በእንተ ቅዱሳን:
አእማደ ምስጢር
አምስቱ አእማደ ምስጢር
እነማ ናቸው እንማራቸው
እነማ ናቸው እንወቃቸው
እነዚህ ናቸው እንወቃቸው
ምስጢረ ሥላሴ - - - እንማራቸው
ምስጢረ ስጋዌ - - - እንወቃቸው
ምስጢረ ጥምቀት - - - እንማራቸው
ምስጢረ ቁርባን - - - እንወቃቸው
ትንሳኤሙታን - - - እንማራቸው
#ምስጢረ ሥላሴ
የእግዚአብሔርን አንድነትን ሰብኮ ሦስትነትን
ምስጢረ ሥላሴ ነው የምንማርበት
ከአብርሃም አባታችን የተወረሰለት
ከዘፍጥረት ምዕራፍ አስራ ስምንት
#ምስጢረ ስጋዌ
አምላክ ወደኛ መጣ ከሰማያት ወርዶ
አዳነን ሰው ሆኖ ከማርያም ተወልዶ
ይኄ ምስጢር አምላክ ሰው የሆነበት
ምስጢረ ስጋዌ ነው የምንማርበት
#ምስጢረ ጥምቀት
በኤፌሶን መልእክት ምዕራፍ አራት
እንደተፃፈ ጥምቀት አንዲት ናት
የእግዚአብሔርን ልጅነት የምናገኝበት
ምስጢረ ጥምቀት ሁለተኛ ልደት
#ምስጢረ ቁርባን
ደሜን ጠጡ ሥጋዬንም ብሉ
ብሎ ተናግሯል ጌታ በወንጌሉ
የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ሁላችን
ምሥጢረ ቁርባንን መቀበል አለብን
#ትንሳኤ ሙታን
ጌታችን ሲመጣ በመጨረሻው ቀን
ፍጥረታቱ ሁሉ ይነሳል ከሙታን
እንደማንቀር እኛ ፈርሰን በስብሰን
በፍጹም እናምናለን ትንሳኤሙታንን
"በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ
አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ"
፩ቆሮ ፲፬፥፱
Join @mahbere_ab
Join @mahbere_ab
Join @mahbere_ab
አእማደ ምስጢር
አምስቱ አእማደ ምስጢር
እነማ ናቸው እንማራቸው
እነማ ናቸው እንወቃቸው
እነዚህ ናቸው እንወቃቸው
ምስጢረ ሥላሴ - - - እንማራቸው
ምስጢረ ስጋዌ - - - እንወቃቸው
ምስጢረ ጥምቀት - - - እንማራቸው
ምስጢረ ቁርባን - - - እንወቃቸው
ትንሳኤሙታን - - - እንማራቸው
#ምስጢረ ሥላሴ
የእግዚአብሔርን አንድነትን ሰብኮ ሦስትነትን
ምስጢረ ሥላሴ ነው የምንማርበት
ከአብርሃም አባታችን የተወረሰለት
ከዘፍጥረት ምዕራፍ አስራ ስምንት
#ምስጢረ ስጋዌ
አምላክ ወደኛ መጣ ከሰማያት ወርዶ
አዳነን ሰው ሆኖ ከማርያም ተወልዶ
ይኄ ምስጢር አምላክ ሰው የሆነበት
ምስጢረ ስጋዌ ነው የምንማርበት
#ምስጢረ ጥምቀት
በኤፌሶን መልእክት ምዕራፍ አራት
እንደተፃፈ ጥምቀት አንዲት ናት
የእግዚአብሔርን ልጅነት የምናገኝበት
ምስጢረ ጥምቀት ሁለተኛ ልደት
#ምስጢረ ቁርባን
ደሜን ጠጡ ሥጋዬንም ብሉ
ብሎ ተናግሯል ጌታ በወንጌሉ
የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ሁላችን
ምሥጢረ ቁርባንን መቀበል አለብን
#ትንሳኤ ሙታን
ጌታችን ሲመጣ በመጨረሻው ቀን
ፍጥረታቱ ሁሉ ይነሳል ከሙታን
እንደማንቀር እኛ ፈርሰን በስብሰን
በፍጹም እናምናለን ትንሳኤሙታንን
"በማኅበር እልፍ ቃላት በልሳን ከመናገር ይልቅ
አምስት ቃላት በአእምሮዬ ልናገር እወዳለሁ"
፩ቆሮ ፲፬፥፱
Join @mahbere_ab
Join @mahbere_ab
Join @mahbere_ab
#ተመስገን_ጌታዬ
ተመስገን (3) ጌታዬ
ባይሳካልኝ ባይሞላ ጓዳዬ
ባንተ ተሸፍኗል ጉድፍ ገመናዬ
#አዝ
ኑሮዬ ቢሆንም እጅጉን መራራ
ሕይወት ለኔ ከብዳ ብትሆንም ግራ
ሁሉን ነገር አንተ ለበጎ አድርገሃል
አምላክ ለስጦታህ ምን ይከፈልሃል
#አዝ
ያሰብኩት ባይሞላም ባይሳካልኝም
ተመስገን እላለሁ አልጎደለብኝም
አላፍርም ጠርቼህ አምናለሁ ጌታዬ
ሁሉ ባንተ ሆኗል ይድረስ ምስጋናዬ
#አዝ
ደመና ባይታይ ንፋስም ባይነፍስ
ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ስሙ ይወደስ
የጓዳዬን ምስጢር የሚያውቀው እርሱ ነው
በጎደለኝ ሁሉ የሚሞላው አለው
#አዝ
ኑሮዬ ቢሆንም እጅጉን መራራ
ሕይወት ለኔ ከብዳ ብትሆንም
ሁሉን ነገር አንተ ለበጎ አድርገሃል
አምላክ ለስጦታህ ምን ይከፈልሃል
Join👉 @mahbere_ab
Join👉 @mahbere_ab
Join👉 @mahbere_ab
ተመስገን (3) ጌታዬ
ባይሳካልኝ ባይሞላ ጓዳዬ
ባንተ ተሸፍኗል ጉድፍ ገመናዬ
#አዝ
ኑሮዬ ቢሆንም እጅጉን መራራ
ሕይወት ለኔ ከብዳ ብትሆንም ግራ
ሁሉን ነገር አንተ ለበጎ አድርገሃል
አምላክ ለስጦታህ ምን ይከፈልሃል
#አዝ
ያሰብኩት ባይሞላም ባይሳካልኝም
ተመስገን እላለሁ አልጎደለብኝም
አላፍርም ጠርቼህ አምናለሁ ጌታዬ
ሁሉ ባንተ ሆኗል ይድረስ ምስጋናዬ
#አዝ
ደመና ባይታይ ንፋስም ባይነፍስ
ኤልሻዳይ እግዚአብሔር ስሙ ይወደስ
የጓዳዬን ምስጢር የሚያውቀው እርሱ ነው
በጎደለኝ ሁሉ የሚሞላው አለው
#አዝ
ኑሮዬ ቢሆንም እጅጉን መራራ
ሕይወት ለኔ ከብዳ ብትሆንም
ሁሉን ነገር አንተ ለበጎ አድርገሃል
አምላክ ለስጦታህ ምን ይከፈልሃል
Join👉 @mahbere_ab
Join👉 @mahbere_ab
Join👉 @mahbere_ab
ሐዋርያው መነኩሴ
============
ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ ለነፍሴ
አ.ዝ---------------------------//
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አ.ዝ---------------------------//
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎተ ምህላው/2/
አ.ዝ---------------------------//
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተማፅነናል /2/
አ.ዝ---------------------------//
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ሥሉስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አ.ዝ-----------------------//
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነወ ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/
@mahbere_ab
@mahbere_ab
@mahbere_ab
============
ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ ለነፍሴ
አ.ዝ---------------------------//
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አ.ዝ---------------------------//
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎተ ምህላው/2/
አ.ዝ---------------------------//
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተማፅነናል /2/
አ.ዝ---------------------------//
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ሥሉስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አ.ዝ-----------------------//
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነወ ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/
@mahbere_ab
@mahbere_ab
@mahbere_ab
ጥር 18 የቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽሙ
…ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉስ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ
ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤
ከዚህም በኃላ እንደመጭመቂያ ሆኖ ከተሰራ የስቃይ መሳሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን
እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ
ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከስጋው ተለየች የሰማእቱን ሰጋ አቃጠሉት ፈጩት
አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ
ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም
መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ
ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ
በብሩ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማእቱን ስጋ
እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ
አረገ፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ
ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው
ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤
በኃላም በሰማእትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን "
ዝርዎተ አጽሙ " ስትል ቤተክርስቲያን ሰማእቱን አዘክራ ትውላለች፤ በስሙ በታነጹለት
አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ህጉ ውጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። ሁላችንም
በያለንበት የበዐሉ በረከት ተሳታፊ ያድርገን።
Join & share
👇👇👇👇👇

“እግዚአብሔርን ማመስገን እንዴት?”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
“ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ ክታቡ እጅግ ብዙ
ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ ይነግረናል፡፡ መንገር ብቻም ሳይሆን የጸጋን ኃይልና ታላቅነትም አብሮ ይነግረናል፡፡በዚህ የእግዚአብሔር ጸጋ ሰው በየጊዜው ይድናል፡፡ ያለዚህ ጸጋ ሰው ማለት በድን ነው፡፡
ወገኖቼ! በራሳችን ጥረት መዳን ሲያቅተን እግዚአብሔር እንዲሁ በጸጋው ስላዳነን እናመስግነው፡፡ ነገር ግን ምስጋና ሲባል እንዲሁ በቃላት ብቻ የሚቀርብ እንዳይመስላችሁ፡፡ ምስጋና እግዚአብሔርን በምግባር ይቀርባል፡፡ ንጹሕ ምስጋና ይሄ ነውና በሕይወታችን እናመስግነው፡፡ መልካም ምግባርን እየሠራን ስናመሰግነው አባታችን ክብሩ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ ስለዚህ ነፃ ከወጣንባቸው ቀንበሮች በመሸሽ ለአባታችን ንጹሕ ምስጋናን እናቅርብለት፡፡
ወገኖቼ! እስኪ ይህን በአንክሮ አስተውሉት፡፡ አንድ
ምድራዊ ንጉሥን ብንሳደብ ምን ይለናል? በጽኑ ቅጣት የሚቀጣን አይደለምን? መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ግን እንዲህ አላደረገብንም፤ ገና ጠላቶቹ ሳለን እንዲሁ ይበልጥ ወደደን፤ አከበረን እንጂ፡፡ እንኪያስ በአንደበታችን ብቻ የምናመሰግን አንሁን፤ ነቢዩ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፤ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው” ብሎ እንደተናገረው እንዳይሆንብን ነፃ ከወጣንባቸው
ቀንበሮች አብዝተን በመሸሽም ጭምር እናመስግነው
እንጂ /ኢሳ.29፡13/፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በአንድ ቦታ ፡- “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ” መዝ.19÷1 ሲል እንደተናገረ ሰው ገና በምድር ሳለ ሰማያዊ ሆኗል፡፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በመልካም ምግባር እንዲመላለስ በማድረግ ጸጋው ሰውን መልአካዊ አድርጎታል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት የምንመለከተው ይህንኑ ነው፡፡ ሰማያት እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑት ድምጽ በማውጣት አይደለም፤ ለሚመለከትዋቸው ግሩም ሆነው መፈጠራቸውን በመመስከር እንጂ በዝምታ ውስጥ የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ግን ከእነዚህ ሰማያት በላይ ነው፡፡ እነዚህ ሰማያት ፍጥረታዊት ፀሐይ ትመላለስባቸዋለች፤ በቅዱስ ጳውሎስ የነፍሱ ሰማይ ግን የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ይመላለስባታል፡፡የሰማይ ከዋክብት ሲፈጠሩ መላእክት አመሰገኑ፤ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ግን እግዚአብሔር “ለእኔ የተመረጠ ምርጥ ዕቃዬ ነው” አለ፡፡ ሰማያት በየጊዜው በደመናት ይሸፈናሉ፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ነፍስ ግን አንድ ቀንም ጕም ዙሮባት አያውቅም፡፡ በፈተና ወቅት እንኳ በጠራራ ቀን ከምታበራው ፀሐይ በላይ የቅዱስ ጳውሎስ ነፍስ ታንጸባርቅ ነበር፡፡ደመና አይጋርዳትም፡፡ ይኸውም በእርሷ ላይ ነግሦ ከሚታየው አማናዊው ፀሐይ የተነሣ ነበር፡፡”

"የቅድስት ሥላሴ ዕምነት የሃይማኖት መጨረሻ ናት፡፡
የሥላሴ ዕምነት መግቢያ በር ወልድ ዋህድ ብሎ ማመን ነው፡፡
የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ሥርዓት በዚህ የሥላሴ አርአያ ተመሠረተ፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም ለታመኑ የሕይወት መታወቂያ ማኅተም ነው ለዝንጉዎች ግን የጥፋታቸው ቁልፍ ነው፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የሕሙማን መፈወሻ የክፉዎች አጋንንት ማባረሪያ ነው፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የአስማተኞችን ወይም የጠንቋዮችን ጥበብ የሚያጠፋና የሟርተኞችን መርዝ የሚያበርስ (የሚያከሽፍ) ነው፡፡
ይህ ግሩም የሥላሴ ስም የበሽተኞች መድኃኒት የሙታን ትንሣኤያቸው ነው፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም አሸናፊ የሆኑ የሰማዕታት የገድላቸው ሞገስ የብሩካን ጻድቃን የጸሎታቸው የመልካም መዓዛ ሽታ ነው፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም የረከሱትን የሚቀድሳቸው የተዳደፉትን የሚያነጻቸው ነው፡፡
ይህ ግሩም የሆነ የሥላሴ ስም እንደ መጎናጸፊያ እጎናጸፈዋለሁ ከእንቁ እንደተሰራ እንደ እራስ ወርቅም እቀዳጀዋለሁ፡፡
በዚህ ግሩም በሆነ የሥላሴ ስም እታመናለሁ በመጎንበስም እሰግድለታለሁ፡፡
ለዚህ ግሩም አስፈሪና አስደንጋጭ ለሆነ የሥላሴ ስም በፊቱ ተንበርክኬ በደስታ እሰግዳለሁ፡፡"
(ሰይፈ ሥላሴ)

#የአበው #ጥንቃቄ
ምንም እንኳን ጾማችንና ሕይወታችን እንደ አባቶቻችን ባይሆንም ቢያንስ ግን የአበውን ብርታትና ጥንቃቄ ማንሳትና ማሳወቅ ግን ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡
እንደሚታወቀው በበዓለ ሃምሳ ረቡዕና ዓርብን ጨምሮ ምንም ዓይነት ጾም የለም
ይህን የምናደርገው ለበዓሉ ክብር ቢሆንም አበው ግን በዘመናት ሁሉ ለምግብ ወይም ለሆድ ያልኖሩ በመሆናቸው አስቀድመው በበዓለ ሃምሳ ውስጥ የሚገኙ የረቡዕና ዓርብን ጾም በዐቢዩ ጾም ውስጥ በጥንቃቄ እንዲካተት አድርገዋል፡፡
በዐቢይ ጾም ውስጥ ያሉት (ከሰኞ-ዓርብ) ያሉት ቀናት ብዛት፦ 8×5=40 ናቸው፡፡
በፍትሐ ነገሥት የተቀመጠው የዐቢይ ጾም የሰዓት ገደብ እንደሌሎቹ አጽዋማት 9:00 ላይ አይደለም፡፡
የሰሙነ ሕማማት አምስቱ ዕለታት ብቻ እስከ ምሽት 1:00 ወይም ኮከብ እስከሚታይ ድረስ ሲሆን የሌሎቹ 35 ዕለታት እስከ 11:00 ድረስ ነው፡፡
አሁን ከተለመደው 9:00 በላይ የሆነበትን ምሥጢር እናንሳ፦
ከ35ቱ ዕለታት የ3 ሰዓታት ልዩነቶችን ወስደን፦ 3×35=105 ሰዓታትን እናገኛለን፡፡
ከሰሙነ ሕማማት 4 ሰዓታት ልዩነት ወስደን፦
4×5= 20 ሰዓታትን እናገኛለን፡፡
በጠቅላላው 105+20=125 ሰዓታትን እናገኛለን፡፡
በበዓለ-ሃምሳ ውስጥ ሰባት ረቡዖችንና ሰባት ዓርቦችን እናገኛለን ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በሚሆነው ጾም ሰዓቱን ስናሰላ፦ 7 ረቡዕ =7×9=63
7 ዓርብ =7×9=63
በድምሩ 63+63=126 ሰዓታት ይሆናሉ፡፡
ይህም በአንድ ሰዓት ልዩነት ብቻ በዐቢይ ጾም ከዘጠኝ ሰዓት አትርፈን እንድንጾም ካዘዙን ሰዓት ጋር እኩል ነው፦Approximately 125 ~126 {~ን እንደ አቅራብ ስሌት ምልክት በመጠቀም)
ስለዚህ 125ቱ ሰዓቶች ለውጦች ናቸው ማለት ነው፡፡
ይህ ደግሞ የሚያሳየው፦
• የበዓለ ሃምሳዎቹ ረቡዕና ዓርብ አስቀድመው እንደተጾሙ
• አበው ስለ ጾም ያላቸውን ጥንቃቄ
• መናፍቃን በበዓል ምክንያት ጾምን ይሽራሉ ብለው ለመንቀፍ ምክንያት እንዳያገኙ ነው፡፡
(የጽሑፍ ምንጭ፦ ፍትሐ ነገሥት አንድምታ ትርጓሜ የእጅ ጽሑፍ፤
የቃል ምንጭ ፡-አባ ደሳለኝ አራጌ ዘምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም )::
አባቶቻችን በእንደዚህ ዓይነት ጥንቃቄ ያቆዩልንን ሥርዓት እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ይርዳን!!!
አሜን!!!
ነቅዐ-ጥበብ
👉 @mehereni_dngl

✝️✝️ እንኩዋን ለታላቁ "የጌታ ጾም (ጾመ እግዚእ)" በሰላም አደረሳችሁ ✝️✝️✝️
👉 @mahbere_ab
+*" ጾመ እግዚእ "*+
👉 @mahbere_ab
=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን
እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት:: "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው:: የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል::
+"7ቱ" አጽዋማት:-
1.ዓቢይ ጾም
2.ጾመ ፍልሠታ
3.ጾመ ሐዋርያት
4.ጾመ ነቢያት
5.ጾመ ድኅነት
6.ጾመ ነነዌ እና
7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::
+በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት
ድረስ መጾም ይገባል:: ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት
አለው:: ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ
አስፈላጊነቱ ነው:: "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ
ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ
መጠየቁ ይቀላል::
+ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ
እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን
መቃወም ነውና:: እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ
አለች:: የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል
እንከራከራለን::
+ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች
በጣም ይገርሙኛል:: ኃጢአትን ለመሥራት : ጾምንም
ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም:: እኛ ግን
¤ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2)
¤አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ.
13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን
እንጾማለን::
+የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው
እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ
ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11
ሰዓት ይጾማል::
በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ
ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል::
+ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ
ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል:: በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ
በጨው እየበላ: ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል::
በእነዚህ 55 ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ
አይጐሰምም:: ጸናጽል አይጸነጸልም:: ተድላ ደስታም
አይደረግም::
+አብዝቶ መብላት : ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም
እንዲሁ አይገባም:: ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡
በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን : በመዓልት ቅዳሴውን :
በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል::
+በእነዚህ 55 ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ
ልትሰለጥን ግድ ነውና:: ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ
ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው:: በዚያውም ላይ
ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን
መስማት (ማንበብ) ይገባል:: በትዳር ውስጥ ላሉም
መኝታን መለየት ግድ ነው::
=>ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም=
1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም
2.የጌታ ጾም
3.ጾመ ሑዳድ
4.የድል ጾም
5.የካሳ ጾም
6.አርባ ጾም
7.የፍቅር ጾም . . .
በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል::
=>የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ=
1.ጾመ ሕርቃል
2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል::
=>ጾሙን የሰላም : የፍቅር : የምሕረት : የፀጋ :
የበረከት ያድርግልን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡
=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ
በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ትን. ኢዩኤል 2:12)
✝️ወስብሐት ለእግዚአብሔር✝️