ ባዕዳ፣ እንደ ባይተዋር የሩቅ ሰው ለመኾን አልነበረም። ግን የማይጠበቀው ይኾናል፣ የማይታሰበው ይከሰታል። ማሸነፍ በማንችለው ድብቅ ራስ ወዳድነት ያሳለፍነው ሁሉ ልቦለድ፣ ያቀድነው ሁሉ ተረት ይኾናል።
.
አሁን እንዴት ካንቺ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ እንደምችል አላውቅም። የሚመጥነኝን መልስ አላገኝም ብዬ እፈራለሁ። ሁሉም አብቅቷል ብዬ መንገድ እጀምርና ነገ የሚጠብቀኝን ፀፀት ፈርቼ እመለሳለሁ። ልቤ ስሔድ ቁም፣ ስመለስት ተው ይለኛል። ልቤ ላይ የታተመው ጠረንሽ ተቀይሮብኛል። ዓይንሽ እንደፊቱ እርጋታ የለውም። ንግግርሽ ውስጥ ተስፋ ጎድሎብኛል። ድልድዩን ተሻግረን ያለምናቸው ነገዎች ጭጋግ አደብዝዟቸዋል። እጄ ላይ የቀሩ የልፋቴን እንቁላሎች ሁሉ ባንቺ ቅርጫት ውስጥ ለማስቀመጥ የልቤ ላይ እምነት አቅም ያንሰዋል።
.
ማጠናከሪያ ትምህርት ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ? ዋናው ትምህርታችን ላይ እንድንጎብዝ ባለን ትርፍ ሰዓት የሚሠጥ ትምህርት ነው። ምናልባት አንዳችን ለአንዳችን ማጠናከሪያ ትምህርት ነበርን። ዋናው ሕይወታችን ላይ እንዳንሰንፍ ለመጠነካከር የተገናኘን!

እነሆ አዲሱ ላፕቶፔን ተዋወቁት!
.
የተጠነሰሰ ነገር ኹሉ ጉዞው ወደ ማክተሚያው ነው። የተጀመረ ነገር ሁሉ የማይመለስ ማብቂያ አለው። ሕይወትም ማለት በጅምሯ እና በፍጻሜዋ መሐል ጉራማይሌ ቀለም ያላት አጭር መንገድ ነው።
.
ከአንድ ወር ገደማ በፊት የእኔና የላፕቶፔ ታሪክ ተፈፀመ። የእሱ ስብራት የእኔም ኾነ። ግን ብዙ ሰዎች አፅናኑኝ። መልካም ተመኙልኝ። ማድረግ ቢችሉ የሚያደርጉ ሰዎችን ዐየሁ። ግድ የማይሠጣቸውንም ሰዎች ለየሁ። ሕይወት ያለ "Apitite" ቀጠለ። (ቀና አስተያየትና መልካም ምኞታችሁን ያሰማችሁኝን ኹሉ እዚህ ጋር አመሥግኜ አልፋለሁ!🙏)
.
በመሐል አንድ ወዳጄ ለዓመታት ከተጠፋፋን በኋላ ደውሎ ከሐገር እንደወጣ ነገረኝ። ክፉ ደጉን አብረን አሳልፈን ከዓመት በላይ ለሚኾኑ ጊዜያት ድምጹን አልሰማሁም።ያለበትን ጥግ አላውቅም ነበር፣ እሱም ያለሁበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያመች ሁኔታ ውስጥ አልነበረም።
.
በቃላት ልውውጣችን መሐል "ምንም እንኳ ገና በሰው ሐገር ኾኜ በሁለት እግሬ ባልቆምም ወይ ስልክ ወይ ላፕቶፕ ልግዛልህ!" ብሎ አጥብቆ ጠየቀኝ። የላፕቶፔን መሰበር አያውቅም። መናገርም አልፈለግኩም። ግን ለችግሩ ጊዜ የነበረኝን ሌላ ላፕቶፕ መሸጤንና ለእሱ ብዬ ብዙ መበደሬን ያውቃል። ለእሱ ውለታ መመለሱ ነበር። ልቤን የነካ ታሪክ ነው። ልበ-ቀና እና ከሚመኝልኝ ስኬት በላይ አብዝቼ የምመኝለት ፈርጀ ብዙ ሰው ነው! (አላህ ሂዳያ እንዲሠጣቸው ከምለምንላቸው ወዳጆቼ አንዱ ነው)
.
በጽሑፎቼ ይተማመንብኛል።"ብዙ መሥራት ትችላለህ" ብለው ከሚያምኑብኝ በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ጎራ ነው። በመጨረሻም "ተቸግረንም ቢኾን ደህና ነገር እንግዛ!" ብሎ ትንሽ ብር ተበድሮ እና ጨምሮበት አዲስ እና ቀልጣፋ ላፕቶፕ ላከልኝ። አሁን ሥራዎቼ ካቆሙበት ይቀጥላሉ። የዛለ መንፈስ የሚያድስ ወዳጅ ኾኖ ብቅ አለ።
.
በዚህ ታሪክ ውስጥ ዋናው ትምህርት "አምላክህ የማይተካልህን ነገር አይነፍግህም!" የሚል ነው። የሚደግፉህን፣ ግድ የማይሠጣቸውን ጠጋኝ ቃል ከማቃበል ጀምሮ ለአንተ ያላቸውን ምልከታ በደንብ ተረድተህ ስታበቃ አምላክህ የነጠቀህን በተሻለ ይተካልሃል።