ኢጃት ድሬ የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓልን ከአረጋውያን ጋር አከበረ።
ጃንደረባው ሚዲያ| መስከረም 1-2016 ዓ/ም
ድሬዳዋ-ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ የአዲሱን ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በአሰገደች አስፋው የድሬዳዋና አካባቢዋ የአረጋውያን መንከባከቢያና ማቋቋሚያ ድርጅት በመገኘት ከአረጋውያን ጋር በድምቀት አከበረ።
በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስር ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው ጃን-ሉቃስ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያኑ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የመድኃኒት ጥቅል በማዘጋጀት በተቋሙ ለሚገኘው ማዕከላዊ ክሊኒክ በማስረከብ እና ከአርጋውያኑ ጋር ልዩ የበዓል መርሐግብር በማድረግ በድምቀት አክብሯል።
ጃን ሉቃስ በ2016 ዓ/ም በተቋሙ በመገኘት ለአረጋውያኑ ነጻ የሕክምና አገልግሎት እና የመድኃኒት ድጋፍ ያደረገ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም እገዛን በሚሹ ማንኛውም አገልግሎቶች በኅብረት እንደሚሠሩ እና የተደረገውም ነገር ለእነርሱም ለአረጋውያኑም ደስታን የፈጠረ መሆኑን በመግለጽ አዲሱን ዓመት የሰላም እና የፍቅር እንዲያደርግልን የተቋሙ መሥራች ዶ/ር አሰገደች አስፋው በመመኘት የማኅበሩም ድጋፍ እንዳይለይ ከጠየቁ በኋላ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#ወደ_ሠረገላው_ቅረብ
#እነሆ_ውኃ

❤65👍31❤🔥8🥰6🔥5😍4🕊3🆒3👏2