Telegram Web Link
ግጭቱን ፈርተው ወደ ሱዳን የገቡ ተፈናቃዮች ቁጥር ከ30 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለፀ

ወደ ሁለት ሳምንት ባስቆጠረው የፌደራል መንግሥትና ትግራይ ክልል ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሺህ እንደበለጠና ከቀን ወደ ቀንም እየጨመረ መሄዱን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ ዩኤንኤችሲአር አስታውቋል።

ግጭቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ መባባሱን የገለፁት በካርቱም የዩኤንኤችሲአር ድንገተኛ ምላሽ አስተባባሪ ጀንስ ሄዝማን ሁኔታውን "አስጊ ነው" ብለውታል።

በድንጋጤ የተዋጡና፣ እራፊ ጨርቅ ላያቸው ላይ ጣል ያደረጉና በፍርሃት የተሞሉ ተፈናቃዮች ወደ ሱዳን ያቀኑ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ታዳጊዎች እንደሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ኢትዮጵያ፣ ትግራይ ክልልና ሱዳንን የሚያዋስነው ድንበር የሚገቡ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች ሁኔታም እየተከታተሉ ያሉት አስተባባሪው ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ በምስራቃዊዋ የሱዳን ግዛት በሶስት ቦታዎች የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመር አሳሳቢም ነው ብለዋል።

በተለይም በሃምዳያት በኩል ከፍተኛ የሆኑ ተፈናቃዮች ቁጥርም እየተመዘገበ ነው፤ በየቀኑም "አስገራሚ" በሚባል ሁኔታም እየጨመረ መሆኑን አስተባባሪው ይናገራሉ።

በትናንትናው ዕለት፣ ህዳር 7/ 2013 ዓ.ም ብቻ 2 ሺህ 300 አዲስ ተፈናቃዮች ሱዳን ገብተዋል። ከትናንት በስቲያ እንዲሁም ከ 5 ሺህ በላይ አዲስ ተፈናቃዮች መግባታቸውንም አስተባባሪው አስረድተዋል።

@livlav
@livlav
34 የህወሃት የፋይናንስ ተቋማትን ማሳገዱን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።‼️

ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን ፣ ጉና የንግድ ስራዎች ፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው።

@livlav
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ‼️

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,778
• በበሽታው የተያዙ - 339
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 163

አጠቃላይ 103,395 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,588 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,293 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

320 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@livlav
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,871
• በበሽታው የተያዙ - 533
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 300

አጠቃላይ 103,928 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,601 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,593 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

305 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@livlav
#fact #animal

🐱 ድመት፤ በሕይወት ዘመኗ እስከ 100 ግልገሎች መውለድ ትችላለች!

💥 Adurreen, jiruu ishee kessatti ilmoolee hanga 100 ta'aan dahuu ni dandessi!

@livlav
ህወሃት የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ‼️

የኢዜአ ምንጮች እንደገለጹት፤ ቡድኑ በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ ይገኛል።

በዚህ ድርጊቱም ዘርፈ ብዙ ጥቅም እየሰጠ ይገኝ በነበረው የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት አድርሷል።

የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአየር ማረፊያ በ526 ሚሊዮን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ ነበር።

የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ስራ ማስተጓጎልን ጨምሮ በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።

በቱሪስቶች ዘንድ የሚያወቀው ይህ አየር ማረፊያ በቀንና በምሽት አገልግሎት የሚሰጥና የተሟላ እንደነበር ኢዜአ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@livlav
@livlav
ይህንን ያውቃሉ

👉እጁን እንዳነሳ የቀረው ሰው
ይህ ሰው የሂንዱ እምነት ተከታይ ነው፡፡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1973 ሳደሁ አማር ባራቲ የተባለ ግለሰብ የሂንዱ አምላክ ክብር ሲል ቀኝ እጁን አነሳ፤ ከዛን ቀን ጀምሮ ለአምላኩ ክብር ያነሳውን እጁን አላወረደም፡፡

@livlav
#FDREDefenseForce

ዛሬ መከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቐለ በሚወስደው መንገድ የምትገኘውን 'እዳጋ ሐሙስ' ከተማን መቆጣጠሩን አሳውቋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቐለ ለመያዝ እየገሠገሠ ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።

@livlav
#UPDATE

ሀገር መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከተማን እና በህግ የሚፈለጉትን የህወሓት ቡድን አባላትን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ስትራቴጂክ ቦታዎችን መያዙን አሳውቋል።

የትግራይ ክልል ህዝብ ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ ለመከላከያ ሰራዊት ወገንተኝነቱን አሳይቷል ብሏል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀውዜን ፣ አል ነጃሺ ፣ አዲቀየህ ፣ ማይመሳኖን እና ውቅሮን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አሳውቋል።

በአድዋ ግንባር የተንቀሳቀሰው መከላከያ ሰራዊት ሃውዜን ፣ አብርሃ ወአፅበሃንና ውቅሮን የተቆጣጠረ ሲሆን አጉላን በግማሽ ቀን መቆጣጠሩን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ አቅራቢያ ወደሚገኘው መሰቦ ተራራ እየገሰገሰ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ይህም መቐለ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው ጠቁሟል።

በሁለተኛው ግንባርም በአዲግራት በኩል ሳንቀጣ እና አልነጃሺን በመቆጣጠር ውቅሮ መግባቱን ገልጿል።

* ዝርዝር መረጃው (በኢዜአ) ከላይ ተያይዟል።

@livlav
የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለጸ !

በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

#MoSHE ከአንድ (1) ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን 3 የትምህርት ሴሜስተር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ለኢቲቪ ገልጿል።

@livlav
🎉🎉 ልክ በዛሬዋ ቀን ከ121 አመት በፊት የስፔኑ ሀያል ክለብ ባርሴሎና ተመሰረተ።

HAPPY BIRTHDAY BARCELONA

@livlav
#Live

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ጠ/ሚ ዐቢይ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በኩል በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

@livlav
የአርሰናል ቀጣይ 6 ጨዋታዎች!

ቶትንሀም ከሜዳ ዉጪ
ዱንዳልክ ከሜዳ ዉጪ
ባርንሌይ በሜዳ
ሳዉዝአምፕን በሜዳ
ኤቨርተን ከሜዳ ዉጪ
ማን.ሲቲ በሜዳ
ቼልሲ በሜዳ

@livlav
#UPDATE

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ "ተመራቂ ተማሪዎች" ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ሪፖርት ያላደረጉ ተመራቂ ተማሪዎች ህዳር 24 እና ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ/ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

@livlav

ሼር ለሁሉም ይድረስ
ሰበር ዜና‼️

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ክልል መረጋጋት እስኪፈጠር እና የኢንተርኔት አገልግሎት እስኪመለስ ይቆያል

ሆኖም በሌሎች አካባቢዎች ያላችሁ ተማሪዎች ዝግጅታቹን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን::



            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗


@livlav
💥ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ‼️

#ለ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

በሃገራችን በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው ትምህርት እንዱቀጥል መወሰኑን ምክንያት በማድረግ ህዳር 24 እና 25 የመግቢያ ቀን መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።



            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗


@livlav
#ሀሰተኛ_መረጃ

"ሱዳን ፖስት" የተባለ ድረ-ገጽ ደቡብ ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለማባረሯ እና ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ በሚገኙ የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ስለመውሰዷ በትናንትናው እለት አስነብቧል።

ሱዳን ፖስት ያሰራጨው መረጃ "ውሸት" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኢትዮጵያ ቼክ ዛሬ ጠዋት አረጋግጠዋል።

የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ተመሳሳይ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን "ይህ ፍፁም ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ነገር አልነበረም፣ ሆን ተብሎ ሀገራቱን ለማጋጨት የሚደረግ ሴራ ነው" ብሏል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ቼክ
@livlav

ሼር ሼር
አርሰናል እንዳረጋገጠው ከሆነ ቶማስ ፓርቴይ ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ እና በርከት ያሉ ጨዋታዎች እንደሚያመልጡት አረጋግጠዋል።

ለአርቴታ ሌላ ከባድ ራስ ምታት !!!

@livlav
ትላንት ምሽት ሜሲ ጎሏን ካስቆጠረ በሆላ ማስታወሻነቷን ለማራዶና ባሰጠበት አጋጣሚ ቢጫ ያሳዬት ዳኛ ከጨዋታው በሆላ :

" ቢጫ ካርዱን ለማውጣት ወደ ኋላ ኪሴ ስገባ ልቤ በጣም ነው የታመመው, እኔ እንደማስበው ከሆነ ለእንደዚህ አይነት ክስተቶች ፊፋ ልዬ የሆነ ህግ ማውጣት አለበት ተጨዋቾች ማህበረሰባቸውን ለመደገፍ ለታላላቅ ኮዋክብቶች ሀዘናቸውን ለመግለፅ እንደዚህ አይነት የደስታ አገላለፆችን ሲጠቀሙ ያለ ቢጫ በዝምታ ሊታለፉ የሚገቡበት ህግ ሊኖር ይገባል, እኔ ስራዬን እየሰራው ነው ነገር ግን ያን በማድረጌ በጣም ሀዘን ተሰምቶኛል ማራዶና የምንጊዜውም ምርጡ እግር ኳስ ተጨዋች ነበር, ፊፋ እና ላሊጋ ይህንን ህግ እንደሚያስወጡት ተስፋ አደርጋለሁ."

"SHARE

@livlav
2024/05/09 04:47:43
Back to Top
HTML Embed Code: