Telegram Web Link
ከምነግርህ ይልቅ የማልነግርህ ብዙ ነገር አለ🥀
💞💞💞💞💞💞💞💞
@loverzonn
 
ሰዎች ባንተ ውስጥ
በጣም ሊወዱት የሚችሉት ነገር

የልብህን ጥሩነት ነው‥ ነገር ግን
ጥሩ ልብ ምን ያህል እንደሚጎዳ

አይገባቸውም ።😢😢
‌‌‌
💞💞💞💞💞💞💞💞💞

@loverzonn
ከኩርፊያህ ጀርባ ስላለው እውነት ፣ ከሳቅህ ጀርባ ስላለው እንባና ብሶት ፣

ካልተናገርካቸው ንግግሮች ጀርባ ስላለው የታመቀ ስሜትህ ። ድንገት

ከአይን ስጠፋ ከመጥፋትህ ባሻገር ስላለው የሂዎት ውጣ ውረድህ

የሚረዳህ ሰው አለ ?🤔 በቃ አንተ እድለኛ ነክ 🙏
💞💞💞💞💞💞💞💞
@loverzonn
ምን አልባት

መናገር የምትፈልጋቸውን ነገሮች

መናገር በማትፈልጋቸው ነገሮች ተደብቀው ቢሆንስ😔

💞💞💞💞💞💞💞💞
@loverzonn
 
❤️. . . ሴት ልጅ 3 ነገር ያለውን
ወንድ ትወዳለች ...
1⃣ ያለሷ የማያይ አይን ያለው...
2⃣ ክህደት የማያውቅ ልብ ያለው እና...
3⃣ ሁሌም የሚያሞግሳት...
💞💞💞💞💞💞💞

@loverzonn


💞#ፍቅር💞

" ሁሉም ጥያቄዎች ብዙ ምላሾች
ሊኞራቸው ይችላል፤ ነገር ግን
የብቸኝነት ብቸኛ ምላሽ
ፍቅር ብቻ ነው። "



💞#ፍቅር💞

" ሁሉም ጥያቄዎች ብዙ ምላሾች
ሊኞራቸው ይችላል፤ ነገር ግን
የብቸኝነት ብቸኛ ምላሽ
ፍቅር ብቻ ነው። "
@loverzonn
😘የቆንጆዋ ጦስ😘

🔥ክፍል 15


.
.
.
ሀኒ ምንድነው እየደማሽ ነውኮ አልኩ በመጮህ ደንግጨ ነበር እሷ ግን ፍፁም መረጋጋት በሞላበት ሁኔታ ነስር ነው አንዳንዴ እንዲህ ይመጣበታል አለች ጎኗ ካለ ፖርሳዋ ሶፍት እያወጣች የመጅልሲ ትራስ ላይ እራሷን አስደግፌላት ውሀ እና ማስታጠቢያ ላመጣ ሄድኩ ከዛም የሀኒን የደማ አፍንጫ በሶፍትና በውሀ ተጋግዘን አፀዳነው ደሙም ምንም ያህል አልቆየም ወዲያው አቆመላት እና በአዲስ መንፈስ ተረጋግታ ቁጭ አለች አስደነገጥሽኝኮ አልኳት ግንባሯን እየሳምኳት ነስር አለብኝ ግን እየቆየም ቢሆን የሚመጣው ብዙውን ግዜ የሚያነስረኝ በተኛሁበት ነው ቀን ላይ ግን አያቀኝም ነበር የኔ አሳቢ አለች በል አሁን ጆሮየን አቁሜ የንተን እና የቤተሰብህን ታሪክ ለመስማት እየጠበኩ ነው ምንድነው ማረሳሳት አለችኝ ኧረ ምን ቼገረሽ ያው እኔ ከዚ በፊት የሚነገር ታሪክ የለኝም ታሪኬ የሚጀምረው አንቺን ካገኜሁበት ሰአት ጀምሮ ነው ስለቤተሰቡ ግን ልንገርሽ ቆይ እንደውም በደምብ ግልፅ እንዲሆንልሽ በፎቶ የታገዘ ገለፃ ላድርግልሽ አልኳትና ከቴሌቪዥን ማስቀመጫ ስር ያለውን አልበም ወደኛ አቀረብኩትና ቤተሰቤን ለሀኒ ማስተዋወቅ ጀመርኩ
እኔ ለቤተሰቤ ሶስተኛ ልጅ እንደሆንኩና ከኔ በላይ አንድ ትልቅ ወንድም እንዳለኝ ከኔ በታች ደግሞ ያለችው አሁን የየሻት እህታችን ናት አልኳት የሆነ የበአል እለት እኔ ትልቁ ወንድሜና እህቴ ሆነን የተነሳነውን ፎቶ እያሳየኋት ወንድምህም እንደ እናንተ ቆንጆ ነው አለችኝ ሃኒ በፈገግታ
ቀጠልኩና አዎ ያኔ ቁንጅና ሲታደል የኛ ቤተሰብ የመጀመሪያ ሰልፍላይ ከፊት ተሰልፎ እንደነበር አያቴ አውርታኛለች አልኳት አብረን ሁለታችንም ሳቅን ,, ቀጠልኩናም እናቴና አባቴ አብረውን ያሉበትን ፎቶ እያሳየኋት እነዚህ ደግሞ እኛን የመሰሉ ቆንጆዎን ወደዚች ምድር ያመጡን እናትና አባትችን ናቸው። ከዛሬ ስድስት አመት በፊት ነበር የተለያዩት
እያልኩ ሃኒ በመሃል ገብታ በጣም አዝናለው አለችኝ ፊቷን ሳየው መረበሿ ይስተዋልባታል
ምንአልባት የሷም ቤተሰብ ልክ እደኛው አይነት ስለሆነ ስሜቱ ተጋብቶባት እንደ ሆነ ገምቻለው በጣም የሚገርመው ግን የኔ የቤተሰብ መለያየት አባዜ ምክኒያቱ ይለያይ ይሆናል እንጂ የብዙ ቤተሰቦችን ጓዳ ያንኳኳ ጉዳይ ነው የኛ እንኳ ትልቅ ከሆንን እና ክፉ ደጉን ከለየን የሆነ ነው አንዳንዶች ግን ገና በልጅነታቸው በእናትና በአባት መለያየት ኑሯቸው ብልሽትሽት ብሎ አንዴ በእናት ናፍቆት ሌላ ግዜ ደግሞ በአባት ናፍቆት እየተሰቃዩ በጨቅላነታቸው ማግኘት ያለባቸውን የቤተሰብ ፍቅር ሳያገኙ ያድጋሉ
ያ ነገር ከፍ እያሉ ሲመጡ ውስጣቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦና ጫና ፈጥሮባቸው ከማህበረሰቡ እራሳቸውን አግልለው የብቸኝነት ሂይወት የሚገፉ እልፍ ናቸው እናትም አባታችሁም አሁንም አብረዋችሁ ያላችሁ የእውነት በጣም እድለኛ ናችው
ግን በምን ምክኒያት ነው የተለያዩት ስትል ከሃሳቤ መለሰችኝ በትዝታ የኋሊት ገሰገስኩና አስታወስኩ ያኔ አባቴ በፈቃድ ጅዳ እየተመላለሰ አልባሳትን እና ሽቶዎችን እንዲሁም የ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በማምጣት የንግድ ስራዎችን ነበር የሚሰራው እዛ በሚሄድበት ግዜ አስራአምስት ቀን ገፋ ካለም አንድ ወር እየቆየ ነበር የሚመጣው ይህ ሲሆን ለካ አባቴ በስራ ምክኒያት ካወቃት መኖሪያዋን እዛው ካደረገች ኢትዮጵያዊት ጋር ጉዳይ ጀምሮ ነበር ይሄንን ማናችንም የምናውቀው ነገር አልነበረም ቆይቶ ግን እዛው ባሉ ዘመዶች አማካኝነት ወሬው እናቴ ጆሮ ይደርሳል ከዛ በኋላ ነው ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በሽማግሌ በዘመድ አዝማድ ብትለመን በአንገቴ ገመድ ይግባ ብላ በቃሏ ጸናች አባቴ ሁለት ሚስት የማግባት ፍላጎት እንደ ነበረው ሁላችንም ብናውቅም እንደዚህ በተደባበቀ መልኩ ያደርገዋል የሚል ለአንድም ቀን ጠርጥረን አናውቅም በቃ ሁሉም ያኔ አለቀ ከተለያዩ በኋላ እናቴ አዲስ አበባ ካለች እህቷ ጋር ለኛ ደግሞ አክስታችን ማለት ነው ከሷ ጋር በጋራ ግዙፍ የሚባል ሱፐርማርኬት ከፍተው መስራት ጀመሩ አባቴም ነገር ቁርጡ ከለየለት በኋላ ከዛችኛዋ ጋር አምርሮ መኖር ጀመረ ከዛም ከእህቴና ከወንድሜ ጋር በሰራተኛ መኖር ጀመርን ብዙም ሳይቆይ ትልቁ ወንድሜ በስራ ምክኒያት ወደ ሌላ ሀገር ተዘዋወረ
ከዛም ይኸው እኔና እህቴ አብረን እንኖራለን
አልፎ አልፎና አመት በዓል ሲመጣ አባታችን ቤት እንሔዳለን ከዛ ውጭ ግን በቃ ደስተኞች ነን ያው አንዳንዴ የሆኑ የሆኑ ነገሮች ያለፈውን ሲያስታውሱሽ ትንሽም ቢሆን መከፋት ቢኖረውም ማለት ነው አልኳት አልበሙን እየዘጋሁ እናትህ ለራሱ ገና ወጣት አይደለች እንዴ አለችኝ በመገረም አይነት ኧረ እንደውም አዲስ አበባ ከገባች በኋላ ፋዘርን ለማስቀናት ነው መሰል በጣም በተለየ መልኩ እራሷን እየጠበቀች ዳግም ፍንዳታ ሆናልኛለች ተሳሳቅን, , በዚህ መልኩ የማስተዋወቅ ስራዬን ጨርሼ ከኛ ቤት ወጥተን ትንሽ ወክ ካደረግን በኋላ ሃኒን ወደ ቤቷ ሸኝቻት ወደ ቤት ተመለስኩ።
እቤት ስገባ ሀዩ ቤት ተቀምጠው ነበር
የውሃ ማስጣጠቢያው ላይ የነበረውን ደም የነካ ሶፍት አይታ ምንድንነው ይሄ ጉድ አለቺኝ
ሃኒን ነስሯት እደሆነ ነገርኳት ከዚህ በፊት ፖስታው ላይ የነበረውን ነገር ነግሬያት ስለነበር ከህመሟ ጋር አስተያይታው ኖሮ በጣም ደንግጣ እንደ ነበር ነገረቺኝ ለካ እህቴ የትናንቱን ተሪክ አልሰማችም ሁሉንም ዘርዝሬ ለእህቴም ለሀዩም አወራሁላቸው ደብዳቤው ላይ የነበረው የህክምና ውጤት የጓደኛዋ እንደ ነበርና እሷም ከሞተች እንደቆየች ሃኒም ከደብረዘይት አባቷን ትታ የመጣችው በጓደኛዋ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ድርሰት አዘጋጅታ መታሰቢያነቱ ለጓደኛዋ ገቢው ደግሞ ለጓደኛዋ እናት የሚሆን ፊልም ለማዘጋጀት እንደመጣች ጨምሬ አወራሁላቸው። እና በቃ ግንኙነታቹ ፀደቀ ማለት ነው አለችኝ እህቴ በጥያቄ ቃና ሀዩ ፊቷን ክስክስ አድርጋው ከተቀመጠችበት ተነሳችና ምንም ሳትል ወጣች ምን ሆናነው ሀዩ? እህቴን ጠየኳት ኧረ እኔንጃ ብላኝ ሀዩ በወጣችበት በኩል ተከትላት ወጣች
ቀናቶች በቀናት ሳምንታት በሳምንት እየተተኩ በመክነፍ ላይ ናቸው እኔና ሃኒም ፍቅራችን ጨምሯል ቶሎ ቶሎ እንገናኛለን በጓደኛዋ ዙሪያ ያለው ድርሰትም እየጻፍን ከመቋጫው ላይ አደረስነው ያው ሃኒም የአርት ተማሪ ስለነበረች ምንም ያህል ሳያስቸግራት ነበር በጥሩ ሁኔታ ተጽፎ የተገባደደው አንድ እሁድ ቀን ሃኒ ምሳ እየጋበዘችኝ ድንገት አንድ ሰርፕራይዝ አለኝ አለችኝ ምንድንነው እሱ የኔ ጥያቄ ነበር የድርሰቱን መጠናቀቅ ምክኒያት በማድረግ አባቴ ጋር ከመመለሴ በፊት ሙሉ ወጪውን ሸፍኜ የአንድ ሳምንት የባህርዳር የጉብኝት እንዲኖረን ፈልጌያለው አለችኝ መልሴን ለመስማት እንደ ጓጓች ከፊቷ ላይ ያስታውቃል በጣም ነበር ሀሳቡን የወደድኩት ባህርዳርን ከዚህ በፊት ሂጄባት ባላውቅም በወሬ ደረጃ ግን ብዙ ብዙ ሰምቼላታለው በዛላይ ደግሞ ከሃኒ ጋር ታየኝ ካሁኑ የትም ይመቸኛል አልኩ በውስጤ
እ... ምን ታስባለህ አለች ሃኒ ዝምታዬን አስተውላ በደስታ እንደተስማማሁ ገለጽኩላት እና ከሶስት ቀናት በኋላ የመኪና ኪራይ አመቻችተን ልንሄድ ተስማምተን ጨረስን በቀሩት ሶስት ቀናቶች ውስጥ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በሙሉ ከውነን ጉዞ ወደ ውቢቷ ባህርዳር ተጀመረ •••

ይቀጥላል

✎ ክፍል 1⃣6⃣ ይቀጥላል...
@loverzon
@loverzonn
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
​​❥⚘⚘..........👇💘

ድምፅሽ ሲርቅ ከጆሮዬ
መጠውለጉን ባየሽልኝ
ያ ገራገር ሰውነቴ
እየራበኝ ሳቅ ጨዋታሽ
አስጨነቀኝ በዝምታሽ
አንቺን የለመደው ቤቴ
ካለሽበት ሰማይ ማዶ
ባሳብ ሲዋኝ ልቤ ነዶ
ሲቀጣጠል አንቺን ወዶ
አይንሽን ላይ ጓጉቻለሁ
ደጀሠላም ውዬ አድራለሁ
ቀን ከለሊት አነባለሁ😢።።

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
መስሎኝ ብታይ
ወድጄሽ ከራሴ
በላይ አልሆን ብሎኝ
ያነንቺስ ጉዳይ ፍቅር
ብሰጥ ሰጠሽኝ ስቃይ🥀

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
ሀሳብ…

የሰው ልጅ ያስባል። ነገር ግን እያሰበ እማያስባቸው ብዙ ነገሮች አሉ በማሰብ ውስጥ የማይታሰቡ ሀሳቦችም ማለት ነው። ሀሳብንም እንደ ሀሳብ በሁለት ልንከፍለው እንችላለን ፈልገን እና ሳንፈልግ የምናስበው ሀሳብ ነው።

ሁሉም ሀሳቦች እውነት ናቸው ወይንም ትርጉም አላቸው ማለት አደለም… ሀሳብ /ትርጉም/ የሌላቸው ሀሳቦችም አሉ ማለትም ምን እያሰብን እንደሆነ ሳናውቅ የምናስበው ማለት ነው።

አሁን ለምሳሌ እሱ (እኔ) ምን አስቦ ነው ይህን የፅፈው ልትል ትችል ይሆናል… ይሄ ሀሳብህ ልክ ነው!… ምን አስቤ እንደፃፍኩት የምታውቀው የኔን ሀሳብ ስታቅ ነው… አየህ ይሄ ሀሳብ ደሞ የሌላ ሰው ሀሳብን የሚጠይቅ ሀሳብ ነው ማለት ነው።

አንድ ሀሳብ በውስጡ ብዙ ሌላ ትናንሽ ሀሳቦች አሉት…መሰረታዊው ነገር ግን ይሄ ነው " የሰው ልጅ ያስባል እሚያስበው ግን አንድ አይነት ሀሳብ ነው ማለት አደለም እንደፊታችን ሀሳባችን እና አስተሳሰባችንም ይለያያል ማለት ነው።"

በመጨረሻም አለማሰብ አይቻልም ሳንፈልግ ማሰባችን አይቀርም… ማስብ ጥቅም አለው… ማሰብ ስንጀምር እራሳችንን ማወቅ እንጀምራለን ፣ እሚያስፈልገንን ከምንፈልገው እንለያለን።
ስናይ ሰንበት 🙏
       ┉┉✽‌»‌»‌✽‌┉┉
            
         ╔══❖••❖══╗
           ❤️
#LOVER ZONE ❤️

        ▫️COMMENT💌 SHARE▫️


   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒🔛@loverzonn

       
አደራ የኔ ፍቅር ይህንን መልእክት እንዳትረሳ ......
ለልብህ እንዲህ በልህ ንገርልኝ ....
ካንተ ውጭ የማይይ አንተን አጥቶ መኖር የማይችል ....
ዘላለም እየወደደህ ላንተ ብቻ የሚኖር 1 ሰው አለ በልልኝ ....🌹

የኔ ባል አፈቅርሃለው
@loverzonn
💖 💖

🙅‍♀አልዋሽህም ማፍቀሬን አልጠላም❤️አንተን ማፍቀሬን ግን በጣም ጠላዋለው ሰው አይደለው ማፍቀር እንጂ ማፈቅረውን መምረጥ አልችልም😢 ነግሬህ የለ መምረጥ ብችል ኖሮ ደስ እያለኝ አላፈቅርህም💔 ነበር😔
@loverzonn
😘የቆንጆዋ ጦስ😘

🔥ክፍል 16


.
.
#ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ይቀረዋል
.
.

የመንገዳችን አቅጣጫ ያደረግነው ከደሴ በመነሳት በምእራብ ወረዳ በመካነ ሰላም በኩል ነበር እኔና ሀኒም የፍቅር ወጋችንን እየሰለቅን መርጦ ለማሪያም ፣ ግንደ ወይን፣ ከዛም ሞጣ እና አዴት የሚባሉ ከተሞቼን አንድ አንድ እያልን አልፈን በፅዳቷ የከተሞች ቁንጮ በመበል ከምትታወቀው የጣና ሀይቅ
መናገሻ ከሆነችው ውቢቷ ባህር ዳር ገባን እነዚህን እና ሌሎች ትናንሽ የከተማ ስሞችን ለማወቅ የቻልኩት በሀኒ አማካኝነት ነበር ,,
እውነትም ባህርዳር በወሬ እንደሰማሁላት ፅዱ ከተማ ናት በተለይ በመንገዶች መሀል በእንክብካቤ የተያዙት ዘንባባዎች ከተማዋን የተለየ ውበት አላብሰዋታል ማረፊያ ሆቴላችን ይዘን ጓዛችንን ካስቀመጥን በኻላ ፍሬሽ አሳችንን እና እጅ የሚያስቆረጥም ሽሯችንን እያጣጣምን ጉብኝታችንን ጀመርን
ባህርዳር ካሳለፍናቸው ቆይታዎች ውስጥ ብዙውን ምሽት ማለት ይቻላል ያሳለፍነው በባህል ምሽት ቤቶች ውስጥ ነበር ባህርዳር ከምትታወቅባቸው ብዙ ነገሮቿ ውስጥ አንዱ በባህል ምሽት ቤቶች ነው እኔና ሃኒም ቀን ቀን በተከራያናት ቪትዝ መኪና እና አንዳንዴም የከተማውን ባጃጆች በመጠቀም ስንዞር እንውልና መሸትሸት ሲል ወደ ባህል ምሽት ቤቱ ጎራ እንላለን የባህል ምሽት ቤቱ ባላገሩ ይሰኛል ከመግቢያው ጀምሮ ያለው የመስተንግዶ አቀባበል እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ደግሞ በኢትዮጵያ የባህላዊ መገልገያ እቃዎች በልዩ መልኩ ተውቦና አምሮ ይቀበልዎታል የቤቱ ማዓዘናት ላይ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ የምንላቸው ማሲንቆ ክራር እና ዋሽንት ተሰቅለዋል ፊትለፊት ያለው ግድግዳ ላይ ደግሞ ለእይታ በሚስብ አይነት ተሰርተው ሞፈር እና ቀንበር፣ አጎዛ፣ ጋሻና ጦር ይስተዋላሉ አስተናጋጆቹ ሳይቀር ሴቶቹ ፀጉራቸውን ሹሩባ ተሠርተው ወገቡ ላይ በመቀነት ሸብ የተደረገ ሽንሽን ቀሚስ ለብሰዋል ወንዶቹ ደግሞ ከካኪ የተሰራ ተነፋነፍ ቦላሌ አድርገው በወጉ የተበጠረ ጎፈሬያቸው ላይ ሚዶ ማበጠሪያ ሰክተዋል በቤቱ ውስጥ የምሺቱን ጨዋታ ለመታደም ከገባው የከተሜ ሰው ውጪ አንድም ከተማን የሚመስል አልያም አሁን ላይ እኛ የስልጣኔ መገለጫ ብለን የምንጠራቸው ቁሶች ማየት ዘበት ነው በቃ ሙሉ የገጠሪቱ ኢትዮጵያን ድባብ የተላበሰ ነው። ይህ አይነት ስሜት የሚሰማኝ ድሮ ላይ ትምህርት ሲዘጋ ከገጠር ያሉት ዘመዶቼ ጋር ስሄድ ነበር በቃ ጎጆ ቤት አይሁን እንጂ ይሄም ገጠር እንዳሉት የዘመዶቼ ቤት ነው ሌላው በጣም የወደድኩት ነገር ቤቱ ውስጥ ምግብ ሲያዙ የሚቀርብልዎት በሞሰቦ ወርቅ ተደርጎ ነው የሚጠጣው ጠጅና ብርዝ ደግሞ በብርሌ ከኛ ፊትለፊት ባለው የመደብ መቀመጫ ላይ ሁለት ወንድና ሁለት ሴቶች በጋራ ሆነው በመሰቦ ወርቅ የቀረበላቸውን ማድ ከበዉ እየተቋደሱ ወዲህ ደግሞ የብርሌ ጠጃቸውን እየተጎነጩ ይስቃሉ ይጫወታሉ።
እኔም እየጠፋ ያለውን ተሰብስበው ለማድ አብሮ የመቀመጥን ባህል ስላሳዩኝ ደስ ብሎኛል በውስጤ ወድጃቸዋለው። እንደ ዛሬ ወቅቱም ሰውም ሳይከፋ በፊት ለብቻ ሆኖ ማድ መቀመጥ እንደ ነውር እንደሚታይ ገጠር ያለው አጎቴ ነግሮኝ እንደ ነበር በጣም አስታውሳለሁ በነገራችን ላይ ገጠር ያለው አጎቴ ሲበዛ ባህሉን የሚወድና የሚያከብር ያሁኑን ዘመን አመጣሽ የስልጣኔ መደናበር ደግሞ የሚጠየፍ ሰው ነው። እንደዛ የሆነው ገጠር ስለሚኖር አሊያም ገበሬ ስለሆነ ብቻ አይደለም እንደዛ ሚሠማው አሁን ላይ ባለው በብዙ ነገር ስለሚማረር ነው የገጠሩ አጎቴ በድሮው የትምህርት ስርዓት እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ ዘልቋል በዛ በቀሰማት የማንበብ ክህሎት በመነሳት ስለ ሐገሩና ስለ ባህሉ ሚጠቅሱትን ነገሮች ባገኘው አጋጣሚ ያነባል ጉዳይ ኖሮት ወደ ከተማ ከዘለቀም የዛ አይነት ይዘት ያላቸውን መጸሐፍት ከኔ ጋር አብረን ሆነን እንገዛና ይዞ ይሔዳል አመለካከቱና ነገሮችን የሚያይበት ይዘት ከተሜ ነን ከሚሉ ሰዎች እጅግ የላቀ ነው እኔም ገጠር እሔድ በነበረበት ግዜ ብዙውን ሰዓቴን የማሳልፈው ከሱ ጎን ቁጭ ብዬ ወሬዎቹን በማዳመጥ ነበር
የሆነ ግዜ ከሱ ጎጆ እሳት ዳር ሳለን በሌማት የቀረበ ቆሎ እየቆረጠምን በጋራ ተሰብስቦ ማድ ስለመቀመጥ ባህል እያወራልኝ ሳለ አንዴ የደረሰብኝን ገጠመኝ ላጫውትህ ብሎ የነገረኝን ሁሌም ነበር ባስታወስኩት ቁጥር የምስቀው እንዲህ ነው የሆነው, ,,ግዜው በጣም ቆይቷል የገጠሩ አጎቴ ለአንዲት ቀጠን ያለች ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ያመራና እዛ ያሉ ዘመዶቻችን ይቀበሉታል እንዳጋጣሚ የደረሰበት ሰአት ምሳ ሰአት ነበር እና ቡና እየተፈላ ተጠቅልሎ የተቆራረጠ እንጀራ ለየብቻቼው ሁነው በሰሀን በሰሀን ያነሳሉ የገጠሩ አጎቴ ደሞ ተሰብስቦ አብሮ ከመብላት ውጭ ሊያውም እንዲህ እንጀራ አራት አምስት ቦታ ተሸንሽኖ ለእያንዳንዱ ሰው ስለሚታደለው ወይም በእኔና በእናንተ አጠራር "የቁርጥ እንጀራ " ስለሚባለው ነገር የሚያቀው አንዳችም ነገር አልነበረውም ••••
እናላችሁ አንድ ሰሀን ያሲዙትና እንጀራ አንሳ ይሉታል የገጠሩ አጎቴም ያው እንደነገርኳችሁ ለነገሩ አዲስ ስለሆነና ቡናም እየተፈላ ስለነበር እንደነሱ ገጠር የቡና ቁርስ ይሆናል በሚል እሳቤ አንድ ቁራጭ እንጀራ አንስቶ ሰሀኑን ዘወር ያደርጋል ጨምር ቢሉት ደሞ ለቡና ቁርስ ይሄ ምን አነሰው ብሎ በሆዱ ይበቃኛል ሲል ድርቅ ይላል ያጎቴን አሻፈረኝ ማለት ያሰሙት ከተሜ ዘመዶቻችንም መንገድ ላይ በልቶ ይሆናል በሚል ይተውታል እሱም ያችን አንድ ንጣይ እንጀራ ቀምሶ ቡናውን ይጠጣና ይጨርሳል እነሱም የተበላበትን የምግብ እቃና የቡና ረከቦት አነሳስተው ቴሌቪዥን ይከፍቱለትና ተጫዎት ብለውት ወደየ ፊናቼው ይሰማራሉ መንገድ ያንገላታው ሚስኪኑ የገጠሩ አጎቴ ካሁን አሁን ምሳ ይቀርባል እያለ ቢያማትር ቢያማትር ከወዴት መጥቶ ያነሳት ቁራሽ እንጀራ በምሳ ስም የተሰየመች መሆኗን ያወቀው ማታም ለእራት በምሳው መልኩ ሲያቀርቡለት ነበር ቡና ቁርስ ብሎ ተሸውዶ ምሳውን ሳይበላ በራበው ሆድ የቆየው የገጠሩ አጎቴ ብልጥ ያለ አንድየ አይበለጥ ብሎ እራት ላይ ያነሳውን የቁርጥ እንጀራ ብዛት ብነግራችሁ እናንተም ትታዘቡታላችሁ ። እዛው በተቀመጥኩበት የገጠሩን አጎቴን በሀሳቤ ሳልኩና ፈገግ አልኩ የባህል ምሽት ቤቱ ጨዋታ በደንብ መድመቅ ሚጀምረው እና የሚደራው ከሁለት ሰአት በዃላ ነው እኔና ሀኒም ያረፍንበት ሆቴል ካለንበት ብዙም ስለማይርቅ ስለሰአቱ መምሸት ምንም አናስብም ሁሉም በየመቀመጫቼው የሚጠጡትን ይዘው ተቀምጠዋል ብዙወቹ ጥንዶች ቢሆኑም ለብቻቼው ሁነው የገቡም አሉ እኔና ሀኒም በብርሌ የቀረበልንን የብርሌ ጠጅ እየተጎነጨን መሀል ላይ ቁመው ጨዋታውን በሚያከፋፍሉት እንድ ወንድ እና አንድ ሴት አዝማሪ ላይ ፈጠናል መቼም ጨዋታው ለጉድ ነው ተቀበል ይልና አንዱ ለአዝማሪው በቅኔ የታሼ ግጥም ይወረውራል ወዲያው ደሞ ከሌላኛው በኩል ሌላ ግጥም ይወረውራል ሚስቱ ጋር የገባው ለሚስቱ ያስገጥማል ሴቷም አንዲሁ ባሏን ማሞገሻ የሚሆን ቃላትን ሰድራ ታቀርባለች ፣ ፍቅረኛሞችም ፍቅራቼውን በግጥም ያፈኩታል በዛው ልክ የከፋውና , ከሚስቱ ወይ ከፍቅረኛው ጋር ተጣልቶ መጥቶ የሆዱን ብሶት በግጥም የሚተነፍስም ዕልፍ ነው የአዝማሪዎቹ ግንባር ላይ ባለ ሀምሳና ባለ መቶ ብር ኖቶች በሽልማት መልክ ወዲያው ወዲያው ይለጠፋሉ ከዛማ ምን አለ ቤቱ በሳቅና ጨዋታ ባንድ እግሩ ይቆማል የብርሌዋ ጠጅ ስራዋን ሰራች መሰል እኔም አስገጥም አስገጥም የሚል አንዳች የግጥም መንፈስ ንሽጥ አደረገኝ ተቀበል አልኩ ማን ከማን ያንሳል
" አይን ማየቻ ነው ጥርስ ለመሳቂያ
ማን አለ እንደደሴ የቆንጆ መፍለቂያ "
አዝማሪው ከኔ ተቀብሎ አስተጋባ እኔም አንድ ያጣላል በሚል አገሬንም ሀኒንም ለማወደስ አሰብኩና ተቀበል አልኩ ሁለተኛ አዝማሪው ወደኔ ዞረ
"ፍረዱ እስኪ እናንተ ስለኛ ቁንጅና
ይሄው አቅርቢያለሁ ሀኒን ለናሙና "
ብየ ወደ ሀኒ ስጠቁም በጭብጨባና በሳቅ አጀቡን ሀኒ የሰው አይን ስላረፈባት መሽኮርመሞ አልቀረም ነበር ወዲያ ከኔ ግጥም ቀጠል አድርጎ አንድኛው እንዲህ ሲል አስገጠመ "ደሴ በቆንጆዎች መሆኗን ገናና
ነበር የሰማሁት ባለፈው ሀቻምና
ዛሬ ግን አመንኩኝ አይቼ ናሙና "
ጭብጨባውና ሳቁ ከቅድሙ ብሶ ጦፈ እኔም እንድም ሀገሬ አንድም የሀኒ ቁንጅና ስለተሞገሰልኝ ከምሽቱ ድምቀት ጋር አብራ ውስጤ በሀሴት ፈነጠዘች የሀኒ ደስታ መቼም የሚወጋም አልነበረም በባህል ምሽት ቤቱ ውስጥ በነበረን ቆይታ ለአዝማሪ የተነገሩ ግጥሞች በጣም ብዙ ቢሆኑም ከነዛ መሀከል ያዝናኑኝና የማስታውሳቼውን አንድ ሶስት ግጥም ለእናንተም ላካፍላችሁ •••
"የማልመጣ መስሏት የማልመለስ
የጤፉ አውድማ ላይ ወቃችበት ገብስ"
*
"ስስምሽ አድሬ ስሞጨሙጭሽ
አልሳመኝም ያልሽው ምንጉደኛ ነሽ"
*
"ባቄላ ምርቱ እንጂ አያምርም ክምሩ
ይምጣ የወሎ ልጅ ከነምንሽሩ "
***
"እምየ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ"


እንዲህ እንዲህ እያልን እጅግ ደስ የሚሉና የማይረሱ ግዚያቶችን በውቢቷ ባህርዳር አሳለፍን በተለይ ለኔ በጣና ሀይቅ ነፋሻማውን አየር እያማግን በጀልባ ላይ ሁነን የቆየንበትን ወቅት መቼም ምረሳው አይመስለኝም ጉማሬ የሚባለውን እንስሳም ለመጀመሪያ ግዜ በቅርብ ርቀት ያየሁት ያኔ ነበር ጉማሬ ከሌሎች እንስሶች የሚለይበት አንድ የሚደንቅ ነገር ከባለ ጀልባውም ሰምቻለሁ "ጉማሬ የሚበላውም የሚፀዳዳውም በአፉ ነው " ሌላው አስደሳቹ ጉዞ የጭስ አባይ ፏፏቴን ለማየት ያደረግነው ነበር ብቻ አሁን ላይ እንደዚህ ዘርዝሬ ማልጨርሳቼው ልዩ ትዝታዎች አልፈዋል በመጨረሻም እኛ ሁሉንም ባናዳርስም ለጉብኝቱ ብለን ያቀድነውን የቀን ገደብ ስለተገባደደ ውቢቷ ባህርዳርን ለጣና ሀይቅ አደራ ሰጥተን ወደ እናት አገር ደሴ የመልስ ጉዞ አደረግን ለራሴ ግን በቅርብ ወደ ባህር ዳር ተመልሼ እንደምመጣና በደንብ እንደምጎበኛት ቃል ገብቼ ነበር •••

ይቀጥላል

#ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀርቶታል ።




━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
https://www.tg-me.com/loverzonn
┄┄┉┉✽‌»‌🌺🌺»‌✽‌┉┉┄┄
TEDDY AFRO - አርማሽ (ቀና በል) - [New! Official Single 2021] - With…
<unknown>
TEDDY AFRO - አርማሽ (ቀና በል) - [New! Official Single 2021] - With Lyrics (8.5mb)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🍁 @loverzonn 🍁
🍁 @loverzonn🍁
Share
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺‌✽‌┉┉┄┄
አትራቂ ከጎኔ

አንድ አንዴ ሲያስብ ያንቺን
መራቅ፣
የሆዴን የቅርቤ ሰው ባያውቅ።
ይተናነቃል እንባዬ ያዝናል ልቤ፣
ባትርቂኝ እያልኩ ሁልም
ካጠገቤ።
ያንቺ ሆኜ በስምሽ ተጠርቼ
መኖር ይሻለኛል ካንቺ
ተጠግቼ።
ማን አለኝ እኔ ካንቺ ወዲያ፣?
ያንቺው ልብ ነው ውሎ
ማደሪያ።
ልብሽን ክፈቺ ልኑርበት ከልብሽ፣
እኔ ያንቺው ነኝ አርጊኝ የራስሽ።
ብቸኝነቴን አይቶ ቢያነባም
አይኔ፣
እወድሀለው በይኝ አትራቂ ከጎኔ

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
።።።።። ዋ! ።።።።።

አይኔ ወደደሽ ስልሽ፣
አይኑን አጥፋው ብለሽ ገባሽ አሉ ስለት
ምኞትሽ ሰመረ
አይኖቼ ጠፉልሽ ይኸው አንደዘበት።

ግን መች ተውሻለው
በልቤ ብሩህ አይን ዛሬም አይሻለው።

ደግሞ አንደዚ ስልሽ አትወጅኝምና
ልቡንም አጥፋልኝ ብለሽ ትሳይና
ፀሎት ያልቅብሻል እሞትብሽና።

#yabu 👏👏

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
ትላንትም ሆነ ዛሬ
ነገም ወድሻለው
እብድነትሽ ደግሞ
የባሰ ገዳይ ነው
ብቻ የምፅፈው አንቺን
አፍቅሬ ነው 😍

Join & Share

@loverzonn
@loverzonn
ወንድነት ማለት
ሁሉም ሴት ስለወደዱህ
ሳይሆን ለ1ሴት ንፁህ ሆነህ
በንፁህ ልብህ አፍቅረሀት
ከሁሉም ሴቶች አስበልጠህ
ንግስት ማድረግ ማለት ነዉ።
ለሁላችሁም ይህን ያድላችሁ
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞
@loverzonn
ከልባችን ስሜት ይልቅ ለአይምሯችን ምክንያት ማድላት አለብን።

አስተውል ለበሰለ ሰው ከስሜት ይልቅ ምክንያት ይቀድማል።


@loverzonn
‌‌‌‌‌‌
2025/07/14 11:23:22
Back to Top
HTML Embed Code: