Telegram Web Link
✞ መርሕ ዘገነት

መርሕ ዘገነት /4/
አንቺ ነሽ/2/ ኪዳንምረህት

ቅድስት እመቤቴ የጌታዬ እናት /2/
ሆንሽ የተመረጥሽ ንፅሕት ቅድስት
አንቺ ነሽ /2/ ኪዳንምረህት

የሲና ሐመልማል የሰው ልጅ ህይወት /2/
አንቺን የመረጠ ይክበር መለኮት
አንቺ ነሽ /2/ኪዳንምረህት

አብ እሳት ወልድ እሳት መንፈስቅዱስ እሳት/2/
እባክህ ክርስቶስ ይህችን ቀን ቀድሳት
አንቺ ነሽ /2/ ኪዳንምረህት

አዘክሪ ድንግል ለልጅሽ በእውነት/2/
በደህና እንዲያደርሰን ለመጪው ዓመት
አንቺ ነሽ /2/ኪዳንምረህት

✝️ @mahbere_ab
✝️ @mahbere_ab
✝️ @mahbere_ab
✝️ እሰይ ነጋ

እሰይ ነጋ ( 2 ) ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኘ ነው (2)

በበደሌ ሳትፈርድትጠብቀኛለህ
ከኔ በላይ ለኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፍው ትጉ እረኛየ
ብርሀኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታየ

አዝ_________________

ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተው አሳልፌ
በሰላም ተኛለሁ ከክንድ አርፌ
ተመስገን ማለትን በብርሀን ጨለማ
 ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ

አዝ_________________

 ትናንትናን ታልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን
 ከንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን
 አንተ ባታነጋው የጨለመውን
  አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀ

አዝ_________________

    ሁሉም የሚሆነው እንደስራአቱ
    ባንተብቻእኮ ነው መጨለም መንጋቱ
    ስላደረክልኝ ምኔን ልክፈልህ
    ተመስገን ብቻ ነው ስላሴ ዋጋህ

አዝ_________________

በብርሀን ተተካ አስፈሪው ጭለማ
እንደኔማ ሳይሆን ምህረትህ ቀድማ
የኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው
በጥበቤ አይደለም በቦጎነትህ ነዉ

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

💚 @mahbere_ab 💚
💛 @mahbere_ab 💛
@maheber_ab ❤️
#የአባ_እንጦንስ_ምክሮች

✞ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት "በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ላለፈው አትጨነቅ፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።"

✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦ "በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው። ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።"

✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል። እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው።

✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።

✞ ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።

✞ ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን።

✞ ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።

✞ የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡

✞ ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡

✞ የቱንም ያህል በመከራ ቢወድቅብህ የቱንም ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍ ይህንን ለጌታዬ ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል እቀበላለሁ በል። ቀላል ይሆንልሀል። የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኃይል ነውና። በእርሱ ማእበሉ ፀጥ ይላል ሰይጣንም ይሸሻል።

✞ ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ ጠበቃ መሆን፤ መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡

(#ከተለያዩ_ጽሑፎች_የተሰበሰቡ)

@mahbere_ab
@mahbere_ab
@mahbere_ab
ማኀበረ አብ pinned «#የአባ_እንጦንስ_ምክሮች ✞ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት "በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ላለፈው አትጨነቅ፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።" ✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦ "በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው። ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን…»
✞ ​​የሲሎንዲስ ጥበብ

የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድሐኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ
ማርያም እወድሻለሁ/፪/

አዝ________________

ተጨንቄአለሁ ልንገርሽ
ምሥጥረኛዬ እናቴ ነሽ
ሠው የአልሠማውን ብርቱ ምሥጢር
ድንግል ሆይ ለአንቺ ለአማክር

ለቁሥለኛውም መድሐኒቱ
ለአዳም ዘር ሁሉ ነሽ ሕይወቱ
መፍትሔ አለ በእጅሽ
ተንበርክኬ ልማጸንሽ

አዝ________________

ሳልናገረው ይገባሻል
የውሥጤ ሁሉ ይታይሻል
ድርሽ እናቴ ተረጅኝ
ያለ አንቺ ለእኔ ማን አለኝ

ደሥታዬ ደሥታ የሚሆነው
በሐዘኔም የምጽናናው
አንቺ ከእኔ ጋር ስለ ሆንሽ
ተጽናንቻለሁ በሥምሽ

አዝ________________

ወንድሞቼ እንኳን ቢሸጡኝ
ሠው ሁሉ ጠላት ቢሆነኝ
በእመ አምላክ ሐይል ከብሬአለሁ
በጠላት ላይ ሠልጥኛለሁ

የረሱኝ ሁሉ የአስቡኛል
የተጣሉኝም የአከብሩኛል
አንቺ አንግሠሽኝ አልወድቅም
እቆማለሁኝ ዘለዓለም

አዝ________________

መንገዴ ረዝሞ ደክሜብሽ
መከራው በዝቶ ታምሜብሽ
ወድቄ ሳዝን ድረሽልኝ
ለባርያሽ ሐይሉን እንድትሠጪኝ

ፍቅርሽ በውስጤ ተንሠራፋ
በእናትነትሽ ልቤ ሠፋ
የሚለያየን ማንም የለም
ማርያም ልበልሽ ለዘለዓለም

መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✞ ​​ኃይልህ ሲገለጽ

ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ(፪)
አቤት ማን ይቆም ይሆን ከፊትህ
ማን ይቆም ይሆን

አቤት ቀንደመለከት ሲነፋ
አዋጅ ሲታወጅ በይፋ
ጻድቃን ሲጠሩ ለተድላ
ምን ይሆን የእኛ ተስፋ

አዝ________________

አቤት መላእክት ሰማዩን ሲያርሱት
ቀድመው ሲሰሙ መባርቅት
ያልታየና ያልተሰማ
ድምጽ ሲሰማ ከራማ

አዝ________________

አቤት ሰባቱ ነፋስ ተከፍተው
ምድርን ሲያውኩት ቀስፈው
ሲታዘዝ የባህር ሞገድ
ምድሪቱን ሊከድናት ለፍርድ

አዝ________________

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሠሩ ብሩካን
በምድር የሠሩት ትሩፋት
ሲያቀርቡ ለአምላክ ስብሐት

አዝ________________

አቤት ኃጥአን ለፍርድ ሲጠሩ
በጨለማ ዓለም ሊቀሩ
የማይጠቅም ዋይታ ሆኖ
መዋረድ ይሆናል አስሉ

አዝ________________

አቤት ሲጠሩ ጻድቃን ቅዱሳን
መልካም የሠሩ ብሩካን
በምድር የሠሩት ትሩፋት
ሲያሰሙ ለአምላክ ስብሐት

መዝሙር
ሊቀመዘምራን ይልማ ኃይሉ

" አምላካችን ይመጣል "
መዝ፶፥፫

✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
ሰዎች ፈረዱብኝ
መዝሙረ ዳዊት|በ ቴሌግራም|
✝️ ማኀበር አብ

ሊቀ-መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ

✝️ ሰዎች ፈረዱብኝ ✝️



✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✞ ገጼን አማትቤ

ገጼን አማትቤ ልጀምር ውዳሴ
በትምህርተ መስቀል በስመ ሥላሴ
ይርቃል ከጎኔ ጠላት ዳቢሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ከትቢያ ከአፈር አንስቶ የሰራኝ
በአፉም እስትንፋስ ህይወትን ያደለኝ
የሥላሴ ስራ ድንቅ ነው ጥበቡ
ከአይምሮ በላይ ነው የእግዚአብሔር ሀሳቡ

አዝ_________________

እክህደከ ሰይጣን ጠላቴን ክጃለው
ለዚህም ምስክር ማርያም ናት ብያለው
በቤተክርስትያን ቆሜ በመቅደሱ
ለቅድስት ሥላሴ ዘመርኩ ለንጉሱ

አዝ_________________

አልነበረም ዘመን እሱ ያል ነበረበት
ዳግመኛም አይኖርም እርሱ ማይኖርበት
የህይወቴ ጣእም ክብርና ሞገሴ
የማይሾሙት ንጉስ ዘላለም ሥላሴ

አዝ_________________

ኪሩቤል ሱራፌል ኃይላት ሊቃናት
መናብርት ስልጣናት ቆመው በአንድ ነት
ያላንዳች ዝምታ ይሉታል በክብር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ሰውነቴ ባንተ ፍቅር ተጠምዳለች
ውለታህን እያሰበች ታለቅሳለች
መከራው ተረሳ ትካዜም ቀረልኝ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ

ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር
ተፈቷ አየዋለው የልቤ ችግር
ወዳጄና አባቴ ምስጢር የተስፋዬ
ቀና እንድል አረከኝ በነፍስ በስጋዬ

አዝ_______________

በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላትህ
ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት
እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረኛል
ውለታህን ሳስብ ልቤ ይቀልጥብኛል

አዝ_______________

ልዩ እኮነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

አዝ_______________

ስለቴን ስትሰማ ሲጠብቀኝ ምልጃህ
ሳጉረመርምብህ ትታገሰኛለህ
የጭንቄ ማረፊያ የህመሜም ፈውስ
አርከ እግዚአብሔር ገብረመንፈስ ቅዱስ

አዝ_______________

ልዩ እኮነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳትሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ

✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
✝️ @mahbere_ab ✝️
Channel photo updated
Forwarded from መሐርኒ ድንግል (Måň)
እኛ የመሐርኒ ድንግል ተከታዮች እና አድሚኖች ግበረ ሰዶምን እንቃወማለን!

ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር

We, the followers and admins of Meharni Dungal, are against Gebre Sodom!

Long live Orthodoxy
#share
@mehereni_dngl
@mehereni_dngl
🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻 አዲስ 🌻🌻
🌻🌻 ዓመት 🌻🌻️
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌼🌻🌻🌻🌻🌻️🌼

🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼 @mahbere_ab 🌼
🌼 @mahbere_ab 🌼
🌼 @mahbere_ab 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Channel photo removed
Channel photo updated
መሐርኒ ድንግል

የወር አበባ ሴት ልጅ ፈጣሪ ለመደበላት ዕጥፍ የሕይወት ሚና ማለትም ሚስት እና እናት ለመሆን መድረሷን የሚያመለክት በመሆኑ ሳትከፍ በጸጋ ትቀበለው ዘንድ ይገባታል ። (ሕይወተ ወራዙት)
Channel name was changed to «ማኀበረ አብ»
🥹
Forwarded from Nice creative
Give away አዘጋጅተናል ለ1 ወር የሚቆይ እሱም ሎጎ በነፃ ማሰራት የምፈልጉ ከዛሬ 2/11/2017 ጀምሮ እዳያመልጦት


በውስጥ ያናግሩን
👉 @nice_creative_bot
2025/09/16 05:51:12
Back to Top
HTML Embed Code: