የ’እንሆ’ ተረኮች
ወራት ነጎዱ:: በየቀኑ የሆዴ ግፋት ይጨምራል:: የምወስንበት ቀኖች እያለቁ ናቸው:: በውዝጋቤ መሃል ዛሬ ትላንት ይሆናል:: ደውዬ ምን ለመወሰን እንዳልጠይቀው እንኳን ስልኩን በቅጡም የፊቱ ወዝ አይመጣልኝም:: በማላውቀው ሃገር ብቻዬን ነኝ:: ደጃፌ ላይ ሚገለጥ መለኮት ጠብቃለው:: መፍትሄን እንዲያውሰኝ:: ቢችል ደግሞ ከቀረጢቱ ጊዜን እንዲያፍስልኝ:: ካልተሳነው በምህረቱ ወደ ትላንት እንዲመልሰኝ:: በዚህ ሁሉ ሃሳብ ውስጥ ነገ ዛሬ ይሆናል:: ለመከራዬ የበቃኝን ያህል ሳላነባ ከማህፀኔ ለማምለጥ መታገል ጀመረች:: እውን ልትሆን ተቃረበች:: አንድ ለሊት ወገቤን ደግፌ አቅራቢያ ካለ ጤና ጣቢያ ሄድኩኝ:: ዘርፋፋ ላብ አይኔን እየጋረደኝ ገፋሁ:: በለቀሶ ይህን አለም ስትቀበል ወፍራም ሙቀት ሞላኝ:: እጄ ላይ ለጥቂትም ሳያስተኟት ይዘዋት ወጡ:: ድንገት የሞላኝ ሙቀት ቀዘቀዘ:: ፍርሃት ሞላኝ:: የተገረበበችውን በር ከፍቶ ሊያግዘኝ የሚገባ ማንም እንደሌለ ገባኝ:: ስሟን በማን ልጠራ ነው? የት ይዣት ልሄድ? ምን ላበላት? ምን ላለብሳት? መጥፋት ፈለኩኝ:: ወደ ትላንቴ ሚወስድኝን ዳና መከተል:: ማን ያግደኛል? ልጄን እዚህ ጥያት ብሄድ አንዱ ማሳደጊያ እኔ ከምሰጣት ኑሮ በላይ ህይወት አይሰጧትም? በእዚህ ሃሳብ ውስጥ እየዋለልኩኝ የጤና ጣቢያ መውጫ ላይ ደርሻለው:: ትቼያት ሄጅያለው:: አሁን መካድ ሚሉት ደሴት ላይ ነኝ:: ውሸት ቢሆንም እሷ የሌለችበት ትናንት ላይ ነኝ::
በጊዜ መሃል ግን ትናንት ዛሬ እና ነገ ሲዋሃዱ የጨቅላነት መልኳ ይታወሰኛል::

❤4
‘It’s cold’
A rather short way of saying it, while the expression, the slow tightening of her arms around mine was more profound.
‘The more I love someone, I find it enticing. I find myself in a spiral where I care to the point of scare. I don’t want them out in the world with all the possibilities but only with me, in a tight space we create.’
Her words drop in to the mist that surrounds us in this brink of the day.
‘Well, I believe the biggest gift our creator gave us due to his love wasn’t life but rather a freedom’
‘But I rather want you bounded to me’
A sequel of seconds, as long as the freeze, as if our eyes met in a spark, as if everything dimmed and our eyes were the lights left, an opening to nirvana.
‘There is freedom in strain’

❤2
ምን ነበር ያ ሀሰት
በእውነት የማልንው
ያልተማረ ክህደት
ዘላለምን ረስተን
ዛሬን ብቻ የኖርንው::
ምን ነበር ያ ውበት
ያ ሸካራ ቆዳሽ
ያ ቀዝቃዛ እጅሽ
ያ ፈዛዛ አይንሽ
ያ ማይጃጃ ፊትሽ::
ምን ነበር ያ ቃልሽ
ብሩሹ ሲቀባሽ
ሲያዘልቅሽ ዘላለም
ሲያደርግሽም ባንዳ
ሲነጥልሽ ካ'ለም::
ምን ነበር ያ ሳቅሽ
ያቺ ምጥን ፈገግ
ጥሳ የወጣችው
በአይኖቼ ደበቃ
ከነፍሴ ያረፈችው::
ምን ነበር ያ ፍቅር
ያ እውነት ሃሰት ነው
የማደርገው ሳጣ
አይኖቼን ከድኜ
ገለጥ ሳደርጋቸው
አፍሽን ከአፌ ያጋጠመው ጣጣ::
ምን ነበር ያ ቅዠት
በስሜት ጠንብዤ
ስራዬን ዘንግቼው
በህመም ሰክሬ
አብሬሽ ያለፈው::
ምን ነበር ጥፋቱ
እስኪ ያስረዱኛ
ቀለሙ ብሩሹ ምን ነካቸውና
መልክሽን ሲያፈርሱት ነፍስ ነሱሽና::
ምን ነበር ያ ደስታ
በእንቅልፌ ያሳቀኝ
እብደት ነው ያ ትዝታ
በውኔ ያስለቀሰኝ::
የነፍሴ ቁራኛ ብቻነቴ የሳለሽ
ያሳቤ ግዋደኛ ሞናሊዛዬ ነሽ::
B’Fkr
@lukeyos
በእውነት የማልንው
ያልተማረ ክህደት
ዘላለምን ረስተን
ዛሬን ብቻ የኖርንው::
ምን ነበር ያ ውበት
ያ ሸካራ ቆዳሽ
ያ ቀዝቃዛ እጅሽ
ያ ፈዛዛ አይንሽ
ያ ማይጃጃ ፊትሽ::
ምን ነበር ያ ቃልሽ
ብሩሹ ሲቀባሽ
ሲያዘልቅሽ ዘላለም
ሲያደርግሽም ባንዳ
ሲነጥልሽ ካ'ለም::
ምን ነበር ያ ሳቅሽ
ያቺ ምጥን ፈገግ
ጥሳ የወጣችው
በአይኖቼ ደበቃ
ከነፍሴ ያረፈችው::
ምን ነበር ያ ፍቅር
ያ እውነት ሃሰት ነው
የማደርገው ሳጣ
አይኖቼን ከድኜ
ገለጥ ሳደርጋቸው
አፍሽን ከአፌ ያጋጠመው ጣጣ::
ምን ነበር ያ ቅዠት
በስሜት ጠንብዤ
ስራዬን ዘንግቼው
በህመም ሰክሬ
አብሬሽ ያለፈው::
ምን ነበር ጥፋቱ
እስኪ ያስረዱኛ
ቀለሙ ብሩሹ ምን ነካቸውና
መልክሽን ሲያፈርሱት ነፍስ ነሱሽና::
ምን ነበር ያ ደስታ
በእንቅልፌ ያሳቀኝ
እብደት ነው ያ ትዝታ
በውኔ ያስለቀሰኝ::
የነፍሴ ቁራኛ ብቻነቴ የሳለሽ
ያሳቤ ግዋደኛ ሞናሊዛዬ ነሽ::
B’Fkr
@lukeyos
❤4👍1
አንድ - ክረምት
ጣቷ በፊቷ ላይ በስሱ ተዘርግቷል:: ፀይም ፀዳል የሚያበሩት አይኖቿ ይሾልኳሉ:: ወተት ጥርሷ ዳማ ፊቷን ይሞላል:: ደረጃው ላይ ቆማ በሃሳብ ትንከራተታለች::
እኔ ቆምያለው:: ልቧ ሚምሰው እኔን ፍለጋ ነው:: ስልኬን አውጥቼ ሳነሳት ትዝታን አስቀድሜ ነው:: ስዘልቅ እናም ህይወት ሲቀጥል ይህን ቅፅበት መርሳት ፈራለው:: ስታገኘኝ እጆቿ ይፈታሉ:: ስታቅፈኝ ለነገም ነው:: በእንሹክሹካዎቿ መሃል ፍቅር ይንጠባጠባል::
ምንሄድበትን ለመወሰን ሰላም የነበረው ወሬያችን ወደ ጭቅጭቅ ይለወጣል:: አጇቿን ፈልጋለው:: መራመዳችንን አናቆምም:: ክረምት ነው:: ቀኑን ሲያላዝን የቆየው ሰማይ ለኛ ይፈግጋል:: ተፈጥሮ ከጎናችን ይቆማል:: ምንሄድበትን እንረሳለን:: በመንገድ ላይ ምሽቱ ያልቃል:: ታሪኮቿ ማብቂያን ያጣሉ:: ዘላለማችንን እዛው እናያለን:: ወፍራም የበቆሎ መአዛ በስሜት ያስደንሰናል:: ስንገዛ በብርዱ እልህ ነው:: በቆሎ ስንበላ ሳቅ ይቀድመናል:: ትንሽ የዝምታ አኮቴት ይሰርጋል:: ይህችን ጥቂት ደቂቃ ትንሽ ስንኖር- ትንሽ ስናረጅ እንደምንናፍቀው እናውቃለን:: ይህን ፈርተን ግን መኖር አናቆምም::
ስንለያይ በናፍቆት ነው:: ስሸኛት ነገን እየሻሁ ነው:: ይቺን ጥቂት ርቀት ምን ያህል ልናረዝማት እንደምንችል እናሰላስላን:: በስስት ከእጄ ትነጠላለች:: በመሳማችን ውስጥ ተስፋን እናትማለን::
...

አንድ - በጋ
ሲያወራኝ በቃላቶቹ ውስጥ የታተመ ስሜት አለ:: በዝምታ በአይኖቼ ከንፈሮቹ ሲንቀሳቀሱ አያለው:: የበጋው ሀሩር ጋብ ያለለት ወደ ምሽትነት ሚጠጋ ከሰአት ነው:: ቃሏን ጠብቃ ምትገባዋን ፀሀይ በስስት እንሸኛታለን:: ነገሮች ሊያበቁ ሲሉ የሚለብሱት የተለየ ገፅ አለ:: ለትውስታ ሚመች::
ካገኘሁት ቆይቻለው። ክረምትም ሳናጣጥመው አለቀ። አደይም በየጉብታው አበበች። የመስቀል ወፍም ብቅ አለች። አመት ሲቀየር እኛ ታዛቢ ሆንን። የኑሮ ግርግር እንዳ'ዲስ አቆጠቆጠ። ህዳር ሳይገባ ሊቀዘቅዝ። ስልክ ስደውል በስራ አሳቦ ይዘጋዋል። መልሶ ሲደውል እጄ ላይ ስራ አይጠፋም። በብዙ ቀጠሮ ዛሬ ላይ ተገናኝን። ቀጣይ መገናኛችን መች ሊሆን ስለማላውቅ ምን ያህል ይቺን ከሰአት ላረዝማት እንደምችል አስባለው።
'ምነው ዝም አልሽ?' ይለኛል። ዝምታዬን ይጠላዋል። ከሱ ጋር ስሆን ሁሌ ሚመጡልኝ ቃላቶች ምጥ ይሆኑብኛል። በግርታ ቅንድቦቹን ፈልጋለው። እጆቹን በአንገቴ ላይ ይጥላል። ሲያቅፈኝ እንደሌለው አድርጎ ነው። በመሃከላችን ጸጥታ ይጸናል። ጸጥታውን ወደዋለው። አለማት አሁን ቢገቱ ግድ አይሰጠኝም።
ሲጨልም መራመድ እንጀምራለን። ሙቅ ንፋስ ይከበናል። በልቡና በልቤ ኪዳን ይታደስ ይፍረስ መለየት ያቅተኛል። መጠይቅ አልፈልግም። ማወቅም አልፈልግም። ዛሬን እንደዛሬ ለመሸኘት ጓጓለው። የነገን ጭንቀት በእለቱ እንጋፈጠዋለን።

❤1