እማ..
ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ
እማ..
ለኔ እኮ ጠረንሽ የአንገትሽ ሥር ሽታ ከናርዶስ ይልቃል
በእስትንፋስሽ ብቻ ውስጤ በሐሴት ሞልቶ ዝንታለም ይኖራል
ላልነቃ ልተኛ እራሴን አሻሽተሽ ሽጉጥ አርጊኝና ከደረትሽ ወለል
ከዚህ አለም ክፋት ከዚህ አለም ተንኮል ከእምነትሽ ልጠለል
ጣቶችሽ በላዬ ሲንሸራሸሩማ ምድርን ለቅቄ ደርሼ ከራማ
የደስታ ጥግ ሥር ከምንጩ ጠጥቼ መንፈሴን አድሼ በሰማይ ከተማ
በእሳት ሠረገላ በዳመና መንገድ በመላዕክት ዜማ
ታጅቤ መጣለሁ እራሴን ሳስታውስ አንቺ ስትናፍቂኝ
ከጎኔ እያለሽ ከእቅፍሽ ውስጥ ሆኜ ያጣውሽ ሲመስለኝ
እማ..
ስጪኝ መቀነትሽን ወገብሽን ዞሮ ሀዘንና ደስታን የሚካፈልሽን
የደረሰብሽን በሆድሽ ያለውን ችለሽ የኖርሽውን
እሱ ይነግረኛል ያንቺን ጥንካሬ ለእኔ የሆንሽውን
ስንት ጊዜ ታመሽ ስንት ጊዜ እንደ ዳንኩ በፀሎት በምልጃሽ
ስንት ጊዜ ርቦሽ ስንት ጊዜ ጠምቶሽ እኔን እያስቀደምሽ
እራስሽን ክደሽ በዚያ ፅኑ ፍቅርሽ ልጄን ልጄን እያልሽ
እናም እናትዬ
ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ
አይበለውና
እንደው አይበለውና አምላክ መጥት ደጅሽ
ወይ መለዓኩን ልኮ የሞት ፅዋ አስይዞ ከእኔ ሊነጥልሽ ተረኛ ነሽ ቢልሽ
በእማ ቀልድ አላውቅም ከገዛ ዙፋኑ እኔው ተሰይሜ
እፋረደዋለው ከእግዜር ችሎት ቆሜ እስከቻለ አቅሜ
ሺ ሟች ሞልቶ በሀገር መንገደኛ ገስጋሽ እሷን ያየኽብኝ
ምን ኖሮኝ ልኖር ነዉ እሷኑ ሰጥተኸኝ መልሰህ ብትነጥቀኝ
እናም ልለምንህ ባለህ ሀይል ሁሉ አትጠቀምብኝ
እንዲህ ጠይቃለው ስለ እናትህ ስትል እናቴን ተውልኝ፡፡
እናቶቻቸውን በጥልቀት ለሚወዱ ሁሉ ይሁንልኝ ፡፡
መልካም የእናቶች ቀን
ከንጉስ አማኑኤል ብርሃኑ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ
እማ..
ለኔ እኮ ጠረንሽ የአንገትሽ ሥር ሽታ ከናርዶስ ይልቃል
በእስትንፋስሽ ብቻ ውስጤ በሐሴት ሞልቶ ዝንታለም ይኖራል
ላልነቃ ልተኛ እራሴን አሻሽተሽ ሽጉጥ አርጊኝና ከደረትሽ ወለል
ከዚህ አለም ክፋት ከዚህ አለም ተንኮል ከእምነትሽ ልጠለል
ጣቶችሽ በላዬ ሲንሸራሸሩማ ምድርን ለቅቄ ደርሼ ከራማ
የደስታ ጥግ ሥር ከምንጩ ጠጥቼ መንፈሴን አድሼ በሰማይ ከተማ
በእሳት ሠረገላ በዳመና መንገድ በመላዕክት ዜማ
ታጅቤ መጣለሁ እራሴን ሳስታውስ አንቺ ስትናፍቂኝ
ከጎኔ እያለሽ ከእቅፍሽ ውስጥ ሆኜ ያጣውሽ ሲመስለኝ
እማ..
ስጪኝ መቀነትሽን ወገብሽን ዞሮ ሀዘንና ደስታን የሚካፈልሽን
የደረሰብሽን በሆድሽ ያለውን ችለሽ የኖርሽውን
እሱ ይነግረኛል ያንቺን ጥንካሬ ለእኔ የሆንሽውን
ስንት ጊዜ ታመሽ ስንት ጊዜ እንደ ዳንኩ በፀሎት በምልጃሽ
ስንት ጊዜ ርቦሽ ስንት ጊዜ ጠምቶሽ እኔን እያስቀደምሽ
እራስሽን ክደሽ በዚያ ፅኑ ፍቅርሽ ልጄን ልጄን እያልሽ
እናም እናትዬ
ምድር ሲሰለችሽ መሄድ ስትፈልጊ በቅቶሽ ስትጠሪ
ሰባቱንም ሰማይ ላውርድልሽና አንዱን መርጠሽ ኑሪ
አትጠራጠሪ ከእነርሱ በአንዱ ነዉ ሚኖረው ፈጣሪ
ለአፍታ ዞር ብለሽ አንቺን ካጣውማ ድንገት ብትቀሪ
ይነጣጠላሉ ነፍስና ሥጋዬ ሆነዉ ለቀባሪ
አይበለውና
እንደው አይበለውና አምላክ መጥት ደጅሽ
ወይ መለዓኩን ልኮ የሞት ፅዋ አስይዞ ከእኔ ሊነጥልሽ ተረኛ ነሽ ቢልሽ
በእማ ቀልድ አላውቅም ከገዛ ዙፋኑ እኔው ተሰይሜ
እፋረደዋለው ከእግዜር ችሎት ቆሜ እስከቻለ አቅሜ
ሺ ሟች ሞልቶ በሀገር መንገደኛ ገስጋሽ እሷን ያየኽብኝ
ምን ኖሮኝ ልኖር ነዉ እሷኑ ሰጥተኸኝ መልሰህ ብትነጥቀኝ
እናም ልለምንህ ባለህ ሀይል ሁሉ አትጠቀምብኝ
እንዲህ ጠይቃለው ስለ እናትህ ስትል እናቴን ተውልኝ፡፡
እናቶቻቸውን በጥልቀት ለሚወዱ ሁሉ ይሁንልኝ ፡፡
መልካም የእናቶች ቀን
ከንጉስ አማኑኤል ብርሃኑ
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
........ለአንድ ግጥም አስር ብር.. ........
#የመንገድ ዳር እውነት!
.
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
ለደረቀ ከንፈር እርጥባን ስትቸር
ክንፏን የተመታች
የወደቀችን ወፍ ጠግነህ ስታበር
ላጎበጠ ጫንቃ ቀንበር ስታነሳ
ተስፋ ለቆረጠው...
ቃላትን ቀምረህ ሀዘን ስታስረሳ
ለዘመመች ጎጆ ማገር ስታቀብል
ለታረዘ ገላ ቡልኮህን ስትጥል
ዕውቀትን ለሚሻ ቆመህ ስታስተምር
መድሀኒት ሰጥተህ ታማሚን ስታሽር
በለሊት ሰዓታት ቆመህ ስትዘምር
ከቀራኸው ቁርአን ...
ከነብዩ ንግርት እውነት ስትዘነዝር
ጠሀይ ላደበነው ጥላ ስትዘረጋ
ብቻውን ከኖረ አብረህ ስታወጋ
ላኖርከው በረከት ላቆየኸው ምፅዋት
እግዜር ይስጥልኝን
ከኔ ቢጤ አንደበት ጠብቀህ ሳትሰማት
እግዜር ይስጥልኝ በል!
ለመንገዱ ነዳይ እጁን ለዘረጋው
ከተቀባይ ይልቅ
የሚሰጥ እጅ ነው የሚልቅ በዋጋው።
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#የመንገድ ዳር እውነት!
.
(ሚካኤል አስጨናቂ)
.
ለደረቀ ከንፈር እርጥባን ስትቸር
ክንፏን የተመታች
የወደቀችን ወፍ ጠግነህ ስታበር
ላጎበጠ ጫንቃ ቀንበር ስታነሳ
ተስፋ ለቆረጠው...
ቃላትን ቀምረህ ሀዘን ስታስረሳ
ለዘመመች ጎጆ ማገር ስታቀብል
ለታረዘ ገላ ቡልኮህን ስትጥል
ዕውቀትን ለሚሻ ቆመህ ስታስተምር
መድሀኒት ሰጥተህ ታማሚን ስታሽር
በለሊት ሰዓታት ቆመህ ስትዘምር
ከቀራኸው ቁርአን ...
ከነብዩ ንግርት እውነት ስትዘነዝር
ጠሀይ ላደበነው ጥላ ስትዘረጋ
ብቻውን ከኖረ አብረህ ስታወጋ
ላኖርከው በረከት ላቆየኸው ምፅዋት
እግዜር ይስጥልኝን
ከኔ ቢጤ አንደበት ጠብቀህ ሳትሰማት
እግዜር ይስጥልኝ በል!
ለመንገዱ ነዳይ እጁን ለዘረጋው
ከተቀባይ ይልቅ
የሚሰጥ እጅ ነው የሚልቅ በዋጋው።
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#የሹም #ሐገር #ሙሾ
ቀብሩ ሰርግ ነበር ይላል የሀገሬ ሰው
ንፍሮ እየዘገነ ድንኳን ሚመለሰው
* * *
ቀብረሽ ላይወጣልሽ ችለሽ ላታምቂ
ስንት ቀን አለፈሽ እንባሽን ስትጨምቂ
? ? ?
ሀዘን ሆድሽ ገብቶ እህ እንዳልሽ ሳይወጣ
ስንት ሌሊት አልፎ ስንት ንጋት መጣ
? ? ?
በሀዘን ሰአት ስሌት
ለልጆች ለመድረስ ምን ያህል ይበቃል
የደሀ አባት ሲቃስ
የአንዲት እናት እንባስ በስንት ቀን ያልቃል
? ? ?
በጊዜ እስኪፈታ ዘመን የቋጠረው
እኔ አቅም የለኝም ባለ ቀን ይቁጠረው
* * *
ብቻ ወየው ልበል !
ወ የ ው ለ እ ና ት የ ው !
ህልሟ ታግቶባት ቅዠት ለምታየው
ወ የ ው ለ ታ ላ ቋ !
ወ የ ው ወ ን ድ ም የ ው !
ጥያቄውን ሰጥቶ መልስ አጥቶ ለቆየው
ወ የ ው ለ አ ባ ት የ ው !
ሐገር ለወንድ ዋይታው ጆሮ ለነፈገው
በሮቹ ተዘግተው
በቴሌቪዥን መስኮት ልጅ ለሚፈልገው
መ ጥ ኔ ለ ኛ !
ለህብረተሰብ ድግስ ቤተሰብ ታረደ
መሀን ቀን ወጣለት መውለድ ተዋረደ
ጡት ምሬት አገተ ማህፀን አደመ
ከግፍ መደብ አይተው ፍትህ እየካደመ
#ጭሱ #እስከሚገለጥ
በዝሆኖች ዛር ስር በዝሆን ከራማ
ለታጋች እውነት ነው የአጋቾች ድራማ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ቀብሩ ሰርግ ነበር ይላል የሀገሬ ሰው
ንፍሮ እየዘገነ ድንኳን ሚመለሰው
* * *
ቀብረሽ ላይወጣልሽ ችለሽ ላታምቂ
ስንት ቀን አለፈሽ እንባሽን ስትጨምቂ
? ? ?
ሀዘን ሆድሽ ገብቶ እህ እንዳልሽ ሳይወጣ
ስንት ሌሊት አልፎ ስንት ንጋት መጣ
? ? ?
በሀዘን ሰአት ስሌት
ለልጆች ለመድረስ ምን ያህል ይበቃል
የደሀ አባት ሲቃስ
የአንዲት እናት እንባስ በስንት ቀን ያልቃል
? ? ?
በጊዜ እስኪፈታ ዘመን የቋጠረው
እኔ አቅም የለኝም ባለ ቀን ይቁጠረው
* * *
ብቻ ወየው ልበል !
ወ የ ው ለ እ ና ት የ ው !
ህልሟ ታግቶባት ቅዠት ለምታየው
ወ የ ው ለ ታ ላ ቋ !
ወ የ ው ወ ን ድ ም የ ው !
ጥያቄውን ሰጥቶ መልስ አጥቶ ለቆየው
ወ የ ው ለ አ ባ ት የ ው !
ሐገር ለወንድ ዋይታው ጆሮ ለነፈገው
በሮቹ ተዘግተው
በቴሌቪዥን መስኮት ልጅ ለሚፈልገው
መ ጥ ኔ ለ ኛ !
ለህብረተሰብ ድግስ ቤተሰብ ታረደ
መሀን ቀን ወጣለት መውለድ ተዋረደ
ጡት ምሬት አገተ ማህፀን አደመ
ከግፍ መደብ አይተው ፍትህ እየካደመ
#ጭሱ #እስከሚገለጥ
በዝሆኖች ዛር ስር በዝሆን ከራማ
ለታጋች እውነት ነው የአጋቾች ድራማ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
"እምዬ ያልታደለች" በበረከት በላይነህ
እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች!
የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል — እየፈጩ ማንጋት
* * *
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ —ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት —ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ —ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት — እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት —ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ —ምግቧን ነው ማጠብ
* * *
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
* * *
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ —ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
* * *
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል —ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል —ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ —የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል —የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
* * *
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
.
.
.
እኮ የምን ጥያቄ ! እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ — ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ —ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
* * *
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
* * *
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
* * *
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
* * *
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር — ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
* * *
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
* * *
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
* * *
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
* * *
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
እምዬ ያልታደለች
ተመዘኚ ሲሏት— መዛኝ ነኝ ትላለች
እምዬ ሰከረች
ልትመዘን ወጥታ — መዛኝ ሆና ቀረች!
የቅቤን ስብራት — በቅመም ለማከም
በወቀጣ መዛል — በድለዛ መድከም
የቅቤን ወለምታ — በቅመም ለማሸት
ሲደቁሱ አድረው — ሲቀይጡ ማምሸት
የቅቤን ጉብዝና — በቅመም ለማትጋት
እያመሱ መዋል — እየፈጩ ማንጋት
* * *
ይልቅ ግድ የለሽም !
ለቅቤ ጥፍጥና
ለቅቤ መአዛ
ቅመም ከመደቆስ —ቅመም ከማበጠር
ከቅቤያችን በፊት —ከብቶቹን ነው ማንጠር
እንስራ ወዝውዞ
በጢሳጢስ ናውዞ
ለቅቤ ከማማጥ —ለአይብ ከማማጥ
ከወተቱ በፊት — እስቲ ላሟ ትናጥ
ማለቢያ ከማስፋት —ማለቢያ ከማጥበብ
ከግቷ አስቀድሞ
ከሆዷ አስቀድሞ —ምግቧን ነው ማጠብ
* * *
ለምሽቱ ድምቀት — ቀኑን ሳይበርዙ
እንዲህ ነው ፊተኞች — ‘ሩቅ የሚጓዙ
እንዲህ ነው መስማማት — መግባባት ከዛፉ
ከስር ሳይመትሩ — አይታይም ጫፉ !
* * *
ግራ ነኝ ይለኛል
ቀኝ ነኝ ይለኛል —መሀል ነኝ ይለኛል
ዳሩ ካልተያዘ — መሀል የት ይገኛል?
እውቀት አባ አያልቄ
እውቀት አባ አይፈሬ —ጥያቄ ሲያድለው
ለግራም የራሱ — ግራና ቀኝ አለው
ለቀኝም የራሱ — ቀኝና ግራ አለው
መሃልም ለራሱ — ሌላ መሀል አለው
* * *
እይዉ!
ሰው መጠየቅ ትቷል
ሰው ፍለጋ ትቷል —ሰው ማጣጣም ትቷል
ለመንስኤ ዝሏል —ለአመክንዮ ታክቷል
በጥድፊያ ሊያስታግስ —የመሰንበት ሱሱን
ጥያቄ ነው ይላል —የከሸፈ መልሱን
ነፍስያን ተብትቦ —በስሜት ሰንሰለት
መቀያየጥ ሆኗል —መጠያየቅ ማለት
መመሳሰል ሆኗል —መመላለስ ማለት
* * *
ኩሬ ነው?
ወንዝ ነው?
ሃይቅ ነው?
ባህር ነው? ጎርፍ ነው?
ገባሩ? ጅረቱ? ማእበሉ? ምንጮቹ?
አዞ አለ? አሳ አለ?
.
.
.
እኮ የምን ጥያቄ ! እኮ የምን ክርክር !
በቃ!
“ዋና ነው!” ይልሽና ከነልብሱ ንክር።
አዎ!
“ዋና ነው!” ይልሻል “አጨብጭቢ!” ይልሻል
“ዋናህስ?” አትበይው
አሽሟጠጠች ብሎ — ችሎት ያቆምሻል
ያው!
ችሎቱ የእነሱ —ችሎታው የሌላ
ይልቅ አጨብጭቢ —አዞ እራቱን ይብላ!
ለንክር ጭብጨባ —ለዝፍዝፍ ጭብጨባ
ሆዱ አሳ ሲለው — አዞ ለሚያረባ
* * *
ተመልከች!
ሽንቁራም እውቀትሽ —ንፋሱን ሲነዛ
ከጋላቢሽ ይልቅ —የሚገለብ በዛ
ንፋሳም እውቀትሽ —ውርጩን እየነዛ
ከሚያነደው ይልቅ —የሚያከስለው በዛ
ግልብልብ እውቀትሽ —ወላፈን ደሞዙ
የሚለበለቡት — ከሚበስሉት በዙ።
እይው!
ማእዘን አፍርሶ —ግድግዳ እያደሰ
ወለሉን ሰውቶ —ጣሪያ እየቀለሰ
ቅርንጫፍ ሊያሳምር —ስር እየበጠሰ
እልፍኝ ተደፈረ —አጥር ተገሰሰ
መስማት ጥንቡን —ጣለ ማየት ረከሰ
ቋንቋ መነመነ — ለትርጉም አነሰ
* * *
ቆይ እኔ የምልሽ!
ተፈጥሮ ሂደቷ — እንዲህ ሳይጓደል
ለመሮጥ መንደርደር — ግድ ነበር አይደል?!
ታዲያ! ቀረ እኮ ነው ‘ምልሽ
መንደርደር መመርመር መፈከር መዘርዘር
አኩርፈው የሄዱት — በየት በኩል ነበር?
* * *
የወል ቀማሽ ሁላ
ድፍርስ እየጠጣ — ሽርክት እየበላ
በግርድፍ አኝኮ — ለግርድፍ ተሻምቶ
“ውጫለሁ!” ይልሻል — ወደ ሆዱ ተፍቶ
* * *
የምር ደስ አይልም!
የጥርስን በአንጀት
የጆሮን በምላስ — ʻያፍንጫን በመዳፍ
ግብር እያቀማሙ — ዋጋና ስም መጻፍ
የምር ደስ አይልም!
የልብን ደረት ላይ
የነፍስን ልብስ ላይ— ቀያይጦ በማፍካት
ጣእምን መመርመር — ውበትን መለካት
ደስስስስስ አይልም!
* * *
እምዬ!
አትላፊ አትዳሪ ከእንክርዳድሽ
ይልቅ
ወንፊት ግዢ ለወንፊትሽ
ሰፌድ ግዢ ለሰፌድሽ
* * *
ቀማሽ ሲደራረብ —ጣእም ተቀያየጠ
ባለቤት ሳያጌጥ —ውበት አመለጠ
ከእህሉም አይደለ
ከቅመሙም አይደል
ጨው አንሶም አይደለ
የምላስ ህመም —ነው ጣእም የገደለ
* * *
ምን አረገሽና!
ቀቃዩ ጠባሹ
ከታፊው አማሹ
ወቃጩ ነስናሹ
ለርካሽነትሽ — ይጠየቅ ቀማሹ
ማገዶ ቢራቀቅ
ምጣድ ቢቀያየር — ጋጋሪ ቢንጋጋ
በቀማሽ ልክ ነው —የገበታሽ ዋጋ
* * *
ኧረ ሚዛን! ሚዛን!
ኧረ መዛኝ! መዛኝ!
በልክ የሚሰፍር በልክ የሚገዛኝ!
እንደየቃናችን — ማድመቅ ያላወቀ
ቀማሽ አሳነሰን — እያደባለቀ!!!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
Welcome!!! We need 10,000 petition to protect our children and the next generation:
URGENT!!!
The Link
https://www.comprehensivesexualityeducation.org/international-map/ethiopia/
Dr. Seyoum:
Our group members have passed well over 18,300 but the petitions signed so far are only 5948 or so.
There are more than 12,000 members who have not signed.
Writing the word signed here does not mean you have signed.
You have to go into the website fill the form and click "submit" !
You'll get an email confirmation!
Sister Saba,
WHY you stand to STOP CSE?
Comprehensive sexuality education ማለት
👨👩👧👦 በንፁህና ክፉውንና ደጉን በቅጡ ለማገናዘብ ባልዳበረ የህፃናት አእምሮና ስነልቦና ላይ ያነጣጠረ አለምአቀፍ ጥቃት ነው።
👨👩👧👦 የአንዲትን ሀገር ህዝቦች ባህል እሴትና የሁሉንም ሐይማኖታዊ አስተምሮቶች በተቃረነ መልኩ ወሲባዊ ልቅነትን ከለጋ እድሜ ጀምሮ እንደ ሰደድ እሣት የሚያቀጣጥል ስውር መሣሪያ ነው።
👨👩👧👦 ልጆችና አፋላ ወጣቶችን እጅግ አደገኛና ለጠንቅ አጋላጭ የሆኑ ልምምዶችን እንዲሞክሩ የሚገፋፋና ሲያደርጉትም ትክክል እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያበረታታ መርዝ ነው።
👨👩👧👦 ልጆችንና አፍላ ወጣቶችን የተለያዮ እንግዳ ልምምዶች በመሞከር በግልም ወይንም በጋራ ወሲባዊ ስካር ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ማስተማርና የማለማመጃ ስልት ነው።
ዉጤቱ
🙈ልጆችን ሴሰኛ ማድረግ /sexualize children
🙈Teach how to consent to sex.
ለሚቀርብላቸው የወሲብ ጥያቄ እሺ ባይ ማድረግ
🙈 Normalize anal & oral sex.
🙈የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትና የተፈጥሮ ፆታን ማስቀየርን ማበረታታት
🙈 በሚለማመዱት ልቅ ወሲባዊ ግንኙነቶች ሣቢያ ለሚፈጠር እርግዝና ደግሞ የውርጃ አገልግሎት ማቅረብ
🔔ለአንዲት ሀገር የወሲብ ነፃነት አንገብጋቢ ጉዳይ ሲሆን የተዋዶ ጤና አደጋ ላይ ይወድቃል።🔔
ይህንን በልጆቻችን በቤተሰባችን በማህበረሰባችን ብሎም በሀገራችን ላይ የተጋረጠብንና ሠርጎ የገባን እጅግ ከፍተኛ አደጋ ለማስቆም "እኔ የልጄ የወንድሜ የእህቴ የጓደኛዬ ጠባቄ ነኝ" ብለን ተነሣን። ስለ ኢትዬጲያ ያገባኛል
🇪🇹 የComprehensive sexuality education ለሀገሬ አያስፈልጋትም።
🇪🇹 Say No for CSE
ስለዚህ ባለቤቴ ዶር ሥዩም በክፍል 3 ያስተላለፈውን በድጋሜ ተመልክታችሁ የምናሰባስበው የተቃሞ ድጋፍ ፊርማ በላክንላችሁ ሊንክ በመግባት ቅፁን በመሙላት ለልጆቻችሁ መቆማችሁ እንድታረጋግጡ እንለምናችኋለሁ።
ሌሎች አይተው ቤታቸውን እዲያስመልጡ ሼር በማድረግ እርዷቸው። በተከታታይ ጉዳዬችን በጥልቀት የምተረዱበትን መረጃዎች እናካፍላችኋለን ።
Sister Saba:
እባካችሁ ውድ የኢትዬጲያ ልጆች የምትጋብዛቸውን ቅፅን በሞልተዉ መመዝገባቸውን እርግጠኖች ሁኑ።
Dr. Seyoum:
ይህንን ታሪካዊ አደራ እድንወጣ በታላቅ አክብሮት አደራ እንላለን!
ይህ ዕድል በህይወት ዘመናችን ከምናገኛቸው ታላላቅ ዕድሎች አንዱ ነውና ታሪክ ሰርተን እንድናልፍ ታላቅ ጥሪ በትህትና እናቀርባለን!!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!
🤓
✍ make sure you signed virtually! Write your name, email and phone no. on the link. Your email will serve as your signature.
Thank you for protecting Children!!!
Dear Members,
Please, please use the following link to sign the petition!
It helps you fill BOTH the Ethiopian petition and the International one AT THE SAME TIME!
https://www.comprehensivesexualityeducation.org/international-map/ethiopia/
URGENT!!!
The Link
https://www.comprehensivesexualityeducation.org/international-map/ethiopia/
Dr. Seyoum:
Our group members have passed well over 18,300 but the petitions signed so far are only 5948 or so.
There are more than 12,000 members who have not signed.
Writing the word signed here does not mean you have signed.
You have to go into the website fill the form and click "submit" !
You'll get an email confirmation!
Sister Saba,
WHY you stand to STOP CSE?
Comprehensive sexuality education ማለት
👨👩👧👦 በንፁህና ክፉውንና ደጉን በቅጡ ለማገናዘብ ባልዳበረ የህፃናት አእምሮና ስነልቦና ላይ ያነጣጠረ አለምአቀፍ ጥቃት ነው።
👨👩👧👦 የአንዲትን ሀገር ህዝቦች ባህል እሴትና የሁሉንም ሐይማኖታዊ አስተምሮቶች በተቃረነ መልኩ ወሲባዊ ልቅነትን ከለጋ እድሜ ጀምሮ እንደ ሰደድ እሣት የሚያቀጣጥል ስውር መሣሪያ ነው።
👨👩👧👦 ልጆችና አፋላ ወጣቶችን እጅግ አደገኛና ለጠንቅ አጋላጭ የሆኑ ልምምዶችን እንዲሞክሩ የሚገፋፋና ሲያደርጉትም ትክክል እንደሆኑ እንዲሰማቸው የሚያበረታታ መርዝ ነው።
👨👩👧👦 ልጆችንና አፍላ ወጣቶችን የተለያዮ እንግዳ ልምምዶች በመሞከር በግልም ወይንም በጋራ ወሲባዊ ስካር ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ማስተማርና የማለማመጃ ስልት ነው።
ዉጤቱ
🙈ልጆችን ሴሰኛ ማድረግ /sexualize children
🙈Teach how to consent to sex.
ለሚቀርብላቸው የወሲብ ጥያቄ እሺ ባይ ማድረግ
🙈 Normalize anal & oral sex.
🙈የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትና የተፈጥሮ ፆታን ማስቀየርን ማበረታታት
🙈 በሚለማመዱት ልቅ ወሲባዊ ግንኙነቶች ሣቢያ ለሚፈጠር እርግዝና ደግሞ የውርጃ አገልግሎት ማቅረብ
🔔ለአንዲት ሀገር የወሲብ ነፃነት አንገብጋቢ ጉዳይ ሲሆን የተዋዶ ጤና አደጋ ላይ ይወድቃል።🔔
ይህንን በልጆቻችን በቤተሰባችን በማህበረሰባችን ብሎም በሀገራችን ላይ የተጋረጠብንና ሠርጎ የገባን እጅግ ከፍተኛ አደጋ ለማስቆም "እኔ የልጄ የወንድሜ የእህቴ የጓደኛዬ ጠባቄ ነኝ" ብለን ተነሣን። ስለ ኢትዬጲያ ያገባኛል
🇪🇹 የComprehensive sexuality education ለሀገሬ አያስፈልጋትም።
🇪🇹 Say No for CSE
ስለዚህ ባለቤቴ ዶር ሥዩም በክፍል 3 ያስተላለፈውን በድጋሜ ተመልክታችሁ የምናሰባስበው የተቃሞ ድጋፍ ፊርማ በላክንላችሁ ሊንክ በመግባት ቅፁን በመሙላት ለልጆቻችሁ መቆማችሁ እንድታረጋግጡ እንለምናችኋለሁ።
ሌሎች አይተው ቤታቸውን እዲያስመልጡ ሼር በማድረግ እርዷቸው። በተከታታይ ጉዳዬችን በጥልቀት የምተረዱበትን መረጃዎች እናካፍላችኋለን ።
Sister Saba:
እባካችሁ ውድ የኢትዬጲያ ልጆች የምትጋብዛቸውን ቅፅን በሞልተዉ መመዝገባቸውን እርግጠኖች ሁኑ።
Dr. Seyoum:
ይህንን ታሪካዊ አደራ እድንወጣ በታላቅ አክብሮት አደራ እንላለን!
ይህ ዕድል በህይወት ዘመናችን ከምናገኛቸው ታላላቅ ዕድሎች አንዱ ነውና ታሪክ ሰርተን እንድናልፍ ታላቅ ጥሪ በትህትና እናቀርባለን!!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!
🤓
✍ make sure you signed virtually! Write your name, email and phone no. on the link. Your email will serve as your signature.
Thank you for protecting Children!!!
Dear Members,
Please, please use the following link to sign the petition!
It helps you fill BOTH the Ethiopian petition and the International one AT THE SAME TIME!
https://www.comprehensivesexualityeducation.org/international-map/ethiopia/
StopCSE.org
Protect Ethiopia Children
Sign the Petition to STOP CSE!
Forwarded from 666( ኢልሙናቲ ) ሀይማኖት ምዝገባ ማእከል via @Josy_Button_Bot
[ከእንጦጦ ሰማይ ስር]
(በመ/ሐ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ)
👉 ጸጥ ባለው ምሽት ነፋስ በበዛበት፤
ሰዎችም ቤታቸው ለዕረፍት በተኙበት፤
ድንቁን የአምላክ ሥራን በምሽት ለማየት፤
በእንጦጦ ተራራ ተገኘሁ በድንገት።
👉 ከዋክብት በሰማይ ያብረቀርቃሉ፤
ፕላኔት በጠፈር ደምቀው ይታያሉ፤
በአንድነት በመሆን የፈጣሪን ጥበብ ይመሰክራሉ።
👉 ቀደምት ኢትዮጵያውያን በዕውቀት የላቁ፤
በጠፈር ምርምር እየተራቀቁ፤
የሰማዩን ምስጢር ጠንቅቀው አወቁ፤
ያወቁትን ምስጢር ምንም ሳይደብቁ፤
በጽሑፍ አኑረው በጥበብ መጠቁ።
👉 ንግሥት ካሲዮፕያ ብትወድ ፈለክን፤
መሠየም ጀመረች ሕብረ ከዋክብትን።
👉 ሴፌውስ በአድናቆት እርሱም አስተውሎ፤
ከአንድሮሜዳ ጋር ፈጠነና ቶሎ፤
ያየውን አኖረ ለትውልዱ ብሎ።
👉 ቀደምቶች ያኖሩት የሰማይ ምስጢር፤
አስተዋይ እስኪኖር የሚመረምር፤
በክብር ይቀመጣል ዕውቀት እስኪከብር፤
በዕውቀት መራቀቅ ጊዜው እስኪጀምር።
👉 ቴሌስኮፑን ቶሎ በፍጥነት አቆምኩት፤
መመልከት ጀመርኩ ሰማዩን በትኩረት፤
የግዮኗ ኮከብ ሳይረስን አየኋት፤
የዐባይን ወንዝ መሙላት ቀደምት ያወቁባት።
👉 ኢዮብ የጠቀሰው የኦርዮን ኮከብ፤
ቀበቶውን አርጎ ውበትን በማበብ፤
ደምቆ እየታየ ተከቧል በክበብ።
👉 አይቼው ዞር ስል በሰሜኑ በኩል፤
ዝሁራ ቬነስ የጠፈር ዕንክብል፤
ደምቃ ትታይ ነበር በከዋክብት መሃል።
👉 ማዛሮትና ድብ እነኢዮብ ያይዋቸው፤
እነ ሔኖክ ቀድሞው የመረመሯቸው፤
የኢትዮጵያ ሊቆች የመዘገቧቸው፤
ይታያሉ በእውነት በደንብ ላጤናቸው።
👉 ደስ በሚል ምሽት የጨረቃም ድምቀት ተጨምሮበታል፤
ውስጧንም መመልከት በእጅጉ ያጓጓል።
👉 የጨረቃ ስሟ አንዴ አሶንያ ሌላ ጊዜ ቀመር፤
ብናሴና ኤራዕ ቢሉ ስሟን በማሽከርከር።
👉 ወርህም ዕብላም ቢሉ ደግሞም ሶልያና፤
ይህን ሁሉ ስሟን ጻፉት በብራና።
👉 አቅርቦ ቢያሳየኝ ቴሌስኮፑ ድንገት፤
እቺን ድንቅ ፍጥረት ለካስ ውብ ደማቅ ናት።
👉 ፈጣሪ ይመስገን እነዚህን ሁሉ በአንድነት ያስገኘ፤
ጥበብን የሚገልጽ በእውነት ለተመኘ።
👉 ከዚያ ከተመስጦው ደስ ከሚል ምሽት፤
የጠፈር ዕንቁዎች ደምቀው ካበሩበት፤
ዕውቀት ከሚያበዛው ደስ ከሚል ሌሊት፤
ጊዜው መሽቷልና ተነሣሁ በድንገት።
👉 ከተማ ደረስኩኝ የወሬ ማዕበል ወደ ሚጎርፍበት፤
ጫጫታና ሁከት ወደሰፈነበት፤
ጽሙና ዕርጋታ ከቶ የሌለበት፤
ተፈጥሮንም ማድነቅ የማይታሰብበት።
👉ቢሆንም!! አምላክ የእጅህ ሥራ በእጅጉ ይደንቃል፤
የዓለም ጫጫታን ከኅሊና ያጠፋል፤
አስተዋይ ልቡናን በደስታ ያራቅቃል፤
መንፈስን ልቡናን በፍቅር ያሞቃል፤
ሕሊናን መስጦ ወደ ላይ ያወጣል።
በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
(ግንቦት 4/ 2012 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6:12 ተጻፈ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(በመ/ሐ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ)
👉 ጸጥ ባለው ምሽት ነፋስ በበዛበት፤
ሰዎችም ቤታቸው ለዕረፍት በተኙበት፤
ድንቁን የአምላክ ሥራን በምሽት ለማየት፤
በእንጦጦ ተራራ ተገኘሁ በድንገት።
👉 ከዋክብት በሰማይ ያብረቀርቃሉ፤
ፕላኔት በጠፈር ደምቀው ይታያሉ፤
በአንድነት በመሆን የፈጣሪን ጥበብ ይመሰክራሉ።
👉 ቀደምት ኢትዮጵያውያን በዕውቀት የላቁ፤
በጠፈር ምርምር እየተራቀቁ፤
የሰማዩን ምስጢር ጠንቅቀው አወቁ፤
ያወቁትን ምስጢር ምንም ሳይደብቁ፤
በጽሑፍ አኑረው በጥበብ መጠቁ።
👉 ንግሥት ካሲዮፕያ ብትወድ ፈለክን፤
መሠየም ጀመረች ሕብረ ከዋክብትን።
👉 ሴፌውስ በአድናቆት እርሱም አስተውሎ፤
ከአንድሮሜዳ ጋር ፈጠነና ቶሎ፤
ያየውን አኖረ ለትውልዱ ብሎ።
👉 ቀደምቶች ያኖሩት የሰማይ ምስጢር፤
አስተዋይ እስኪኖር የሚመረምር፤
በክብር ይቀመጣል ዕውቀት እስኪከብር፤
በዕውቀት መራቀቅ ጊዜው እስኪጀምር።
👉 ቴሌስኮፑን ቶሎ በፍጥነት አቆምኩት፤
መመልከት ጀመርኩ ሰማዩን በትኩረት፤
የግዮኗ ኮከብ ሳይረስን አየኋት፤
የዐባይን ወንዝ መሙላት ቀደምት ያወቁባት።
👉 ኢዮብ የጠቀሰው የኦርዮን ኮከብ፤
ቀበቶውን አርጎ ውበትን በማበብ፤
ደምቆ እየታየ ተከቧል በክበብ።
👉 አይቼው ዞር ስል በሰሜኑ በኩል፤
ዝሁራ ቬነስ የጠፈር ዕንክብል፤
ደምቃ ትታይ ነበር በከዋክብት መሃል።
👉 ማዛሮትና ድብ እነኢዮብ ያይዋቸው፤
እነ ሔኖክ ቀድሞው የመረመሯቸው፤
የኢትዮጵያ ሊቆች የመዘገቧቸው፤
ይታያሉ በእውነት በደንብ ላጤናቸው።
👉 ደስ በሚል ምሽት የጨረቃም ድምቀት ተጨምሮበታል፤
ውስጧንም መመልከት በእጅጉ ያጓጓል።
👉 የጨረቃ ስሟ አንዴ አሶንያ ሌላ ጊዜ ቀመር፤
ብናሴና ኤራዕ ቢሉ ስሟን በማሽከርከር።
👉 ወርህም ዕብላም ቢሉ ደግሞም ሶልያና፤
ይህን ሁሉ ስሟን ጻፉት በብራና።
👉 አቅርቦ ቢያሳየኝ ቴሌስኮፑ ድንገት፤
እቺን ድንቅ ፍጥረት ለካስ ውብ ደማቅ ናት።
👉 ፈጣሪ ይመስገን እነዚህን ሁሉ በአንድነት ያስገኘ፤
ጥበብን የሚገልጽ በእውነት ለተመኘ።
👉 ከዚያ ከተመስጦው ደስ ከሚል ምሽት፤
የጠፈር ዕንቁዎች ደምቀው ካበሩበት፤
ዕውቀት ከሚያበዛው ደስ ከሚል ሌሊት፤
ጊዜው መሽቷልና ተነሣሁ በድንገት።
👉 ከተማ ደረስኩኝ የወሬ ማዕበል ወደ ሚጎርፍበት፤
ጫጫታና ሁከት ወደሰፈነበት፤
ጽሙና ዕርጋታ ከቶ የሌለበት፤
ተፈጥሮንም ማድነቅ የማይታሰብበት።
👉ቢሆንም!! አምላክ የእጅህ ሥራ በእጅጉ ይደንቃል፤
የዓለም ጫጫታን ከኅሊና ያጠፋል፤
አስተዋይ ልቡናን በደስታ ያራቅቃል፤
መንፈስን ልቡናን በፍቅር ያሞቃል፤
ሕሊናን መስጦ ወደ ላይ ያወጣል።
በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
(ግንቦት 4/ 2012 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6:12 ተጻፈ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
የቅናት ዛር
"""""""""""""
እቀናለሁ እኔ
ሌላ ሲያይሽ በአይኑ፤
እቀናለሁ እኔ
አይኖችሽ ሲኳሉ፤
ለአይንሽ ወከክ ሲል ፥የአዳም ዘር በሙሉ!
እቀናለሁ እኔ
ፀጉርሽ ሲነሰነስ፤
በጎንሽ ያለፈ ፥አይኑ ሲቅበዘበዝ፤
ውስጤ ይላል ትክን
አንጀቴም ይላል ጨስ!
እቀናለሁ እኔ
በቁመትሽ ሎጋ፤
በአንገትሽ መቃ፤
ሰው ከፈዘዘበት መልሶ ሲነቃ!
እቀናለሁ እኔ
በጥርስሽ ውበቱ
በከንፈርሽ ቅርፁ ፥በአፍንጫሽ ስንደዶ፥
ሰውም ልቡ ሲሞቅ ፥በውበትሽ ተማግዶ!
እቀናለሁ እኔ
ልቤ ለውበትሽ ፥እጅጉን ቢረታ፤
መንገዱን ስትሄጂ ፥በአጀብ በሆታ፤
በሁለት ጥንድ መንገድ ፥ውስጠቴ ቢፈታ፤
ስትስቂ ትካዜ...ዝም ስትይ ፈገግታ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
"""""""""""""
እቀናለሁ እኔ
ሌላ ሲያይሽ በአይኑ፤
እቀናለሁ እኔ
አይኖችሽ ሲኳሉ፤
ለአይንሽ ወከክ ሲል ፥የአዳም ዘር በሙሉ!
እቀናለሁ እኔ
ፀጉርሽ ሲነሰነስ፤
በጎንሽ ያለፈ ፥አይኑ ሲቅበዘበዝ፤
ውስጤ ይላል ትክን
አንጀቴም ይላል ጨስ!
እቀናለሁ እኔ
በቁመትሽ ሎጋ፤
በአንገትሽ መቃ፤
ሰው ከፈዘዘበት መልሶ ሲነቃ!
እቀናለሁ እኔ
በጥርስሽ ውበቱ
በከንፈርሽ ቅርፁ ፥በአፍንጫሽ ስንደዶ፥
ሰውም ልቡ ሲሞቅ ፥በውበትሽ ተማግዶ!
እቀናለሁ እኔ
ልቤ ለውበትሽ ፥እጅጉን ቢረታ፤
መንገዱን ስትሄጂ ፥በአጀብ በሆታ፤
በሁለት ጥንድ መንገድ ፥ውስጠቴ ቢፈታ፤
ስትስቂ ትካዜ...ዝም ስትይ ፈገግታ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
እናቴን ስገልፃት!
(አኑ)
ልንገርሽማ
ልገጥምልሽ ሞከርኩና
ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው
.........
እያለ የዘፈነ
ስላንቺ ማንነት ቤት መምታት ያልቻለ
ስለ ሚስት ሲሆን
ቃላት እያቦካ
ቤት መምታት የሚችል አንድ ዘፋኝ አለ
ህዝቡ እሱን ያምነዋል
ስለእናቱ ሊፅፍ ቤት መምታት ከበደው
እያሉ ሲያወሩ
አልገጠምኩም ብሎ
ድንቅ ግጥም ነበር ለህዝብ ያደረሰው
ተመልከቺ እስቲ
"ልገጥምልሽ ሞከርኩና ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው"
እልፍ ስሜቶቼን
በሁለት ስንኞች ሲገልፀው ውብ አርጎ
አልገጠምኩም ሲል
ስለ ፍፁም ፍቅርሽ ሊገጥም ፈልጎ
ልንገርሽ እያለ
መንገር ሲያቅተው የፍቅርሽን ልኬት
የልፋትሽ ዋጋ
መተመን ሲያቅተው በአለማዊ ስሌት
እጆቹን አንስቶ
ወረቀት ላይ ይሰዳል
ልንገርሽ ይልና አንቺ ሚገልፅበት ቃላቶችን ያጣል
የቃላትን ጉልበት
በአንቺ ማንነት ውስጥ ሲደበቁ ያያል
...................
ብዕሩን ይተዋል
ጥበብን ይረግማል
ፊደልን ይሰድባል
ከቃላት ይጋጫል
አንደበቱ ይዘጋል
ከራስ ጋር ግብግብ
ከቃል ጋር ድብድብ
አንድ አንቺን ለመግለፅ ይለፋል ይተጋል
ልፋትሽን አይቶ
ትጋትሽን አይቶ ስላንቺ ለሰዎች ደጋግሞ ያወራል
ክብርሽ እንዳይጎድል
ሌሎች በማያቁት
በሆነ አይነት ቋንቋ እንዲህ ሲል ይጮሀል
................
ፈኤኤር ቤቴቦ ቄሬጦስ ጮጾና
ጲፂፂል ኬሪሳ ፈቄሌት ዴቆና
ጥርሳጥሽ ቆራሼ ቤፀል ሚሎሎቶ
ራጎስ ቢታዊ ክለጅ ሜጣን ዮቶ
ጥራቢስ ኮሮሚ ጆራስ ፊካ ጵላ
እዝራቅ ብራሽቅቦ ዴላሮስ ውህላ
....
ምናምን እያለ
ሰዎች በማያውቁት ቋንቋ ይገልፅሻል
ለሱም አይገባውም
ክብርሽ ከፍ እንዲል ሲል በአደባባይ ይጮሀል
ምክንያቱም በዚ ሀገር
የማያውቁት ነገር ከፍ ያለ ነው ክብሩ
የሚያውቁት ቋንቋ
የሚያውቁት ነገር ይናቃል ከስሩ
አንቺን ላለማስናቅ
አንቺን ለማስከበር
በማያውቁት ቋንቋ እኔም ልፅፍ ነበር
ግና ምን ዋጋ አለው
የማላቀው ቋንቋን
ለማውቀው ፍቅርሽ እንዴት እፅፋለሁ?
የማውቀው ፍቅርሽን
በማውቀውስ ቋንቋ ምን ብዬ እገልፃለሁ?
የማውቀውን ፊደል
ከማላውቀው ጋራ ብፅፍ እችላለሁ?
..
ል
ክ
እ
ን
ደ
ዚ
ህ
....
ቆአጦስ ጎሮሮስ ቤላጦስ ጦዝቻ
ስላንቺ ከማውራት ዝም ማለት ብቻ!!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(አኑ)
ልንገርሽማ
ልገጥምልሽ ሞከርኩና
ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው
.........
እያለ የዘፈነ
ስላንቺ ማንነት ቤት መምታት ያልቻለ
ስለ ሚስት ሲሆን
ቃላት እያቦካ
ቤት መምታት የሚችል አንድ ዘፋኝ አለ
ህዝቡ እሱን ያምነዋል
ስለእናቱ ሊፅፍ ቤት መምታት ከበደው
እያሉ ሲያወሩ
አልገጠምኩም ብሎ
ድንቅ ግጥም ነበር ለህዝብ ያደረሰው
ተመልከቺ እስቲ
"ልገጥምልሽ ሞከርኩና ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው"
እልፍ ስሜቶቼን
በሁለት ስንኞች ሲገልፀው ውብ አርጎ
አልገጠምኩም ሲል
ስለ ፍፁም ፍቅርሽ ሊገጥም ፈልጎ
ልንገርሽ እያለ
መንገር ሲያቅተው የፍቅርሽን ልኬት
የልፋትሽ ዋጋ
መተመን ሲያቅተው በአለማዊ ስሌት
እጆቹን አንስቶ
ወረቀት ላይ ይሰዳል
ልንገርሽ ይልና አንቺ ሚገልፅበት ቃላቶችን ያጣል
የቃላትን ጉልበት
በአንቺ ማንነት ውስጥ ሲደበቁ ያያል
...................
ብዕሩን ይተዋል
ጥበብን ይረግማል
ፊደልን ይሰድባል
ከቃላት ይጋጫል
አንደበቱ ይዘጋል
ከራስ ጋር ግብግብ
ከቃል ጋር ድብድብ
አንድ አንቺን ለመግለፅ ይለፋል ይተጋል
ልፋትሽን አይቶ
ትጋትሽን አይቶ ስላንቺ ለሰዎች ደጋግሞ ያወራል
ክብርሽ እንዳይጎድል
ሌሎች በማያቁት
በሆነ አይነት ቋንቋ እንዲህ ሲል ይጮሀል
................
ፈኤኤር ቤቴቦ ቄሬጦስ ጮጾና
ጲፂፂል ኬሪሳ ፈቄሌት ዴቆና
ጥርሳጥሽ ቆራሼ ቤፀል ሚሎሎቶ
ራጎስ ቢታዊ ክለጅ ሜጣን ዮቶ
ጥራቢስ ኮሮሚ ጆራስ ፊካ ጵላ
እዝራቅ ብራሽቅቦ ዴላሮስ ውህላ
....
ምናምን እያለ
ሰዎች በማያውቁት ቋንቋ ይገልፅሻል
ለሱም አይገባውም
ክብርሽ ከፍ እንዲል ሲል በአደባባይ ይጮሀል
ምክንያቱም በዚ ሀገር
የማያውቁት ነገር ከፍ ያለ ነው ክብሩ
የሚያውቁት ቋንቋ
የሚያውቁት ነገር ይናቃል ከስሩ
አንቺን ላለማስናቅ
አንቺን ለማስከበር
በማያውቁት ቋንቋ እኔም ልፅፍ ነበር
ግና ምን ዋጋ አለው
የማላቀው ቋንቋን
ለማውቀው ፍቅርሽ እንዴት እፅፋለሁ?
የማውቀው ፍቅርሽን
በማውቀውስ ቋንቋ ምን ብዬ እገልፃለሁ?
የማውቀውን ፊደል
ከማላውቀው ጋራ ብፅፍ እችላለሁ?
..
ል
ክ
እ
ን
ደ
ዚ
ህ
....
ቆአጦስ ጎሮሮስ ቤላጦስ ጦዝቻ
ስላንቺ ከማውራት ዝም ማለት ብቻ!!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ጻፊልኝ አትበለኝ!
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።።።።
ብዕር ለግሞብኝ፥
"አልጻፍ ያለኝን ፥ቃላት መትተው አድማ
ልቤ ጥጋት ጸድቆ፥
እንደ ቆንጥር ቧጦ ፥ ውስጤን እያደማ
የሚንጥን ሀሳብ፥
የማይድን ህመሜን ፥ ደግሞ ሊያስገረሸው
"ጻፊልኝ "ይለኛል፥
ድንግዝግዝ ንጋቴን ፥ መልሶ ሊያስመሸው።
"ይህንን ጻፊልኝ……"
"ከመራቅሽ ክሮች
ከመሄድሽ ጉንጉን ፥ ከቁጉ ምዕራፍ
የጸጸት አለንጋ፥
ለኔ መገረፊያ ፥ ተገመደ ጅራፍ!
ከገፋሁሽ ወዲያ፥
ደግሞ ልማስንሽ፥ ወጥቼ ስባዝን
እንዳላገኝሽ ሳውቅ፥
እርቃን ነፍሴ ባክና ፥ አየሁ ስትዛዝን።
በቀን ዐይኔ እያየ፥
አንቅፎ ቢጥለኝ ፥ ጎባጣ "ቀንጠፋ"
በምናልባት ሙዳይ፥
የሰነቅሁት ምኞት ፥ እኔን ይዞ ጠፋ።
እናም ይኼው ዛሬ…
መሄድሽ ሲገባኝ ፥ ላይመልስሽ መንገድ
መኖሬን ጠላሁት፥
በህሊና ችሎ ፥ ከበደኝ መታገድ።
የህሊና ዳኛ፥
ስንዝር አያራምድ ፥ ከመክሰስ ቦዝኖ
ምዕራፍ አያልቅበት፥
(ለቅጣቴ 'ሚሆን፥ )
አንቀጽ ያጣቅሳል ፥ ኬትም ኬትም ባዝኖ።"
እያለ ይለኛል
እረመጥ አራግቦ ፥ ዳግም ሊያቀጣጥል
ጭላንጭል ድኅነቴን፥
በግርሻ ትኩሳት ፥ ከደዌ ላይ ሊጥል።
በልብህ ላይ ፈርደህ፥
በታይታ ኪዳን ፥ ጣትህን ካሰርከው
በቀለበት ማግስት፥
ከተገለጠልህ ፥ ፍቅሬን ካስታወስከው
የሌላ ነህና…
እርሳኝ ግዴለህም፥
የጠገገ ቁስሌን፥ በሾህ አትከከው።
እናም ስሞትልህ
ጻፊልኝ አትበለኝ!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(ዳግም ህይወት)
።።።።።።።።።።።።
ብዕር ለግሞብኝ፥
"አልጻፍ ያለኝን ፥ቃላት መትተው አድማ
ልቤ ጥጋት ጸድቆ፥
እንደ ቆንጥር ቧጦ ፥ ውስጤን እያደማ
የሚንጥን ሀሳብ፥
የማይድን ህመሜን ፥ ደግሞ ሊያስገረሸው
"ጻፊልኝ "ይለኛል፥
ድንግዝግዝ ንጋቴን ፥ መልሶ ሊያስመሸው።
"ይህንን ጻፊልኝ……"
"ከመራቅሽ ክሮች
ከመሄድሽ ጉንጉን ፥ ከቁጉ ምዕራፍ
የጸጸት አለንጋ፥
ለኔ መገረፊያ ፥ ተገመደ ጅራፍ!
ከገፋሁሽ ወዲያ፥
ደግሞ ልማስንሽ፥ ወጥቼ ስባዝን
እንዳላገኝሽ ሳውቅ፥
እርቃን ነፍሴ ባክና ፥ አየሁ ስትዛዝን።
በቀን ዐይኔ እያየ፥
አንቅፎ ቢጥለኝ ፥ ጎባጣ "ቀንጠፋ"
በምናልባት ሙዳይ፥
የሰነቅሁት ምኞት ፥ እኔን ይዞ ጠፋ።
እናም ይኼው ዛሬ…
መሄድሽ ሲገባኝ ፥ ላይመልስሽ መንገድ
መኖሬን ጠላሁት፥
በህሊና ችሎ ፥ ከበደኝ መታገድ።
የህሊና ዳኛ፥
ስንዝር አያራምድ ፥ ከመክሰስ ቦዝኖ
ምዕራፍ አያልቅበት፥
(ለቅጣቴ 'ሚሆን፥ )
አንቀጽ ያጣቅሳል ፥ ኬትም ኬትም ባዝኖ።"
እያለ ይለኛል
እረመጥ አራግቦ ፥ ዳግም ሊያቀጣጥል
ጭላንጭል ድኅነቴን፥
በግርሻ ትኩሳት ፥ ከደዌ ላይ ሊጥል።
በልብህ ላይ ፈርደህ፥
በታይታ ኪዳን ፥ ጣትህን ካሰርከው
በቀለበት ማግስት፥
ከተገለጠልህ ፥ ፍቅሬን ካስታወስከው
የሌላ ነህና…
እርሳኝ ግዴለህም፥
የጠገገ ቁስሌን፥ በሾህ አትከከው።
እናም ስሞትልህ
ጻፊልኝ አትበለኝ!
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
###***ደረትና_እውነት***###
የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ፤
ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ
የነገርሽኝ ነገር ፤
ትላንት ስትከጂኝ ፤ትዝ ብሎኝ ነበር፤
እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?
ብዬ ስጠይቅሽ ፤ በለጋ አንደበቴ
ምንም
ምንም
ምንም አላለም ፤
ብለሽ የመለስሽው ፤ ከሆድሽ አይደለም
ደግሞም አውቅሻለሁ ፤ ቅጥፈት ስታስቢ
እንዳንች ቀጣፊ የለም
ንገሪኝ በሞቴ ፤
ሳይቦዝዝ ቅላቴ፤
እቴ ሜቴ እያልኩሽ ፤ በተባ አንደበቴ
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?ብዬ 'ምጠይቅሽ፤
እውነት አምሮኝ እንጂ ፤ ቀንቼ 'ንዳይመስልሽ
አየሽ...
በውሸት ሀገር ላይ ፤ እውነት የሚናገር
ውሸታም ይባላል ፤ በሀቀኞች ሰፈር
ውሸት ተደጋግሞ ፤ ከእውነት ሚስተካከል፤
ከእውነት 'ሚሳከር ፤
ረስተሽ ይሆን እንጂ ፤ የኛ ሀገር ነበር
እውነቱን ከውሸት ፤
ውሸቱን ከእውነት ፤ ስላደባለቅነው
ያንቺን የውሸት እውነት ፤
እንዴት አምንሻለው?
በውሸታም ሀገር እውነት ተናጋሪ
ውሸታም ይባላል
በውሸቶች ሀገር መሲህ ይሰቀላል
እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?
ምንም አላለኝ፤
ትዳርሽን ፈቶ ልውሰድሽ አለኝ
በጨዋታ መሀል ፤ ቅር አለኝ መሠለኝ
የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ
ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ
የነገርሽኝ ነገር ፤
እድሜ ተቀይሮ ፤ ጥለሽኝ ስትሄጂ ፤
ትዝ ብሎኝ ነበር
(በረከት ታደሰ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ፤
ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ
የነገርሽኝ ነገር ፤
ትላንት ስትከጂኝ ፤ትዝ ብሎኝ ነበር፤
እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?
ብዬ ስጠይቅሽ ፤ በለጋ አንደበቴ
ምንም
ምንም
ምንም አላለም ፤
ብለሽ የመለስሽው ፤ ከሆድሽ አይደለም
ደግሞም አውቅሻለሁ ፤ ቅጥፈት ስታስቢ
እንዳንች ቀጣፊ የለም
ንገሪኝ በሞቴ ፤
ሳይቦዝዝ ቅላቴ፤
እቴ ሜቴ እያልኩሽ ፤ በተባ አንደበቴ
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?ብዬ 'ምጠይቅሽ፤
እውነት አምሮኝ እንጂ ፤ ቀንቼ 'ንዳይመስልሽ
አየሽ...
በውሸት ሀገር ላይ ፤ እውነት የሚናገር
ውሸታም ይባላል ፤ በሀቀኞች ሰፈር
ውሸት ተደጋግሞ ፤ ከእውነት ሚስተካከል፤
ከእውነት 'ሚሳከር ፤
ረስተሽ ይሆን እንጂ ፤ የኛ ሀገር ነበር
እውነቱን ከውሸት ፤
ውሸቱን ከእውነት ፤ ስላደባለቅነው
ያንቺን የውሸት እውነት ፤
እንዴት አምንሻለው?
በውሸታም ሀገር እውነት ተናጋሪ
ውሸታም ይባላል
በውሸቶች ሀገር መሲህ ይሰቀላል
እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ፤
ያ ሰውዬ ምን አለሽ ማታ?
ምንም አላለኝ፤
ትዳርሽን ፈቶ ልውሰድሽ አለኝ
በጨዋታ መሀል ፤ ቅር አለኝ መሠለኝ
የልጅነት ነገር ፤ ቴሜቴ ጨዋታ
ደረቴን ስትደቂ ፤ ደረትሽን ስመታ
የነገርሽኝ ነገር ፤
እድሜ ተቀይሮ ፤ ጥለሽኝ ስትሄጂ ፤
ትዝ ብሎኝ ነበር
(በረከት ታደሰ)
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ፍካቱን እንኑር
፡
አበቦቹ ሁሉ ንብ ፍቅር ታደሉ
ስሞ አሳሳማቸው እንዳዲስ በቀሉ።
፡
የኔና አንቺ ፍቅር ጎደለው ንብነት
ቀስሞ አላዋሃደን ጣጥሎን ለምክነት።
፡
እንቡጦች አማሩን
በኛው ቀለም በቅለው በኛው ቀለም ሚያድጉ
ተያየን ሳንረግፍ
ፈራን ላናፈራ ላይቀር መጠውለጉ።
፡
ተዪኝ አልሰማሽም
ምን ብትሰበሪ አትበዪኝ ዘር ተካ
ምን ይሆነኝ ብለሽ
ባንቺ ተፀንሶ ጭንሽ ስር ካልፈካ!
፡
ምን ተዳችን እኛ
ዓለም ነው የቀረባት ቀለምሽ ቀለሜ
የእንቡጥ ወዳጄ ነይ
ፍካቱን እንኑር ማን ይቀርለታል የመርገፍ ፍፃሜ!
#Fekadu Getachew
@Asgeramiii 👈
@Asgeramiii 👈
@Asgeramiii 👈
፡
አበቦቹ ሁሉ ንብ ፍቅር ታደሉ
ስሞ አሳሳማቸው እንዳዲስ በቀሉ።
፡
የኔና አንቺ ፍቅር ጎደለው ንብነት
ቀስሞ አላዋሃደን ጣጥሎን ለምክነት።
፡
እንቡጦች አማሩን
በኛው ቀለም በቅለው በኛው ቀለም ሚያድጉ
ተያየን ሳንረግፍ
ፈራን ላናፈራ ላይቀር መጠውለጉ።
፡
ተዪኝ አልሰማሽም
ምን ብትሰበሪ አትበዪኝ ዘር ተካ
ምን ይሆነኝ ብለሽ
ባንቺ ተፀንሶ ጭንሽ ስር ካልፈካ!
፡
ምን ተዳችን እኛ
ዓለም ነው የቀረባት ቀለምሽ ቀለሜ
የእንቡጥ ወዳጄ ነይ
ፍካቱን እንኑር ማን ይቀርለታል የመርገፍ ፍፃሜ!
#Fekadu Getachew
@Asgeramiii 👈
@Asgeramiii 👈
@Asgeramiii 👈
ዶሮው ርግብ አፈቀረ።
የተበተነውን ጥሬ
እስኪለቅሙ አብረው ቢቆሙ
ተታለለ።
ከጎኑ ስላያት እኩያው... ቢጤው መሰለችው።
ክንፏ ሲርገበገብ፣
ቅንቅኑን ሊያራግፍ ክንፉን አርገበገበ።
ስታኮበኩብ አጎበጎበ።
«መብረር» ይሉት ታምር እንዳለ መች አወቀ?
ቀና ብላ ሄደች።
አቀረቀረ።
ዶሮው ርግቧን ጠላት።
«የማይበር ክንፉን አስታወሰችው...»
ርግቤ ሙዚቃ ነበረች።
ሰማኋት ብዬ የምድር ስበት ሕግ ላይ አመጽኩ።
እስትንፋሳችን
ለቅጽበታት ቢተሳሰር ...ዜማ ቢጤዬ ነው አልኩ።
ከምቱ እኩል
ተርገብግቤ
... ተንገብግቤ
ላርግ ቅፅበት ሲቀር ...
የሰወረኝ ዜማ ወደማልከተለው ሩቅቅቅቅ ይሰወርብኛል።
ከትኩስ ፈጣን ትንፋሼ ጋር ብቻዬን እቀራለሁ።
ሙዚቃን ጠላኋት።
አብሯት የማይበር ክንፌን...
አብሯት የማይሰወር ስጋዬን
ታስታውሰኛለች።
#Rediet_Aseffa
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
የተበተነውን ጥሬ
እስኪለቅሙ አብረው ቢቆሙ
ተታለለ።
ከጎኑ ስላያት እኩያው... ቢጤው መሰለችው።
ክንፏ ሲርገበገብ፣
ቅንቅኑን ሊያራግፍ ክንፉን አርገበገበ።
ስታኮበኩብ አጎበጎበ።
«መብረር» ይሉት ታምር እንዳለ መች አወቀ?
ቀና ብላ ሄደች።
አቀረቀረ።
ዶሮው ርግቧን ጠላት።
«የማይበር ክንፉን አስታወሰችው...»
ርግቤ ሙዚቃ ነበረች።
ሰማኋት ብዬ የምድር ስበት ሕግ ላይ አመጽኩ።
እስትንፋሳችን
ለቅጽበታት ቢተሳሰር ...ዜማ ቢጤዬ ነው አልኩ።
ከምቱ እኩል
ተርገብግቤ
... ተንገብግቤ
ላርግ ቅፅበት ሲቀር ...
የሰወረኝ ዜማ ወደማልከተለው ሩቅቅቅቅ ይሰወርብኛል።
ከትኩስ ፈጣን ትንፋሼ ጋር ብቻዬን እቀራለሁ።
ሙዚቃን ጠላኋት።
አብሯት የማይበር ክንፌን...
አብሯት የማይሰወር ስጋዬን
ታስታውሰኛለች።
#Rediet_Aseffa
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(((እኔም #ገጣሚ_ነኝ)))
ስሙኝ.......
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
በሶሻል ሚዲያ
ስሜ ያልተጠራ
ብዙም ያልታወኩኝ....
በደሳሳ ጎጆ
ህልሜን ያጠበብኩኝ
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
*
*
*
ከምሁራን ተርታ
ፈፅሞ ያልተሰለፍኩ
ከእውቅ ፀሀፊያን
መሀል ያልተካተትኩ
እኔም #ደራሲ_ነኝ!
በሰላች ብእሬ
ስሜቴን የገለፅኩ
*
*
ነገር ግን......
እንደነ እንትና
እስካርፕ አልጠመጠምኩ
እንደ ሀያሲያን
ሸሚዝ በከረባት
ታጥቄ አለበስኩ
በአምስቱ ጣቶቼ
የእከሌን መፅሀፍ
ይዤ አልተሽከረከርኩ....
በሄድኩበት ሁሉ
#ደራሲ_ነኝ እኔ
እውቅ ነው ሀሳቤ
ብዬም አልተናዘዝኩ.....
*
*
.........ግናም እፅፋለሁ........
ብእር ከወረቀት
እያዋደድኳቸው
ለሰው የማይገባ
ዝብርቅርቅ ሀሳባት
እኔም አፈሳለሁ ...
በሀሳቤ አርግዤው
ለአእላፉ ቀናት
እያብሰለሰልኩት
ይዤው እከርማለሁ...
የቁርጥ ቀን መቶ
እስክገላገለው
ወረቀት ከብእር
እስከማጋጥመው
ብዙ አምጣለሁ...
ያማጥኩት ተባርኮ
በመድብል ሲወለድ
ማየትን እሻለሁ..
*
*
እና እንደሌሎቹ.....
#እኔም_ገጣሚ ነኝ!
ብዬ አልዘባርቅም...
የገጠምኩት #ግጥም
የደረስኩት ድርሰት
የከሌ ነው ታሪክ ነው
ብዬ አልናገርም...
*
*
እውነቱ ገብቷቸው
አንተ #ደራሲ_ነክ
የሰዎችን እውነት
በብእር የገለፅክ
ብለው እስኪረዱኝ
በቤቴ የምኖር
እኔም #ገጣሚ_ነኝ
✍ተፃፈ በ ማክቤል
ግንቦት 1,2012
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
T.me/hutoffun 👈
ስሙኝ.......
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
በሶሻል ሚዲያ
ስሜ ያልተጠራ
ብዙም ያልታወኩኝ....
በደሳሳ ጎጆ
ህልሜን ያጠበብኩኝ
እኔም #ገጣሚ_ነኝ!
*
*
*
ከምሁራን ተርታ
ፈፅሞ ያልተሰለፍኩ
ከእውቅ ፀሀፊያን
መሀል ያልተካተትኩ
እኔም #ደራሲ_ነኝ!
በሰላች ብእሬ
ስሜቴን የገለፅኩ
*
*
ነገር ግን......
እንደነ እንትና
እስካርፕ አልጠመጠምኩ
እንደ ሀያሲያን
ሸሚዝ በከረባት
ታጥቄ አለበስኩ
በአምስቱ ጣቶቼ
የእከሌን መፅሀፍ
ይዤ አልተሽከረከርኩ....
በሄድኩበት ሁሉ
#ደራሲ_ነኝ እኔ
እውቅ ነው ሀሳቤ
ብዬም አልተናዘዝኩ.....
*
*
.........ግናም እፅፋለሁ........
ብእር ከወረቀት
እያዋደድኳቸው
ለሰው የማይገባ
ዝብርቅርቅ ሀሳባት
እኔም አፈሳለሁ ...
በሀሳቤ አርግዤው
ለአእላፉ ቀናት
እያብሰለሰልኩት
ይዤው እከርማለሁ...
የቁርጥ ቀን መቶ
እስክገላገለው
ወረቀት ከብእር
እስከማጋጥመው
ብዙ አምጣለሁ...
ያማጥኩት ተባርኮ
በመድብል ሲወለድ
ማየትን እሻለሁ..
*
*
እና እንደሌሎቹ.....
#እኔም_ገጣሚ ነኝ!
ብዬ አልዘባርቅም...
የገጠምኩት #ግጥም
የደረስኩት ድርሰት
የከሌ ነው ታሪክ ነው
ብዬ አልናገርም...
*
*
እውነቱ ገብቷቸው
አንተ #ደራሲ_ነክ
የሰዎችን እውነት
በብእር የገለፅክ
ብለው እስኪረዱኝ
በቤቴ የምኖር
እኔም #ገጣሚ_ነኝ
✍ተፃፈ በ ማክቤል
ግንቦት 1,2012
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
T.me/hutoffun 👈
Telegram
የጥበብ ጎጆ
እነሆ ለጥበብ አፍቃሪዎች የተከፈተ ምርጥ ቻናል!
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
በቻናላችን
📚 ግጥም
📚 ወግ
📚 መነባንብ
📚 ቀልዶች
📚 በ አለማችን ላይ ያሉ አስደናቂ እውነቶችን ከሚገርም አቀራረብ ጋር በዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ።
👇ተቀላቀሉን👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFS2M9K62l4CabPUjQ
ለአስተያየትዎ👉 @TeweldeBot
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
በቻናላችን
📚 ግጥም
📚 ወግ
📚 መነባንብ
📚 ቀልዶች
📚 በ አለማችን ላይ ያሉ አስደናቂ እውነቶችን ከሚገርም አቀራረብ ጋር በዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ።
👇ተቀላቀሉን👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFS2M9K62l4CabPUjQ
ለአስተያየትዎ👉 @TeweldeBot
(የእናቴ ልጅ ነኝ)
ወዳጄን ባጣ፣
እውነት ቢርቀኝ፣
አካል ታቅፌ ፣
ሰው ቢናፍቀኝ ፣
የማልበገር፣
የእናቴ ልጅ ነኝ።
እንክርዳድ ትቼ፣
ፍሬ ምዘራ ፣
እሾህን ነቅዬ፣
በራሴ የምኮራ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ፣
ልበ ጠንካራ ።
ቅመሙን ደቁሼ ፣
ቅቤውን ማጋራ፣
ጣእምን ቀምሼ፣
የምጥል አሻራ ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ላሟን የማጣራ።
ጆሮዬን አቁሜ ፣
ሀቅን የምቀዳ፣
እንከኔን ጠርጌ ፣
ማስወግድ በጓዳ ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ሆዴን የማፀዳ።
ፍረሀት ወቅጦ፣
ያለደቀቀኝ ፣
ወንጀል ጠጥሮ፣
ያልጨፈለቀኝ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ታሪክ ያፀደቀኝ።
✍ ቤዚቾ ( @Poetesss )
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
ወዳጄን ባጣ፣
እውነት ቢርቀኝ፣
አካል ታቅፌ ፣
ሰው ቢናፍቀኝ ፣
የማልበገር፣
የእናቴ ልጅ ነኝ።
እንክርዳድ ትቼ፣
ፍሬ ምዘራ ፣
እሾህን ነቅዬ፣
በራሴ የምኮራ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ፣
ልበ ጠንካራ ።
ቅመሙን ደቁሼ ፣
ቅቤውን ማጋራ፣
ጣእምን ቀምሼ፣
የምጥል አሻራ ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ላሟን የማጣራ።
ጆሮዬን አቁሜ ፣
ሀቅን የምቀዳ፣
እንከኔን ጠርጌ ፣
ማስወግድ በጓዳ ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ሆዴን የማፀዳ።
ፍረሀት ወቅጦ፣
ያለደቀቀኝ ፣
ወንጀል ጠጥሮ፣
ያልጨፈለቀኝ፣
የእናቴ ልጅ ነኝ ፣
ታሪክ ያፀደቀኝ።
✍ ቤዚቾ ( @Poetesss )
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
አምስቱ የስሜት ህዋሳት ስንት ናቸው?
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
#መፈንቅለ_አመል
.
ሳይወድ በግዱ.......በወራት ጭካኔ ፣
በልኩ ሰው ጭኖ
አንበሳ ሲጠግብ ፥ አስተውዬ ባይኔ ፣
ባገም ጠቀም ምስጠት....
ድቅን ሲልብኝ ፥ ያለፈ ዘመኔ፣
በመስኮት ተክዬ
ከውስጥ ወደ ደጁ፥በሩቁ ስማትር ፥ ከወደዚህ እኔ
ከወደዛኛው ጥግ
#የተረገመ_ቀን !!
ሁሉ ተቀምጦ...በወንበሩ ስግስግ፣
እንዴት ...እጄን ልላክ ?
እንዴት ኪስ ልሟግግ...?
ይላል ከደጁ ላይ ...ከመቁረጡ አርፎ ፣
የጅ ቢጢፋ እንኳ...
ካንዷ ኮረዳ ጋር...ማሻሸት አትርፎ ፣
በዘንግ አመሀኝቶ ...ዘንጉን አስደግፎ ፣
እስኪሟሟ ድረስ ...የሴት ዳሌ አልፍቶ ፣
በተለይ ሲጨልም...ቻርኔላውን ፈቶ ፣
የለመደው ሁሉ ...
ትኩሳተ ስራው ፣
አንድም ለብስጭት፥ አንድም ለወገራው፣
እያዘዋወረ....ህዝቡን እንዳልገራው ፣
አሁን ላይ ቢቀየር..ሰልፉ ሆኖ ማግኛው ፣
መታፈግ #ቢፀየፍ
ስርዐት ቢከጅል ... #የኮረና ጥላው ፣
ዛሬ...ባሱን ሸሸ... ፤
ዛሬ ...ባሱን #ጠላው ።
በዚህ #ለውጠ_ልማድ
ከሸገር ....ባሻገር ፥ ቀን ያጋለጠውን እያገላበጠ ፣
እያለፍ ፣ እያለፍ ፥ ኪሱን እያጠጠ ፣
ግፊያውን #ይጋፋል...፣
ሰልፉን #ይሰለፋል...፣
ምን በሩጋ ቢደርስ ... #ምንግዜም_ይተርፋል ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
አዳሜ እና ሄዋኔ..
ሿ..ሿው ከበረንዳ ጀምሯል...
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
.
ሳይወድ በግዱ.......በወራት ጭካኔ ፣
በልኩ ሰው ጭኖ
አንበሳ ሲጠግብ ፥ አስተውዬ ባይኔ ፣
ባገም ጠቀም ምስጠት....
ድቅን ሲልብኝ ፥ ያለፈ ዘመኔ፣
በመስኮት ተክዬ
ከውስጥ ወደ ደጁ፥በሩቁ ስማትር ፥ ከወደዚህ እኔ
ከወደዛኛው ጥግ
#የተረገመ_ቀን !!
ሁሉ ተቀምጦ...በወንበሩ ስግስግ፣
እንዴት ...እጄን ልላክ ?
እንዴት ኪስ ልሟግግ...?
ይላል ከደጁ ላይ ...ከመቁረጡ አርፎ ፣
የጅ ቢጢፋ እንኳ...
ካንዷ ኮረዳ ጋር...ማሻሸት አትርፎ ፣
በዘንግ አመሀኝቶ ...ዘንጉን አስደግፎ ፣
እስኪሟሟ ድረስ ...የሴት ዳሌ አልፍቶ ፣
በተለይ ሲጨልም...ቻርኔላውን ፈቶ ፣
የለመደው ሁሉ ...
ትኩሳተ ስራው ፣
አንድም ለብስጭት፥ አንድም ለወገራው፣
እያዘዋወረ....ህዝቡን እንዳልገራው ፣
አሁን ላይ ቢቀየር..ሰልፉ ሆኖ ማግኛው ፣
መታፈግ #ቢፀየፍ
ስርዐት ቢከጅል ... #የኮረና ጥላው ፣
ዛሬ...ባሱን ሸሸ... ፤
ዛሬ ...ባሱን #ጠላው ።
በዚህ #ለውጠ_ልማድ
ከሸገር ....ባሻገር ፥ ቀን ያጋለጠውን እያገላበጠ ፣
እያለፍ ፣ እያለፍ ፥ ኪሱን እያጠጠ ፣
ግፊያውን #ይጋፋል...፣
ሰልፉን #ይሰለፋል...፣
ምን በሩጋ ቢደርስ ... #ምንግዜም_ይተርፋል ።
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
አዳሜ እና ሄዋኔ..
ሿ..ሿው ከበረንዳ ጀምሯል...
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
@hutoffun 👈
Potassium
Almunium
Calcium
፨ልቤ'nium
Chemist ነን ባዮች
Professor ተብዮች
Element ፈጣሪዎች
ግማሹን በቦታው
ግማሹን እንደየሁኔታው
አንዳንዱን በስማቸው
ሌሎቹን በሀገራቸው
ሲሰያይሟቸው
የእኔ ግን ይለያል
ፍፁምም ይረቃል
የልቤን ቀማኛ
ያደረገኝን ህመምተኛ
Element ፈጥሬ
የህዝቡን ዝማሬ
ውስጤ ሳላስገባ ላንዴም ሳላስበው
በእንባ የረጠበውን የልጁን ትውስታ መቼም እንዳረሳው
ያንን የልብ ሌባ ያን ነፍሰ ገዳይ
እንዲሆን ስል የዓለም ጉዳይ
በስሙ ሰይሜ ጭራሽ ከማነግሰው
ልቤን እንደቀማ ሁሌ እንዲያስታውሰው
ሠፈሬን ቀዬውን
ወርውሬ ሀገሬን
ልቤ'nium ኣልኩት
ለ፩ዲቷ ልቤ ስላራራላት።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ለልብ ሌቦች
@hutoffun
Almunium
Calcium
፨ልቤ'nium
Chemist ነን ባዮች
Professor ተብዮች
Element ፈጣሪዎች
ግማሹን በቦታው
ግማሹን እንደየሁኔታው
አንዳንዱን በስማቸው
ሌሎቹን በሀገራቸው
ሲሰያይሟቸው
የእኔ ግን ይለያል
ፍፁምም ይረቃል
የልቤን ቀማኛ
ያደረገኝን ህመምተኛ
Element ፈጥሬ
የህዝቡን ዝማሬ
ውስጤ ሳላስገባ ላንዴም ሳላስበው
በእንባ የረጠበውን የልጁን ትውስታ መቼም እንዳረሳው
ያንን የልብ ሌባ ያን ነፍሰ ገዳይ
እንዲሆን ስል የዓለም ጉዳይ
በስሙ ሰይሜ ጭራሽ ከማነግሰው
ልቤን እንደቀማ ሁሌ እንዲያስታውሰው
ሠፈሬን ቀዬውን
ወርውሬ ሀገሬን
ልቤ'nium ኣልኩት
ለ፩ዲቷ ልቤ ስላራራላት።
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ ለልብ ሌቦች
@hutoffun
በሞትክ
ባሌ ሙት ባሌ ሙት
ሞት ነው ላንተ ያለኝ ምኞት
እንድትሞትልኝ ነው የኔ ፍላጎት
መቼም አልዋሽህም
አይንህን እያየውም
ኣንተንም ማስመሠልም
እኔ ኣልችልም
ቢሳካ ስለቴ
ቢረዳኝ እምነቴ
እግዜሩ ቢሰማኝ
መላዕኩ ቢራዳኝ
ኣንተ እንድትሞትልኝ
ነበረ ፀሎቴ
አድምጠኝ ምክንያቴ
የሔዋን ዘር በዛ
ፈላጊህ ተባዛ
ዓይኖች ኣንተን ሻቱ
ልቦች ላንተ ተከፈቱ
ከኣንዷ ሳስጥልህ
ኣንዷ እየቀማችኝ
ስለተቸገርኩኝ
'ላይ ከፈጣሪ ቀኝ
ተቀምጠህ ቆየኝ
ኣልቀርም ጠብቀኝ::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ በባሎቻችሁ ውበት ለተጨናነቃችሁ😂
@hutoffun
ባሌ ሙት ባሌ ሙት
ሞት ነው ላንተ ያለኝ ምኞት
እንድትሞትልኝ ነው የኔ ፍላጎት
መቼም አልዋሽህም
አይንህን እያየውም
ኣንተንም ማስመሠልም
እኔ ኣልችልም
ቢሳካ ስለቴ
ቢረዳኝ እምነቴ
እግዜሩ ቢሰማኝ
መላዕኩ ቢራዳኝ
ኣንተ እንድትሞትልኝ
ነበረ ፀሎቴ
አድምጠኝ ምክንያቴ
የሔዋን ዘር በዛ
ፈላጊህ ተባዛ
ዓይኖች ኣንተን ሻቱ
ልቦች ላንተ ተከፈቱ
ከኣንዷ ሳስጥልህ
ኣንዷ እየቀማችኝ
ስለተቸገርኩኝ
'ላይ ከፈጣሪ ቀኝ
ተቀምጠህ ቆየኝ
ኣልቀርም ጠብቀኝ::
(የዱድያሌብ ገፅ)
ይድረስ በባሎቻችሁ ውበት ለተጨናነቃችሁ😂
@hutoffun