❤️❤️❤️❤️ ፍቅር❤️❤️❤️❤️
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
ሰለፍቅር ሲተረክ ምንጊዜም ሰማለሁ፣
የፍቅር መኖሪያ የት ይሆን እላለሁ፣
ያም ፍቅር ያም ፍቅር ፣
በሄድኩበት ሀገር ፣
በዘመትኩት መንደር፣
💞💞💞💞💞💞💞💞💞
ለራሴም ይህን አልኩ ይህ ሁሉ ቃላትየሚተረክልህ፣
ቅኔ የሚቀኝልህ ግጥም የሚፃፍልህ፣
የእውነት ፍቅር የት ነህ ????
💞💞💞💞💞💞💞💞
አንዳንዶች ይሉኛል ....
ፍቅር እኮ ህይወት ነው ፣
ፍቅር እኮ የደስታ ምንጭ ነው ፣
እያሉ ይሰብኩኛል ፣
የኔም ፍላጎቴ ይበልጥ ጨምሮብኛል፣
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ታጥቄ ተነሳሁ ፍቅርን ፍለጋ፣
ማልጄ ልፈልግ ሌሊቱ ሳይነጋ፣
በየ አውራ ጎዳናው ፍቅርን ስፈልግ፣
ፍቅርን አገኘሁት ከዛፍ ስር ይዞ ጥግ፣
💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘
ሳየው ደነገጥኩኝ ግራ እየተጋባኝ ፣
የተነገረኝና ያየሁት አልመጣጠንልሽ ብሎኝ፣
ቀርቤ አዋየሁት .......
ቆይ ፍቅርኮ እውነት ነው ሲሉኝ አልነበረ፣
ፍቅር እኮ ሀሴት ነው ሲሉኝ አልነበረ ፣
ታድያ ምነው አዘንክ ስቃይህ ጨመረ??
ብየ አዋየሁት ......
ባአመድ ጭቃ ተለውሶ ታሞ ሲያቃስት፣
💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜
እውነትማ እውነት ነኝ .....
ጠብቆ ለያዘኝ ለተከባከበኝ ፣
ላልተገባበረኝ ግን እኔም ሸክላ ነኝ ፣
💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔
ወንዱ ይችንም ያችንም ሲላት አፈቀርኩሽ፣
አበድኩ መሞቴነው እኔማ በፍቅርሽ፣
ፍቅር ሙች እያልኩሽ ፣
እያለ በስሜ በሀሰት ይምላል ፣
ለቀይዋም ለጥቁራም ልሙትልሽ ይላል፣
፨
፨
ሴቷም ......
ይህንን አጎቴ ያንንም ወንድሜ ጓደኛየ እያለች፣
ባሏጋ ተቀምጣ ሌላ እየተመኘች ፣
በእውነት ስሜ ጠፍቶ በሀሰት ሲምሉብኝ፣
የወሬ ማድመቂያ እርእሳቸው ሲያደርጉኝ፣
እንደትስ አላዝን እንደትስ አይከፋኝ፣
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
ይሄ ነው ያስከፋኝ ልቤን የሰበረው፣
ከለላ ሚሆነኝ አንድ ሰው ባጣነው፣
እንጂማ ..........
የእውነት ፍቅርን ይዞ ለተገባበረኝ፣
ቀንን ብሩህ የማደርግ የእውነት ፍቅር ነኝ፣
ሁሉን የማከብር ጎንበስ ቀና እያልኩኝ፣
💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘
በሚያሳዝን አንደበቱ ይህንን ሲነግረኝ ፣
የእውነት ፍቅር ማለት ምን እደሁ ተረዳሁኝ፣
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ፍቅር ከባህር ብዘፈቅ ከውቂያኖስ ብጠልቅ፣
የማይበርድ ትኩሳት የሌለው መድሀኒት፣
ሰው የገዛ ልቡ ጠላቱ ሆኖበት ፣
ማደሪያውን ትቶ ሰርክ ሲንከራተት ፣
ማረፊያ አጥቶ ሁሌ ሲከንፍ አየሁት፣
💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜
ለካስ ፍቅር ኖሯል ሰውን ሰው ሚያደርገው፣
ሀገርን የሚያስወድድ ሰውን በአንድነት በሰላም ሚያኖረው፣
ለካስ ፍቅር ኖሯል ህይወትን ሚያቀናው
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
ሰለፍቅር ሲተረክ ምንጊዜም ሰማለሁ፣
የፍቅር መኖሪያ የት ይሆን እላለሁ፣
ያም ፍቅር ያም ፍቅር ፣
በሄድኩበት ሀገር ፣
በዘመትኩት መንደር፣
💞💞💞💞💞💞💞💞💞
ለራሴም ይህን አልኩ ይህ ሁሉ ቃላትየሚተረክልህ፣
ቅኔ የሚቀኝልህ ግጥም የሚፃፍልህ፣
የእውነት ፍቅር የት ነህ ????
💞💞💞💞💞💞💞💞
አንዳንዶች ይሉኛል ....
ፍቅር እኮ ህይወት ነው ፣
ፍቅር እኮ የደስታ ምንጭ ነው ፣
እያሉ ይሰብኩኛል ፣
የኔም ፍላጎቴ ይበልጥ ጨምሮብኛል፣
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ታጥቄ ተነሳሁ ፍቅርን ፍለጋ፣
ማልጄ ልፈልግ ሌሊቱ ሳይነጋ፣
በየ አውራ ጎዳናው ፍቅርን ስፈልግ፣
ፍቅርን አገኘሁት ከዛፍ ስር ይዞ ጥግ፣
💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘
ሳየው ደነገጥኩኝ ግራ እየተጋባኝ ፣
የተነገረኝና ያየሁት አልመጣጠንልሽ ብሎኝ፣
ቀርቤ አዋየሁት .......
ቆይ ፍቅርኮ እውነት ነው ሲሉኝ አልነበረ፣
ፍቅር እኮ ሀሴት ነው ሲሉኝ አልነበረ ፣
ታድያ ምነው አዘንክ ስቃይህ ጨመረ??
ብየ አዋየሁት ......
ባአመድ ጭቃ ተለውሶ ታሞ ሲያቃስት፣
💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜
እውነትማ እውነት ነኝ .....
ጠብቆ ለያዘኝ ለተከባከበኝ ፣
ላልተገባበረኝ ግን እኔም ሸክላ ነኝ ፣
💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔💔
ወንዱ ይችንም ያችንም ሲላት አፈቀርኩሽ፣
አበድኩ መሞቴነው እኔማ በፍቅርሽ፣
ፍቅር ሙች እያልኩሽ ፣
እያለ በስሜ በሀሰት ይምላል ፣
ለቀይዋም ለጥቁራም ልሙትልሽ ይላል፣
፨
፨
ሴቷም ......
ይህንን አጎቴ ያንንም ወንድሜ ጓደኛየ እያለች፣
ባሏጋ ተቀምጣ ሌላ እየተመኘች ፣
በእውነት ስሜ ጠፍቶ በሀሰት ሲምሉብኝ፣
የወሬ ማድመቂያ እርእሳቸው ሲያደርጉኝ፣
እንደትስ አላዝን እንደትስ አይከፋኝ፣
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
ይሄ ነው ያስከፋኝ ልቤን የሰበረው፣
ከለላ ሚሆነኝ አንድ ሰው ባጣነው፣
እንጂማ ..........
የእውነት ፍቅርን ይዞ ለተገባበረኝ፣
ቀንን ብሩህ የማደርግ የእውነት ፍቅር ነኝ፣
ሁሉን የማከብር ጎንበስ ቀና እያልኩኝ፣
💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘💘
በሚያሳዝን አንደበቱ ይህንን ሲነግረኝ ፣
የእውነት ፍቅር ማለት ምን እደሁ ተረዳሁኝ፣
💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕
ፍቅር ከባህር ብዘፈቅ ከውቂያኖስ ብጠልቅ፣
የማይበርድ ትኩሳት የሌለው መድሀኒት፣
ሰው የገዛ ልቡ ጠላቱ ሆኖበት ፣
ማደሪያውን ትቶ ሰርክ ሲንከራተት ፣
ማረፊያ አጥቶ ሁሌ ሲከንፍ አየሁት፣
💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜💜
ለካስ ፍቅር ኖሯል ሰውን ሰው ሚያደርገው፣
ሀገርን የሚያስወድድ ሰውን በአንድነት በሰላም ሚያኖረው፣
ለካስ ፍቅር ኖሯል ህይወትን ሚያቀናው
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
<<አንቺ ዓለም>>
በደዌ ሲማቅቅ ባ'ልጋ የከረመ
'ሰው አጣሁ እያለ' ድኅነት የቃረመ
'ልትድን ትወዳለህ?' በሚል ስጦታ ቃል
አልጋህን ተሸከም ተመላለስ ቢባል
ውለታ ዘንግቶ
የሀሰት ክስ መዝገብ የሚያገለባብጥ
ስላዳነው ፋንታ
እጅ መንሻ አይደለ ጥፊ ምት የሚሰጥ
መፃጉዕ የሞላብሽ
አንቺ ዓለም ህመም ነሽ!"
ቡሩክ ወልደ ዳዊት ሆሳዕና እያለ
ዝማሬ ቃል ሲሰጥ ላይክድ እንዳልማለ
መሬት አይንካው ሲል
ልብሱን ከመሬትላይ ሲያነጥፍ እንዳልዋለ
ዘንባባውን ቀጥፎ
እያወዛወዘ " ረቡኒ" እንዳላለ
ዐርብ ቀን ስትመጣ
ይሰቀል እያለ...
ያሸበሸበ እጁን ለፍርድ የቀሰረ
በርባን እንዲፈታ መምህሩን ያሰረ
የውሉደ አይሁድ መኖሪያ አጸድ የሆንሽ
አክሊለ ሦክ ጎንጓኝ አንቺዓለም እሾህ ነሽ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
በደዌ ሲማቅቅ ባ'ልጋ የከረመ
'ሰው አጣሁ እያለ' ድኅነት የቃረመ
'ልትድን ትወዳለህ?' በሚል ስጦታ ቃል
አልጋህን ተሸከም ተመላለስ ቢባል
ውለታ ዘንግቶ
የሀሰት ክስ መዝገብ የሚያገለባብጥ
ስላዳነው ፋንታ
እጅ መንሻ አይደለ ጥፊ ምት የሚሰጥ
መፃጉዕ የሞላብሽ
አንቺ ዓለም ህመም ነሽ!"
ቡሩክ ወልደ ዳዊት ሆሳዕና እያለ
ዝማሬ ቃል ሲሰጥ ላይክድ እንዳልማለ
መሬት አይንካው ሲል
ልብሱን ከመሬትላይ ሲያነጥፍ እንዳልዋለ
ዘንባባውን ቀጥፎ
እያወዛወዘ " ረቡኒ" እንዳላለ
ዐርብ ቀን ስትመጣ
ይሰቀል እያለ...
ያሸበሸበ እጁን ለፍርድ የቀሰረ
በርባን እንዲፈታ መምህሩን ያሰረ
የውሉደ አይሁድ መኖሪያ አጸድ የሆንሽ
አክሊለ ሦክ ጎንጓኝ አንቺዓለም እሾህ ነሽ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
............"ህመሜ ሆንክብኝ".......
ምንድነው እውነታው ጨለማ ያስመኘክ
በተስፋ እየኖርክ ጥፋትን ያሳየክ
እሩቅን አስበህ በቅርብ የቀረከው
ደስታህን ሰንቀክ በሀዘን የራከው
ለምን ይሆን ከቶ እኛን ያልፈለከው
ንገረኝ ወንድሜ ልስማው ህመምክን
ተስፋ አስቆርጦ ለሞት ያበቃክን
እውነቱን ደብቆ ውሸት የሰጠክን
መኖርን አልጠላም ምንም ባይሳካ
ነገን አየዋለው ጊዜውም ሲተካ
አሁን ባይሞላልኝ ወደፊት ይሆናል
ቀኖች ሲቀየሩ ጨለማው ይጠራል
የልጅነት ህልሜ ስኬቱ ይሰምራል
ትለኝ ነበር እኮ ዛሬስ ጨክነሀል
መቀበል አቃተኝ እንዴትስ ቻልከው
ሕይወትህን ጠልተክ በገመድ ያኖርከው
ራስን ለማጥፋት በምን ተመኘከው
እውነቱን ባላውቀው ቆመ ባትነግረኝም
ተስፈኛው ወንድሜ ይህን አይመኝም
ማነው የሰቀለህ በነፍስህ ጨቅኖ
የነገህን ተስፋ ፍካቱን አዳፍኖ
በላ ተነስና ልስማው ችግርህን
ልቡን አደንድኖ ለሞት የሰጠህን
በገመድ አውሎክ ስቆ ያስነባህን
ይህን ሀሉ እውነት ይዘከው ሄደክ
ሀዘንን ተክተክ ዘላለም ጠፋክ
ለጣረችው ነፍስህ ሳልሆንላት አዳኝ
ዳግም ላላገኝክ ህመሜ ሆንክብኝ
አሁን እረፍዶብኝ መፍትሄውን ባልነግርህ
ህመም ቢዳፈን ቢቀበር በውስጥህ
ምንም አላገዝኩ
ሌላ ቃል የለኝም
አምላክ በምህረቱ ሀፂያትክን ሽሮልህ
በአፀደ ገነት በክብር ያኑርህ::
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ምንድነው እውነታው ጨለማ ያስመኘክ
በተስፋ እየኖርክ ጥፋትን ያሳየክ
እሩቅን አስበህ በቅርብ የቀረከው
ደስታህን ሰንቀክ በሀዘን የራከው
ለምን ይሆን ከቶ እኛን ያልፈለከው
ንገረኝ ወንድሜ ልስማው ህመምክን
ተስፋ አስቆርጦ ለሞት ያበቃክን
እውነቱን ደብቆ ውሸት የሰጠክን
መኖርን አልጠላም ምንም ባይሳካ
ነገን አየዋለው ጊዜውም ሲተካ
አሁን ባይሞላልኝ ወደፊት ይሆናል
ቀኖች ሲቀየሩ ጨለማው ይጠራል
የልጅነት ህልሜ ስኬቱ ይሰምራል
ትለኝ ነበር እኮ ዛሬስ ጨክነሀል
መቀበል አቃተኝ እንዴትስ ቻልከው
ሕይወትህን ጠልተክ በገመድ ያኖርከው
ራስን ለማጥፋት በምን ተመኘከው
እውነቱን ባላውቀው ቆመ ባትነግረኝም
ተስፈኛው ወንድሜ ይህን አይመኝም
ማነው የሰቀለህ በነፍስህ ጨቅኖ
የነገህን ተስፋ ፍካቱን አዳፍኖ
በላ ተነስና ልስማው ችግርህን
ልቡን አደንድኖ ለሞት የሰጠህን
በገመድ አውሎክ ስቆ ያስነባህን
ይህን ሀሉ እውነት ይዘከው ሄደክ
ሀዘንን ተክተክ ዘላለም ጠፋክ
ለጣረችው ነፍስህ ሳልሆንላት አዳኝ
ዳግም ላላገኝክ ህመሜ ሆንክብኝ
አሁን እረፍዶብኝ መፍትሄውን ባልነግርህ
ህመም ቢዳፈን ቢቀበር በውስጥህ
ምንም አላገዝኩ
ሌላ ቃል የለኝም
አምላክ በምህረቱ ሀፂያትክን ሽሮልህ
በአፀደ ገነት በክብር ያኑርህ::
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
..................የ 'እኛ 'ኑሮ.................
ክፋት ምቀኝነት ገብቶ ከልባችን፣
ቂምና ተንኮል ሆነው ከደማችን፣
እኔን አስቀደምን ከእኛ አስበልጠን።
እንደዚህ አድርጌ እንደዚያ ብናገር፣
እነሱም ተጣልተው ጉዳዩ ሲከር፣
ሀገር ስትታመስ ስትጦዝ በነገር።
ይሄን ላገኝ ነው እኔም ልጠቀም ነው፣
ክብርን ከሞገስ ጋር ይሰጠኛል ሰው፣
ይላል ባለማወቅ ሳይገባው ስራው።
ደግሞም ይመጣና ይነግራል በኩራት፣
ስለሰራው ስህተት ልክ እንደጀግንነት፣
መሆኑን ዘንግቶት የታሪክ ተወቃሽ፣
የጊዜው እንቅፋት ትውልዱን አስለቃሽ።
ቢያውቅማ ኖሮ ቢረዳው ሀሳቡን
እኔ የምኖረው በእኛ ውስጥ መሆኑን፣
እንኳንስ ሊያወራው ያደረገውን፣
አያስበውም ነበር በጭራሽ ነገሩን።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ክፋት ምቀኝነት ገብቶ ከልባችን፣
ቂምና ተንኮል ሆነው ከደማችን፣
እኔን አስቀደምን ከእኛ አስበልጠን።
እንደዚህ አድርጌ እንደዚያ ብናገር፣
እነሱም ተጣልተው ጉዳዩ ሲከር፣
ሀገር ስትታመስ ስትጦዝ በነገር።
ይሄን ላገኝ ነው እኔም ልጠቀም ነው፣
ክብርን ከሞገስ ጋር ይሰጠኛል ሰው፣
ይላል ባለማወቅ ሳይገባው ስራው።
ደግሞም ይመጣና ይነግራል በኩራት፣
ስለሰራው ስህተት ልክ እንደጀግንነት፣
መሆኑን ዘንግቶት የታሪክ ተወቃሽ፣
የጊዜው እንቅፋት ትውልዱን አስለቃሽ።
ቢያውቅማ ኖሮ ቢረዳው ሀሳቡን
እኔ የምኖረው በእኛ ውስጥ መሆኑን፣
እንኳንስ ሊያወራው ያደረገውን፣
አያስበውም ነበር በጭራሽ ነገሩን።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
.........."አልገባኝም እኔ?"...........
ያ የእኛ ፍቅር -- ያ የኛ መዋደድ
የልቦቻችን ቃል -- ቋንቋቸው መላመድ
ሀሳብህ ከሀሳቤ -- መጋጠም መምሰሉ
ደስታዬም በደስታህ -- ቢሆን እንኳን ውሉ
ያቺ የቀን ሳንካ -- ያቺ የቀን እርጉም
በጭጋግ የዋጠች -- የኛን የሳቅ አለም
ያቺ የቀን መጥፎ -- ከአይን ያስገባችን
ከቀኚዎቻችን ጋር -- ያስተዋወቀችን
በቅናት ልባቸው -- የውሸት ዱለታ
እኛን ሊለያዩ -- ሲፈጥሩ ጭምጭምታ
እያየን አልፈን የል -- ሁሉን እንዳላየን
ትተን ሄደን የል ወይ -- ሰምተን እንዳልሰማን
ታዲያ ምንድን ይሆን -- እኛን የለያየን
"አልገባኝም እኔ"?
እየተዋደድን -- ከሚዋደድ በላይ
እየተፋቀርን -- ከሚፋቀር በላይ
እየተሳሰብን -- ከሁሉም በላቀ
ከምኔው ነጥፎ ነው -- ፋቅራችን ያለቀ
አልገባኝም እኔ
አሁንም ማመኑ -- አልተዋጠልኝም
መለያየታችን -- እውን አይመስለኝም
...........................
እናማ ልንገርህ -- አድምጠኝ ሙኬዋ
ፍቅሬ የማይቆም ነው -- እንደ ወራጅ ውሀ
............................
በቃ ና ተመለስ መራራቁ ይብቃን
ለየቅል መሆኑ ኢምንት ነው አየን
ደግሞም አልጠቀመን፡፡
በቃ ና እንመለስ ወደ በፊታችን
ወደ ወደር አልባው ጣፍጩ ፍቅራችን
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ያ የእኛ ፍቅር -- ያ የኛ መዋደድ
የልቦቻችን ቃል -- ቋንቋቸው መላመድ
ሀሳብህ ከሀሳቤ -- መጋጠም መምሰሉ
ደስታዬም በደስታህ -- ቢሆን እንኳን ውሉ
ያቺ የቀን ሳንካ -- ያቺ የቀን እርጉም
በጭጋግ የዋጠች -- የኛን የሳቅ አለም
ያቺ የቀን መጥፎ -- ከአይን ያስገባችን
ከቀኚዎቻችን ጋር -- ያስተዋወቀችን
በቅናት ልባቸው -- የውሸት ዱለታ
እኛን ሊለያዩ -- ሲፈጥሩ ጭምጭምታ
እያየን አልፈን የል -- ሁሉን እንዳላየን
ትተን ሄደን የል ወይ -- ሰምተን እንዳልሰማን
ታዲያ ምንድን ይሆን -- እኛን የለያየን
"አልገባኝም እኔ"?
እየተዋደድን -- ከሚዋደድ በላይ
እየተፋቀርን -- ከሚፋቀር በላይ
እየተሳሰብን -- ከሁሉም በላቀ
ከምኔው ነጥፎ ነው -- ፋቅራችን ያለቀ
አልገባኝም እኔ
አሁንም ማመኑ -- አልተዋጠልኝም
መለያየታችን -- እውን አይመስለኝም
...........................
እናማ ልንገርህ -- አድምጠኝ ሙኬዋ
ፍቅሬ የማይቆም ነው -- እንደ ወራጅ ውሀ
............................
በቃ ና ተመለስ መራራቁ ይብቃን
ለየቅል መሆኑ ኢምንት ነው አየን
ደግሞም አልጠቀመን፡፡
በቃ ና እንመለስ ወደ በፊታችን
ወደ ወደር አልባው ጣፍጩ ፍቅራችን
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ይኼው በአይን የሚታይ ነገር እኮ
ነው።እምቦጭ ሐይቁን እያደረቀ ነው።ጣና ወደሜዳነት ተቀይሮ የከብቶች የግጦሽ መሬት ሁኗል።ከዚህ በኋላ ገዳም ለመጎብኙት በጀልባ መጓዝ ሊቀር ነው ሐይቁ ወደኋላ እየሸሸና እየደረቀ ወደ ደሴቶች ተቃርቧል።
መጻፍ ባትችሉ share አድርጉ
ነው።እምቦጭ ሐይቁን እያደረቀ ነው።ጣና ወደሜዳነት ተቀይሮ የከብቶች የግጦሽ መሬት ሁኗል።ከዚህ በኋላ ገዳም ለመጎብኙት በጀልባ መጓዝ ሊቀር ነው ሐይቁ ወደኋላ እየሸሸና እየደረቀ ወደ ደሴቶች ተቃርቧል።
መጻፍ ባትችሉ share አድርጉ
....."መምጣትሽን አምናለሁ".......
መኖርሽን ለምጄ ሳጣሽ ይጨንቀኛል
ከጎኔ ሆነሽ ውለሽ ስቴጅ ይከፋኛል
መለየት ሲለየን ፍፁም ስትርቂ ካይኔ
በሀሣብ ሠመመን ያሳለፍሽዉን ከኔ
በትዝታ ዛሬውን ትቼ ከትላንት እቀዝፋለሁ
አብረሽኝ በሆንሽ ብዬ ፍፁም እተክዛለሁ
ትላንትናችን አልፎ ዛሬ ላይ ብንቆምም
ዛሬም በሀሳቤ ሁሌም ካንቺዉ ጋር ነኝ
ጠረንሽን ንፋሡ በሄድኩበት እያሣበኝ
ጨዋታ ሣቅሽን ልቤ እያስታወሠኝ
ትመጫለሽ ብዬ ዛሬም አስባለሁ
ከዛ ከቸትዝታ ባህ ር ከቀዳንበት
ከዛ በፍቅር ባህር ከሠመጥንበት
እኔና አንቺ ብቻ ከምናውቀው ቦታ
ዛሬ ትመጣ ይሆን
ነገ ትመጣ ይሆን
እያልኩ እጠብቃለሁ
መምጣትሽን ዛሬም አምናለሁ
መቅረትሽን ማሠብ ለኔ ህመሜ ነው
ትዝ ይልሻል ከዛ ትልቁ ዛፍ ያኖርነው
ላርቅሽ ላትርቂኝ ብለን ተማምለን
ለዛ በድን ዛፍ ያኖርነው ቃላችን
ዛሬ ግን የለሽም ያለነው እኔና ቃላችን
አሁንም ተስፋዬ ሙሉ ነዉ
መምጣትሽን ዛሬም እመኛለሁ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
መኖርሽን ለምጄ ሳጣሽ ይጨንቀኛል
ከጎኔ ሆነሽ ውለሽ ስቴጅ ይከፋኛል
መለየት ሲለየን ፍፁም ስትርቂ ካይኔ
በሀሣብ ሠመመን ያሳለፍሽዉን ከኔ
በትዝታ ዛሬውን ትቼ ከትላንት እቀዝፋለሁ
አብረሽኝ በሆንሽ ብዬ ፍፁም እተክዛለሁ
ትላንትናችን አልፎ ዛሬ ላይ ብንቆምም
ዛሬም በሀሳቤ ሁሌም ካንቺዉ ጋር ነኝ
ጠረንሽን ንፋሡ በሄድኩበት እያሣበኝ
ጨዋታ ሣቅሽን ልቤ እያስታወሠኝ
ትመጫለሽ ብዬ ዛሬም አስባለሁ
ከዛ ከቸትዝታ ባህ ር ከቀዳንበት
ከዛ በፍቅር ባህር ከሠመጥንበት
እኔና አንቺ ብቻ ከምናውቀው ቦታ
ዛሬ ትመጣ ይሆን
ነገ ትመጣ ይሆን
እያልኩ እጠብቃለሁ
መምጣትሽን ዛሬም አምናለሁ
መቅረትሽን ማሠብ ለኔ ህመሜ ነው
ትዝ ይልሻል ከዛ ትልቁ ዛፍ ያኖርነው
ላርቅሽ ላትርቂኝ ብለን ተማምለን
ለዛ በድን ዛፍ ያኖርነው ቃላችን
ዛሬ ግን የለሽም ያለነው እኔና ቃላችን
አሁንም ተስፋዬ ሙሉ ነዉ
መምጣትሽን ዛሬም እመኛለሁ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
............... "አዲስ ነው"................
ይሄ ነው ማልለው በቃል የማልገልፀው፣
ከልቤ ግርጌ ላይ ፀንቶ የታነፀው፣
አንዳች ነገር አለ በውል የማልገልፀው፣
ስሜቱ የሲቃ ወይም የደስታ ነው፣
.
.
.
ብቻ.....
ስሙ ሲጠራ ነው አካሌ ሚርደው፣
ድንገት ሳገኘው ነው በላብ ምጠመቀው፣
ማልሆነውን ሁሉ ድንገት የምሆነው፣
ልብ አልባም ምሆነው እሱን ሳገኝ ነው።
.
.
.
ድንገት.....
ውል የለሽ ቃል ከአፌ ይዘንባል፣
አትሂድ ለማለት አይኔ ይንከራተታል፣
ምስኪን ክብ ፊቴ አትጥፋ ይለዋል፣
አንጀቴም ሳይታክት ሁሌ ይሳሳለታል።
.
.
.
ብቻ.....
ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ፣ ይሰማኛል የስሜት ፍካሬ፣
ከብዙዎች እሱን አምጪ የሚል ዝማሬ፣
ከአንደበቴ አይጠፋ ስሙም ከከንፈሬ።
.
.
.
ልቤማ.....
ልቤማ ቤቱ ነው እሱ እንኳን ወዳጁ፣
በለሊትም በቀን ሁሌ አስተናጋጁ።
ጠባብ የየሆነ ክፍሉ ለሱ ሲል ይሰፋል፣
ያለ ልክ አስቦት ልኩን ያጣለታል.....
ካሻው ምት አቁሞ ለእርሱ ይዘምራል፣
እንግዳ ነገር ነው እንዴት ልብ ይቆማል፣
ለምን ይዘምራል .......
ከአካሉ አብልጦ ለሌላው ያደላል፣
.
.
.
ብቻ.....
አዲስ ነገር ነው እኔ እኔን ጥሎ ለሌላው ልሙት ሲል።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ይሄ ነው ማልለው በቃል የማልገልፀው፣
ከልቤ ግርጌ ላይ ፀንቶ የታነፀው፣
አንዳች ነገር አለ በውል የማልገልፀው፣
ስሜቱ የሲቃ ወይም የደስታ ነው፣
.
.
.
ብቻ.....
ስሙ ሲጠራ ነው አካሌ ሚርደው፣
ድንገት ሳገኘው ነው በላብ ምጠመቀው፣
ማልሆነውን ሁሉ ድንገት የምሆነው፣
ልብ አልባም ምሆነው እሱን ሳገኝ ነው።
.
.
.
ድንገት.....
ውል የለሽ ቃል ከአፌ ይዘንባል፣
አትሂድ ለማለት አይኔ ይንከራተታል፣
ምስኪን ክብ ፊቴ አትጥፋ ይለዋል፣
አንጀቴም ሳይታክት ሁሌ ይሳሳለታል።
.
.
.
ብቻ.....
ከራስ ፀጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ፣ ይሰማኛል የስሜት ፍካሬ፣
ከብዙዎች እሱን አምጪ የሚል ዝማሬ፣
ከአንደበቴ አይጠፋ ስሙም ከከንፈሬ።
.
.
.
ልቤማ.....
ልቤማ ቤቱ ነው እሱ እንኳን ወዳጁ፣
በለሊትም በቀን ሁሌ አስተናጋጁ።
ጠባብ የየሆነ ክፍሉ ለሱ ሲል ይሰፋል፣
ያለ ልክ አስቦት ልኩን ያጣለታል.....
ካሻው ምት አቁሞ ለእርሱ ይዘምራል፣
እንግዳ ነገር ነው እንዴት ልብ ይቆማል፣
ለምን ይዘምራል .......
ከአካሉ አብልጦ ለሌላው ያደላል፣
.
.
.
ብቻ.....
አዲስ ነገር ነው እኔ እኔን ጥሎ ለሌላው ልሙት ሲል።
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
.............."የሰማዩ ችግኝ"...........
ፈጣሪ እኔን ሲያቅ
እኔ ግን እኔንም አላቅ
እኔ እሱን ብመርጥ ባልመርጥ
እሱ ግን ወድዋል እኔን መምረጥ
ሳላውቀው ያወቀኝ ሳልመርጠው የመረጠኝ
ሳልጠራው መጥቶ ነው ከክፉ
ያራቀኝ
ፊተን አዙሬበት ከመንገዱም ርቄ
በሰፊው መንገድ ላይ እራሴን ለቅቄ
የሰማዩ ዋርካ ለካስ እያየኝነው
ነፃ ፍቃድ ሰቶኝ በነፃ ለቆኝነው
ነፃ ፍቃድ ሚያቅ የነፃነት ዋርካ
ዋርካ ሆኖ ሳለ (ለኔ) ችግኝ ሆኗል ለካ
ሳልመርጠው የመረጠኝ
ቀና ብዬ ሳየው በስስት ነው ሚያየኝ
ፍቅሩና ጥበቃው እስካሁን አልተለየኝ
ይሀን ሁሉ ሁኖ የምድሩ ዋርካ መጠልያ መሰለኝ።
አድኚኝ አድኚኝ የሰማይዋ ችግኝ
ውቧ አበባ ውቧ ችግኝ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ፈጣሪ እኔን ሲያቅ
እኔ ግን እኔንም አላቅ
እኔ እሱን ብመርጥ ባልመርጥ
እሱ ግን ወድዋል እኔን መምረጥ
ሳላውቀው ያወቀኝ ሳልመርጠው የመረጠኝ
ሳልጠራው መጥቶ ነው ከክፉ
ያራቀኝ
ፊተን አዙሬበት ከመንገዱም ርቄ
በሰፊው መንገድ ላይ እራሴን ለቅቄ
የሰማዩ ዋርካ ለካስ እያየኝነው
ነፃ ፍቃድ ሰቶኝ በነፃ ለቆኝነው
ነፃ ፍቃድ ሚያቅ የነፃነት ዋርካ
ዋርካ ሆኖ ሳለ (ለኔ) ችግኝ ሆኗል ለካ
ሳልመርጠው የመረጠኝ
ቀና ብዬ ሳየው በስስት ነው ሚያየኝ
ፍቅሩና ጥበቃው እስካሁን አልተለየኝ
ይሀን ሁሉ ሁኖ የምድሩ ዋርካ መጠልያ መሰለኝ።
አድኚኝ አድኚኝ የሰማይዋ ችግኝ
ውቧ አበባ ውቧ ችግኝ
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
♒♒♒♒♒♒
ተወዳዳሪ - ዳዊት ካሳዬ (ባባ
💫💫💫💫💫💫
✨✨ኮድ -3✨✨
❖❖❖❖❖❖❖❖❖
.........."አልገባኝም እኔ?"...........
ያ የእኛ ፍቅር -- ያ የኛ መዋደድ
የልቦቻችን ቃል -- ቋንቋቸው መላመድ
ሀሳብህ ከሀሳቤ -- መጋጠም መምሰሉ
ደስታዬም በደስታህ -- ቢሆን እንኳን ውሉ
ያቺ የቀን ሳንካ -- ያቺ የቀን እርጉም
በጭጋግ የዋጠች -- የኛን የሳቅ አለም
ያቺ የቀን መጥፎ -- ከአይን ያስገባችን
ከቀኚዎቻችን ጋር -- ያስተዋወቀችን
በቅናት ልባቸው -- የውሸት ዱለታ
እኛን ሊለያዩ -- ሲፈጥሩ ጭምጭምታ
እያየን አልፈን የል -- ሁሉን እንዳላየን
ትተን ሄደን የል ወይ -- ሰምተን እንዳልሰማን
ታዲያ ምንድን ይሆን -- እኛን የለያየን
"አልገባኝም እኔ"?
እየተዋደድን -- ከሚዋደድ በላይ
እየተፋቀርን -- ከሚፋቀር በላይ
እየተሳሰብን -- ከሁሉም በላቀ
ከምኔው ነጥፎ ነው -- ፋቅራችን ያለቀ
አልገባኝም እኔ
አሁንም ማመኑ -- አልተዋጠልኝም
መለያየታችን -- እውን አይመስለኝም
...........................
እናማ ልንገርህ -- አድምጠኝ ሙኬዋ
ፍቅሬ የማይቆም ነው -- እንደ ወራጅ ውሀ
............................
በቃ ና ተመለስ መራራቁ ይብቃን
ለየቅል መሆኑ ኢምንት ነው አየን
ደግሞም አልጠቀመን፡፡
በቃ ና እንመለስ ወደ በፊታችን
ወደ ወደር አልባው ጣፍጩ ፍቅራችን
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
ተወዳዳሪ - ዳዊት ካሳዬ (ባባ
💫💫💫💫💫💫
✨✨ኮድ -3✨✨
❖❖❖❖❖❖❖❖❖
.........."አልገባኝም እኔ?"...........
ያ የእኛ ፍቅር -- ያ የኛ መዋደድ
የልቦቻችን ቃል -- ቋንቋቸው መላመድ
ሀሳብህ ከሀሳቤ -- መጋጠም መምሰሉ
ደስታዬም በደስታህ -- ቢሆን እንኳን ውሉ
ያቺ የቀን ሳንካ -- ያቺ የቀን እርጉም
በጭጋግ የዋጠች -- የኛን የሳቅ አለም
ያቺ የቀን መጥፎ -- ከአይን ያስገባችን
ከቀኚዎቻችን ጋር -- ያስተዋወቀችን
በቅናት ልባቸው -- የውሸት ዱለታ
እኛን ሊለያዩ -- ሲፈጥሩ ጭምጭምታ
እያየን አልፈን የል -- ሁሉን እንዳላየን
ትተን ሄደን የል ወይ -- ሰምተን እንዳልሰማን
ታዲያ ምንድን ይሆን -- እኛን የለያየን
"አልገባኝም እኔ"?
እየተዋደድን -- ከሚዋደድ በላይ
እየተፋቀርን -- ከሚፋቀር በላይ
እየተሳሰብን -- ከሁሉም በላቀ
ከምኔው ነጥፎ ነው -- ፋቅራችን ያለቀ
አልገባኝም እኔ
አሁንም ማመኑ -- አልተዋጠልኝም
መለያየታችን -- እውን አይመስለኝም
...........................
እናማ ልንገርህ -- አድምጠኝ ሙኬዋ
ፍቅሬ የማይቆም ነው -- እንደ ወራጅ ውሀ
............................
በቃ ና ተመለስ መራራቁ ይብቃን
ለየቅል መሆኑ ኢምንት ነው አየን
ደግሞም አልጠቀመን፡፡
በቃ ና እንመለስ ወደ በፊታችን
ወደ ወደር አልባው ጣፍጩ ፍቅራችን
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
"አንዴ ነው " ይሉኛል ፣ "በፍቅር መጎዳት"
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻላ ፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስ ነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻላ ፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስ ነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
#samuel_alemu
ስትናፍቂኝ ጊዜ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፎቶሽን ታቅፌ፣
ምላሽ ጠብቃለው
"ይናገራል ፎቶ" የሚል ግጥም ፅፌ፣
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
ስትናፍቂኝ ጊዜ
ከኔ ዘንድ የቀረ ፎቶሽን ታቅፌ፣
ምላሽ ጠብቃለው
"ይናገራል ፎቶ" የሚል ግጥም ፅፌ፣
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
ነይ ደግሜ ላግባሽ
.
.
የስሚዛው ቅጠል እንጀራ ነው ተብሎ
ለሚመጣው ወዳጅ
አፈር ከውሃ ጋር በስስ ተቀላቅሎ
ደጋሹ ገላጋይ ብሉልኝ ጠጡልኝ እያለ ሲማፀን
በጥሎሹ ብዛት ቤታችን ሲመዘን
የልጅነት ቋንቋ የእቃቃ ዘመን ዳር
በመፈላለግ ሀቅ ሲያበቃን ለትዳር
አሸወይና ነው ወይ ወይስ ችቦ አይሞላም
የሚዜመው ላንቺ
ለልቤ ከፍታ ለክፍተቴ ግጣም።
ነይ ደግሜ ላግባሽ...
ልጅነትን ፍቀን በሚያጣምረን ወግ
ከኛ የቀደሙት እስከ አሰመሩት ጥግ።
----------------------------------------
አማኑኤል ደርበው(አማን)
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
.
.
የስሚዛው ቅጠል እንጀራ ነው ተብሎ
ለሚመጣው ወዳጅ
አፈር ከውሃ ጋር በስስ ተቀላቅሎ
ደጋሹ ገላጋይ ብሉልኝ ጠጡልኝ እያለ ሲማፀን
በጥሎሹ ብዛት ቤታችን ሲመዘን
የልጅነት ቋንቋ የእቃቃ ዘመን ዳር
በመፈላለግ ሀቅ ሲያበቃን ለትዳር
አሸወይና ነው ወይ ወይስ ችቦ አይሞላም
የሚዜመው ላንቺ
ለልቤ ከፍታ ለክፍተቴ ግጣም።
ነይ ደግሜ ላግባሽ...
ልጅነትን ፍቀን በሚያጣምረን ወግ
ከኛ የቀደሙት እስከ አሰመሩት ጥግ።
----------------------------------------
አማኑኤል ደርበው(አማን)
@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
#መስታወት_ፊት_ቆሜ_እንዲህ_እላለሁ
"በለስ ፍሬ ባትሰጥ"፣ሎሚ መሽተት ቢሳናት
ኤሊ ላባ ብትለብስ፣ ወፌን ድንጋይ ቢጫናት
ሰማይ እንዳለት ቢወቀር
ጊዜ ደክሞት ቆሞ ቢቀር
ጨረቃ አመድ ብትቅም
ፀሐይ ጥርሷን ብትለቅም
ስልጣኔን ነቀዝ በልቶት፣ኦና ቢሆን አገር
ምድሩ
ፒራሚዶች ባንድ ሌሊት፣ የኩበት ክምር ሆነው ቢያድሩ
ተፈጥሮ ለሕዝብ ቅነሳ
ሰው በሰው ላይ ብታስነሳ
አንዱ ካንዱ ቢተራረድ
ጠፈር በከል ቢጋረድ
ሙሴን ባሕር ቢበላው፣የኖህ መርከብ ቢሰጥም
ሕይወት ምስጢር ባትገልጥም
የድል ድርሻየን ጥዋ፣ ጭላጭ ሳይቀር እስካጣጥም
የምሻውን እስከማገኝ፣ ለመሸነፍ እጅ አልሰጥም
እንኳን ተስፋ፣ ጢም አልቆርጥም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
"በለስ ፍሬ ባትሰጥ"፣ሎሚ መሽተት ቢሳናት
ኤሊ ላባ ብትለብስ፣ ወፌን ድንጋይ ቢጫናት
ሰማይ እንዳለት ቢወቀር
ጊዜ ደክሞት ቆሞ ቢቀር
ጨረቃ አመድ ብትቅም
ፀሐይ ጥርሷን ብትለቅም
ስልጣኔን ነቀዝ በልቶት፣ኦና ቢሆን አገር
ምድሩ
ፒራሚዶች ባንድ ሌሊት፣ የኩበት ክምር ሆነው ቢያድሩ
ተፈጥሮ ለሕዝብ ቅነሳ
ሰው በሰው ላይ ብታስነሳ
አንዱ ካንዱ ቢተራረድ
ጠፈር በከል ቢጋረድ
ሙሴን ባሕር ቢበላው፣የኖህ መርከብ ቢሰጥም
ሕይወት ምስጢር ባትገልጥም
የድል ድርሻየን ጥዋ፣ ጭላጭ ሳይቀር እስካጣጥም
የምሻውን እስከማገኝ፣ ለመሸነፍ እጅ አልሰጥም
እንኳን ተስፋ፣ ጢም አልቆርጥም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
@hutoffun 👈🏾
@hutoffun 👈🏾
< < ምንድን ነው ብሄሩ? > >
( (አራጋው ሙሃመድ) ) # Ethiopia
አባቱ ወሎ ነው መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸው ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካ'ሠላዋ ቆንጆ ተጋብተው ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫው ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፋር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተው ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ! ሲሉ
አፖስቶ ነው አቦ! ሀረሪ ባህሉ
ወሎ ከቤኒሻንጉል ልጅ ወልደው ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነው ብሄሩ??
@hutoffun👈🏾
@hutoffun 👈🏾
( (አራጋው ሙሃመድ) ) # Ethiopia
አባቱ ወሎ ነው መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸው ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካ'ሠላዋ ቆንጆ ተጋብተው ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫው ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፋር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተው ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ! ሲሉ
አፖስቶ ነው አቦ! ሀረሪ ባህሉ
ወሎ ከቤኒሻንጉል ልጅ ወልደው ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነው ብሄሩ??
@hutoffun👈🏾
@hutoffun 👈🏾