መልካም ረመዳን ይኹንልን! የነፍስ እድሳት፣የቀልብ ሰላም የምናገኝበት ጾም ያድርግልን!🖤
Forwarded from 📃ከብጥስጣሽ ወረቀቶች📄 (⚖️ Mati 💉)
ምላሽ የመስጠት ጥበብ


አንድ አህያ ከመስጂድ ፊት ለፊት ሞቶ ተገኘ። ይህን የተመለከቱት ኢማም ከንቲባውን ጠርተው እንዲህ አሉት፡-“ክቡር ፕሬዝዳንት አንድ አህያ ከመስጂድ ፊት ለፊት ሞታለች”

ከንቲባው፡-“ሼኽ ሆይ ከኔ ምን ፈልገው ነው ታድያ?”

ኢማሙም መለሱ፡-“የማዘጋጃ ቤቱ ሃላፊዎችን ጥራቸው። ሰራተኞቹ መጥተው አህያውን ከመስጂዱ ያንሱልን።”

ከንቲባው በኢማሙ ላይ እየተሳለቀ፡-“ያ ሼይኹ እኔ በሃይማኖታችን እንደተማርኩት ከሆነ እናንተ ናችሁ ሟችን አጥባችሁ የመቅበር ግዴታ ያለባችሁ”

ኢማሙም በተረጋጋ መንፈስ መለሱ፡-“ልጄ የተናገርከው ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ አህያዋ መሞቷን ግን ለአንተ መናገር ነበረብኝ ምክንያቱም እኛ አጥበን የመቅበር ግዴታ እንዳለብን ሁሉ፤ የሟች ቤተሰብ የቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ለመጨረሻ ግዜ ሬሳውን እንዲሰናበት የማሳወቅ ግዴታም አለብን”
🙂



         📌 ማጋራት አይዘንጋ !

  ⭐️https://www.tg-me.com/From_broken_papers
  ⭐️
https://www.tg-me.com/From_broken_papers
  ⭐️
https://www.tg-me.com/From_broken_papers
  ⭐️
https://www.tg-me.com/From_broken_papers

              🚸  ይቀላቀላሉን 🫵
. . .of the day!😎
. . .of the day!😎
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይኼ ፖኬጅ ላላችሁ ብቻ የተጋበዘ ነው!😋
@huluezih
. . .of the day!😔
"አንዳንዶቻችን መኖራችን የሚታወቀው ስንሞት ነው!"

ምን ማለት ይመስላችኃል?
. . .of the day!😎
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምወደውን ግጥም ጋበዝኳችሁ! (ቲክቶክ ላይ ደሞ ብትመጡልኝ...እፈልጋችኅለሁ!🥰

https://www.tiktok.com/@feysel_amin?_t=ZM-8w1ZJvedRTh&_r=1
Forwarded from 📃ከብጥስጣሽ ወረቀቶች📄 (⚖️ Mati 💉)
እውነት ግን ትወጂኛለሽ፧ ካንጀትሽ ከልብሽ ጓዳ ትተሽኝ አትኮበልዪም፧ ብታመም ወይም ብጎዳ?

እውነት ግን ትወጂኛለሽ?

እውነት ግን ታፈቅሪኛለሽ?

ዘላለም ነሽ ከኔ ጋራ፧ወይንስ ሌላ ታያለሽ?

ተዪው

:

ለመልሱ አትብሰልሰዪ ለመልሱ አትጨነቂ

ሰው እንጂ አምላክ አይደለሽ…

እንኳንስ የዘላለሙን የነገን እንኳን አታወቂ!

                   🥀🥀🥀
                        



📌 ማጋራት አይዘንጋ !

  📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers

               🚸  ይቀላቀላሉን 🫵
Forwarded from 📃ከብጥስጣሽ ወረቀቶች📄 (⚖️ Mati 💉)
ለኔ ብለሽ ትሞቻለሽ አዎ !
አይ.......አይ  ቆይ  ይህ  ቀላል ነው ፤
ለኔ ብለሽ ትኖሪያለሽ ! ¿?
😒


📌 ማጋራት አይዘንጋ !

  📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers
 
📮https://www.tg-me.com/From_broken_papers

               🚸  ይቀላቀላሉን 🫵
. . . of the day!😎
. . . Of the week🙄
የማለዳ ማስታወሻ #157
.
ሔጄ ተመለስኩ። የሔድኩት ወደ 'ማይደሰስ፣ ወደ 'ማይታይ እና ወደ 'ማይጨበጥ ስሜታዊ ሁኔታ ነው። የማላውቀውን የራሴን ስብዕና ዐይቼ ራሴን ያደነቅኩበት፣ ራሴን የጠላሁበት ደግሞ "አገኘሁት" ብዬ የማስበውን ማንነቴን እንደ ጭስ የበተንኩበት ሁኔታ ውስጥ ነው ሔጄ የተመለስኩት።
.
መማር ከፈለግክ ከሕይወት የተሻለ መምህር የለም። "እንዲህ ዓይነት ሰው ነኝ!" ብለህ ስለ ራስህ እርግጠኛ የኾንክበት እምነትህ የሚናድበት ቀን ይመጣል። አሁን የምታውቀው ማንነትህን ያወቅከው እዚህ ስለኾንክ ብቻ ነው። የነገው ማንነትህ ሕይወት ነገ በምታደርስህ ቦታ እና ሁኔታ ላይ ይወሰ'ናል።
.
የዛሬው ማንነቴን ትናንት እንደ ነብይ ተንብያችሁ ብትነግሩኝ ኖሮ አላምናችሁም ነበር። "ፈጽሞ አላደርግም!" ያልኩትን አድርጌያለሁ፣ "ብሞት አልኾንም!" ስል የከረምኩትን ኾኜያለሁ። ከሕይወት ገጾች አይገመቴነቷ ይስበኛል።
.
"ማምለጫ" ብለህ የዘለቅከው በር ወህኒ ቤትህ ኾኖ ይገኛል፣ መሻገሪያ ያልከው "ጀልባ" መስጠሚያህ ይኾናል። ሕይወት የገባህ ቀን በበሩም በጀልባውም አትፈርድም። ያንተም ጥፋት አታደርገውም። ሕይወትን የምታይበት አንፃር(Angle) ያንተ ምርጫ አይደለም። ሕይወት ፐውዛ ያስቀመጠችህ ቦታ ነው ዕይታህን የሚመርጥልህ!
.
ይልቅ ስሕተትንና መዘዘኛ አጋጣሚን የሕይወት አንድ አካል አድርገህ ተቀብለህ ከሌላኛው ጫፍ ለመነሣት ትሞክራለህ። "ረዥም ዕድሜ እኖራለሁ!" ብለህ እያሰብክ ለውሳኔህ አትዘግይ...ማንም አይኖርልህም፣ ማንም አይሞትልህም....ታዲያ ለምን ሥርዓት፣ ሰዎች አልያም ሆድህ ይወስንልሃል?
(ማንምም አይወስንልህ!)
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
የፈራሁት!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ኦና ለታቀፈ፣ጊዜ ለሰበረው፤
ከተቸረው ሁሉ፣ቅንጣትም ላልቀረው፤
ተስፋ ነው 'ሚገድለው. . .
ተስፋ ነው 'ሚያኖረው!
.
የእኔም ጥያቄ ነው. . .
በዚህ ጨለማ ውስጥ፣
ልቤ እየበረታ፣ በተስፋ እያስመኘኝ፤
እንጃ ለምን ይኾን?!
የፈራሁት ብቻ ነው ደጋግሞ 'ሚያገኘኝ!!
.
@huluezih
@huluezih
2025/06/28 18:08:22
Back to Top
HTML Embed Code: