Telegram Web Link
የሺሀረግ ሆንሽብኝ::

የሺዬ... ማህሙድ አህመድ የልብ ልብ ሰጠሽ::

እንደወለል ሚበርድ አልጋ ላይ ነበርኩ:: ትኩስ እንባ በጉንጬ ይፈሳል:: እንባው የመተከዝ አይደለም:: የተስፋ መቁረጥ እንጂ:: ከሃዘን ይከፋል:: በሃዘን ውስጥ ተስፋ አለ::

የሴት አያቴ ሰርግ ፎቶ ከፍ ብሎ ተሰቅሏል:: እንደጥጥ ሚያበራ ግዋንት ጣቷን ሸፍኗል:: ወንዱ አያቴ ጠይም ፊቱን ጨምድዷል:: ረጅም ትከሻው ሱፉን ይሞላዋል:: እዛ እንደነበርኩ ሁሉ የሽቶ መአዛ ይወረኛል:: ሴት አያቴ የሾለከ ፈገግታ ፊቷን ያደምቀዋል:: መልኳ ሚዜምለት ነበር:: ምን ያህል ጊዜ ይሆነዋል ይሄ ፎቶ? አርባ ሃምሳ አመት? ጊዜ ግፈኛ ነው:: የሺዬ... ጊዜ ግፈኛ ነው:: ለኩራትሽ ኢምንት ርህራሄ አይኖረውም:: አባትሽ ቤት ያወዛሽ ጮማ ይቅርብሽ:: ነይ... በ'ኔ ልብ ተክዢ::

አባይ እንደዋጣት ሴት አትሆኝም:: ፅልመት ጨለማ ውስጥም... ፈራጅ በማይኖርበትም... አልጥልሽም:: ገላጋይ በሚታጣበት ወና ምድርም አንጣላም:: ጠጅ እንደ ወንዝ በሚቆርበት ከተማ ውስጥም ካ'ንቺ ጋር ካልሆነ አልሰክርም:: ውርጭ ለሊት ላይ ጋቢሽ ነኝ:: ብርሃን ቢክድሽ መሪሽ ነኝ:: ይዤሽ ስነጉድ የትም ብሄድ አይከፋኝም:: በበርሃ የሙሴ በትሬ ነሽ:: አባይ ጎርምሶ ግብፅ ቢወስደን መውጫ አለን::

አባትሽ ሳቀብኝ:: ፍቅር... የሞኝ ተስፋ ነው ብሎ:: የሺዬ... እኔ ሁለቱንም ሆኛለው...ሞኝም ተስፈኛም:: ጥጋብሽ ፈተነኝ:: ፍቅርሽ እልሀኛ አረገኝ:: የእጅሽ እትማት ደረቴን እስኪያቀልመው ማልዳለው:: በጨረቃ ይዤሽ እስክጠፋ መዘዙን ውጠዋለው:: የማይጠፋብኝ ህልሜ ነሽ::

የሺሃረጊቱ...
ይራቅ እንጂ አይቀርም...
👏2❤‍🔥1
ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል... እንኳን ደስ አላችሁ!
7
1
🔥1
ሰፊ ሰሌዳ:: ብዙ ታሪክ:: አንድ ጠመኔ::
1👌1
1
ቀን እንደ ናና ከረሜላ ሳይጠገብ ሚሟሟበት ከተማ ውስጥ እንኖራለን:: ሊስትሮው ዝናቡ የቀደሰለትን የእለት እንጀራ ያጭዳል:: ተላካፊ ረዳት የሰፈር ስም ይጠራል:: የመሸበት ሰራተኛ በዝለት ይራመዳል:: በወፍራም ሽቶ የታጠነ ነጠላ የጠመጠሙ አዛውንቶች ብርድን ያማሉ:: ያለፈው ጥር ያንቀላፉ ነፍሳት ጥር ሲደግም ይነቃሉ:: ሶስት ሰዎች ፣ የልብሳቸው ቀለም እንደ ባንዲራ ተዛንፎ የተሳከረ ፣ ቆመው ይሳሳቃሉ:: የህይወት ሀቅ መንገደኛ መሆኑን ይረሳሉ:: ዛሬ ቢያልፍ ነገ ይቀጥላል:: አስፋልቱ መሃል ከደመና የተፀነሰ ኩሬ ይተኛል:: የሹፌር እርግማን ይጠጣል:: ተሻጋሪ መልኩን ያይበታል:: አውቶብስ እንደ እባብ ይርመሰመሳል:: የመንገድ አምፖሎች ፈዛዛ ብርሃን ይለግሳሉ:: ፀሀይ በልዝብ ስንብት ይጠልቃል:: የጨለማ ወጋገን እንደወረርሽኝ ሰማይ ይሞላል:: ሽፍታ ዝንጉ ሰው በአይኑ ያስሳል:: ችኩል እርምጃዎች ይበረታሉ:: ተገናኝተው የቆዩ ሰዎች ባልጠበቁት ጎዳና ላይ ይገጣጠማሉ:: ታክሲ ሰው ይደርባል:: የታሪፍ ዋጋ ያሰዳድባል:: ሹፌር ትራፊክ ሲያይ ሃይማኖቱ ይታወሰዋል:: ቀኑ አራት ነጥቡ ላይ ይደርሳል:: ጭለማው ሁሉንም ያመሳስላል:: ወዳጆች በ'ቻው' 'ቻው' ይለያያሉ::

ዛሬም ትናንት ይሆናል::
👌5
4
1💯1
1
4
❤‍🔥2
5
ሃብሏ ደረቴ ላይ ተኝቷል:: ወርቃማ መስቀል::

'ሞተሽ አልነበር እንዴ?'

አይኗን አሸች::

'ከሞት በህዋላ ምን ያለ ይመስልሃል'

መሽቷል:: ደቃቃ ኮከቦች ፀይም ሰማይ ላይ እንደ ጨው ተበትነዋል::

'እምነት'

አይኗን አሸች::

'ለምን?'

'ምርጫ አለን?'

ጥርሷ የሐምሌ ጨረቃ:: ያፅናናል::

'አንቺስ'

'ትነት'

በአይኔ አይኗን ፈልጋለው:: ትኩስ እስትንፈሷ አንገቴን በስሱ ይገርፋል::

'እንደተረሳች ውሃ ጠብታ... ምተን ይመስለኛል'

ለደቂቃዎች የልቤ ምት ብቻ ይሰማል:: ትከሻዬ ላይ ሚፋጅ እንባ ከጉንጯ ያርፋል:: አንድ ጠብታ... የጉንጯን እጥፋት የሚከተል ዳና::

'አለአ... ስተን ግን የተለያየ ቦታ ምበተን ይመስለኛል:: የቡና ሃሜት ላይ- የስካር ታሪኮች ሲወዙ- ቡኒ ቀለም ሲነሳ- በደበዘዙ ጠባሳዎች ውስጥ... አላቅም... ምታወስ ይመስለኛል:: የትውስታው እድሜ ግን እንደ ትነት ነው:: ስሜ በተጠራ በዛው ቅፅበት ይረሳል::'

የተናገረችውን ሁለታችንም በፀጥታ ለመዋጥ እንታገላለን:: ጣራው ከወትሮው በላይ የቀረበ ይመስላል::

'መች ኖረህ ነው ግን ሞት ሚያስጨንቅህ?'

ምናልባት ልክ ነች:: ደክሞኛል:: አይኖቼን በስሱ ለመክደን እታገላለው:: የሰጠችኝን ሃብል በጣቶቼ ፈልጋለው::

...
2
በቆሎ ሻጯ ትዝ ትልሃለች? ያቺ ምስኪን ጠይም እናት የጨሰች ቢጫ ካኔቴራ ምታዘወትር ልጇ ከጡቷ ማይጠፋ? እንዴት ትረሳታላህ? ጭምት ፊት እና ችግሯን ሚክድ ፈገግታ ነበራት:: ልጇ አድጎ መንገድ ላይ አመድ ልሶ ሲሯሯጥ አገኘሁት:: እሷን አይመስልም:: ጠርቼው እናትህስ? ስለው ማናባህ ነህ ብሎኝ ሮጠ:: ጀርባ ጀርባውን እየሰጠኝ እየተከተልኩት እንዳልሆነ ለማየት አስሬ ወደ እኔ እያየ ሲሮጥ አድጦት ገኒ ሱቅ ፊት ያለው ቱቦ ውስጥ ፈረጠ:: ሮጬ ስደርስ ወጥቶ ለማምለጥ ይታገላል:: ግማሽ ሰውነቱ ተለውሷል:: ደህና ነህ? ስለው ግራ ትከሻውን ይዞ እያነከሰ ለመሮጥ ሞከረ:: እዛው ከገኒ ሱቅ አቦለድ ገዛሁለት:: ትንሽ ፍርሃቱ ለቀቀው:: እኔ ፊት መብላት አልፈለገም:: እናትህን ሰላም በላት ብዬው ወደ ቤቴ ገባሁ:: አንዳንዴ ሁሉም ታሪክ እንዳለው ይዘነጋኛል:: ማን የማን እንደሚበልጥ እድል ፈራጅ ነች:: በነጋታው በቆሎ በምትሸጥበት መንገድ ከስራ ተመለስኩ:: ልጇ ከጎኗ ተደግፏት ከሰል ያርገበግባል:: ቀና ብሎ አየት አድርጎኝ አንገቱን ደፋ:: በቆሎ ተወዷል:: ትኩስ ካለ ስጠይቃት እዛው እሳቱ ላይ ከነበረው ጠቅልላ ሰጠችኝ:: ጭምት መልኳ አልፈዘዘም:: ሁለት ጨምሪልኝ አልኳት:: እሳቱ ላይ የቀሩትን ሁለት ጠቅላላ ልትሰጠኝ ስትል አንዱን ለእሷ እና አንዱ ለእሱ እንድታደርግ ነገርኳት:: ፈገግታዋ ሲያምር:: አጠገባቸው ያለ ድንጋይ ላይ ተመቻቼ ተቀመጥኩ:: ብዙ አታወራም:: ከልጇ ጋር ስለኳስ አወራን:: በቆሎዬ ሲያልቅ ተነሳው:: በደንብ ሲጨልም ታወቀኝ:: ሰፈሩ አይታመንም:: ቤት ገብቼ ጥሩ እንቅልፍ ተኛው:: እድል ፈራጅ ብትሆንም ማቅለያ አንቀፅ ግን ለሰው- ሰው ነው::
👌81👍1🤯1
We have no scar to show for happiness
2025/11/07 04:22:31
Back to Top
HTML Embed Code: