Telegram Web Link
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
የጥያቄ መልስ ሌሎችም እንዲህ ደረስ  ሼር  የአብዛኛው ቤት ውስጥ ችግር ስለሆነ ነው 


ሴት ከወለደች በኋላ (Post-Partum) የሚደርስባት የአዕምሮ ጭንቀት

ብዙ ሴቶች ከወለዱ በኋላ በትልቅ የአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ያልፋሉ። በከባድ ምጥ ውስጥ ሲያልፉ የሚሰማቸው የድካም ምልክት እንደሆነ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ...ሙሉውን ለማንበብ


ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
@binigirmachew
@binigirmachew
@binigirmachew
👍21
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
ከ1 ደቃቃ በኋላ ሰለሚጠፋ አሁኑኑ JOIN በማድረግ ተቀላቀሉ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ነው በእርግጠኝነት ይወዱታል።
         ይ🀄️🀄️ሉን
       ❤️👇🏽👇🏽👇🏽❤️
https://www.tg-me.com/addlist/y3ylvr101dAyNmU0
👍1
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
🤗አንብብ እና የሰላም እንቅልፍ ተኙ።😴

☝️አንድ ጊዜ አስበኝ

ጸሎተ ሶምሶን


ለቤተሰቤ ብርቅ ነበርሁ ፣ የኋላ ወርቅ ተብዬ የተጠራሁ ፣ “ሰማኸኝ ጌታዬ” ተብዬ ስእለት የተከፈለብኝ ፣ ሳልፀነስ የተናፈቅሁ ነኝ ፤ የመኳንንት ዘር አይደለሁም ፣ የፍቅር ጌትነት ባለበት ቤት ፣ በሚጸልይ ቤተሰብ ውስጥ የተወለድሁ ነኝ ። ጌታዬ ሆይ ! በመንፈስ ጀምሬ በሥጋ እንዳልጨርስ እባክህን አንድ ጊዜ አስበኝ ። “ነበርሁ” ብሎ መናገር ለኃጢአት እንጂ ለጽድቅ የሚዘገንን ነው ። ከቤተሰቤ በፊት አንተ አይተኸኛል...ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ


      👇ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን👇
https://www.tg-me.com/+H4EA_Zxb-MI4ZDU0
https://www.tg-me.com/+H4EA_Zxb-MI4ZDU0
👍51
Forwarded from ️ ️Bini Girmachew
ብቻ ዝም በል !

• ባትማርም ዝም በል ፣ ሊቅ ነው ብለው ያከብሩሃል ።

• ባትሰጥም ዝም በል ፣ ቸር ነው ብለው ያወሩልሃል ።

• ባይገድህም ዝም በል ፣ ጸሎተኛ ነው ብለው ያደንቁሃል ።

. ተበሳጭተህ ዝም በል፣ ትዕግሥተኛ ይሉሃል ።

. መንግሥትን ተቃውመህ ዝም በል፣ ሰላማዊ ዜጋ ብለው ይሾሙሃል፣ ይሸልሙሃል ።

. ረግጠውህ ዝም በል፣ ቻይ ነው ፣ መሬት ነው ይሉሃል።

እያወቅህ ዝም በል፣ የዋህ ነው ይሉሃል ።

ምግቡ ባይጥምም ዝም በል፣ ጥሩ ባል ነው ብለው ያወሩልሃል።

• ባትራራም ዝም በል ፣ ሁሉ በልቡ ነው ብለው ያዝኑልሃል ።

• ባታለቅስም ዝም በል ፣ ኀዘን አንጀቱ ውስጥ ገብቷል ብለው ይተነትኑልሃል ።

• ባትመርቅም ዝም በል ፣ ኀዳጌ በቀል ነው ብለው ያውጁልሃል ።

• ባይገባህም ዝም በል አስተዋይ ነው ብለው ይቀኙልሃል ።

• ወገንተኛ ሆነህ ዝም በል ፣ ሁሉን ሰብሳቢ ነው ብለው ይማጸኑሃል ።

• ቂመኛ ሆነህ ዝም በል ፣ የይቅርታ ሰው ነው ይሉሃል ።

• አያገባኝም ብለህ ዝም በል ፣ የፍቅር ሰው ነው ብለው ይናገሩልሃል ።

• አገር ይገልበጥ ብለህ ዝም በል ፣ እርሱ ታይቶታል ብለው ነቢይ ያደርጉሃል ።

• ፈርተህ ዝም በል ፣ ያስፈራል ይሉሃል ።

• መልከ ቀና ሆነህ ዝም በል ፣ መልአክ የመሰለ ብለው ከፍ ያደርጉሃል ።

• መልከ ጥፉ ሆነህ ዝም በል ፣ ደርባባ አቡን የመሰለ ብለው ይኩሉሃል ።

• ሰድበውህ ዝም በል ፣ ሊበቀለን ነው ብለው ይሰግዱልሃል ።

• ግራ ገብቶህ ዝም በል ፣ ውስጥ ውስጡን እየሄደ ነው ብለው ይክቡሃል ።

• ተማርረህ ዝም በል ፤ አመስጋኝ ፣ ዳግማዊ ኢዮብ ነው ይሉሃል ።

ዝምታ ለጻድቃን ጥበብ ፣ ለብልጦች መሣሪያ ፣ ለፖለቲከኞች ማስገበሪያ ናት ።

የዝምታህን ትርጉም የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ ።

ሁልጊዜ ዝምታ ፣ ሁልጊዜ ንግግር አይጥምም ።

Bini Girmachew ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew
👍337🥰4😱2
😃ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
   ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እራሳችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ 250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍112
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ጸሎት ጸሎት ጸሎት መቼ እንዴት የት⁉️

ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት ልጸልይ?

የጸሎት ቦታ እንዴት ላዘጋጅ?

1. የጸሎት ጊዜያት
ልበ አምላክ ነቢየ ልዑል ቅዱስ ዳዊት ”ስብዓ ለእለትየ እሴብሐከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ ፣ስለ ጽድቅህ ፍርድ በቀን ሰባት ጊዜ አመሰግንሃለው”/መዝ 118-164/ብሎ እንደተናገረ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ሰባት ጊዜ በየእለቱ እንዲጸልይ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡

ሰባቱ የጸሎት ጊዜያትም የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.1 ጸሎተ ነግህ
ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ” መዝ 62÷11  እንዳለ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ ሲተካ፣ከመኝታችን ስንነሳ ምንጸልየው የጸሎት ዓይነት ጸሎተ ነግህ ይባላል፡፡
በዚህ ጊዜ የሚከተሉትን ምስጢራት እያሰብን መጸለይ ይገባናል፡፡

ሌሊቱን አሳልፎ ቀኑን ስለተካልን እያመሰገንን ወጥተን እስክንገባ በሰላም ጠብቆ ውሎአችንን የተባረከ እንዲያደርግልን እንጸልያለን።

የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረበትም ሰዓት በመሆኑ ያንን እያሰብን እንጸልያለን፡፡

የሰውን ልጅ በመዓልትና በሌሊት የሚጠብቁ መላእክት ለተልዕኮ ሲፋጠኑ የሚገናኙበት ሰዓት ነው፡፡
የሌሊቱ መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሲቀርብና ሲተካ የሚገናኙበት በመሆኑ በዚህም ሰዓት እንጸልያለን፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች በደል በጲላጦስ አደባባይ የቆመበት ሰዓት በመሆኑ እንጸልያለን።

1.2 ጸሎተ ሠለስት (3 ሰዓት)
ከነግህ በመቀጠል የምንጸልየው ጸሎት ጸሎተ ሠለስት (የሦስት ሰዓት) ጸሎት ይባላል፡፡ይህ የጸሎት ጊዜ
- ሔዋን የተፈጠረችበት
- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርኤልን ብሥራት የሰማችበት
- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት
- ነቢዩ ዳንኤል ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም አቅጣጫ መልሶ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት
- ለአባቶቻችን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት /በኢየሩሳሌም ጸንተው በመቆየታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህንን ታላቅ ጸጋ የተቀበሉበት /ሰዓት ነው፡፡

1.3 ቀትር(6 ሰዓት)

በእለቱ እኩሌታ ላይ የምናገኘው ይህ ሰዓትም እንደዚሁ የጸሎት ጊዜ ነው፡፡ይህም ጊዜ
- ሰይጣን አዳምን ያሳተበት
- በዕፀ በለስ ምክንያት ለስሕተት የተዳረገውን አዳምን ለማዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ የዋለበት
- የቀን እኩሌታ በመሆኑ የፀሐይ ሙቀት የሚያይልበት የሰው ልጅ ለድካም የሚዳረግበት በዚህም ምክንያት አጋንንት የሚበረታቱበት ጊዜ ነው።
- ስለዚህ የአዳምን ስሕተት፣ የዳግማዊ አዳም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀልና መሞት፣እያሰብን የቀን እኩሌታ በመሆኑ መዳከማችንን ተገን አድርጎ አጋንንት እንዳይሰለጥንብን እየለመንን እንጸልያለን፡፡

1.4 ተሰዓተ ሰዓት (9 ሰዓት)

ዘጠኝ ሰዓት ላይ አራተኛውን ጸሎት እናደርሳለን።በዚህ ጊዜ
- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነጻ ለማውጣት በፈቃዱ ቅዱስ ሥጋውን ከቅድስት ነፍሱ የለየበት ሰዓት ነው።
- ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን በጎም ሆነ ክፉ ተግባር ወደ ፈጣሪ የሚያሳርጉበት ነው
- ቆርኖሌዎስ የተባለ መቶ አለቃ በጸሎት ጸንቶ ደጅ ሲጠና ከሰነበተ በኋላ ከፈጣሪው ምላሽ ያገኘበት ሰዓት ነው (ሐዋ 10÷ 9)

በዚህ ጊዜ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ እና ሞት አያሰብን ቅዱሳት መላእክት ከፈጣሪያቸው እንዲያስታርቁን እየለመንን የቆርኖሌዎስ እድል እንዲገጥመን እየተማጸንን እንጸልያለን፡፡

1.5 ጸሎተ ሰርክ (11 ሰዓት)
አምስተኛው የጸሎት ጊዜ የሠርክ ጸሎት ነው፡፡ስለዚህ የጸሎት ሰዓት ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል፡፡”ጸሎቴን እንደ ዕጣን በፊትህ ተቀበልልኝ እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን” (መዝ 140 ÷2)
·ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ከለየ በኋላ ወደ መቃብር የወረደበት ሰዓት ነው፡፡ (ማቴ. 27÷ 57)

1.6 ጸሎተ ንዋም (የመኝታ ጊዜ ጸሎት)
ይህ ጊዜ ዕለቱን በሰላም አሳልፈን ለሌሊቱ ዕረፍት የምንዘጋጅበት ነው፡፡በሰላም ላዋለን ፈጣሪ በሰላም አሳድረን ብለን ራሳችንን በእምነት የምናስረክብበት ነው፡፡እኛ ተኝተን የሚሆነውን አናውቅም እርሱ ግን የማያንቀላፋ እረኛ ስለሆነ ይጠብቀናል።ስለዚህ ከመተኛታችን በፊት ሊሌሊቱን እንዲባርክልን እንጸልያለን።
በዚህ ጊዜ፡-
- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ ዛሙርቱን በጌቴሴማኒ ጸሎት አስተምሯቸዋል፡፡
- ቀኑ አልፎ በሌሊቱ ይተካል
ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጸሎት ማስተማሩን እያሰብን እንጸልያለን፡፡ሰላም አሳድረንም ብለን ለፈጣሪ ራሳችንን በእምነት አደራ እናስረክባለን፡፡
1.7 መንፈቀ ሌሊት (እኩለ ሌሊት)

- እኩለ ሌሊትም እንደ ቀናቱ የጸሎት ሰዓታት የተለያዩ ትርጉሞች አሉት ።
ቅዱሰ ዳዊት ‘’መንፈቀ ሌሊት እትነሣእ ከመ እግነይ ለከ በእንተ ኵነኔ ጽድቅከ”“ስለ ጽድቅህ ፍርድ በእኩለ ሌሊት አመሰግነህ ዘንድ እነሳለሁ”/መዝ 118-62/በማለት ይህ ሰዓት ከእግዚአብሔር ጋራ የሚነጋገርበት እንደሆነ ገልጿል፡፡
- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ዋሻ የተወለደበት ሰዓት ነው።
- ሞትን ድል አድርጎ በታላቅ ኃይልም የተነሳው በሌሊት ነው።
- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ለፍርድ ሚመጣበትም ሰዓት ነው።
ከዚህ የተነሳ ለእኛ ሲል ከሰማየ ሰማያት መውረዱን፣ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን በማሰብ ሞትን ድል እንደነሳልንም አስበን በማመስገን ዳግመኛ ለፍርድ ሲመጣ በቀኙ ከሚያቆማቸው ወገን እንዲያደርገን እየለመንን በዚህ ሰዓት እንጸልያለን፡፡
ሰባቱን የጸሎት ጊዜያት ጠብቀን መጸለይ ካልተቻለንስ?

በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት የተቻለንን ያህል እንድንጸልይ ታዘናል፡፡
እነዚህን የጸሎት ሰዓታት በገዳም ያሉ መነኮሳት በየበረሃው የሚዞሩ ባሕታውያን ይጠብቋቸዋል፡፡ ይጸልዩባቸዋልም፡፡በከተማ በሥራ ምክንያት ሩጫ በዝቶበት በሁሉም ሰዓት መጸለይ የማይችል ክርስቲያን ግን ቢያንስ በማለዳ ከእንቅልፉ ሲነሳ እና ማታ ወደ መኝታው ሲያመራ መጸለይ ይገባዋል።ጠዋት እና ማታ በመጸለይ ከፈጣሪ ጋራ ያለው የአባትና ልጅ ግንኙነት እንዳይቋረጥ ማድረግ ይገባዋል፡፡

ምን እንጸልይ?

    ይቀጥላል...

ስለዚህ በርቱ ጸልዩ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን፡፡አሜን

 
ለሌሎችም ሼር ማድረግ አትርሱ

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍3113😱3🎉2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (ዲ/ን አቤንዔዘር ሙሉ)
የኦርቶዶክስ ልጆች ዛሬ ተባበሩን ገብታችሁ ለጓደኞቻቹ ሼር በማድረግ ቤተክርስቲያኑን መርዳት እንድንችል እገዛችሁን አክሉ

በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02p1VKrg4Zb6eUHHjdMRtfz4zis1kD9a5sKD71Kn8wXwEBijEMyTgAJfq1GCvG16CDl&id=100066470276758&mibextid=Nif5oz
👍2
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
🛑ክፍል 2 ተለቀቀ።

ምን እንጸልይ?

በመደበኛነት ልንጸልያቸው የሚገቡ ጸሎታት በቤተክርስቲያናችን አባቶች በገዳማቱ በአድባራቱ የሚዘወተሩ እለታዊ ጸሎታት እነኚህ ናቸው፡፡

1 መዝሙረ ዳዊት

መዝሙረ ዳዊት በገዳማት ከሚኖሩ አበው መነኮሳት ባህታውያን ጀምሮ በካህናት፣ምእመናን በሁሉም ዘንድ በየእለቱ የሚጸለይ ጸሎት ነው።አባቶች ከፊደል ቆጠራው ቀጥሎ ዳዊቱን ያጠኑና ከዚህ ጊዜ ጀምረው እየደገሙት፣እየጸለዩበት ይኖራሉ።ዳዊት ሳይደግሙ ወደ ዕለታዊ ተግባራቸው አይሰማሩም።መዝሙረ ዳዊት እንደሌሎች ጸሎታት ሁሉ በየዕለቱ ተለይቶ የሚጸለይ አለው

ቀጥለን እንመልከት
ሰኞ ከ 1 - 30፣ማክሰኞ ከ 31-60፣ረቡዕ ከ 61-80፣ሐሙስ ከ 81-110፣አርብ ከ 111-130፣ቅዳሜ ከ 131-150

እሁድ- ጸሎተ ነቢያት እና መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ይጸለያል፡፡
አንድ ንጉሥ
መዝሙረ ዳዊትን ስንጸልይ ለዕለቱ የታዘዘውን ሃያ እና ሰላሳ መዝሙር ማድረስ ባንችል እንኳን አንድ ንጉሥ ማድረስ ይገባናል።

አንድ ንጉሥ የሚባለው፦አስር መዝሙር ነው፡፡ለምሳሌ ሰከኞ አንድ ንጉስ ለማድረስ ከፈቀዱ ከ 1-10 ያለውን ያደርሳሉ፡፡ከማክሰኞ ከሆነ ደግሞ ከ 30-40 ያውን የመጀመሪያውን አስር መዝሙር ያደርሳሉ ማለት ነው፡፡ይህን ሁሉ ማድረስ ያልተቻለው ግን የተወሰኑ መዝሙራትን መርጦ በየእለቱ ያደርሳል፡፡


2. ውዳሴ ማርያም
ውዳሴ ማርያም ከተቻለ የሰባቱን ዕለታት ካልተቻለ የእለቱን ማድረስ ተገቢ ነው።የዘወትር ጸሎት ካደረስን በኋላ የዕለቱን ውዳሴ ማርያም አድርሰን ይዌድስዋ መላዕክትን ደግመን ከእመቤታችን በረከት ተሳታፊ መሆን ተገቢ ነው፡፡

በዋልድባ የሚኖሩ መነኮሳት ውዳሴ ማርያም ከቅዳሴ ማርያም ሳያደርሱ ውለው አያድሩም፡፡ እኛም ከአበው ተምረን ማታ ከመኝታ በፊት ወይም ጠዋት ስንነሳ ይህን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው፡፡

3. ወንጌል ዘዮሐንስ
የዮሐንስ ወንጌልን በየምዕራፍ ከፋፍለን በየእለቱ ማንበብ ሌላው ጸሎት ነው፡፡አባቶች ይህንን ጸሎት በየእለቱ እያደረሱ ብዙ ተጠቅመውበታል።

4.ሌሎች ጸሎታት
ውዳሴ አምላክ፣ ሰኔ ጎለጎታ፣ መልክአ ኢየሱስ፣ መልክአ ማርያም ፣ በመዝገበ ጸሎት እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍት ላይ ያሉትን ሌሎች ጸሎታት፣እንዲሁም ገድላት፣ተአምራትን፣እንደ ችሎታችን በየዕለቱ እናደርሳለን፡፡ቢያንስ ግን ይህ ሁሉ ባይሆንልን ከላይ የጠቀስነውን የመዝሙረ ዳዊትና፣ውዳሴ ማርያምን ጸሎት ማድረስ ይገባናል፡፡

አጭር ጸሎት
በተቻኮልን እና መጻሕፍትን ለማንበብ ጨርሶውን ጊዜ በማይኖረን ሰዓት ይህንን እንድንጸልይ አንዳንድ አባቶች ይመክሩናል።አቡነ ዘበሰማያት፣ጸሎተ ሃይማኖት፣ሰላም ለኪ /ስለ ውዳሴ ማርያም ፈንታ/፣አቡነ ዘመሰማያት፣አንድ ከመዝሙረ ዳዊት/ መዝሙር 150/ በመዝሙረ ዳዊት ፈንታ/በመጨረሻም አቡነ ዘበሰማያት ማድረስ ብንችል መልካም ነው ።ጸሎተ ሃይማኖት የህይማንት መግለጫ በምህኑ እንጸልየዋለን። በመካከል ሰላም ለኪ በመድገማችንም የውዳሴ ማርያም በረከት ይደርሰናል። መዝሙረ ዳዊት 150 ስናደርስ ደግሞ ሁሉንም መዝሙራት የደገምን ያህል ይሆንልንና የዳዊቱን በረከት እናገኛለን፡፡ይህንን ሁሉ ማድረስ ካልተቻለን ግን ቢያንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን አቡነ ዘበሰማያት ብለን ከቤታችን ልንወጣ ይገባናል።አጭር ጸሎት ከሥፍራ ሥፍራ ሊለያይ ይችላል ዘጠኝ ሰላም ለኪ፣አስራ ሁለት አቡነ ዘበሰማያት በገዳማት ያሉ አበው ያደርሳሉ።
የጸሎት ቅደም ተከተል
አቡነ ዘበሰማያት: አንድ ከመዝሙረ ዳዊት:ውዳሴ ማርያም: እና ሌሎችም ቀጥሎም አቡነ ዘበሰማያት በእንተ እግዘዕትነ ማርያም ጸሎተ ሃይማኖት በመጨረሻም አቡነ ዘመሰማያት ኪርያላይሶን 41 ግዜ።
አጭር ጸሎትን እንደ መደበኛ ማድረግ ለፈተና ያጋልጣል
አጭር ጸሎት የምንጸልየው በጣም በተቸገርንበት፣ጊዜ ባጣንበት ሰዓት ነው።ይህንን ጸሎት እንደመደበኛ ይዞ በየእለቱ አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብቻ መድገም ግን ስንፍና እንዳይሆን ያስፈራል።

ይልቁንም በክርስትና ሕይወት ጅማሬ ላይ ያሉ ምእመናን/ወጣንያን/
ክርስትናውን እስኪላመዱ ጸሎታቸው አጭር ሊሆን ይችላል።እየቆዩ ሲሄዱ ግን በጸሎት እየበረቱ ወደ መደበኛው ጸሎት መድረስ አለባቸው።

ይህ አይነቱ አካሄድ የእግዚአብሔርን ቸርነት ለስንፍና ምክንያት አድርጎ መጠቀምም ነው።ከዚህ ጋር በቤተክርስቲያን አገልገሎት ላይ ያለንም ዳዊት መድገም ውዳሴ ማርያም ማድረስ ይጠበቅብናል።

የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ፣ዲያቆናት፣ቀሳውስት፣ሰባክያነ ወንጌል፣መዘምራን……እነዚህን ጸሎታት መጸለይ ይጠበቅባቸዋል።አልያ ግን እያወቅን ጸሎት ማድረስ እንዳለብን ብዙ ጊዜ ተምረን እንዳልተምርን ቸል ብንል ለፈተና መጋለጥ ይመጣል።ከእግዚአብሔርም ቸርነት እንድንርቅ ያደርገናል።
አቡነ ዘበሰማያት የጸሎታችን መነሻና መድረሻ ጸሎት ስናደርስ የጸሎታችን መነሻ (መጀመሪያ) አቡነ ዘበሰማያት ነው፡፡

በመካከል ጸሎት አቋርጠን ከሰው የምንነጋገርበት ጉዳይ ቢገጥመን በአቡነ ዘበሰማያት ማሰር ተገቢ ነው፡፡በአቡነ ዘበሰማያት አስረን የገጠመንን ጉዳይ ፈፅመን እንመለሳለን፡፡

ከዚያም አቡነ ዘበሰማያት ብለን ካቆምንበት እንቀጥላለን።ጸሎታችንን በአቡነ ዘበሰማያት ሳናስር በመሃል እንዳሻን እንዳናቋርጥ አበው ያስተምሩናል፡፡


የማህበር ጸሎት

በቤታችን ከምንጸልየው ጸሎት በተጨማሪ በቤተክርስቲያን ተገኝተን ጸሎት ማድረስ ተገቢ ነው።

ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንደመሆና በእርሱ የሚጸለይ ጸሎት ከጸሎታት ሁሉ የላቀ ነው።በካህናት እየተመራ ፣በሕብረት ሆነን የምናደርሰው በመሆኑ ታላቅ ኃይል አለው።

እግዚአብሔር በቤተ መቅደስ የምንጸልየውን ጸሎት እንደሚሰማ ሲያመለክተን እንዲህ በማለት ነግሮናል።”አሁንም በዚህ ሥፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዓይኖቼ ይገለጣሉ ፣ጆሮቼም ያደምጣሉ።

ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም ዓይኖቼ እና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።”/2 ዜና መዋ 7-15/ ከዚህ አንጻር በቤተ መቅደስ እየተገኘን መጸለይ ተገቢ ነው።በሰንበት ቀን ኪዳን ማድረስ ፣ ቅዳሴ ማስቀደስ የመጀመሪያው እና ዋነኛው ተግባራችን መሆን አለበት።በሰንበት ያለ በቂ ምክንያት ቅዳሴ የሚያስታጉል በቀደሙ አባቶች /አባ ሚካኤል ወአባ ገብረኤል/ቃል መወገዙን የተአምረ ማርያም መቅድም ይነግረናል።

ከዚህ ጋር በሰዓታት ፣በማኅሌት ጸሎታት ላይ በመገኘት ቤተ ክርስቲያናችን ካዘጋጀችልን የማይጠገብ ማእድ ልንሳተፍም ይገባናል።

የሃይማኖታችን ፍጹም ፍቅር የሚኖረን ከእነዚህ ጸሎታት ጋር ስንተዋወቅ ነው።አልያ የእንጀራ ልጅ መሆን ይመጣል።

የመናፍቃንን አዳራሽ መናፈቅ ይመጣል።
ከላይ በተመለከተው የጸሎት ጊዜ እየተጠቀምን፣የጸሎት ዓይነቶችንም በምንችለው መልኩ እያደረስን፣በቤተ መቅደስ እየተገኘን ኪዳን እያደረስን፣ቅዳሴ እያስቀደስን ከፈጣሪን ጋራ እለት እለት እንነጋገር ጸሎት ከሌለ መንፈሳዊነት ጥያቄ ውስጥ ይገባል፡፡

ከጄነሬተሩ ተቋርጦ ገመዱ ተበጥሶ ብቻውን እንደተንጠለጠለ አምፖል መሆን ይመጣል፡፡


ስለዚህ በርቱ ጸልዩ ፈጣሪ ለሁላችንም ብርታቱን ያድለን አሜን።

ለሌሎችም ሼር ማድረግ አትርሱ!!

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

👇🏾📽የግእዝ ትምህርት በyoutube🖥👇🏾
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍419🥰1
የግእዝ ቋንቋ ለሁለት ወር ስልጠና ተጀምሯል
መሠረታዊ የቋንቋ ትምህርት
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን

ለበለጠ መረጃ
☎️በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍15
በዚህ ቻናል ከዚህ በኋላ በትክክል የግእዝ ትምህርት መሰጠት እንጀምራለን እስከዛሬ በትእግስት ስለጠበቃችሁን እናመሠግናለን በተጨማሪ በግል መማር የምትፈልጉ @asrategabriel ላይ ማናገር ትችላላችሁ ።
🙏7👍2
🔅 መሠረታዊ ቃላት

👀 አካለ ሰብእ ( የሰውነት ክፍሎች )
      ክፍል ፩


ስእርት ➺ ጸጉር
ገጽ ➺ ፊት
ዐይን ➺ ዐይን
ፍጽም ➺ ግንባር

አንፍ ➺ አፍንጫ
ልሳን ➺ ምላስ
አፍ ➺ አፍ
አስናን ➺ ጥርስ

ከንፈር ➺ ከንፈር
መልታሕት ➺ ጉንጭ
እዝን ➺ ጆሮ
እድ ➺ እጅ


      #የሰውነት_ክፍሎች
         -▣ ✦✧ ▣-
      ◎ ልሳነ ግእዝ ለኩልነ ◎
@lesangeez128
👍236
የግእዝ ቋንቋ ለሁለት ወር ስልጠና ተጀምሯል
መሠረታዊ የቋንቋ ትምህርት
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን

ለበለጠ መረጃ
☎️በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍2
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
አምነህ እየተኛህ አምነህ መውጣትን አትፍራ ።

ስትበላ ድሀ አደጎችን ፣ ስትጠጣ በበረሃ የሚኖሩትን ፣ ስትለብስ የተራቆቱትን ፣ ወደ ቤትህ ስትገባ ጎዳና የወደቁትን ፣

ስትተኛ ዕረፍት ያጡ በሽተኞችን...ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ


         ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
            BINI GIRMACHEW
👍112😱1
Forwarded from ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 (🤴ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ🤗)
ሕማማት @eotc_books_by_pdf (1).pdf
74.2 MB
📚⛪️ሕማማት📚⛪️

ብዙዎቻቹ በውስጥ መስመር ያለ watermark ይሰራ ብላችሁ ስለጠየቃችሁን ተሰርቶ ቀርቧል እናንተም በበኩላችሁ ለሌሎች በማካፈል አንብቡ አስነብቡ።

🤗መልካም የበረከት ጾም ይሁንልን🤗

አዘጋጅ ፦ @Ethio_Pdf_Books
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

  🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾


➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺
👍7
Forwarded from ማራናታ ᴘʀᴏⓂᴏᴛɪᴏɴ
👬15ቱ የመልካም ጓደኛ ባህሪያት
    

1.Encouragers
   በጣም በከፋ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ነገ መልካም ይሆናል ብለው ተስፋ የሚያሳዩ እና የሚያበረታቱ።

2. The Hand Lifters
   በጣም የወረደ ስሜት እና መከፋት ውስጥ ስንሆን የማይለዩ።

3. Destiny Helpers
   ራእይ እና ሀሳባችንን ማሳካት እንድንችል በሚችሉት ሁሉ የሚያግዙ.....ተጨማሪ ለማንበብ

                  👇👇
www.tg-me.com/BiniGirmachew
www.tg-me.com/BiniGirmachew
www.tg-me.com/BiniGirmachew
👍3
የግእዝ ቋንቋ ለሁለት ወር ስልጠና ተጀምሯል
መሠረታዊ የቋንቋ ትምህርት
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን

ለበለጠ መረጃ
☎️በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓
👍191🙏1
ልሳነ ግእዝ ለኩልነ pinned «የግእዝ ቋንቋ ለሁለት ወር ስልጠና ተጀምሯል መሠረታዊ የቋንቋ ትምህርት   🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን። #ለሁለት ወር…»
2025/10/27 13:22:54
Back to Top
HTML Embed Code: