እንኳን ለቀዳሜ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመት ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜
ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!
ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከ7ቱ አገልጋይ ዲያቆናት አንዱ ሆኖ፣ ጥቅምት 17 ቀን የተሾመና ከጌታ ዕርገት በኋላ 2 ዓመት ክርስትናን አስተምሮ በተወለደባት ጥር 1 ቀን በ35 ዓ.ም በወጣትነት እድሜው ከጌታ ቀጥሎ፣ ከሐዋርያት ቀድሞ ሰማዕትነትን የተቀበለና በኢየሩሳሌም የክርስቶስ የመጀመሪያው ሰማዕት ነው፣ የሐዋርያት ሥራ 7፥20-50
እስጢፋኖስ ማለት፣ በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው።
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም ይገብር መንክረ፣
እንዘ ፃዕረ ሞት ያረስዕ ወያስተጥዕም መሪረ፣
በመዓዛ ጽጌኪሰ (እመዓዛ ጽጌኪሰ) ለዘበዓውደ ስምዕ ሰክረ፣ ውግረተ አዕባን ይመስሎ ሐሠረ፣
እሳትኒ ማየ ባሕር ቈሪረ፡፡
ማርያም ሆይ የፍቅርሽ ተአምር የሞት ጣርን አስረስቶ፣ መራራውንም አጣፍጦ ድንቅ ተአምርን ያደርጋል፣ በልጅሽ መዓዛ (ከልጅሽ መዓዛ የተነሣ) በሰማዕትነት አደባባይ ለተመሰጠ ሰው፣ በድንጋይ መወገር ገለባን፣ እሳትም የቀዘቀዘ የባሕር ውሃን ይመስለዋል፡፡
የማኅሌተ ጽጌ ትርጉምና ታሪክ ገጽ 64

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆኑ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን፤ ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 21ቀን 2017ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃ ለድሬደዋ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ።
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜
ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድሬደዋ ሀገረ ስብከት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን ለአንድነቱ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ድጋፍ ተደረገ።
በዕለቱም የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ እማምሰው ፣ የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ሐላፊዎች ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት መርሐ ግብሩ የተከናወነ ሲሆን በመርሐ ግብሩም በአንድነቱ ቀጣይ አገልግሎት ዙሪያ ታዳሚዎችን ያሳተፈ ምክክር ከተደረገ በኋላ የተገዛውን ንብረት ለአንድነቱ ተ/ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ሀብታሙ ሽፈራው ክቡር መልአከ ኃይል አባ ተስፋዬ ያስረከቡ አስረክክበዋል። በማስከተልም የወጪ ዝርዝር ሪፖርት ለእንግዶች በማሰማት ይህን ስራ ሲያስተባብሩ ለነበሩ የኮሚቴ አባላት እና ለደብራት አለቆች ዕውቅና ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ተስፋዬ ይህን ስራ ከመነሻው እስከ መድረሻው በቅርብ በመከታተል አባታዊም አስተዳደራዊም መመሪያ በመስጠት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሀገረ ስብከቱን ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስን ያመሰገኑ ሲሆን በተመሳሳይ ለአጥቢያ አለቆች እና ለአንድነቱ አባላትም በሙሉ በዚህ ስራ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና በማቅረብ መርሐ ግብሩን በጸሎት ዘግተዋል።
መረጃው የድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ነው።

ተዝካረ ስቅለቱ ለእግዚእነ
እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ዝክረ ጥንተ ስቅለት አደረሳችሁ አደረሰን::
ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተ ክርስቲያናችን ጌታችን በመስቀሉ ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ “ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ”በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።
ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኀ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ “ …እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ ” እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች ።
መጋቢት ፳፯ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን ዐርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርዓት ሠርተዋል፡፡መጋቢት ፳፯ ቀን በዐቢይ ጾም ስለሚውልና በወቅቱም ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት ፳፯ ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች ።
ጲላጦስ አይሁድን ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ ቢላቸው በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው አሉ። ጲላጦስም በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው። ማቴ ፳፯ ፥፳፭
መጋቢት ፳፯ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯ )፡፡
ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ ጋር ቤተ ክርስቲያን በ15ኛው መ.ክ.ዘ የነበሩትን አቡነ መብዓ ጽዮንን ታስባለች፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ በዕለተ ዓርብ የተቀበልከውን መከራ ግለጽልኝ ››ብለው በጸለዩ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ የተቀበላቸውን መከራዎች ሁሉ አሳያቸው፡፡
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስን መከራ ካዩበት ቀን ጀምሮ ሕማሙን መከራውን ግርፋቱን እስራቱን በጠቅላላ አሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ ራሳቸውን በዘንግ ይመቱ ነበር፡፡
የጌታችንን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያለቅሱ ዐይናቸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ነገር ግን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይናቸውን ቀብታ አድናቸዋለች፡፡ በዚህ የተነሣ ‹‹በትረ ማርያም›› እየተባሉ እንደሚጠሩ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ በዚህ መሠረት ጥቅምት ፳፯ ቀን ለአቡነ መብዓ ጽዮን ቃልኪዳን የገባበት ቀን በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱ ጋር ይከበራል፡፡
ስንክሳር ዘወርኃ ጥቅምት

የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተዝካረ ስቅለቱ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ !
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜
ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተዝካረ ስቅለቱ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጅማ፣ የየም፣ የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ክቡር መልዐከ ሠላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የመመሪያ ኃላፊዎች፣ የአድባራት እና የገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት በጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።