Telegram Web Link
አንድ ሰው ብዙ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰው ግን አንድ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡

የአንድ ሰው ብዙነት ከዕድሜው የሚያገኛቸው ብዝሃ ማንነቱ ነው፡፡ አንድ ሰው በልጅነቱ የልጅነት አስተሳሰብና ማንነት አለው፤ በወጣትነቱም የወጣትነቱን ሰውነትና የትኩስነት ማንነቱን ይይዛል፡፡ ያው አንዱ ሰው ሲጎለምስም የጉልምስና ሰውነትን ያንፀባርቃል፡፡ በአዛውንትነት ዕድሜውም በተረጋጋው ማንነቱ ሰውነቱን ያበጃጃል፡፡ በስተመጨረሻም በዘመነ እርጅናው ትናንቱን እየወቀሰና እያሞገሰ፣ ዛሬ ላይ መካሪና ዘካሪ እየሆነና ወዳለፈው ጊዜ በሃሳብ ፈረስ እየጋለበ፣ ትዝታውንም እያቀነቀነ ወዳማይቀረው ይሄዳል፡፡

እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ማንነቶች በአንድ ግለሰብ ህይወት ላይ ወጥተው የሚገቡ፤ ገብተው የሚወጡ ማንነቶች ናቸው፡፡

አምላክ የሰው ልጅ ተፈጥሮን አንድ ጊዜ ቢሰራውም ሰው ግን ማንነቱን ብዙ ጊዜ ያበጃጃዋል፡፡ እንደእውቀቱ መጠን፤ እንደአስተሳሰቡ ደረጃ፣ እንደሕይወት ገጠመኙ፣ እንደአኗኗር ሁኔታው፣ እንደአስተዳደግ ዘዬው ራሱን ይለዋውጣል፤ አዕምሮውን ያድሳል፤ ሃሳቡን ያገላብጣል፡፡

ከተፈጥሯዊው የእድሜ ጉዞው በተለየም ሰው ዕውቀትን ሲጨምር፣ አስተሳሰቡን ሲያድስ፣ ኑሮውን ሲቀይር አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ሲከተል አዲስ ሰውነትን ይጎናፀፋል፡፡ ያው አንዱ ሰው ብዙ የተለያዩ ማንነቶችን ለራሱ ይጋብዛል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው ስንት ነው? ብዙ ነዋ!

አንድ ጥንታዊ ፈላስፋ ያነሳው ግሩም ጥያቄ ነበር፡፡ ጥያቄውም፡-

‹‹እኔ ራሴ አንድ ሰው ሆኜ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ እንደህፃን፣ ቀጥሎም እንደወጣት፣ ከዚያም እንደጎልማሳ፣ በመጨረሻም እንደሽማግሌ ኖሬአለሁ፡፡ ከሞት በኋላ ሕይወት ቢኖር እንኳን ዘላለማዊውን ሕይወት እንደማን ሆኜ ነው የምኖረው? እኔ የሕይወት ተሞክሮ ውጤት ነኝ፡፡ ስለሆነም ሁለትና ሶስት ወይም ከዚያ በላይ የሰው ባሕሪያትን በውስጤ ይዤ በምድር ላይ ከኖርኩ በኋላ ብሞት በምኖረው ሕይወት የመገለጫዬ ባህርይ ማን ሊሆን ነው?›› ሲል ይጠይቃል፡፡

ጥያቄው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

ሰው ከሞት በኋላ የማንነት መገለጫው ማን እንደሆነና በየትኛውስ ማንነቱ ሊፈረጅ እንደሚገባ ማወቅ አጓጊ ነው፡፡ እንደእኔ ግን ሰው ከሞት በፊት በመጨረሻ ሕይወቱ የያዘው ማንነቱ በዕድሜው ሙሉ ያያቸውና የተለዋወጠባቸው ማንነቶች ድምር ውጤት በመሆኑ የሚፈረጀውም፣ የሚከሰሰውም፣ የሚደነቀውም ሆነ የሚከበረው በኋለኛው የህይወት ማንነቱ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው ሕይወቱ የዕድሜው ሁሉ መጠቅለያ ማንነት ነው፡፡

ሰው በዕድሜው ካያቸው የራሱ የተለያዩ ማንነቶች የሚወሰደውን ወስዶ፣ የሚጣለውን ጥሎ መልካሙን ማንነት መያዝ የእሱ ድርሻ ነውና፡፡ ከራስ መማርን የመሰለ ምን ወሳኝ ትምህርት አለ?! ምንም!

እድሜ ካልተማርንበት ቁጥር ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ቁጥር ብቻ ደግሞ ዋጋ የለውም፡፡ ዋጋ ያለው ሕይወት እውን የሚሆነው የሰው ልጅ ዕድሜ በበጎ ስራ ሲቆጠርና ሲተመን ብቻ ነው፡፡ በዚች አስገራሚ ዓለም ሽማግሌ ሆነው እንደ ልጅ የሚኖሩ፤ ልጅ ሆነው እንደአዋቂ የሆኑ መኖራቸው ሃቅ ነውና፡፡

ከሞት መለስ በሕይወት እያለ የሰው ልጅ መጠየቅም፣ መኮነንም፣ መደነቅም ሆነ መከበር ካለበት በአሁናዊው ማንነቱ ነው፡፡ ዛሬ ማንነቱን በበጎ አስተሳሰብ የዋጀ ሰው ትናንት ባጠፋው መወቀስ የለበትም፡፡ የትናንቱ ጥፋት በትናንት ማንነቱ ነው ሊፈረጅ የሚገባው፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና!

የአመክንዮ ሕግም በትናንት ማንነቱ የዛሬውን አዲስ ማንነቱን የሚደመድሙ ሰዎች ልክ እንዳልሆኑ ይናገራል፡፡ ይሄንንም Miss-representation Fallacy ሲል ይገልፀዋል፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና የትናንቱን ሽሯል፡፡ የትናንት አሮጌ አስተሳሰቡን በአዲስ አስተሳሰብ አድሷል፡፡ የትናንት አላዋቂነቱን በዛሬ ዕውቀቱ ቀይሯል፡፡ ትናንት ያልገባው ዛሬ ገብቶታልና፡፡

ታላቁ የነፃነት ታጋይ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይሉናል፡-

‹‹በስኬቴ አትዳኙኝ፡፡ ይልቁንስ ምን ያህል ጊዜ ወድቄ ምን ያህል ጊዜ መልሼ እንደተነሳሁ አይታቹህ ፍረዱኝ ›› ይላሉ፡፡

አዎ! የአወዳደቅህ ሳይሆን የአነሳስህ ሁኔታ ያንተን ማንነት አጥርቶ ያሳያል፡፡ የወደቁ ሳይሆን ከውድቀታቸው የተነሱ አዕምሯቸው ሰፊ ስለመሆኑ ክርክር አያሻውም፡፡

በጠባቡ አስተሳሰባቸው ወድቀው በሰፊ አስተሳሰባቸው ሕይወታቸውን ያሰፉና ከውድቀታቸው የተነሱ ትንሳኤ ብሩሃን የሆኑ ሊደነቁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም በመውደቅ መነሳታቸው መካከል ያገኙት ትምህርት እንዴት ከውድቀት መነሳት እንደሚቻል አዲስ ዕውቀት አስጨብጧቸዋል፡፡ ተስፋ ቆርጠው ወድቀው አለመቅረታቸው የሚያሳየው የአስተሳሰባቸው ጮራ ምን ያህል የበራ እንደነበረ የሚያሳይ ነውና፡፡

አዎ! ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን በተለያዩ ውድቀቶችና አወዳደቆች ተፍገምግመናል፡፡ የሚያሳፍረውና የሚያስፈራው ነገር ከውድቀታችን ለመነሳት ፍላጎቱም ሆነ ቁርጠኝነቱ የሌለን መሆኑ ነው፡፡

👉 አንዳንዶች በዘረኝነት ወድቀዋል፣ 👉 ጥቂቶች በትእቢት በአፍጢማቸው ተተክለዋል፡፡
👉 ቀላል ቁጥር የሌላቸው አወቅን ብለው ደንቁረዋል፤ ሰፋን ብለው ጠብበዋል፡፡
👉 ሰለጠንን ያሉት እቡያን ሰይጥነዋል፡፡
👉 ከዕድሜአቸው ያልተማሩ፤ ከብዝሃ ማንነታቸው ቀለም ያልቆጠሩ፣ መልካሙን ያልኮረጁ ቆመ-ቀሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡
👉 ከብዝሃ ማንነታቸው ያልተማሩ በአንዱ ማንነታቸው የሙጥኝ ያሉ አዲስ ሃሳብ ያስደነግጣቸዋል፤ ለውጥ ይቀፋቸዋል፤ አዲስ ማንነት ያስፈራቸዋል፡፡

አዎ! አንድ ሰው ብዙ ነው፡፡ ብዙነቱን ግን እውን የሚያደርገው በሰፊው አስተሳሰቡ ሲሰፋ ነው፡፡

ከተፈራረቁበት ማንነቶቹ ጠቃሚውን ማንነት ፈልቅቆ የሚያወጣ ብልህ ሰው ከብዙነቱ እልፍ ትምህርት ቀስሟል፡፡ ቅስሙን የሚሰብር ሳይሆን ቅስሙን በአዲስ አስተሳሰብ የሚጠግን ጀግና ካለፈው ሕይወቱ ብዙ የተማረ ነው፡፡ ከውድቀቱ የሚማር መላልሶ መነሳት አይቸግረውምና፡፡

ወዳጄ ሆይ…

👉 አንተ አንድ ሰው አይደለህምና እንደብዙ ሰው አስብ!

👉 መውደቅን አትፍራ! ነገር ግን እንዴት ከወደቅበት ቦታ መነሳት እንደምትችል አዕምሮህን አሰራ፡፡

👉 መውደቅ በማንም ላይ የሚደርስ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ወድቆ መቅረት ነው አሳፋሪው ነገር፡፡

ቸር መነሳት! ቸር ትንሳኤ! ቸር ብዝሃነት!

✍️ እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ይህን ፅሁፍ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ
-----------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤው አደረሳችሁ።
ወተት ከተበላሸ እርጎ ይሆናል፤ እርጎ ግን ከወተት የበለጠ ዋጋ አለው። ወተት የበለጠ የከፋ ከሆነ ወደ አይብነት ይቀየራል። አይብ ግን ከእርጎ እና ከወተት የበለጠ ዋጋ አለው።

የወይን ጭማቂ ወደ ጎምዛዛነት ከተለወጠ ወደ ወይን ጠጅ ይለወጣል፤ ይህም ከወይኑ ጭማቂ የበለጠ ውድ ያደርገዋል።

ስህተት ስለሰራህ አበቃልህ ማለት አይደለህም። ስህተቶች እንደ ሰው የበለጠ ዋጋ እንዲኖርህ የሚያደርጉ ልምዶች ናቸው።

ክሪስቶፈር ኮሎምበስ አሜሪካን እንዲያገኝ ያደረገው በአሰሳው ወቅት ስህተት በመስራቱ ነው።

የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ ስህተት ፔኒሲሊን እንዲፈጥር አድርጎታል።

ስህተቶችህን እንድትወድቅ ሳይሆን የተሻለ እድሎችን የምትፈልግባቸው መሰላል አድርጋቸው።

ፍጹም የሚያደርገን ልምምድ አይደለም። ፍፁም የሚያደርገን የተማርንባቸው ስህተቶች ናቸው!

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share #ማድረግን አትርሱ 🙏
1. ‹‹መከራ ሠውን ይሠራዋል፤ ቁሳዊ ብልፅግና ግን አስፈሪ ጭራቅ ያደርገዋል፡፡››

2. ‹‹ከሁሉ መጀመሪያ ሠው ሁን! የሠብዓዊነትን ቀንበር ለመሸከም አትፍራ፡፡››

3. ‹‹መሞት ምንም አይደል፡፡ አለመኖር ግን አስከፊ ነው፡፡››

4. ‹‹ብልህ ሠዎች ከሕይወት መከራ መፅናኛቸውን የሚፈልጉት ከመፅሐፍ ነው፡፡››

5. ‹‹ጊዜው ከደረሠ ሃሳብ በላይ ሃይለኛ የለም፡፡››

6. ‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››

7. ‹‹የሃብታሞች ገነት የተሠራው ከደሃዎች ሲዖል ነው፡፡››

8. ‹‹የማያለቅሱ ማየት አይችሉም፡፡››

9. ‹‹ምንም ዓይነት ጦር ወይም መሣሪያ ጊዜው የደረሠ ሃሳብን ሊያስቆመው አይችልም፡፡››

10. ‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››

11. ‹‹ሕሊና ማለት በሠው ውስጥ የፈጣሪ መኖር ነው፡፡››

12. ‹‹ልማድ ወይም ሱስ ስህተቶችን መንከባከቢያ ስፍራ ነው፡፡››

የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? comment አድርጉልን።

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡

ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና እዚያው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።

ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመሩ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡

ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች።

በሂደት በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
------------------------------
የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡

አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡
------------------------------
በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡
------------------------------
በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው!

ልክ እንደ አህያዋ (የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው) ሁሉ እኛም በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀምን በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልገናል።
------------------------------
ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው!

ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ እንጓዝ!!
------------------------------
እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተጠቀምክበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!

------------------------------
መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ!

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
"የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለሁ ሁለት ቁልፍ ፈተናዎች ነበሩብኝ ሆኖም ሁለቱንም ወደኩ….

የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁም ፈተና ከመውደቅ አልዳንኩም ለውድቀት ሶስት ጊዜ እጄን ሰጠሁ፡፡

👉 ኮሌጅ ለመግባት ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም መግቢያ ፈተናዎቹን ሁለቴ ወስጄ በሽንፈት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ያመጣሁት ውጤት አሳዛኝ ነበር። መውደቅ አንድ ነገር ቢሆንም በሂሳብ ትምህርት ከ120 ነጥብ 1 ማምጣት ግን በርግጥም ከባድ ነበር፡፡

ውድቀቴ ይቀጥላል…

👉 ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ 10 ጊዜ አመልክቼ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡

👉 ከኮሌጅ ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ስራ የመቀጠር ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም 30 ስራ እድሎች በተከታታይ ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡

KFC ስራ አወጣ ተደሰትኩ በዚህኛው ግን ስራ ለማግኘት የማደርገው ጥረት በድል እንደሚደመደም አስቤ ተራመድኩ፡፡

ኦብዙ ፈተናዎችን አልፈን ለስራ የመጣነው 24 ነን፡፡ 23 ሰው አለፈ በሚደንቅ ሁኔታ የወደቀው አንዱ ሰው እኔ ነበርኩ፡፡"

ይህንን ያለው ጃክ ማ ነው።

ይህ ሰው ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ ቻይናን የቀየረ አማዞንን መሰል የአሜሪካ ካምፓኒዎችን የሚገዳዳረውን አሊባባን የመሰረተ እና እዚህ ያደረሰ ስኬታማ ሰው ነው፡፡

"በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ዛሬ ከባድ ነው…ነገም የከፋ ሊሆን ይችላል… ከነገወዲያ ግን መልካም ይሆናል!!!"
– Jack Ma

------------------------------
መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ!

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፦
ከንባብም ሆነ ከህይወት ተሞክሮ ያገኛችሁትን ሌሎችን ሊያስተምር የሚችል ማንኛውንም #እይታና #እሳቤ ይህን 👉 https://www.tg-me.com/higher_perspective_group የቴሌግራም ግሩፕ በመቀላቀል #አጋሩን! እርስበርስ እንማማር!

ወዳጅ ጓደኞቻችሁ ይህን ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ዘንድ #ሊንኩን👆 #copylink #share በማድረግ ጋብዟቸው🙏
ሀና ቴይለር ሽሊትዝ ትባላለች። የአንድ ዓመት ሕፃን ሳለች በ2000 ዓ/ም ነበር በአሳዳጊዎቿ አማካኝነት ከአርባ ምንጭ ወደ አሜሪካ ያቀናችው።

ሀና ባለፈው የካቲት ወር 16ኛ ዓመት ልደቷን አክብራለች። ከቴክሳስ የሴቶች ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ በመመረቅ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ በዚህ ዕድሜ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘች ትንሿ ተማሪ ለመሆን በቅታለች።

ይኸው ዩኒቨርሲቲ ሀና የፒ ኤች ዲ ትምህርቷን እንድትከታተል የተቀበላት ሲሆን፣ ይህም ሀናን በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ትንሿ የፒ ኤች ዲ ተማሪ አድርጓታል።

ቤተሰቦቿ በቤት ውስጥ ያዘጋጁትን ስርዓተ ትምህርት ተከታትላ በሚኖሩበት ቴክሳስ ግዛት ስኬታማ ተማሪ መሆን የቻለችው ሀና፣ በልጅነቷ ወላጅ እናቷን ያሳጣትን የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ግንዛቤን ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋራ እየሠራች ትገኛለች።

በማህበረሰብ ሳይንስ ላይ አተኩራ መስራት የምትፈልገው ሀና፣ ሰው አዋቂ ሆኖ በመፈጠር ሳይሆን በርትቶ በመስራት ስኬትን ሊቀዳጅ እንደሚችል ከአሳዳጊዮቿ መማሯን ትገልጻለች።

ምንጭ:- ፎክስ ኒውስና ቪኦኤ አማርኛ

@ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰርቪስ
1. ስኬትህ የምታደርገው ነገር ነፀብራቅ ነው

ከቀደመው ማንነታችን የተሻልን ለመሆን ጥረት ባደረግን ቁጥር በዙሪያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ የተሻሉ መሆን ይጀምራሉ።

~ የተሻለ ሰው መሆንህ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ማለትም የአኗኗር ዘይቤህን፣ ቤተሰብህን፣ ጓደኞችህን፣ ማህበረሰብህን የሚጠቅም ተዘዋዋሪ ተጽእኖ ይፈጥራል።


2. የምናብ ሰው ሁን

" አለምን የማየው እንዲከሰት ከምፈልገው ነገር አንፃር እንጂ ከሚታየው ነገር አንፃር አይደለም።"

~ ሰዎች ዓለምን እንዳለች መቀበልን ቢመርጡ ኖሮ ታላላቅ ፈጠራዎች አይከሰቱም ነበር።

~ ታላላቅ ስኬቶች እና ፈጠራዎች ‘አይቻልም’ የሚል አስተሳሰብን ችላ በማለት ይጀምራሉ።

3. በራስህ መንገድ ላይ አተኩር

ሌሎች ሰዎች ተጽእኖ ሊያሳድሩብህ ይችላል፤ ነገር ግን የሌላ ሰው ህይወት መኖር ከጀመርክ ግራ የተጋባ ሰው ትሆናለህ።

~ ምክር መቀበል እና ከሌሎች መማር ምንም ችግር የለውም፣ ነገር ግን የምትሄድበት መንገድ ከአንተ ፍላጎት እና ዝንባሌ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ።

4. አሰልቺውን ተመሳሳይ ህይወት ስበረው

እያንዳንዱ ቀን ከቀጣዩ ቀን ጋር ተመሳሳይ በሚሆንበት ጊዜ ሰዎች በየቀኑ በሕይወታቸው ውስጥ የሚከናወኑትን መልካም ነገሮች ለይተው ማወቅ ስለሚያቅታቸው ነው።

~ ምስጋና በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ ጥሩውን የማግኘት ልምምድ ነው።

5. ፍርሃት ከሚያጋጥምህ ማንኛውም እንቅፋት የበለጠ ትልቅ እንቅፋት ነው።

~ ፍርሃትህን አትፍራው ብትፈራውም ከማድረግ አታፈግፍግ!

6. አሁንን ተቀበል
ሁልጊዜ አሁን ባለህ ነገር ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ።

~ ባለፈው መኖር እና ያለፈው ህይወትህ አንተን እንዲገልፅ መፍቀድ ወይም ስለወደፊቱ መጨነቅ ምንም ፋይዳ የለውም።

7. ወስን
አንድ ሰው ሲወስን፣ መጀመሪያ ውሳኔውን ሲወስን አያውቃቸው ወደነበሩ ቦታዎች የሚወስደው ኃይለኛ ፍሰት ውስጥ እየገባ ነው።

~ ድርጊት በውሳኔህ ላይ ከመተማመን የሚመነጭ ነው። አጥር ላይ መቀመጥ የትም አያደርስም። ስለዚህ ወስን! የውሳኔ ሰው ሁን!

8. ሁልጊዜ እርምጃ ውሰድ

" ለመማር አንድ መንገድ ብቻ ነው ያለው፤ ይህም ተግባር ብቻ ነው""

9. እንደገና መነሳትህን ቀጥል

" የሕይወት ምስጢር ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው።"
ምክንያቱም ስምንተኛው ጊዜ የአንተ ግኝት ሊሆን ይችላል።

ይህን #post ከወደዳችሁትና ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን ይዘን እንድንመጣ የምትፈልጉ ከሆነ #like #repost #copylink #share በማድረግ አብራችሁን መሆናችሁን አሳዩን 🙏🙏🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mXU7H3qlPB&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
#Urgent

Lighthouse Training and Consulting PLC is currently looking experianced trainers on International Financial Reporting Standards (IFRS). Please message us your full name and contact number as soon as possible through this 👉 https://www.tg-me.com/Lighthouse_Training_Center telegram address. Thanks
የሰው ልጅ ትናንት በበላው ብቻ ዛሬ አይኖርም፡፡ ትናንት አዲስ ብሎ የገዛው ጨርቅ ዛሬ ይሠለቸዋል፡፡ በአሮጌ ልብስ አይዘነጥም፡፡ ባረጀና ባፈጀ ሃሳብም ሕይወትን ማሳመር አይቻልም፡፡ ...

ሰው ተፈጥሮው በየሰዓቱና በየዕለቱ የሚታደስና የሚለወጥ በመሆኑ ዘወትር ግብዓት ይፈልጋል፡፡ ሆድ በሰዓቱ የሚፈልገውን ካላገኘ ጥያቄ ያነሳል፡፡ ጥያቄውን መመለስ የሚቻለው በጊዜው የሚፈልገውን ማቅረብ ሲቻል ነው፡፡ በርግጥ ሰው ምግብ ሳይበላ ለቀናት ሊቆይ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቆይታው የስቃይ ነው የሚሆነው፡፡ ምግብ ያላገኘ ሰው መላ ሰውነቱ ይደክማል፤ ማሰብ ያቅተዋል፤ በእጆቹ ሊሰራቸው የሚፈልጋቸውን ስራዎች በቀላሉ መስራት አይችልም፡፡ አቅም፣ ጉልበትና ብርታት ያጣል፡፡

የሰው ልጅ አዕምሮም እንደዛው ነው፡፡ በየቀኑ የሚፈልገውን አዲስ ሃሳብ፣ የተለየ መረጃና ዕውቀት ካላገኘ ይራባል፡፡ ማዕዱ ካልተሟላ ነፍስያው እንደተራበ፣ መንፈሱ እንደከሳ ዕድሜውን ይጨርሳል፡፡ ውስጣዊ ደስታው ይራቆታል፡፡ ማሰብ መመራመር፣ ነገሮችን አብጠርጥሮ ማወቅ አይችልም፡፡ አቅሙና ጉልበቱ ድሮ በተመገበው ሃሳብ ብቻ ይወሰናል፡፡ ወደፊት አሻግሮ ማየት ይሳነዋል፡፡ ጊዜውን የሚዋጅ ሃሳብ ያጣል፡፡ ከዘመኑ ጋር መስተካከል ያቅተዋል፡፡ ነፍስያው ይመነምናል፤ መንፈሱ ይከሳል፣ አዕምሮው ይደክማል፣ ሚዛኑ ይዋዥቃል፣ አስተውሎቱ ይጠብባል፣ አስተሳሰቡ ያንሳል፣ ዕይታው ይጭበረበራል፡፡

ዕውቀት የተራበ ጭንቅላት፤ ሃሳብ የታረዘ ሕሊና ለዓለሙ ያለው ምልከታ የተሳሳተ ይሆናል፡፡ ለፍረጃና ለጭፍን አመለካከት ይጋለጣል፡፡ በደረሰበትና በቆመበት የሃሳብ ሳጥን ብቻ ተወስኖ ሰፊውን ዓለም ሳይመረምርና ሳያውቅ በነሲብ ይደመድማል፡፡

አሜሪካዊው ደራሲ ሪቻርድ ራይት “Native son” በተባለ መፅሐፉ፡-

‹‹የሰው ልጅ ከእንጀራ የበለጠ ሊርበው የሚገባው ራሱን ወይም ማንነቱን ማወቅ ነው›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ራስን ማወቅ የዕውቀት መጀመሪያ ነው፡፡ ነገር ግን ራስን ለማወቅ ዓለሙንና አስተሳሰቡን፤ ውስጣውስጥ አመለካከቱን ጠንቅቆ ማወቅ ግድ ይላል፡፡

አለሙን ለማወቅ ደግሞ አዕምሮን በያይነቱ በሆነ መረጃ መመገብ ያስፈልጋል፡፡ መረጃውን በደንብ ማብላላትና የሚጠቅመውን መዋጥ፣ የማይጠቅመውን መትፋት ያሻል፡፡ ጥሩ የተመገበ በፊቱ እንደሚታወቀው ሁሉ በጥሩ ሃሳብ የተሞላ ጭንቅላትም በአኗኗሩ፣ በሕይወቱ፣ በሃሳቡና በተግባሩ ይታወቃል፡፡

አዎ! ሕሊና እንዲያድግ አዳዲስ ሃሳቦችን ዕለት ዕለት መመገብ ግድ ይላል፡፡ ትናንት ያስበብበት በነበረው መንገድ ብቻ እንዳይወሰን አዲስና ከቀድሞው የተለዩ መንገዶችን ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡ የሕይወት አቅጣጫውን ከወዲሁ እንዲያውቅ፣ የወደፊቱን ቀድሞ ይተነብይ ዘንድ እንዲችል ተራማጅ አዕምሮ ያስፈልገዋል፡፡ የትናንቱን እያዛመደ፣ የዛሬውን ሃሳብ እየፈተሸ የወደፊቱን መንገድ ማበጀት ግድ ይለዋል፡፡

ንጉስ ዳዊት፡-

‹‹በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ይሰበሰባሉ፡፡›› ይላል፡፡

እውነት ነው! ንጉስ ዳዊት ምናምንቴ የሚለውን ወደዚህ ዘመን ብናመጣው ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ራስወዳድነት፣ ማስመሰል ወዘተ ክፉ ነገሮች ሁሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዛሬ አብዛኛው ሰው ለዘረኝነትና ለገንዘብ ጣዖት እየሰገደ ነው፡፡ ለጣኦቱም የምስኪን ሕይወት እየተገበረለት ይገኛል፡፡

በዚህ ዘመን ጣኦቱ የበዛው ምናምንቴ አስተሳሰብ ስለበዛ ነው፡፡ አዎ ጭንቅላቱ የተራበ ሰው ለምናምንቴ ሃሳብ እጅ ይሰጣል፡፡ ለማይጠቅመው ያጎበድዳል፡፡ ራሱን የረሳ ጭንቅላት ህሊናውን በወጉ ያልመገበ ነው፡፡ ራሱን መመገብ ያቃተው ራሱን በራሱ ማስተዳደር ያልቻለ ነው፡፡

ለራሱ መሆን ያቃተው ጭንቅላት ለሌሎችም ሆነ ለዓለሙ ዕዳ ነው፡፡ የሌሎች ባሪያ እንጂ የራሱ ጌታ መሆን አይችልም፡፡ በነዱት የሚነዳ፤ ሲገፉት የሚገፋ ጋሪ ይሆናል፡፡

ሃሳብ ያነሰው አዕምሮ ባትሪው እንዳለቀ ስልክ ነው፡፡ በቁሙ ይተኛል እንጂ አይነቃም፤ ያለ ይመስላል እንጂ የለም፡፡ ቢቀሰቅሱት አይሰማም! ሃይል ጨርሷላ!

ወዳጄ ሆይ.... ዕለት ዕለት፣ በየጊዜው አንጎልህን በአዲስ ሃሳብ ቻርጅ አድርገው፡፡ ቀስ በቀስ አቅሙ እንዳይደክምና ሃይሉን እንዳይጨርስ ጭንቅላትህን አዲስ ዕውቀት ሙላው፡፡ ምናምንቴው ሃሳብ ህሊናህን እንዳይገዛ ጥሩ ጥሩውን መግበው፡፡

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ጭንቅላትህን በየጊዜው በአዲስ ሃሳብ/እይታ ቻርጅ ለማድረግ ፍላጎትህ ከሆነ ይህን ገፅ #follow በማድረግ ተከተለው!!!

ፅሁፉን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mXU7H3qlPB&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
2024/06/01 12:44:49
Back to Top
HTML Embed Code: