+ ያደረግሽው ምንድር ነው? +

አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ::

ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት::

እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት ክሱን ትቶ ከሳሾቹን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል::
ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል::

ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት::

እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል::

ያደረግሽው ምንድር ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው::
እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው::
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት
"ያደረግሽው ምንድር ነው?"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
✞✞✞ በእንተ ቅዱሳን ✞✞✞
https://youtu.be/xcL_xGK9dTY
☝️

<< የእመቤታችንን ምሳሌያት በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት >>
📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭

ሰላም ውድ የዚህ ምህላፍ ተከታታዬች ተቋርጦ የነበረ አገልግሎታችንን ቸር አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከቀድሞ በተሻለ መልኩ እንቀጥላለል ።

በምህረቱ ያልተለየን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ።

https://www.tg-me.com/kidusan_z_ethiopia

📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭
✞✞✞ በእንተ ቅዱሳን ✞✞✞ pinned «📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 ሰላም ውድ የዚህ ምህላፍ ተከታታዬች ተቋርጦ የነበረ አገልግሎታችንን ቸር አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከቀድሞ በተሻለ መልኩ እንቀጥላለል ። በምህረቱ ያልተለየን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ። https://www.tg-me.com/kidusan_z_ethiopia 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭 📖💭»
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ሥርዓተ ሱባዔ   ሱባዔ ምንድን ነው? ሱባዔ በሰዋስው ትርጉሙ ሰባት ማለት ነው፡፡ ሱባዔ በመንፈሳዊ አተረጓጎም አንድ ሰው ከዚህ ቀን እስከዚህ ቀን ከፈጣሪዬ እገናኛለሁ ብሎ የሚያቅደው መንፈሳዊ ዕቅድ ነው፡፡
የልዑለ ባሕርይ አምላችን ጋር የምንገናኝባቸው መንገዶችም ፡-
› ጸሎት
› ጾም
› ስግደት
› ምጽዋት እና እሊህ የመሰሉ መንፈሳዊ ድብራት ናቸው ፡፡

ሱባዔ በልቦናችን እግዚአብሔርን በመፍራት ፤ በኅሊናችን በሥነ-አምልኮት ሆነን ፤ በሕይወታችን ቃሉን የምንገልጥበት ሰሙን ፤ ለሥጋችን ሥምረት ለነፍሳችን ድኅነት የምናድርበት የተጸምዶ ወቅት ነው ፡፡

ሰባት ቁጥር በእስራኤላውያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው፡፡
ለምሳሌ፡- ፈጣሬ ዓለማት ገባሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር ማረፉ ፣ ለጸሎት የሚተጉ ምእመናን በቀን ለሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል፡፡ ዘፍ.2.2፤ መዝ.118.164፡፡ ከዚህ አንጻር አንድ ሰው ለሰባት ቀናት ቢጾም «አንድ ሱባዔ ጾመ» ይባላል፡፡ ለዐሥራ አራት ቀን ቢጾም «ሁለት ሱባዔ ጾመ» እያለ እየጨመረ ይሄዳል፡፡



ይቀጥላል . . .

ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤፤
።።።።።።።።+++ ነሐሴ 7 +++ ።።።።።።።።።
ꔰ ።።።።። ቅዱስ ኢያቄም ወ ሐና ።።።።።።።።። ꔰ
ጽንሰታ ለማርያም ድንግል

እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ፡፡ ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ ፡-
ኢያቄም:-"አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ:፡
ሃናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ(ውሃ) ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ:: ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።
✣ ✣ ✣


ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ጾመ መድኃኒት ያድርግልን አሜን ፡፡
📖 አቡነ_ኪሮስ 📖
አቡነ ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገራቸው ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡
💎አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡ በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስተው ወስዶው ገነትን አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

💎ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹህ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በሕግ በሥጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው በዛሬዋ ዕለት #ሐምሌ 8 ዐረፈዋል
ከቅዱሳን ሁሉ ረድኤታቸውንና በረከታቸውን አሳድርብን፡፡

በድፍረት፣ በትዕቢት በመናቅም በቅዱሳን ላይ የሚናገሩ የሽንገላ አንደበት ዲዳ ይሁኑ መዝሙር 30፡18 አንዳንዶችን በቅዱሳን ላይ ተነስቷልና ይቅር ይበላቸው፤ ልቦና ይስጣቸው መድኃኔዓለም የሚያደርጉትን አያቁምና ይቅር በላቸው ያለው ጌታ ይቅር ይበላቸው፡፡ …እንግዲህ እግዚአብሔር የመረጠውን ማን ይከሳል።
💎ሮሜ 8፡28-31 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል እናንተን የጣለ እኔን ይጥላል እኔን የጣለ የላከኝን ይጥላል።” ሉቃ. 10፡16

💎“ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ መዝሙር” 111፡6

💎…ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል… እውነት እላችዃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም…+++። ማቴ.10፡40-42
በዓለ ደብረ ታቦር

ክፍል አንድ


ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የምናከብረው የደብረ ታቦር በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት በመሆኑ በየዓመቱ  በድምቀት ይከበራል፡፡ (ማቴ .፲፯፡፩፣ ማር.፱፡፩፣ሉቃ.፱፡፳፰)፡፡

ደብረ ታቦር፡- ‹‹ደብረ ታቦር›› ደብር እና ታቦር ከሚባሉ ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ‹‹ደብር›› ማለት ተራራ ማለት ነው፤ ‹‹ታቦር›› ደግሞ በናዝሬት አካባቢ በሰማርያ አውራጃ በገሊላ የሚገኝ የረጅም ተራራ ስም ነው፡፡ የደብረ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ  ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ ፭፻፸፪ ሜትር ነው፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” በማለት አስቀድሞ ተናግሮ ነበር፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪) ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ብርሃነ መለኮቱን በመግለጡ የነቢያት ትንቢት ተፈጽሟል፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሳራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነበር፡፡ (መሳ. ፬፥፮)፡፡ የዚህም ታሪክ ምሳሌነቱ ባርቅ የጌታችን ሲሳራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ ተራራ ነቢዩ ሳሙኤል ትንቢት ተናግሮበታል፡፡ ንጉሥ ሳኦልም ከሦስት ሰዎች ጋር ተገኝቶበታል (፩ኛ ሳሙ.፲፡፫)፡፡ ርእሰ አበው አብርሃምና ኖኅ በዚህ ተራራ ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ያዩ ሲሆን አባታችን ኖኅ ይህንን ተራራ ‹‹መካነ ብርሃን፤ የብርሃን ቦታ›› ብሎ ጠርቶታል፡፡
የሐዲስ ኪዳን ወንጌል ጸሓፊያን ግን ‹‹ረጅም ተራራ፣ ቅዱስ ተራራ›› በማለት ጠርተውታል፡፡ ሆኖም ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ተራራ ላይ ክብሩን እንደገለጠና የዚህም ተራራ ስም ታቦር መሆኑን ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው ገልጠዋል፣ በትውፊትም ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም ይህንን ረጅም ተራራ ደብረ ታቦር እያለ በድጓው አስፍሮታል፡፡

በዚህ በዓል አምላክነት፣ ጌትነት፣ ንግሥና የባሕርይ ገንዘቡ መሆኑን፣ የድኅነታችን መሠረቱም የጌታችን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆን (የተዋሕዶ ምሥጢርን)  የገለጸበት በዓል ነው፡፡ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማእከለ ምድር/ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፣ በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ” (መዝ.፸፪፡፲፪) በማለት ትንቢት የተናገረው ለዚህ ነው፡፡ ማእከለ ምድር በተባለች በቀራንዮ ሰው የሆነ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ቤዛነት ዓለሙን ሁሉ አድኗልና፡፡ ሆኖም ግን የጌታችን ነገረ ተዋሕዶ ምሥጢር በሥጋዊ ዕይታ ውስጥ ለሆኑት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል፡፡

ብርሃነ መለኮቱ የተገለጠበት  ምሥጢር፡-

ሦስቱ ሐዋርያት በተራራው ሳሉ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልኩ በፊታቸው ተለወጠ፡፡ ይህ የብርሃነ መለኮቱ የመገለጥ የተዋሕዶ ምሥጢር እንጂ ውላጤ/መለወጥ/ አይደለም፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል፡፡(ሚል ፫፥፮)፡፡ ሦስት ክንድ ከስንዝር አካል ምሉዕ ብርሃን ሆኗል፡፡ ፊቱም እንደ ፀሐይ ብሩህ ሆነ፡፡ ልብሱም እንደ በረድ ጸዓዳ ሆነ፡፡ ይህ ሁሉ ነገረ ተዋሕዶን እንዲረዱ የተደረገ የተዋሕዶ ምሥጢር ነው፡፡ ሰውነቱን ባይክዱም አምላክነቱን ግን ተጠራጥረው ስለነበር እነር በሚያውቁት በባሕርየ ትስብዕቱ አምላክነቱን ከሰውነቱ አዋሕዶ ምሥጠረ ተዋሕዶን ገለጠላቸው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በ፴፪ ዓመት ከ፮ ወር ከ፲፫ ቀን፣ በዘመነ ማቴዎስ፣ በወርኃ ነሐሴ በዕለተ እሑድ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል፡፡

ሙሴንና ኤልያስን በደብረ ታቦር ለምን አመጣቸው?

ሙሴን ከመቃብር ጠርቶ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት ጌታችን አምለካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡ ሙሴ ከመቃብር ተነሥቶ ስለጌታችን የሰጠው ምስክርነት፡- “እኔ ባሕር ብከፍልም፣ውኃ ከዓለት ላይ ባፈልቅም፣ በዓመደ ደመና ዕብራውያንን እየመራሁ ጠላትን ድል ባደርግም፣ ደመና ብጋርድም፣መና ከደመና ባወርድም በአንተ መልካም ፈቃድ ነው፤ ብዙ ተአምራንት እንዳደርግ የረዳኝን የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ነው ይሉሃል? የሙሴ አምላክ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ሲል ኤልያስም ደግሞ “እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም፣ እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” በማለት የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ ሙሴና ኤልያስ የተጠሩበት ሌላው ምሥጢር ሙሴ “ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴን ግን አይታይም” ተብሎ ስለነበር (ዘፀ.፴፫፡፳፫) ከሞትም ከብዙ ዘመናት በኋላ ተነሥቶ ጌታን በአካል የማየትና ምስክርንት የመስጠት የቃል ኪዳን ተስፋ መፈጸሙን፣ ኤልያስም “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ሲሆን ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስን ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያት በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንና ሥርዐት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላን እንደሚወርሷት ለማስተማር ሁለቱን ወደ ድበረ ታቦር አምጥቷቸዋል፡፡

መድኃኒታችን ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን “መነይብልዎ ሰብእ ለወልደ እጓለ እምሕያው፤ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ብሎ ጥየቋቸው ነበርመና ሲመልሱ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ›› ብለውት ነበርና (ማቴ.፲፮፡፲፬)፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ‹‹በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር›› ያለውም የነበራቸውን ክብር ታላቅነት ያስረዳል፡፡

በባሕርዬ አይተህ ደንግጠህ እንዳትሞት በብርሃን ሠረገላ ሆኜ እስካልፍ ድረስ ቀዳዳ ባለው ዋሻ እሠውርሃለሁ፡፡ በብርሃን ሠረገላ ሆኜ ካለፍሁ በኋላ እጄን አንሥቼልህ ከወደ ኋላዬ ታየኛለህ እንጂ በባሕርዬ ግን ፊቴን ማየት አይቻልህም›› የሚል ምላሽ ሰጥቶት ነበር (ዘፀ. ፴፫፡፲፫-፳፫)፡፡ ይህም በፊት የሚሄድ ሰው ኋላው እንጂ ፊቱ እንደማይታይ ጌታም በባሕርዩ አለመገለጡን ያስረዳል፡፡ ምሥጢሩም አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም አምላክ ሰው ሆኖ ሥጋን ተዋሕዶ በደብረ ታቦር በባሕርዩ እስኪገለጥለት ድረስ ሙሴ በመቃብር ተወስኖ እንደሚቆይ ያጠይቃል፡፡ በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ከሙታን ተነሥቶ ከዘመናት በፊት የተመኘውን የአምላኩን ፊት ለማየት የታደለው ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተወለደውም በዚህች ዕለት ነው፡፡ ነቢዩ ኤልያስም “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” የተባለው ትንቢትም በዚህች ዕለት ተፈጸመ፡፡

ይቀጥላል...
📜 "የምወደው ልጄ ይህ ነው" 📜

ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።

እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)

በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10)

ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።

እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ ጋርዶት ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያቱ "እርሱን ስሙት" የሚለውን ቃል ራሱ ክርስቶስ ለራሱ የተናገረው ሊመስላቸው በቻለ ነበር።

ቅዱስ ጴጥሮስ "አትሙት" ያለው መምህሩን በፍጹም ልቡ ስለሚወደው መሆኑ አያጠራጥርም። ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን የቱንም ያህል ቢወደው፣ ፍቅሩ ግን ከወለደው ከባሕርይ አባቱ ከአብ አይደለም ሊበልጥ ሊነጻጸርም አይችልም። ታዲያ አብ በእርሱ ደስ የሚለው፣ የሚወደው፣ አንድያ ልጁ እንዲሞት ፈቃዱ ከሆነ፣ የአብን ያህል ሊወደው የማችለው አረጋዊው ጴጥሮስ ለምን "አትሙት" እያለ ይቃወማል?!

አብ ምትክ የሌለው ልጁ ወልድ ሰው ሆኖ በክፉዎች እጅ ሲንገላታ እና እስከ መስቀል ሞት ሲደርስ እያየ ዝም ያለው ስለማይወደው አይደለም። ዓለም ያለ ልጁ መከራና ሞት ስለማትድን ነው እንጂ። ከዚህ ምን እንማራለን? ዛሬም ወደ መከራ የምንገባ የጸጋ ልጆቹ የምንሆን እኛ ክርስቲያኖች "እግዚአብሔር እንዲህ ስሆን ዝም ያለኝ ስለማይወደኝ ነው" አንበል። ባገኘን ጥቂት የሥጋ መከራና ሕመም የሚበልጠውን የነፍስ ጤና የምንሸምት ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ይላል። ዝም የሚለው መከራችንን ስለማያይ ሳይሆን ከመከራው ጀርባ ያለው ዓላማ ታላቅና የተቀደሰ እንደ ሆነ ስለሚያውቅ ነው።

ስብሐት ለእግዚአብሔር !
+ እረፍተ ወላዲተ አምላክ ንጽሕት ድንግል ማርያም +
📜📖 📜📖 📜📖 📜📖 📜📖 📜📖

💭 በዓለ ፍልሰታ ወዕርገታ ለማርያም ወፍልሰተ አጽሙ ለሊቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት 💭

ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡
እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን
#በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው።
የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለ መኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።

ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ ከሀገረ ስብከቱ (ሕንድ) ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።
ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።
ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል።

በዚህችም ዕለት ከፋርስ ወደ ልዳ የሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍለሰተ አጽም ሆኗል፡፡

ስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር

📜📜📜
ድንግልማ በእውነት ተነሥታለች ።

ለእመቤታችን በዓለ ዕርገት እንኳን አደረሳችሁ፡፡

ዘሰ ይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር ተአምርኪ[ትንሣኤኪ ወዕርገትኪ] ክርስቲያናዊ፤
ኢክርስቱን ውእቱ አይሁዳዊ ወሠርፀ እስጢፋ ሐሳዊ፤
አንሰ እቤ በማኅሌተ ሰሎሞን ሰንቃዊ፤
አፈቅሮ ለፍግዕኪ ወለተ ይሁዳ ወሌዊ፤
ከመ መርዓቶ ያፈቅር ጽጌኪ መርዓዊ፡፡

እንደ ይሁዳ ስሙን የሚቃረን ግብር ሁልጊዜም የሚሠራውና ራሱን ‹‹ አባ ሰላማ ›› ብሎ የሚጠራው የተሐድሶዎች ብሎግ አንድ የሚያስደንቅ ጽሑፍ ሰሞኑን አስነብቦናል፡፡ የሚያስደንቅ ያልኩት ራሴን ባስደነቁኝ ሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ለርእስነትና ሐሳቡን ለማስተላለፍ መሪ አድርጎ የተጠቀመው ጥቅስ መልእክቱ ከነገረ ጉዳዩ ያለውን ርቀትና አንድ ሰው ከካደ በኋላ ጥቅሶችን እስከምን ድረስ ሊያጣምም እንደሚችል ሳስብ አሁንም እደነቃለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ክርስትና ከተመሠረተበትና በይፋ በብዙዎች ተቀባይነት እያገኘ ከመጣበት ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ብዙ የዓይን ምስክሮች አይተው ያስተላለፏቸውን ትውፊቶች ሁሉ ምን ያህል እንደሚጠሉ ሳስብ በዚያ ዘመን የነበሩ አይሁድ በአካለ ሥጋ የመመለስ እድል ገጥሟቸው ቢጠየቁ እንኳ"እንዴት ከእኛ በላይ ጠላችኋቸው" ብለው የሚገረሙባቸው ስለሚመስለኝ እደነቃለሁ፡፡ ሦስተኛውና ሁልጊዜም ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ተሐድሶዎች የምደነቀው ደግሞ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ባላቸው ጥላቻ ነው ፡፡ አስተውሎ ለሚያይ ሰው ጽሑፍ ነክ ነገር ላይ ከተነሡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ወቅታዊ ነገር ላይ ከተነሡ ማኅበረ ቅዱሳንን አንዳንድ ጊዜ ሁለቱንም አንድ ላይ ካላመቻቸውም የሚጽፉበትን ሰው ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ዘርዐ ያዕቆብ ነክ አድርገው ካላቀረቡ መንፈሳቸው የሚቀጣቸው ይመስለኛል፡፡

ዓለም አቀፍና ልዩነት የሌለበት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ነባር ትውፊቶች መካከል አንዱ የሆነውን የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ለዘርዓ ያዕቆብ መስጠት ማለት ምን ያህል ድፍን ቅልነት ይሆን? እንዲህ የምለውና የምደነቀውም ብዙ ጊዜ የስሕተትና የክህደት ጽሑፍ ቢጽፉም እውነቱ የያዙትና በዚያም እንጸድቃለን ብለው የሚያስቡና ለዚያም እውነት ለመሰላቸው የሚተጉ ይመስለኝ ስለነበረ ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ ሳየው ግን "ኦርቶዶክስን እንዴት እናስጠላለን፤ ሰውንስ ከእምነት እንዴት እንለያለን?" በሚል መንፈስ ብቻ እንደሚሠሩ ስለተረዳሁ ነው፡፡ አሁን አሁንማ እንደ መሸታ ቤት በየሥርቻው በከፈቷቸው ብሎጎቻቸው ዓይን ያወጣ ስድብና ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው የስም ማጥፋት ቅርሻቶቻቸውን በመትፋት ላይ መሆናቸውን ሳይ አውሬው ብስጭቱ እየጨመረ የመጣው ወደፊት ሰማዕትነትን አይቶ እየፈራ ይመስላል ፡፡

በርግጥ ይህ ብሎግ በመኖሩ "ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው" /ራእ 13፤ 5/ ተብሎ የተነገረለት አውሬው ሥራውን እያበረታ መሆኑን እናያለን፡፡ በማያቋርጠው የሐሰትና የጠብ ፤ የስድብና የስም ማጥፋት እንዲሁም የኑፋቄና የክህደት ጽሑፎቻችሁም "እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ" /ራእ 12 ፤ 15/ የተባለውን አውሬው በገቢር የሚያሳይባችሁ የክሕደትና የኑፋቄ የአውሬው የትፋት ወንዞች መሆናችሁን ታረጋግጡልናላችሁ። ነገር ግን "ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው" /ራእ 12 ፤16/ ተብሎ እንደተጻፈው ምድር የተባለች ቤተ ክርስቲያን የእናንተን የክህደት መርዝ ታሰርገዋለች ፡፡ አሁንም እንደተለመደው ሁሉ ስሕተቶቻችሁን ከማሳየት እንጀምር፡፡

አውሬ ያበከተውን አትብሉ

በመጽሐፍ "በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ እኔ እግዚአብሔር ነኝ" /ዘሌ 22 ፤ 8/ ተብሎ እንደተጻፈ አውሬ ያቆሰለው ደሙን መጥጦ ያበከተው የጫረው ሁሉ እንዳይበላ በኦሪቱ ታዝዟል፡፡ በላይኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ አውሬው ማን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናል፡፡ አንድ ሰው በጉ ወይም በሬው የእርሱ ቢሆንም አውሬ ሊበላው ጭሮ ካቆሰለው ደሙን መጥጦ ከገደለው እንዳይበላው እንደተከለከለው ሁሉ ለሕይወታችን ምግብ በአምልኮታችንም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገን ከምናቀረበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት አንዱን ለይተው ልክ አውሬ በጉን ከመንጋው ለይቶ እንደሚበላው ወይም እንደሚያቆስለው አውሬ የተባለ መና*ፍቅ ወይም ከሐዲ ከእናቱ ወይም ከመንጋው ለይቶ በተሳሳተ ትርጉም ያቆሰለውን ወይም የጫረውን ወይም በክህደት አስተምህሮ የገደለውን መብላት ለእኛ የተከለከለ ነው፡፡ በኦሪቱ ትእዛዝ እንዳየነው በጉ ንብረትነቱ የሰው ቢሆንም አውሬ ስለነካው ብቻ እንደተከለከለው ሁሉ ጥቅሱ የእኛውና ከእኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ቢሆንም አውሬ መና*ፍቅ በጥርጥርና በክህደቱ መርዙ የወጋውን በልተን እንዳንጎዳ የተከለከለ ነው፡፡ ስለዚህም ጥቅስን እኛ ለነፍሳችን የምንመገበው በአውሬ መና*ፍቃን ትምህርት ያልተጫረና ያልረከሰ ሲሆን ብቻ መሆኑን ማስተዋል አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ መና*ፍቃን በተሳሳተ መንገድ ያጣመሙትን ሁሉ ለነፍሳችን ማቅረብ ራስን መቅጣት መሆኑን ማወቅና መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡

ለምሳሌ እመቤታችን አልተነሣችም አላረገችም ብሎ ለመካድ የግድ ጥቅስም የሚያስፈልገው አልነበረም፡፡ "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም " / ዮሐ 3 ፤13/ የሚለውን ጠቅሶ እጂግ በተዛባ መንገድ እመቤታችን አላረገችም ለማለት መጥቀስ ልክ በበጎቹ አውሬ እንደሚያደርገው የበጉን ደሙን ( የጥቅሱን ነፍሱን ምስጢሩን ወይም ዋና መልእክቱን ) መጥጦ ገድሎ አበክቶ መስጠት ነው፡፡ ቀጥታ በዚህ መንገድ እንተርጉመው ካልንማ መጀመሪያውኑ የሚለው ወደ ሰማይ የወጣው ከሰማይ የወረደው ከሆነ ክርስቶስ ያረገው በተዋሐደው ሥጋ ነውና በውኑ ሥጋውን ከሰማይ ይዞ ወርዷልን? እንዲህማ ከሆነ የሰው ልጅ ተብሎስ እንዴት ሊጠራ ይችላል? እንዲህማ ከሆነ የራሱ ትምህርትና ንግግርም ሆነ ስለ እርሱ ሐዋርያትና ሊቃውንት ያስተማሩት ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡ ከሰማይ በመውረድማ ከሆነ መላእክቱን እንኳ ብንተዋቸው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛ ሰማይ የተነጠቀው ጥንቱን ከዚያ ቢመጣ ነውን? ወይስ ሔኖክና ኤልያስ ያረጉት ድሮውንም ከሰማይ የወረዱ በመሆናቸው ነው?

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ወርደው ያልተመለሱም አሉ፡፡ ለይስሐቅም ምትክ ሆኖ የተሰዋው ከሰማይ የወረደ ነበር፡፡ ለኤልያስም እንጎቻ በመሶብ ውኃም በማሠሮ ወርዶለት ነበረ፡፡ ጥቅሶችን የምትተረጉሙት እንደዚህ ከሆነ "እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም" / ዮሐ 5 ፤ 31/ የሚለውንስ ምን ትሉለታላችሁ? በእውነት ጥቅስን እንዲህ ያለ ቦታውና ያለመልእክቱ መጠቀም በገዳመ ቆሮንቶስ ለጌታም ጥቅስ እየጠቀሰ ለመፈታተን ያላፈረውንና አሁንም ይህን ከማድረግ የማያፍረውን የማይሰለቸውንም ዲያብሎስን ያስመስላችሁ ወይም በእርሱ መንፈስ የምትሠሩ ፈታኞች መሆናችሁን ታረጋግጡ ካልሆነ በቀር የምትፈጥሩት ነገር የለም፡፡ ልክ ክፉ አውሬ በጉን ከመንጋው ለይቶ አድክሞ ይዞ ደሙን መጥጦ እንደሚገድለው ጥቅስንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ከመንጋውና ከመልእክቱ ለይቶ ምሥጢር ደሙን መጥጦ በማብከት ተሐድሶዎችን የሚተካከል ያለ አይመስለኝም፡፡
2024/04/27 20:26:32
Back to Top
HTML Embed Code: