Telegram Web Link
ከእጄ ላይ ሚነትብ ሲጋራ በመሃላችን ብቸኛ ፀዳል ሆኖ ይጤሳል:: ሜላት ግድግዳውን ተደግፋ ከፀጉር ላስቲኳ ጋር ትጫወታለች:: ፅልመት- ቢገፋ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ቢሆን ነው::

'ሳሚ ደወለልሽ?'

ድምፅዋ እንደለዘዘ ቆሎ ያናደኛል:: ቃላቶቹን ስትላቸው እየተንሳፈፉ ሚጏዙ ይመስል ይረዝማሉ::

'Ya, ትንሽ ደቂቃ አውርተን ትራፊክ ሊያስቆመኝ ነው ብሎ ዘጋው'

'ህ...'

ፊቷ በጭላንጭል ቢታየኝም የበለጠ ስትደበዘዝ ታወቀኝ:: ሳሚን እሷ ጋር ላድር ከመምጣቴ በፊት ጠይም ቆዳው ላይ ታትሜ እንደነበር እንዳልነግራት የደደብ ሰው ጭካኔ የለኝም:: በጭለማ ውስጥ ስትተክዝ እሷን በጠራበት ስም እንደጠራኝ ሳታውቅ ነው:: እሷ ላይ ያረፉት የከንፈሩ ዳናዎች ትንሽ ካኔተራዬን ዝቅ ብታደርግ ታገኛቸዋለች:: ልንለያይ ስንል በነሸጣ እጆቼን ወጥሮ ይይዛል:: እንደ ተራበ ለማኝ በፅናት ይማፀነኛል:: ስሜን በብዙ ዜማዎች ይደጋግማል:: ለደቂቃዎች ሚሰልብ ሀሳብ ይገባኛል:: የ'ሱ መሆንን ስስ ቆዳዬ ይዳዳል:: ማንነቴን ያስጠፋኛል:: እምነቴን ያስከዳኛል:: ሰመመኔ ይተናል:: ድንገት እንዳልወደድኩት ሁሉ አጥንት ሚሰነጥቅ ብርድ ይሞላኛል::

ሜላትን በጭሱ መሃል ፈልጋታለው:: በለሊቱ ስለተዋጠው መልኳ እሳሳለው::

'ይደውልልሻል ሜ, don’t worry’

ቃላቶቼ የከሃዲ ናቸው:: ክንዱ ላይ ተንተርሼ ትኩስ እንባ ሲያርፍበት ፊቴን በቀስታ ወደ ፊቱ ይስባል:: በሜላት ልብ ላይ ምናወርደውን ቅስፈት በፍቅር ያሳባል:: እንባዎቼን ሲያብስ የ'ሱ የሆንኩ ያክል አስመስሎ ነው:: የጠላኝ አንድ ቀን ሳይጥል እንደዘነጋው ሀይላንድ ሳይራራ እንደሚያሽቀነጥረኝ ግን በልቤ አውቄ ነው::

'ስንት ሰአት ሆነ?'
'ለ11 ሩብ ጉዳይ'
'ህ...'

ማለዳ ሊገለጥ ጥቂት ሰአታት ይቀራሉ:: የቀረኝን አንድ ሲጋራ እያጨስኩ ብናኝ ትዝታችንን አነደዋለው …
👍3
🔥1
If by chance
A honey rained on us
And we celebrated by a kiss
What would be the absolute bliss
The honey or your lips?
🔥3❤‍🔥2
2
‘This black sunglass…’

He holds it with his elongated fingers. He makes everything fragile and precious when positioned in his hands.

‘I love … it’

He stills quietly. He looks at it as if they’re having a deep conversation.

‘But… it is … ruined.’

His emotions facade on his face. They’re unpredictable and unsettling like a sea at midnight. He puts the glass with its broken temple on the table. He suffers its pain. He suffers it with silence.

‘You know, it was simply a point of escape. It was a cover to hide. I felt safe wearing it till the point I felt insecure without it.’

His eyes escalate with each words. He finds a mirror, turn to it and search for himself. He gazed for a minute and finally smiled. He didn’t recognize that glimpse.

The sun will reflect on his eyes and then, finally, his brown eyes will respond, and it’ll hurt, but the secrecy isn’t escaping the pain but embracing it, making it your own.
👀2
In the mirror, I do not see my reflection but my feelings. It’s suddenly a disgust and spontaneously a muse. It’s not a paradox, it’s mimicry. What I feel stains my perception. How do you actually see me? What’s my name in your diary? Which split persona greeted you? Perception is conflicted by reciprocation. Am I a horror because you stepped on my shoes? Did you tell your father about me and my hotheaded reaction? Did you tell your mother about my kindness when I helped the elderly cross the road? Didn’t she love me? Didn’t I restore the ounce of faith towards humanity?

There is a depth in us we couldn’t comprehend. You don’t know me. I don’t know you. I don’t know me. You don’t know you.
Nostalgia bias rules us. Our mind plays tricks and suddenly what burned us in the past feels like warmth. What we were deceives us. We forget that yesterday has no fist on now. The past is a train you hopped off. It won’t come back. Don’t stand waiting. You’re liberated now. For better or for worse.
2
It's a mere detail. Your hands suddenly feel cold. The goodbye roughens. The possibility scares you. You might never see them again. The feeling fills you like a butterfly. You reminisce the days you wasted. You lengthen your hug to make up for the future. The 'maybe' dims. The feeling reappears as a lesson. You start to love with depth. Your gratefulness blossoms.

At the end, when it's all said and done, you'll find it irresistible.
የሺሀረግ ሆንሽብኝ::

የሺዬ... ማህሙድ አህመድ የልብ ልብ ሰጠሽ::

እንደወለል ሚበርድ አልጋ ላይ ነበርኩ:: ትኩስ እንባ በጉንጬ ይፈሳል:: እንባው የመተከዝ አይደለም:: የተስፋ መቁረጥ እንጂ:: ከሃዘን ይከፋል:: በሃዘን ውስጥ ተስፋ አለ::

የሴት አያቴ ሰርግ ፎቶ ከፍ ብሎ ተሰቅሏል:: እንደጥጥ ሚያበራ ግዋንት ጣቷን ሸፍኗል:: ወንዱ አያቴ ጠይም ፊቱን ጨምድዷል:: ረጅም ትከሻው ሱፉን ይሞላዋል:: እዛ እንደነበርኩ ሁሉ የሽቶ መአዛ ይወረኛል:: ሴት አያቴ የሾለከ ፈገግታ ፊቷን ያደምቀዋል:: መልኳ ሚዜምለት ነበር:: ምን ያህል ጊዜ ይሆነዋል ይሄ ፎቶ? አርባ ሃምሳ አመት? ጊዜ ግፈኛ ነው:: የሺዬ... ጊዜ ግፈኛ ነው:: ለኩራትሽ ኢምንት ርህራሄ አይኖረውም:: አባትሽ ቤት ያወዛሽ ጮማ ይቅርብሽ:: ነይ... በ'ኔ ልብ ተክዢ::

አባይ እንደዋጣት ሴት አትሆኝም:: ፅልመት ጨለማ ውስጥም... ፈራጅ በማይኖርበትም... አልጥልሽም:: ገላጋይ በሚታጣበት ወና ምድርም አንጣላም:: ጠጅ እንደ ወንዝ በሚቆርበት ከተማ ውስጥም ካ'ንቺ ጋር ካልሆነ አልሰክርም:: ውርጭ ለሊት ላይ ጋቢሽ ነኝ:: ብርሃን ቢክድሽ መሪሽ ነኝ:: ይዤሽ ስነጉድ የትም ብሄድ አይከፋኝም:: በበርሃ የሙሴ በትሬ ነሽ:: አባይ ጎርምሶ ግብፅ ቢወስደን መውጫ አለን::

አባትሽ ሳቀብኝ:: ፍቅር... የሞኝ ተስፋ ነው ብሎ:: የሺዬ... እኔ ሁለቱንም ሆኛለው...ሞኝም ተስፈኛም:: ጥጋብሽ ፈተነኝ:: ፍቅርሽ እልሀኛ አረገኝ:: የእጅሽ እትማት ደረቴን እስኪያቀልመው ማልዳለው:: በጨረቃ ይዤሽ እስክጠፋ መዘዙን ውጠዋለው:: የማይጠፋብኝ ህልሜ ነሽ::

የሺሃረጊቱ...
ይራቅ እንጂ አይቀርም...
👏2❤‍🔥1
2025/10/22 07:47:47
Back to Top
HTML Embed Code: