ስንቴ ነው ? 🤔

እኔን ባቀፍክበት በሳቅንበት ቦታ
በተላፋንበት በዛች ውብ ትዝታ
በዛ ውብ በሆነው በዛ በሔድንበት
ስንቴ ነው ከሷ ጋር የተራመድክበት
ስንቴ ነው🤔 ስንቴ ነው ?
በሳቅንበት ቦታ ከሷ የተኛኸው
ስንቴ ነው ንገረኝ
ስንቴ ነው ስትዋሸኝ ፍቅርህ ያሳዋረኝ
ስንቴ ነው ጉዴን ልስማ
አኩርፌህ እያለ ወጥተን ከዛ ማማ
ይቅር ያልኩበትን ያልካት እሷን ማማ
ስንቴ ነው ስንቴ ነው
በተፋቀርንበት እሷን ያዝናናኸው
ስንቴ ነው ?😔

ሜሮን ገነነ
@buchula36

28/11/2014
*መልካም ልደት*

🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
ወደዚኛው ዓለም ስትመጪ ያን ዕለት፣
ዙሪያሽ ያለው ሲስቅ እልል ሲባልለት፣
አንቺን ለመቀበል የሽር ጉድ አይነት፣
ባላወቅሽው ምድር ሆነሽ እንደ ንግስት፣
🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
አንቺ ግን፣

አንቺ ግን ውድዬ ታለቅሺ ነበረ፣
ከሳቃቸው ጋራ ሳቅሽ አላበረ፣
ከደስታቸው ጋራ ደስታሽ አላደረ፣
አንደበትሽ ከፍቶ ድልን አልዘመረ፣
🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
ያቺም ቀን ዛሬ ናት፣
የተወለድሽባት፣
እቺን ዓለም በዕንባ የተቀበልሽባት፣
🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
እናምልሽ ውዴ፣

ከብርም ያማረ ከዕንቁ የላቀ፣
ዘመንን ተመኘሁ ልቤ አንቺን መረቀ፣
🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
ኑሪ ብዙ ዓመት እንደ ማቱሳላ፣
ይባረክ ዘመንሽ ያሰብሽውም ይሙላ፣
ሀዘን ካንቺ ይራቅ ይሸልምሽ ተድላ፣
🎂🎂❤️🍫🍫🍬🍬🍭🍭
እንደ እንግዳ ሆነሽ ምድርን ያየሽሻት፣
በእንባ በለቅሶ የተቀላቀልሻት፣
በዛሬዋ ቀን ነው በደስታ አክብሪያት፣
እንኳንም ተወለድሽ ውዴ መልካም ልደት፣
To sofi....yaki
በወደቅሽ ቁጥር የእንባ ትርፉ ሌላ ህመም መምዘዝ እንደሆነ እወቂ. . .
ትከሻን ማቅናት እድሜ ከመቁጠር ወደ መኖር የሚታደግበት ሀ ሁ ነው። ለሙሾ ወራጆች ተፈጥሮ ሁሌም ለቅሶ አታጣም . . .
    ለእንባሽ    ፊት     አትስጪው.. . .

#mis_s. . .🍂
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••                          
         ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
      ━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ጥሩ ጓደኛ ልክ እንደ መስታወት እና ጥላ ነው መስታወት አይዋሽም ጥላ መቼም ትቶ አይሄድም !
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                     :¨·.·¨:
                 🌺 እኔ እና እሷ🌹
              ┈┈••◉❖◉●••        
           ••●◉Join us share◉●••                   
          ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
   ━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
🦋🦋
  መውደድ ስለጋረደው  ልብሽ እናውጋ እስኪ?. . .
የትኛው የትእግስት ጥበብሽ ነው እንዳሻቸው እየሆኑብሽ ካለነሱ ያስባለሽ? ....የትኛው ጥንካሬሽ ነው ለሺ በደሎቻቸው ይቅርታን በነፃ የሚያሳድልሽ?. .  .  የቱስ የተለየ ቃል ይዞሽ ነው አንዱን ቃላቸውን ሚሊዮን ጊዜ እያጠፉ ለአንዱ ቃልሽ ፀንቶ ያስኖረሽ?? ምንስ ይሆን እንዲ በተስፋ የሞላሽ? 
... . . ብቻ ምንም ይሁን ያለፍሽባቸውን መንገዶች አቅልዬ በቃሽ አልልሽም ግን ዛሬሽን ልብ በይ ያለሽን አስተውይ ምናልባት ያጣሽው ከሚመስልሽ በላይ ያለሽ ይበልጥ ይሆናል. . . . እንደዛ ይሰማኛል...🦋

🦋🦋 #. . .
Remedan keriiiiiiiim wendim ihitoche❤️❤️❤️❤️❤️❤️👍👍👍👍👍👍🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••                          
         ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
      ━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
🦋🌷....ህይወት ብዙ ነገር ታስተምረናለች መቻልን..ወድቆ መነሳትን...አልቅሶ መሳቅን...አግኝቶ ማጣትን..ወዶ መለየትን..........ሁሉም ከባድ ነገር ሲጀመር የሚያቅተን የማንችለው የማይረሳ መስሎን ነበር...ግን ቀስ በቀስ የተቀደደው ገፅ በአዲስ ገፆች እየተተካ ያዘንበትና ልባችንን የሰበረው ታሪክ በእርሳስ እንደተፃፈና በላጲስ እንደሚጠፋ ፅሁፍ ሙልጭ ብሎ ሲተን እናስተውላለን .. አንድ ቀን ላይም የማንንም እጅ ሳንይዝ ደስተኛ እንሆናለን.....
     🌛🌜 
      #.....

┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
             ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••    
            ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
🦋💐...
የፌሽታሽ 'ለት አቶስቷሹ
የደስታሽ ቀን ሳቅ ቀዳሹ
አይገኝም በእንባሽ ጊዜ
ይተውሻል ለኑዛዜ
ይሸጥሻል ምሬት ስሞ
አያይሽም ላፍታ ቁሞ

እውነት ስልሽ
ስትወድቂ ነው ሰው ሚርቅሽ
ስታጪ ነው ሰው ሚሸሽ

ልብ በይ
ከሐዘንሽ ነው አዳም መቅዳት
ጽልመት ሚገፍ እንደ ንጋት
ከውድቀት ነው ባልን ማፈስ
ሚሳለሙት እንደ መቅደስ


┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
             ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••    
            ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ  እንዳይመስላትና  ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ  ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ 👋

«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»  😊

አላህ ከ እናቶቻቹ እቅፍ አያርቃችሁ።
©️
#Ramadan_28
اللهم تقبل صيامنا ، وقيامنا 🙏🙏

🧢Yaki
  
. . .ቀንህን ስትጀምር ለተሰጠህ እድል አመስግነህ ጀምር .....የዛሬዋን ጀምበር ማየትህ ለነገዋ ዋስትና አይሆንህም.... በማማረር ብቻ እድሜህን አትጨርሰው!! ትላንት በምእራብ የገባችው ፀሀይ በምእራብ አትወጣም!! ሁሉም ነገር ላይ ያለውን ለውጥ ተመልከት... ካልተሳኩልህ ነገሮች ጀርባ ያሉትን አቅጣጫዎች ልብ በል!! ተመሳሳይ አቅጣጫን እየተጠቀምክ ከሆነ መውጫውን ቀይረህ ሞክረው!. . .

አይመስህልም??
                          .  ..
     #.....
..🧚‍♀🧚‍♀

ሂጂ እስኪ..... እግርሽን ብቻ ለመራመድ አትጠቀሚው.... ባታውቂው ነው እንጂ ልብም እኮ ይሄዳል..... ልብሽን ራቅ በይበት.... ከሚያሳዝኑሽ . . . ከሚያከስሙሽ. . .ከሚሸኑቁሩሽ . . . ከሚያደሙሽ. . .ሁሉ ወደራስሽ. . .ወደውስጥሽ. . . ከልብሽ. . ወደልብሽ. . .ሂጂበት. . .ተሸሸጊበት. . .


  . . .
          🧚‍♀🧚‍♀
    #.....
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
              ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••    
            ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ልብን እንደ መሰጠት መልሶ መቀበልም ቀላል ቢሆን ኖሮ😔 ልቦች ባልተሰበሩ ነበር አይኖችም ባላነቡ ነበር ምሽቶች የሀዘን ማራገፊያ ባልሆኑ ነበር💔
Abi...
  
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••                          
         ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
         
. . . .እዳው ተችሎ ነው ሰው የሚወደደው......
 
   #Mis_s.. 🥀
🍁🌹....
ለአንዳንድ ሰዎች ፍቅር ማለት አፍቅሬሻለው ስትላቸው እኔም ብሎ መመለስ ብቻ ይመስላቸዋል።


┄┄┄┄┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ተስፋ ከእምነት ከተሰራ፣
ያሻግራል ከመከራ፤


    ┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••                       
         ❤️ @Lovers_Zonn
      ━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉--Leo_07--◉
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
ስለራሳችን ነን ብለን የምናስበውን ብንሆን የተሻለ ማንነት ይኖረን ነበር . . . .

#Mis_s..
ቅኔ ነው ትዝታ..
...
"መተው" መዳኛ ነው ....
...ተመልከት..

ባህር ላይ የወደቁት
ትተው ስለናቁት
እየዋኙ ወጡ...
ባህሩን የታገሉት
እያዩ ሰመጡ. . .

#.... 🥀
Abi
ያጣናቸው ሰዎች ከላያችን ላይ ቦጭቀው የሚወስዱብን ነገር አለ።በመሄዳቸው ያጎሉብናል። እነዚህ ጉድለቶች ቀን በገፋ ቁጥር ልብ ላይ ዘልቀው የሚፈጥሩት ህመም በቀላሉ አይሽርም። ወደ ውስጥ በተመለከትን ቁጥር ጎዶሎነታችን ላይ የምንደርስበት ሰዎች አለን። በራሱ ጨለማ ተውጦ የማያውቅ ማነው?.... አመታት ቢያልፉም እንደ አዲስ የምናለቅስለት ሰው አናጣም። ይህ ስቃያችን በጎጇችን ሰላም፤ በመኝታችን ደግሞ እንቅልፍ ይከለክለናል ....

ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?

    ┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
                    :¨·.·¨:
                 🌺 እኔ እና እሷ🌹
                 ┈┈••◉❖◉●••        
          ••●◉Join us share◉●••                       
         ❤️ @Lovers_Zonn ❤️
      ━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
                 ◉--Leo_07--◉
                  ◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
በደረትህ ላይ ከባድ ስሜት እንዳለ ለጓደኞችህ እና ለቤተሰብህ ማስረዳት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንነጋገር . . .?

┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
:¨·.·¨:
🌺 እኔ እና እሷ🌹
┈┈••◉❖◉●••
••●◉Join us share◉●••
❤️ @Lovers_Zonn ❤️
━━━━━✦✿🌹✿✦━━━━━━━
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
◉--ᴀʙɪ-ʙᴀʙᴀ--◉
◦◦✧✢🍁✢✧◦◦
2024/05/29 03:39:52
Back to Top
HTML Embed Code: