Telegram Web Link
ብስራት

ሰማይን የሚደርስ ያክል ሀጥያት ብትፈፅምና ወደ ጌታቹም ብትመለሱ እርሱ ተውበታችሁን ይቀበላቹሀል።
"እናንተ በነፍሶቻቹ ላይ ድንበር ያለፋቹ ባሮቼ ሆይ ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ አላህ ሀጢያቶችን በመላ ይምራልና።"(አል ቁርዓን)
@islam_hiwote
ዑመር ኢብኑ አብዱል ዐዚዝ እንዲህ ይላሉ፦የአምልኮ ቁልፉ ብዙ መስገድና መፃም ሳይሆን ምላስን ከሰዎች ክብር መቆጠብ እንደሆነ የሚያምኑ ሰለፎችን አግኝተናል የሌሊት ሰጋጅና የቀን ፁዋሚ ምላሱን ካልጠበቀ ባዶውን ይቀራል።
ከነብዩ ሀዲሶች
1 ለተቸገረ ሰው ያገራ አላህ ዱንያ አኼራውን ያገራለታል
2 ነገ የቂያማ ቀን መዝገቡን ሲያይ መደሰት የፈለገ ሰው እስቲግፋር ያብዛ።
@islam_hiwote
አባት ለልጁ እንዲህ ብሎ መከረው
ልጄ ሆይ በሕይወትህ በሦስት ነገሮች ላይ አትደራደር-
1- ምርጥ ምግብን ተመገብ
2- በጥሩ ፍራሽ ላይ ተኛ
3- ምርጥ ቆንጆ በሆነ ቤት ኑር
ልጁም - አባቴ እኛ ድሆች ነን እነዚህን ነገሮች እንዴት ማድረግ እችላለሁ? አባቱ መለሰ -

1️⃣ ሲርብህ ብቻ ከበላህ የምትመገበው ምርጥ ምግብ ይሆናል።
2️⃣ ጠንክረህ ከሰራህና ለማንም ጥላቻ በልብህ ውስጥ ከሌለ መኝታህ ጥሩ ፍራሽ ላይ ይሆናል
3️⃣ አላህን እየተገዛህ የሱ ሀቅ የሆነችዋን ሱጅድህ ላይ ከጠነከርክ የዛኛውን አለም ቤት ትገነባለህ
በህይወትህ ላይ የሌሎችን መብት እየጠበክ ሰዎችን በደግነት ከያዝክ በልቦቻቸው ውስጥ ትኖራለህ እናም ቆንጆና መልካም ቤቶች ውስጥ ኖርክ ማለት ነው
«በአላህ ና በመጨረሻው አለም ያመነ እንግዳውን ያልቅ። በአላህ ና በመጪው አለም ያመነ ዝምድናን ይቀጥል። በአላህና በመጪው አለም ያመነ መልካም ይናገር። ወይም ዝም ይበል።» ረሱል ሰዐወ
@islam_hiwote
Forwarded from Tofik Bahiru
«አላህ ሦስት ነገሮችን ጠላባችሁ: ‐
⚀ አሉባልታ፤
⚁ ገንዘብን ማባከን፤
⚂ ጥያቄ ማብዛት።»
ተወዳጃችን [ﷺ]፤ ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት።
:
አላህ አሉባልታን እንደማይወድ የተረዳ ሙስሊም በማይጠቅም ወሬ ጊዜውን አያቃጥልም። በማይመለከቱት ክስተቶች ተወጥሮ እድሜውን አይፈጅም። ለዱንያውና ለዲኑ በሚፈይዱት ነገሮች ላይ ትኩረቱን ያውላል።
#ረመዷን 88 ቀን ቀረው!😱
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
ውዷ እህቴ ሆይ!:::::::::::❥

ባለቤትሽን ስለ መልካምነቱ ማመስገንሽ ፍቅራችሁን ከማጎልበቱና እሱን ለበለጠ መልካምነት ከማበረታታቱ ባሻገር አላህን ማስደሰት ነው!!

قال صلى الله عليه وسلم : (لا ينظر الله إلى امرأة لا تشكر لزوجها و هي لا تستغني عنه) رواه النسائي و صححه الألباني في الصحيح 289

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «ከባሏ የማትብቃቃ ስትሆን ባሏን የማታመሰግን ሴት፣ አላህ በእዝነት አይኑ አይመለከታትም።” ኢማሙ ነሳኢ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሒህ ብለውታል
ጉዳይህ እስከሚሳካ ሚስጥር ይሁን!
~~~~~~~
ትና ስንት ጉዮች አሉን፣ ሰው በማውራታችን የተጨናገፉ?! ያሰብከው ጉዳይ አለህ? እንግዲያው አስፈላጊ ሆኖ ካላገኘሁ በስተቀር እስከሚሳካ ድረስ በሚስጥር ያዘው። በሚስጥር መያዝህ የስኬትህ አንድ ሰበብ ነው። ተወዳጁ ነብያችን ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላ፞ህ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል: –
"استعينوا على قضاء حوائجكم بالكتمان فإن كل ذي نعمة محسود".
"ጉዳዮቻችሁን ታሳኩ ዘንድ በመደበቅ ታገዙ። እያንዳንዱ ባለ ፀጋ ምቀኛ አለበትና።" [አሶ፞ሒሐህ: 3/439]

ቁርኣን ላይ እንደተገለፀው የዕቁብ ለልጃቸው ለዩሱፍ እንዲህ ብለዋል:–

(قَالَ یَـٰبُنَیَّ لَا تَقۡصُصۡ رُءۡیَاكَ عَلَىٰۤ إِخۡوَتِكَ فَیَكِیدُوا۟ لَكَ كَیۡدًاۖ إِنَّ ٱلشَّیۡطَـٰنَ لِلۡإِنسَـٰنِ عَدُوࣱّ مُّبِینࣱ)
« ‘ልጄ ሆይ! ህልምህን ለወንድሞችህ አትንገር፡፡ ላንተ ተንኮልን ያሴሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልፅ ጠላት ነውና’ አለ።» [ዩሱፍ: 5]

ታላቁ ሙፈሲ፞ር ዒማዱዲን ኢብኑ ከሢር ረሒለሁላ፞ህ ከዚህ አያይዘው እንዲህ ይላሉ:–
"አንድ ፀጋ እስከሚገኝና ግልፅ እስከሚሆን ድረስ ሊደበቅ እንደሚገባ ከዚህ ይወሰዳል።"
አንዳንድ ክርስቲያኖች የባይብልን ጥቅስ በማጣመም ኢየሱስ ቅድመ ሕልውና (Pre-Existence) እንዳለ ስለዚህም አምላክ እንደሆነ ለማስረዳት ይዳክራሉ፣ የሚያሳዝነው ግን አንድም ጥቅስ ኢየሱስ «ቅድመ-ሕልውና» እንዳለው ፍንጭ አይሰጥም። የሚገርመው ደግሞ በቤተክርስቲያን መጽሐፍት ላይ ማሪያም ቅድመ-ሕልውና እንዳላት (ከፍጥረታት በፊት እንደነበረች) በግልጽ ተጽፏል።

‟የተመሰገነች፣ የተቀደሰች እና የተባረከች እርሷ ማርያም ሰማይ እና ምድር ሳይፈጠር እና የገነት ምድር ሳይመሠረት ነበረች።
— ነገረ-ማርያም ቅዱስ ያሬድ ምዕራፍ 1

አይገርምም ? ማሪያም የክርስቲያኖች አራተኛ አምላክ ናት የምንለው በምክንያት ነው። ከፍጥረት በፊት ከአምላክ ውጪ ማንም አልነበረም ኢየሱስ ግን አብ ዘንድ ስለሆነ አምላክ ነው ብለው የነበሩ ሰዎች በመጽሐፋቸው ላይ ማሪያም ቅድመ-ሕልውና እንዳላት የሚናገረውን ክፍል ሲያዩ ምን ይውጣቸው ይሆን ?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አርበዒን
#1
عن أمير المؤمنين أبي حفص عمر بن
الخطاب رضي الله عنه قال :سمعت
رسول الله صل الله عليه وسلم يقول: إنما الأعمال بالنيات،وإنما لكل امرئ ما نوي،فمن كانت هجرته الي الله ورسوله فهجرته الي الله ورسوله ،ومن كانت هجرته لدنيا يصيبها أو امرأة ينكحها فهجرته الي ما هاجر إليه".
የአማኞች መሪ ከሆኑት አቡ ሀፍስ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው አሉ "ስራዎች በኒያዎች ነው የሚታሰቡት ።ለሁሉም ሰው ደግሞ ያሰበው ነው ያለው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው የሆነ ሰው ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ነው። ስደቱ ሊያገኛት ወደ ሚያስባት አዱኛ ወይም ሊያገባት ወዳሰባት ሴት የሆነ ስደቱ ወደ ተሰደደለት ነው።"
Note:
ኒያ ማለት አንድን ተግባር ለመፈፀም በልብ የሚታሰብ ቁርጠኛ ውሳኔ ነው። የሰው ልጅ የሚያገኘው ያሰበውን ነው፡ መልካም ካሰበ መልካም መጥፎ ካሰበ መጥፎ።
@ islam_hiwote
اللهم بك أصبحنا،وبك أمسينا،وبك نحيا،وبك نموت،وإليك النشور
አላህ ​ሆይ! በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል። በአንተ ለምሽት እንበቃለን። በአንተ ህያው ሆነናል። በአንተም እንሞታለን።መመለሻ ወደ አንተ ነው።
@islam_hiwote
2024/05/16 05:15:27
Back to Top
HTML Embed Code: