ትችትን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ. .ምንም አለመሥራት. . .ምንም አለመናገር በአጠቃለይ ምንም መሆን ነው! !
Aristotle
Join & share us 🙏
~የኛ ሳይኮሎጂ~
@yegna_psychology
@yegna_psychology
"#መሳሳት አንዱ የህይወት አካል ነው!! ካልተሳሳትክ አትማርም፡፡ ካልተማርክ አትለወጥም፡፡"

መሞከር አይከፋም😉❗️❗️❗️
"ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም ። ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ ፡፡"
.
ዶ/ር ምህረት ደበበ
#Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
የቅንነትህን ፍሬ ወዲያዉኑ ላታየው ተችላለህ ነገር ግን እያንዳንዷ እምታበረክታት መልካም ተግባር ዓለማችንን የተሻለ ቦታ ለማድርግ የራሷ አስተዋጽኦ አላት።
Lisa Qurrie
Join & share us 🙏
~የኛ ሳይኮሎጂ~
@yegna_psychology
@yegna_psychology
በህይወት ውስጥ ትልቁ ፈተና የልብህን እውነት ሰዎች እንዲረዱህ ማድረግ ነው። ቤተሰብ፣ ወዳጅ የልቤ የምትለው ጓደኛ ላይረዳህ ሁሉ ይችላል፤ የሚሻለው መተው ነው።

እነሱ እንዲረዱህ የምታባክነውን ጉልበትና ልፋት ራስህን ለማሳደግ ብታውለው ብዙ ርቀት ትጓዛለህ። በህይወትህ ላይ ልዩነት የምትፈጥረው ራስህ ላይ ስትሰራ ብቻ ነው!
አስተሳስብህን ተመልከት፤ ቃላት ይሆናሉ፣ ቃላትህን ተመልከት፤ ድርጊት ይሆናሉ፣ ድርጊትህን ተመልከት፤ ልማድ ይሆናሉ፣ ልማድህን ተመልከት፤ ባህሪህ ይሆናል፣ ባህሪህን ተመልከት፤ መዳረሻህ ይሆናል !
--Lao Tez--
@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
ጠንካራ ጓደኝነት በየዕለቱ ቃላት መለዋወጥ አያስፈልገውም፣ ሁልጊዜ አብሮ መሆንንም አይጠይቅም ። ጓደኝነቱ በልብ እስካለ ድረስ እውነተኛ ጓደኝነት መቼም አይፈርስም !
--Auliq Ice
@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
ህይወት ልክ እንደ ፒያኖ ነች። ነጫጮቹ ቁልፎች የደስታ ቀናት ሲሆኑ ጥቁሮቹ ደሞ የሀዘን ቀናት ናቸው። አስታውስ ! ሙዚቃን ለመፍጠር ግን ሁለቱም ያስፈልጉሀል !
--Unknown
@yegna_psychology
@yegna_psychology
@yegna_psychology
#ተው
ማን ሲሞት ተደሰትክ
ማን ሲሞት አለቀስክ
ማንን በሳቅ ሸኘህ
ለማን እንባ አነባህ
ተው ይቅርብህ ህዝቡን አትመርዘው!
የሰው ደም አንድ ነው!
ቀይ ነው ቀለሙ ሲወጋ ሚፈሰው!

@Henilogy [ሄኖክ ፀጋዬ]

@wetiopia
@wetiopia
Forwarded from Inspire Ethiopia  (ɴᴀᴛᴀɴɪᴍ_፳፯)
ከሰው መጠበቅ አቁም!
Forwarded from MALEDA HUGE MARKET (21)
ነዳጅ

ኢምሬትስ Vs ኢትዮጵያ 🇪🇹 Vs 🇦🇪

ጥያቄ :- የመኪና ቤንዚን ከኢትዮጵያ ና ከኢምሬትስ ውድ የት ሀገር ነው ?

ኢምሬትስ በአለም ካሉ ነዳጅ ካላቸውና ለአለም ገበያ ከሚያቀርቡት ብዙ ቢሊዮን ዶላር ከሚሰበስቡት 8 ሀገራት ወይንም የOPEC አባል ውስጥ አንዷ ስትሆን

ነዳጅ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እልል ብሎ እየጨመረ ነው

ነዳጅ ካላት ኢምሬትስ ና ነዳጅ ከሌላት ኢትዮጵያ የአንድ ሊትር የመኪና ቤንዚን ዋጋ ስንት ይሆናል:-

በኢምሬትስ በዚህ ወር 1 ሌትር ቤንዚን

* 2 ድርሀም ከ66 ፊልስ ሲሆን ወደ ብር ሲመነዘር
ደሞ :-
* 34 ብር ከ74 ሳንቲም ይሆናል

ኢትዮጵያ ደሞ ትላንትና በወጣ የወሩ ሂሳብ:-

* 1 ሊትር የመኪና ቢንዚን 31 ብር ሆኖል

ይህ ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ከውጪ የሚያስገባውን ቤንዚን ለህብረተሰብ ትርፍ ሳያገኝ እያከፋፈለ ስለሆነ

ነዳጅ እያላት ውድ ከምትሸጠው ኢምሬትስ ነዳጅ ሳይኖራት ከውጪ እያስገባች ለዜጎቿ ከስራ በእርካሽ የምታከፋፍለውን እማማ ኢትዮጵያውያን ማመስገን ግድ ይላል

👏 👏 👏🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ጉርሻ page
You can raise up from anything.
You can completely recreate yourself.
Nothing is permanent.
You are not stuck.
You have choices.
You can think new thoughts.
You can learn something new.
You can create new habits.

All the matter is you decide today and never look back.

#Share📌
🔖@motivationofstudent
ስብከት በቆንጆ ሴት አፍ!
«ዘውድአለም ታደሠ»

በዚች ምድር ላይ ስኖር ልለምደው ያልቻልኩት ነገር ምንድነው? ዝናብ እየ ዘነበ በጠኋት መነሳት! ውይ! ምርር እኮ ነው ሚለኝ እውነት። ሲዘንብ ከአልጋ መውረድ ከስልጣን የመውረድ ያክል ይከብደኛል። ህይወት ለጥቂት ሰአት ትደብረኛለች!
ዛሬም እንደፈረደብኝ በጠኋት ተነስቼ ካፊያውን ተቋቁሜ ወደስራ አዘግማለሁ። ብርዱ አክቲቪስት ያሳቅፋል! :) ወደቤቴ ተመልሼ የመጣው ይምጣ ጥቅልል ብዬ ልተኛንዴ? የሚል ሃሳብ እየታገለኝ ስጓዝ ጠላታችሁ ክው ይበል የክላክስ ድምፅ ክው አረገኝ! (ይሄንማ ባዲስ መስመር ነው ምነግራችሁ)

ዞር ስል አጠገቤ እንደመስታወት የሚያበራ ጥቁር መኪና ቆሟል! መቼስ እነዚህ አሽከርካሪዎች እግረኛውን እንደጂፒኤስ ነው ሚጠቀሙበት መንገድ ሊጠይቀኝ ይሆናል ብዬ ጠጋ ስል የመኪናው መስታወት በቀስታ ወርዶ አንዲት ውብ ሴት ከውስጥ ብቅ አለች!! (ልክ መስታወቱ ሲከፈት መኪና ውስጥ የሞላው ውበት ወደውጪ የፈሰሰ ነው የመሰለኝ)
እንደድሮ ደራሲ ውበቷን እየተነተንኩ አላዝጋችሁም ባጭሩ ቁንጅና ብትወዳደር ብቻዋን ከአንድ እስከአስር ምትወጣ አይነት ሴት አርጋችሁ አስቧት! (ባለትዳሮች አታስቧት ይቅርባችሁ ሃሃ)

እኔ ደሞ ጥሎብኝ ያው የሴት ልጅ ውበት አድናቂ ነኝ ታውቃላችሁ። ቆንጆ ሴት ሳይ ለጥቂት ሰከንድ ሃውልት የሚያረገኝ ነገር አለ። ሴት ልጅ የኔ ሆነችም አልሆነች ቆንጆ ስትሆን ደስ ይለኛል በቃ! እዚህ ጋር ዋናው የውስጥ ውበት ነው ምናምን የሚል ምክር አልቀበልም። ወንድ ልጅ የሆነ ነገሯን ወዶ ካልቀረባት ውስጧን በምን አባቱ ያውቀዋል? ስንታይ የኤክስሬ ማሽን እንመስላለን እንዴ? ምን ትላለች እቺ!

«ወዬ ምን ልታዘዝ?» አልኳት በትህትና። እስቲ ወደፊት ሄድ ብለህ አስፓልቱ ላይ ተኛና ልግጭህ ብትለኝ ሁሉ ምስማማ ይመስለኛል
«አይ መንገዳችን አንድ ከሆነ ልሸኝህ» አለችኝ። ገና ልሸኝህ የሚለው ቃል ከአፏ ከመውጣቱ ጋቢና ገብቼ ተቀምጫለሁ :)

መኪና ውስጥ ለስለስ ያለ የሊሊ መዝሙር ይሰማል ... ውስጡ ገላዋ ላይ በበተነችው ማራኪ ሽቶ ታውዷል። መሪ ምታሽከረክርባቸውን ቀያይ ጥፍር ቀለም የተቀቡ ጣቶቿን አየኋቸው! ማሽ አላህ አለ አብዱ! እቺ ልጅ በሽንት ቤት መኪና ሁሉ ሊፍት ብትሰጠኝ ደስ እያለኝ ነው ምሳፈረው
ከመዝሙሩ ጋር በለሆሳስ ትዘምራለች
«ልክ እንዳበደ ሰው
አይምሮውን እንዳጣ
አመሰግናለሁ ወዳንተ ስመጣ
የሌለኝን ሳይሆን ያለኝን እያየሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ»

ትላለች ሊሊ! በአንድ ግዜ ንጭንጭና ድብርቴ ጠፋ! ገንዘብ ደስታን አይገዛም ምናምን ያለው ሰውዬ ማን ነበር? ብቻ ማንም ሆነ ማን የመሃል ጣቴን ሰጥቼዋለሁ :) ብራዘር የድህነት አስከፊነት የሚገባህ አንተ አጥንትን በሚሰረስር ብርድ ካፊያ እየዘነበብህ እንደገብረ ጉንዳን ታክሲ ጥበቃ ተሰልፈህ መስታወት ከፍተው በተወለወለ መኪና አስፓልቱ ላይ ፈልሰስ የሚሉ ሹፌሮችን ስታይ ነው! ያኔ አያቶቻችን ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ያሉት ከመሬት ተነስተው እንዳልሆነ ይገባሃል!

መዝሙሩን በግማሽ ልቤ እየሰማሁ እሷ ላይ ተመስጫለሁ። እሷ መኪናዋን በእርጋታ እያሽከረከረች ትዘምራለች። ፊቷ ላይ ቢከፋፈል ለአፍሪካ የሚበቃ ሰላም አለ! በቃ ሰላም አስከባሪ ፊት ታውቃላችሁ? ስታዩት የተዋከበ ነፍሳችሁን የሚያረጋጋ ፀጥታ የሰፈነበት ፊት!! ትንሽ እንደተጓዝን ድንገት
«ጌታ ይወድሃል» አለችኝ!
«እኔም እወድሻለሁ ... ውይ የኔ ነገር... እኔም እወደዋለሁ ማለቴ» አልኩ ተደናብሬ

ከዛ ቀለል አርጋ ትሰብከኝ ጀመር። እኔም አንዴ ስብከቱን አንዴ የከንፈሮቿን እንቅስቃሴ እያደነቅሁ ዝም ብዬ ተከታተልኳት (ትምርቴን እንዲህ ብከታተል ይሄኔ ሰው ሆኜ ነበር

እውነት ለመናገር ስብከት እንዲህ ገብቶኝ አያውቅም :D ከዚህ በፊት ብዙ ፕሮቴስታንቶች ሰብከውኝ ያውቃሉ። ግን እንዲህ ሮማንቲክ በሆነ መንገድ ስላልሰበኩኝ ነው መሰለኝ አስፈራሩኝ እንጂ አልማረኩኝም። አንዳንዶቹማ በአንድ እጃቸው መፅሃፍ ቅዱሳቸውን ይዘው የአንድ እጅ ሌባ ጣታቸውን ወደኔ እየጠቆሙ ዛቻ የሚመስል ስብከት ነው የሰበኩኝ። አለ አይደል
«ወየውልህ .... ብትድን ይሻልሃል .... ሲኦል ትገባታለህ ... እናትህ አፈር ትብላ ንስሃ ግባ» አይነት ስብከት!

እቺ ግን በቃ ሲኦል የለ ምን የለ ስለክርስቶስ ፍቅር ነው ምትሰብከኝ። ነፍሱን ላንተ ብሎ ሰጥቶሃል። ላንተ ያለው ፍቅር ጥልቅ ነው። ምናምን ስትለኝ ያው ውበቷም ተጨምሮበት እምባ ተናነቀኝ አረ አሁኑኑ ጌታን ተቀበል ተቀበል ሁሉ ብሎኛል። ከዚች ሴት ጋር አይደለም ገነት ሲኦል ራሱ መግባት ያዋጣል። አልኩ በልቤ
መጨረሻ ላይ ፈቃደኛ ከሆንክ ቸርች ልጋብዝህ? ስትለኝ አላቅማማሁም። እንኳን ቸርች ቀለል ያለ ጦርነት ላይ ብትጋብዘኝ ምንሽር ተሸክሜ የምሄድ ይመስለኛል። ሃሌሉያ!

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@life of singles
12ኛ ክፍል ወደኩ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ አላለም...

ዩኒቨርስቲ የገባ ሁሉ አይመረቅም። የተመረቀ ሁሉ ስራ አይዝም። ስራ ያለው ሁሉ ደስተኛ ኑሮ አይኖርም... So my brother don't give up ! go forward and choose another option... ከ 100 መንገድ አንዱ ነው የተዘጋብህ 99 ክፍት ብሮች አሉህ። Feel free and relax no one is a result of your happiness except yourself. ያለፋቹህ Congrats ደግሞ እዛ ሔዳቹ ዱላ ይዛቹ ዘረኛ እንዳትሆኑ... ያላለፋችሁም Congrats በአቋራጭ ዝነኛ፣ ሐብታም፣ ታዋቂ መሆን ትችላላቹህ።
2024/05/03 09:40:20
Back to Top
HTML Embed Code: