Telegram Web Link
ሀና ቴይለር ሽሊትዝ ትባላለች። የአንድ ዓመት ሕፃን ሳለች በ2000 ዓ/ም ነበር በአሳዳጊዎቿ አማካኝነት ከአርባ ምንጭ ወደ አሜሪካ ያቀናችው።

ሀና ባለፈው የካቲት ወር 16ኛ ዓመት ልደቷን አክብራለች። ከቴክሳስ የሴቶች ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ በመመረቅ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በዚህ ዕድሜ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘች ትንሿ ተማሪ ለመሆን በቅታለች።

ይኸው ዩኒቨርሲቲ ሀና የፒ ኤች ዲ ትምህርቷን እንድትከታተል የተቀበላት ሲሆን፣ ይህም ሀናን በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ትንሿ የፒ ኤች ዲ ተማሪ አድርጓታል።

ቤተሰቦቿ በቤት ውስጥ ያዘጋጁትን ስርዓተ ትምህርት ተከታትላ በሚኖሩበት ቴክሳስ ግዛት ስኬታማ ተማሪ መሆን የቻለችው ሀና፣ በልጅነቷ ወላጅ እናቷን ያሳጣትን የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ግንዛቤን ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋራ እየሠራች ትገኛለች።

በማህበረሰብ ሳይንስ ላይ አተኩራ መስራት የምትፈልገው ሀና፣ ሰው አዋቂ ሆኖ በመፈጠር ሳይሆን በርትቶ በመስራት ስኬትን ሊቀዳጅ እንደሚችል ከአሳዳጊዮቿ መማሯን ትገልጻለች።

ምንጭ:- ፎክስ ኒውስና ቪኦኤ አማርኛ

@ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰርቪስ
1. ስኬትህ የምታደርገው ነገር ነፀብራቅ ነው

ከቀደመው ማንነታችን የተሻልን ለመሆን ጥረት ባደረግን ቁጥር በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ የተሻሉ መሆን ይጀምራሉ።

~ የተሻለ ሰው መሆንህ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ማለትም የአኗኗር ዘይቤህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ማህበረሰብህን የሚጠቅም ተዘዋዋሪ ተጽእኖ ይፈጥራል።


2. የምናብ ሰው ሁን

" አለምን የማየው እንዲከሰት ከምፈልገው ነገር አንፃር እንጂ ከሚታየው ነገር አንፃር አይደለም።"

~ ሰዎች ዓለምን እንዳለች መቀበልን ቢመርጡ ኖሮ ታላላቅ ፈጠራዎች አይከሰቱም ነበር።

~ ታላላቅ ስኬቶች እና ፈጠራዎች ‘አይቻልም’ የሚል አስተሳሰብን ችላ በማለት ይጀምራሉ።

3. በራስህ መንገድ ላይ አተኩር

ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህ ይችላል፤ ነገር ግን የሌላ ሰው ህይወት መኖር ከጀመርክ ግራ የተጋባ ሰው ትሆናለህ።

~ ምክር መቀበል እና ከሌሎች መማር ምንም ችግር የለውም፣ ነገር ግን የምትሄድበት መንገድ ከአንተ ፍላጎት እና ዝንባሌ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ።

4. አሰልቺውን ተመሳሳይ ህይወት ስበረው

እያንዳንዱ ቀን ከቀጣዩ ቀን ጋር ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከናወኑትን መልካም ነገሮች ለይተው ማወቅ ስለሚያቅታቸው ነው።

~ ምስጋና በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ ጥሩውን የማግኘት ልምምድ ነው።

5. ፍርሃት ከሚያጋጥምህ ማንኛውም እንቅፋት የበለጠ ትልቅ እንቅፋት ነው።

~ ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ!

6. አሁንን ተቀበል
ሁልጊዜ አሁን ባለህ ነገር ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ።

~ ባለፈው መኖር እና ያለፈው ህይወትህ አንተን እንዲገልፅ መፍቀድ ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ምንም ፋይዳ የለውም።

7. ወስን
አንድ ሰው ሲወስን፣ መጀመሪያ ውሳኔውን ሲወስን አያውቃቸው ወደነበሩ ቦታዎች የሚወስደው ኃይለኛ ፍሰት ውስጥ እየገባ ነው።

~ ድርጊት በውሳኔህ ላይ ከመተማመን የሚመነጭ ነው። አጥር ላይ መቀመጥ የትም አያደርስም። ስለዚህ ወስን! የውሳኔ ሰው ሁን!

8. ሁልጊዜ እርምጃ ውሰድ

" ለመማር አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤ ይህም ተግባር ብቻ ነው""

9. እንደገና መነሳትህን ቀጥል

" የሕይወት ምስጢር ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።"
ምክንያቱም ስምንተኛው ጊዜ የአንተ ግኝት ሊሆን ይችላል።

ይህን #post ከወደዳችሁትና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን ይዘን እንድንመጣ የምትፈልጉ ከሆነ #like #repost #copylink #share በማድረግ አብራችሁን መሆናችሁን አሳዩን 🙏🙏🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mXU7H3qlPB&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
#Urgent

Lighthouse Training and Consulting PLC is currently looking experianced trainers on International Financial Reporting Standards (IFRS). Please message us your full name and contact number as soon as possible through this 👉 https://www.tg-me.com/Lighthouse_Training_Center telegram address. Thanks
የሰው ልጅ ትናንት በበላው ብቻ ዛሬ አይኖርም፡፡ ትናንት አዲስ ብሎ የገዛው ጨርቅ ዛሬ ይሠለቸዋል፡፡ በአሮጌ ልብስ አይዘነጥም፡፡ ባረጀና ባፈጀ ሃሳብም ሕይወትን ማሳመር አይቻልም፡፡ ...

ሰው ተፈጥሮው በየሰዓቱና በየዕለቱ የሚታደስና የሚለወጥ በመሆኑ ዘወትር ግብዓት ይፈልጋል፡፡ ሆድ በሰዓቱ የሚፈልገውን ካላገኘ ጥያቄ ያነሳል፡፡ ጥያቄውን መመለስ የሚቻለው በጊዜው የሚፈልገውን ማቅረብ ሲቻል ነው፡፡ በርግጥ ሰው ምግብ ሳይበላ ለቀናት ሊቆይ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቆይታው የስቃይ ነው የሚሆነው፡፡ ምግብ ያላገኘ ሰው መላ ሰውነቱ ይደክማል፤ ማሰብ ያቅተዋል፤ በእጆቹ ሊሰራቸው የሚፈልጋቸውን ስራዎች በቀላሉ መስራት አይችልም፡፡ አቅም፣ ጉልበትና ብርታት ያጣል፡፡

የሰው ልጅ አዕምሮም እንደዛው ነው፡፡ በየቀኑ የሚፈልገውን አዲስ ሃሳብ፣ የተለየ መረጃና ዕውቀት ካላገኘ ይራባል፡፡ ማዕዱ ካልተሟላ ነፍስያው እንደተራበ፣ መንፈሱ እንደከሳ ዕድሜውን ይጨርሳል፡፡ ውስጣዊ ደስታው ይራቆታል፡፡ ማሰብ መመራመር፣ ነገሮችን አብጠርጥሮ ማወቅ አይችልም፡፡ አቅሙና ጉልበቱ ድሮ በተመገበው ሃሳብ ብቻ ይወሰናል፡፡ ወደፊት አሻግሮ ማየት ይሳነዋል፡፡ ጊዜውን የሚዋጅ ሃሳብ ያጣል፡፡ ከዘመኑ ጋር መስተካከል ያቅተዋል፡፡ ነፍስያው ይመነምናል፤ መንፈሱ ይከሳል፣ አዕምሮው ይደክማል፣ ሚዛኑ ይዋዥቃል፣ አስተውሎቱ ይጠብባል፣ አስተሳሰቡ ያንሳል፣ ዕይታው ይጭበረበራል፡፡

ዕውቀት የተራበ ጭንቅላት፤ ሃሳብ የታረዘ ሕሊና ለዓለሙ ያለው ምልከታ የተሳሳተ ይሆናል፡፡ ለፍረጃና ለጭፍን አመለካከት ይጋለጣል፡፡ በደረሰበትና በቆመበት የሃሳብ ሳጥን ብቻ ተወስኖ ሰፊውን ዓለም ሳይመረምርና ሳያውቅ በነሲብ ይደመድማል፡፡

አሜሪካዊው ደራሲ ሪቻርድ ራይት “Native son” በተባለ መፅሐፉ፡-

‹‹የሰው ልጅ ከእንጀራ የበለጠ ሊርበው የሚገባው ራሱን ወይም ማንነቱን ማወቅ ነው›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ራስን ማወቅ የዕውቀት መጀመሪያ ነው፡፡ ነገር ግን ራስን ለማወቅ ዓለሙንና አስተሳሰቡን፤ ውስጣውስጥ አመለካከቱን ጠንቅቆ ማወቅ ግድ ይላል፡፡

አለሙን ለማወቅ ደግሞ አዕምሮን በያይነቱ በሆነ መረጃ መመገብ ያስፈልጋል፡፡ መረጃውን በደንብ ማብላላትና የሚጠቅመውን መዋጥ፣ የማይጠቅመውን መትፋት ያሻል፡፡ ጥሩ የተመገበ በፊቱ እንደሚታወቀው ሁሉ በጥሩ ሃሳብ የተሞላ ጭንቅላትም በአኗኗሩ፣ በሕይወቱ፣ በሃሳቡና በተግባሩ ይታወቃል፡፡

አዎ! ሕሊና እንዲያድግ አዳዲስ ሃሳቦችን ዕለት ዕለት መመገብ ግድ ይላል፡፡ ትናንት ያስበብበት በነበረው መንገድ ብቻ እንዳይወሰን አዲስና ከቀድሞው የተለዩ መንገዶችን ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ የሕይወት አቅጣጫውን ከወዲሁ እንዲያውቅ፣ የወደፊቱን ቀድሞ ይተነብይ ዘንድ እንዲችል ተራማጅ አዕምሮ ያስፈልገዋል፡፡ የትናንቱን እያዛመደ፣ የዛሬውን ሃሳብ እየፈተሸ የወደፊቱን መንገድ ማበጀት ግድ ይለዋል፡፡

ንጉስ ዳዊት፡-

‹‹በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ይሰበሰባሉ፡፡›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ንጉስ ዳዊት ምናምንቴ የሚለውን ወደዚህ ዘመን ብናመጣው ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ራስወዳድነት፣ ማስመሰል ወዘተ ክፉ ነገሮች ሁሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ሰው ለዘረኝነትና ለገንዘብ ጣዖት እየሰገደ ነው፡፡ ለጣኦቱም የምስኪን ሕይወት እየተገበረለት ይገኛል፡፡

በዚህ ዘመን ጣኦቱ የበዛው ምናምንቴ አስተሳሰብ ስለበዛ ነው፡፡ አዎ ጭንቅላቱ የተራበ ሰው ለምናምንቴ ሃሳብ እጅ ይሰጣል፡፡ ለማይጠቅመው ያጎበድዳል፡፡ ራሱን የረሳ ጭንቅላት ህሊናውን በወጉ ያልመገበ ነው፡፡ ራሱን መመገብ ያቃተው ራሱን በራሱ ማስተዳደር ያልቻለ ነው፡፡

ለራሱ መሆን ያቃተው ጭንቅላት ለሌሎችም ሆነ ለዓለሙ ዕዳ ነው፡፡ የሌሎች ባሪያ እንጂ የራሱ ጌታ መሆን አይችልም፡፡ በነዱት የሚነዳ፤ ሲገፉት የሚገፋ ጋሪ ይሆናል፡፡

ሃሳብ ያነሰው አዕምሮ ባትሪው እንዳለቀ ስልክ ነው፡፡ በቁሙ ይተኛል እንጂ አይነቃም፤ ያለ ይመስላል እንጂ የለም፡፡ ቢቀሰቅሱት አይሰማም! ሃይል ጨርሷላ!

ወዳጄ ሆይ.... ዕለት ዕለት፣ በየጊዜው አንጎልህን በአዲስ ሃሳብ ቻርጅ አድርገው፡፡ ቀስ በቀስ አቅሙ እንዳይደክምና ሃይሉን እንዳይጨርስ ጭንቅላትህን አዲስ ዕውቀት ሙላው፡፡ ምናምንቴው ሃሳብ ህሊናህን እንዳይገዛ ጥሩ ጥሩውን መግበው፡፡

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ጭንቅላትህን በየጊዜው በአዲስ ሃሳብ/እይታ ቻርጅ ለማድረግ ፍላጎትህ ከሆነ ይህን ገፅ #follow በማድረግ ተከተለው!!!

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mXU7H3qlPB&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
የKFC መስራች አይበገሬው አዛውንት ኮሎኔል ሳንደርስ:-

☞በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ

☞በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ

☞በ17 ዓመቱ 4 የተለያዩ ስራዎቹን አጥቶ ነበር

☞ከ18 እስከ 22 ዓመቱ የባቡር ትኬት ቆራጭ ሆኖ ሰራ ነገር ግን አልተሳካለትም

☞የሀገሩን መከላከያ ቢቀላቀልም ተባረረ

☞ህግ ለመማር አመለከተ አልተሣካለትም

☞ለአንድ ኢንሹራንስ ድርጂት ግብይት ሰራተኛ ሆነ..ይህም አልተሣካለትም፡፡

☞በ19 ዓመቱ ደግሞ ልጅ ወልዶ ነበር 2ዐ ዓመቱ ላይ ሚስቱ ልጃቸዉን ይዛ ጥላዉ ሄደች፡፡

☞በአንዲት ትንሽየ ካፌ ምግብ አብሳይና ሰሃን አጣቢነት መስራት ጀመረ
.
.
.
☞65 ዓመት ሲሞላዉ ጡረታ ወጣ

☞ጡረታ በወጣ በመጀመሪያዉ ቀን የ$105 ቼክ ከመንግስት ደረሠዉ..እሱ ግን የተረዳዉ መንግስት "ራስህን መመገብ አትችልም" እንዳለዉ ነበርና ከዚህ በኋላ መኖሩ ጥቅም እንደሌለዉ ራሱን አሣምኖ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረግ....ይህም ሳይሆን ቀረ፡፡

☞አንድ እለት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ምኞቶቹን ወረቀት ላይ ማስፈር ፈለገ የፃፈዉ ግን በህይወቱ ሊያደርጋቸዉ እየቻለ ሳያደርጋቸዉ ስለቀሩ ነገሮች ነበር...

ከዝያም በእርግጠኝነት ማድረግ እንደሚችለዉ የሚያዉቀዉን አንድ ነገር አሰበ...ምግብ ማብሰል፡፡

☞ወዲያዉም የመንግስትን የዉለታ ቸክ መልሶ $87 ተበደረ፡፡

☞በዚያች ብድርም ቅመሞቹን ሸምቶ ፍራይድ ችክን አዘጋጀ...

እናም በኬንታኬይ ለሚኖሩ ጎረቤቶቹ በራቸዉ ድረስ እየሄደ መሸጥ ጀመረ፡፡

☞ ከዚያም በ68 ዓመቱ የኬንታኬይ ፍራይድ ችክን KFC ኢምፓየር መስራች ቢሊየነር ሆነ!!!

ኮሎኔል ሳንደርስ እንዳለው:-

"ስኬታማ ለመሆን ከሌሎች የበለጠ ረዘም ያለ ጊዜ ስለወሰደብህ ብቻ ወድቀሃል ማለት አይደለም!"

አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን የምናጋራበትን ይህን ቻናል join በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ🙏
እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...

እያልሽ ይሆናል።

ትክክል ብለሻል። ይሁንና ጨርሰሽ መርሳት የሌለብሽ.....

ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች። ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቂ!

ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።

እኩዮችሽ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችሽ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችሽ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችሽ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችሽ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችሽ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችሽ ሆነው አንች የምትኖሪውን ኑሮ የሚናፍቁና በአንቺ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሻል!

ምናልባት የምትፈልጊው ስፍራ ላይ አልተቀመጥሽ ወይም የምትመኝውን ነገር አላገኘሽ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነሽ። ስለዚህም ፈጣሪሽን ባለሽ ነገር አመስግኝው።

አንች ለብቻሽ የሆነብሽ ነገር የለም። አንች ጋር የጎደለሽን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎሽ ነው። ባወቅሽው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝኝ! የራስሽንም አታቃይ። ያወቅሽ የመሰለሽ ያላወቅሽው ብዙ አለና።

ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆኝ ደስታን ምርጫሽ አድርጊ። ሰላምንም ውደጃት።

ሁልጊዜም በፈጣሪሽ ደስ ይበልሽ!
በተሰጠሽ ነገር ፈጣሪሽን አመስግኝ!!!

አንተም እንደዚሁ!!!

መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏
አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል።

አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ።

ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ።

ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት።

አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት !

እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ሴንቲ ግሬድ ቃጠሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት ከሰሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል።

በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree centigrade ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው?" ስትሉ ....

አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣
ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣
የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣
እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት:-

አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል።

ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።

አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።

አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን።

የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም።

የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ።

ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው።

... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።

ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mwqCRwSCd4&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
ለአንድ ግለሰብም ሆነ ኅብረተሰብ፣ ቤተሰብም ሆነ አገር የዕድገትም ሆነ የውድቀት ቁልፉ መሬቱ ሳይሆን አዕምሮ ላይ ነው። መሬቱ የሚቆለፈው የሰው አዕምሮ ሲቆለፍ ነው።

አንድ ሰው አዕምሮው ሲከፈትለት ሁሉ ነገር ይከፈትለታል። የአንድ ሀገር ሕዝብ አዕምሮው ሲቆለፍ፣ ሁሉ እያለው ምንም እንደሌለው ሁሉም ነገር ይዘጋጋል።

.... ሌብነት ብትይ ሙስና፣ አምባገነንነት ብትይ ጦርነት፣ ዘረኝነት ብትይ የሐይማኖት ግጭት፣ ሁሉም የአዕምሮ መቆለፍ ምልክት ናቸው።

ስለዚህ አሁን አንገብጋቢውና ትልቁ ቁም ነገር መንገድ መሥራት ወይም ሕንጻ መገንባት ሳይሆን ይህንኑ ማድረግም ሆነ በተሰራው በቅጡ መጠቀም የሚቻለው የሰው አዕምሮ ሲከፈትና ከተኛበት የዘመናት እንቅልፍ ሲነቃ ብቻ መሆኑ ላይ ነው።" ...

ምንጭ:- "የተቆለፈበት ቁልፍ" በምሕረት ደበበ (ዶ/ር)

መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት በርካቶች ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ
በድፍን አሜሪካ ዝናዋ የገዘፈና ሰፊ እውቅናን ያገኘች ጋዜጠኛ ስም እንጥራ ካልን #ኦፕራ ዊንፍሬይ ለማለት እንገደዳለን።

ታዲያ ይህች የሚዲያው አለም ንግስት ለአመታት ከነገሰችበት የጋዜጠኝነት ሙያ ድንገት ጡረታ እንደምትወጣ አሳወቀች። በዘርፉ ላበረከተችው መጠነ ሰፊ አገልግሎት ሊያመሰግኗትና ሊያከብሯት በመሻት የጡረታ ስንብቷን በአንድ ትልቅ ስቴዲየም አደረጉ።

አስደናቂው ነገር ግን በዛ ቀን ማንም ሳያውቅ ለ25 ዓመታት 65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ/ ድሆችን ትረዳ እንደነበር መታወቁ ነው። ይታያችሁ በሩብ ምዕተ-ዓመት ስልሳ አምስት ሺህ ድሆችን ረድታ ኑሯቸውን ማቃናት ችላለች።

ይህም ሊታወቅ የቻለው በእሷ እገዛ ከትናንት ማንነታቸው ተላቀው ዛሬን በተሻለ ህይወት ላይ የሚኖሩት አብዛኞቹ በስታዲየሙና በፕሮግራሙ በመታደማቸው ነው።

ከታዳሚዎቹ መሃል 450 ሰዎች ሻማ እያበሩ ወጡ....ከነዚህ 450 ሰዎች መካከል ደግሞ አምስቱ በሃርቫርድ ዩንቨርሲቲ ባለ ሙሉ ማዕረግ ፕሮፌሰሮች ናቸው። እነዚህን ሰዎች ወክሎ ንግግር ያደረገው ፕሮፌሰር ሲናገር " የኦፕራ እገዛ ባናገኝ ኖሮ፣ ምናልባት መገኛችን እና ማንነታች ሌላ ቦታ ላይ ሊሆን ይችል ነበር" አለ።

👉አያችሁልኝ?? አንዲት ልበ-ቀና እንስት የ65,000 ሰዎችን ህይወት እንዴት እንደቀየረች???

#የሰውነት_ልኬት

"ሰብዓዊነት ኃይማኖት አይደለም ፣ግን የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የሚቆናጠጡት የህይወት ልህቀት ደረጃ ነው" ያለው ሶቅራጥስ በምክንያት መሆኑን ኦፕራ ማሳያ ትሆናለች ብዬ አምናለሁ።

የሃገራችን ሚሊየነሮች ምናለ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፋሽኑ አልቆ ውራጅ የሚሆንን አልባሳት፣ ህንፃ፣ መኪና ቅብጥርስ ከማሳደድ ተቆጥበው.....የድሃ ልጆችን ተንከባክበው የሰብዓዊነት ዋልታና ማገር ቢሆኑ!!!!

👉ፈጣሪ ሆይ እንደ ኦፕራ አይነት ደግ ልብ የቸርካቸውን ባለ ሃብቶች በሃገራችን አብዛልን!!
✍️አለበል ንጋቱ
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።

በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።

አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።

በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።

በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።

በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።

አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።

#አንተስ "በህይወት የምትቆየው ለአንድ ዓመት ብቻ ነው" ብትባል ምን ታደርጋለህ?


#ይህን ጥያቄ መመለስ በውስጣችን የተዳፈነውን ልዩ ችሎታችንን ወይም አቅማችንን አውጥተን እንድንጠቀም የሚረዳን አይመስላችሁም?

ሃሳባችሁን አጋሩን!

መልእክቱን ከወደዳችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8n6rRbMIYje&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
አንዳንድ ሰዎች የማንነታቸውን ዋጋ የሚመዝኑት ካሳለፉት መከራና ከደረሰባቸው ችግር አንጻር ነው፡፡ የደረሰባቸውን የኑሮ ውጣ ውረድ በአካላቸውና በኑሮአቸውም ላይ ያደረሰውን ጉዳት በቀጥታ ከማንነታቸው ዋጋ ጋር ያዛምዱታል፡፡ ሲቸገሩና ሲጎሳቆሉ የማንነታቸውን ዋጋ ይቀንሱታል፡፡

በአንጻሩ ነገሮች በመልካም ሲሄድላቸውና የተሳካላቸው ሲመስላቸው ለራሳቸው የሚሰጡትን ዋጋ ከፍ ያደርጉታል፡፡ ሰዎችም ካለማቋረጥ ይህንኑ መልእክት ለህሊናው እንዲናገሩ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ ውጤቱም የወደቀ ማንነትን ነው፡፡

በአንድ በዝቅተኝነት ስሜት የተጎዱ ሰዎች ለምክር በሚመጡበት ማእከል ውስጥ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ችግራቸው አንድ ነው፣ የኑሮአቸው ሁኔታ በራሳቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት ደብድቦ ጥሎታል፡፡ በራሳቸው ላይ የወደቀ አመለካከት አላቸው፡፡

አሰልጣኙ በምን መልኩ ከዚህ አመለካከት ሊያወጣቸው እንደሚችል ካሰበ በኋላ አንድን ምሳሌ ነገራቸው፡፡

በእጁ አንድ ድፍን መቶ ብር ይዟል፡፡ ወደ ሰዎቹ ዘወር አለና፣

“የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?” አላቸው፡፡

የሁሉም መልስ እንደተጠበቀው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡

የሚቀጥለው ጥያቄ፣

“ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡

ሁሉም በመሽቀዳደም ምን ሊገዛ እንደሚችል መናገር ጀመሩ፡፡

በመቀጠልም፣ ይህንን መቶ ብር በመዳፉ አጅግ ጨመደደው፣ ከዚያም ወደ መሬት ጣለውና ረገጠው፡፡ በእጁ አንስቶ ከጨመደደው በኋላ ያንኑ ጥያቄ ጠየቃቸው፣

“የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?”፡፡

የሁሉም መልስ እንደቀድሞው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛውንም ጥያቄ ደገመው፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡ መልሳቸው እንደቀድሞው ነበር፡፡

ከዚያም የሚከተለውን ነገራቸው:-

“ይህ ብር ተጨማደደ፣ ወደቀ፣ ተረገጠ፣ … ዋጋው ግን ያው ነው፡፡ የእናንተም ዋጋ እንዲሁ ነው፡፡ ምንም አይነት ነገር በሕይወታችሁ ቢያልፍ፣ ዋጋችሁ ግን ያው ነው - የውጪ ገጠመኛችሁና ሁኔታችሁ የማንነታችሁን ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይችልም”፡፡

“አንተነትህን የያዘው የሆንከው ማንነትህ አይደለም፣ ነኝ ብለህ ያሰብከው ሃሳብህ እንጂ” - Unknown Source

ከተወለድክባት ቀን ጀምሮ ያለፍክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ተመልከታቸው፡፡

የወደቅክባቸውንና የተነሳህባቸውን፣ ያዘንክባቸውንና የተደሰትክባቸውን፣ የብቸኝነትህን ጊዜና በወዳጆች የተከበብክባቸውን ጊዜአት … አስባቸው፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች የተለያዩ የስሜት ከፍታዎችንና ዝቅታዎችን እንድታሳልፍ ዳርገውሃል፣ ሆኖም በማንነትህ ላይ ጥቂት እንኳ የዋጋ መቀነስ ተጽእኖ የላቸውም፡፡

ማንነትህ፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፍም ያው ማንነትህ ነው፡፡
ስኬታማ ሆንክም አልሆንክ፣ ባለጠጋ ሆንክም አልሆንክ፣ እነዚህ ነገሮች ከማንነትህ ጋር በፍጹም አይገናኙም፡፡

በማንነትህ ላይ ያለህ አመለካከትና ለማንነትህ የሰጠኸው ዋጋ ግን በስኬታማነትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ያለፈው ታሪክህ፣ አሁን የምታልፍበት የኑሮ ጫናም ሆነ ያለህና የሌለህ ነገር በአንተነትህ ዋጋ ላይ ተመን እንዲያስቀምጡበት የምታደርገው አንተው ብቻ ነህ፡፡ ሰው የመሆንህ ክቡርነት በፍጹም በዋጋ ሊተመን ስለማይችል፣ ከፍም ሆነ ዝቅ ማለት አይችልም፡፡ በራስህ ላይ ያለህ ግምት ግን ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አመልካችነቱ የስሜትን ከፍታና ዝቅታ እንጂ የማንነትን ዋጋ ከፍታና ዝቅታ አይደለም፡፡

ዋጋህን ሳትቀናንስ፣ ካለፈውና ከአሁኑ ሁኔታህ ላይ አይኖችህን አንስተህ በፊትህ ወዳለው መልካም የወደፊት ስኬት እንድትዘልቅ የሚከተሉትን እውነታዎች ማሰላሰሉ ጠቃሚ ነው፡፡

👉 የሆነልህን እንጂ የሆነብህን አትቁጠር

“ከሃዘኖችህ ይልቅ ሃሴቶችህን፣ ከጠላቶችህ ይልቅ ደግሞ ወዳጆችህን ቁጠር” - Irish Proverb

👉 ራስህን አክብር

“ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በስተቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም” - Mahatma Gandhi

(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👇 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8n8zcdM80z0&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
2024/06/14 09:18:13
Back to Top
HTML Embed Code: