Telegram Web Link
ተለቀቀ ተለቀቀ
🎉🎉🎊🎊🎊🎈🎈🎈🎈
ታሪኩ ቶሎ ቶሎ #Share አድርጉ ብዙ እይታ ካለው ቶሎ ቶሎ ይለቀቃል።
አሰላሙ ዐለይኩም

ከደቂቃዎች ብኋላ ተወዳጁ ትረካ ክፍል 9 ይለቀቃል።

የቴሌግራም ፕሮፋይል

join ያድርጉ ቻናሉን @mahbubil
👍2
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 9



 እንደምንም ብሎ የሰኞ የሀሳብ ለሊት አልቆ ማክሰኞን ተካ ወደ ምማርበት ቦሌ Priparatoty   ጓደኜቼ ጋር ትምህርት ቤት ተገናኘን ደብረዘይት የሰራሁት ወንጀል ያዩኝ ያዩኝ ይመስል ፈራሆቸዉ እንደዚህ ወንጀል መስራት ያሳፍራል ማለት ነዉ?? ሂክማ ትናንት የቀረሽዉ በሰላም ነዉ እያሉ በጥያቄ አፋጠጡኝ ..ጓደኞቼም አይፈረድባቸዉም ከትምህርት ቀርቼ አላቅም ስቀር ተደናግጠዉ ነዉ፡፡
........እኔም አዎ እቤት ስራ ይዤ ነዉ ብየ ሌላ ዉሸት ዋሸሁ፡፡ ዉሸትን ለመደበቅ ግድ ሌላ ዉሸት አይደል የምንሰጠዉ  ከጓደኞቼን ሰላም ተባብለን ወደ ክላሳችን ገባን፡፡

መምሆሮቹም እንደ ጓደኞቼ ጠየቁኝ በሰላም እደቀረሁ ነገርኳቸዉ፡፡ ክላስ ሁኜ በሰራሁት ስራ በቃ እየገረመኝ የሆነ የማላቀዉ ነገር የወረረኝ ይመስለኛል፡፡ በጓደኝቼ በመምህሮቼ ተወዳጅ እንደ ሂክማ ሁኑ የምባለዉ ልጅ ከአሁን ቡሀላ አይደለሁም እፍረትም ተሰማኝ፡፡ ከትምህርት ስወጣ ደወልኩለት አንስቶ ትንሽ አዉርተን ወደ ቤቴ ሆድኩኝ ፡፡
     ግን እቤቴ ከገባሁ ቡሃላ ማታ ተኝቼ ከየት መጣ የማይባል ፍርሀት ወረረኝ ምን ሆኜ ነው?? ምን ነካኝ ብየ ራሴን ጠየኩ መልስ ባላገኝም
.........ከዚህ በኃላ የኔ ህይወት በሀይደር እጅ እደሆነ ገባኝ አሁንስ ቢተወኝ አልፈልግሽም ቢለኝ ብየ ሳስብ የምሆነውን አጣሁ ይህ ሀሣብ ውስጤ ላይ የፈጠረው ፍርሀት ይሁን ቁጭት ባላውቅም ጩሂ ጩሂ አለን ግን ደግሞ ለመጮህም ምክንያት ያሥፈልጋል ፡፡
ጠዋት ወደ ትምህርት እየሄድኩ ስደዉልለት ስልክ አያነሳም ነበር፡፡ ምን ሆነ እያልኩ አሰብኩኝ እሱም  ከትምህርት ስንለቀቅ  ደወለልኝ  ሂኩ አሁን ለማዉራት የማይመች ቦታ ነኝ መልሼ እደዉላለሁ አለኝ ፡፡ እኔም እሺ ብየ የደስደስ ነገር ተሰማኝ፡፡ ግን አልደወለም፡፡ በመነገታዉም  ትምህርት ቤትም ቢሆን ስልኬን ደብቄ ይዤ ነዉ የዋልኩት ግን ሙሉቀን አልደወለልኝም ለምን ይሆን ???

  የውስጥ ህመም ሆነብኝ  በፊት በእረፍት ሰአት  እና ከትምህርት ስንለቀቅ አስቦ የሚደዉልልኝ ሀይደር ይህን ሁለት ሶስት ቀን ግን  አልደወለም፡፡ እቤቴ ገባሁ  telegram ላይ ስገባ on line ነበረ፡፡ አላህ ይወቅ telegram on line መግባቴን አይቶ እንደሆነ አላቅም ወዳዉ ደወለ ፡፡
......እኔም አነሳሁት ሂኩ በጣም ይቅርታ ስራ ላይ ቢዚ ሁኜ ነበር ያልደወልኩት አሁንም ለማዉራት አይመችም ታቂያለሽ እቤት ቤተሰቦቼ ስላሉ ማታ ማታ ስልክ እንደማላወራ አለኝ፡፡ እራት በላሽ ብዙ ነገሮችን አዉርቶኝ.....  ደግሞ እንዳትረሽ አወድሻለሁ አለኝ እኔም እወድሀለሁ ብየ ሥልኩን ዘጋሁ
.....እወድሻለሁ ስላለኝ ደስ አለኝ 

ግን ቀናቶች በሂዱ ቁጥር  እንደበፊቱ ሁሌ መደወል ቀዘቀዘብኝ telegram ስገባ አላገኘዉም ፡፡ አንድ ቀን በሂወታችን በጀመርን ቁጥር ይህ ቀን ለመሞታችን እየቀረብን ነዉ፡፡ እኔ ከዛሬ ነገ ይስተካከላል ሁሉም ነገር ቦታ ይይዛል ስል  ሀይደር እየራቀኝ ስልክም መደወል እያቆመ መጣ በጣም ግራ ተጋባሁ፡፡ደግሞ ለኔ መርዶ የሆነ profile pictur አየሁት ለጊዜዉ በዚህ acount  ስለማልጠቀም በዚህኛዉ ነዉ የምታገኙኝ ብሎ profie አርጎታል፡፡ በጣም ግራ ገባኝ ሌላወን ቁጥሩን አላቀዉም፡፡  ...

በጣም ከምነግራችሁ በላይ ተጨነኩኝ ተወዛገብኩኝ፡፡ 
......በመጥፋቱ ብናደድም ቢያንገበግበኝም ግን ስራ ስላልተመቻቸለት ነው ይደውላል እወድሻለሁ ብሎኛል እያልኩ ራሴን ለማሳመን ከራሴጋር ሙግት ገጠምኩ ያለፈውን የፍቅር ወሬ በህሊናየ እየሳልኩ እፅናናለሁ በtelegram ያወራናቸዉን message እያየሁ እገረማለሁ መልሼ  እንደ መፅሀፍ ከላይ ጀምሬ ማታ ማታ አነባቸዋለሁ፡፡በዚህ መልኩ ቀን ቀንን እየተካ 20 ቀን ሆነን በዚህ ቀናት ውስጥ ሶስት ቀን ብቻ ደውሎልኛል በፊት በቀን ሁለቴ ሶስት ጊዜ ይደውል ነበር  እኔ ስጋት ውስጥ ነኝልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡
...... በአንድ በኩል ቢተወኝ ምንድነው የምሆነው?? እላለሁ መልሽ ደግሞ ቃል ገብቶልኛል ሙስሊም ነው ለዛዉም አላህን ፈሪ ነዉ ፡፡እንደዚህ አያደርግም እላለሁ ሀሳቤ ተበታትኗል፡፡
አሁን መደወል አቆመ ግራ ገባኝ አላስችለኝ አለ፡፡ ስደዉልለት ስልክ አያነሳም .......
........በሌላ ሰዉ ስደዉልበት ያነሳዉና...የእኔ ድምፅ መሆኑን ሲያዉቅ ይዘገዋል፡፡ በጣም ተጨነኩ ግን ይተወኛል ብየየየየየየየየየየ አስቤ አላቅም ፡፡ ሀይደር ምን ሆነብኝ ሀይደር ምን ሆነብኝ ሀይደር ምንሆነብኝ?? ሁኗል ሀሳቤ ፡፡ ስልክ እየቀያየርኩ መደወል አልተዉኩም፡፡ የእኔ ድምፅ መሆኑን ካወቀ አንስቶ ይዘገዋል፡፡ telegram የሚጠቀምበትንም ቁጥር ቀይሯል በምን ላግኘዉ ፡፡ ተጨነኩኝ ወይኔ
ሂክማ የምሆነውን አጣሁ በሀሣብ ታመምኩ

ክላስ ቁጭ ብየ የሂሳብ መምህራችን ታሞ አልመጣም ነበር ...እስኪ ሀይደርን facebook ላይ ልፈልገዉ ብየ... በስሙ ፈለኩት ላገኘው አልቻልኩም ፡፡ ግን እሱ  ለራሱ ያወጣም ስም አለ ነግሮኝ ነበር በስሜ ከምጠሪኝ ሱደይስ ብለሽ ጥሪኝ የመጀመሪያ ልጄ ስም ሱደይስ ነዉ የምንለዉ ይለኝ ነበር ስሙንም እወደዋለሁ በእሱ ጥሪኝ ይለኝ ነበር ፡፡ ትዝ አለኝ.. ከዛ fb ላይ ሱደይስ እና የአባቱን ስም አንድ ላይ ፅፌ search አረኩት ፡፡ ብዙ ሱደይስ ቢኖሩም የአላህ ነገር የfb....profile pictur ፎቶ ነበር ይገርማል ፎቶ profile ማረግ ወንጀሉ ለሴቱ ብቻ ነዉ እያልኩ ተገራረምኩ እኔን ፎቶ አታርጊ ብሎ የመከረኝ ሀይደር እሱ ፎቶ አርጎ አገኘሁት ..አሁን ይሄን የማስብበት ጊዜ አይደለም ብቻ እሱን fb ላይ ማግኘቴ በጣም ደስ አለኝ በface book እናወራለን አልኩኝ ብቻየን አወራለሁ የዋህ ነኝ እኮ፡፡

     face book ላይ time line እና profile pictur ማየት ጀመርኩ፡፡ profile pictur ሳይ  ያየሁትን ማየት አቃተኝ ድርቅ ብየ ቀረሁ፡፡ ልቤ ምቱን ያቆመ መሰለኝ እንባየ ይፈሳል አፌ ቃል ማውጣት ተሳነኝ ከጎኔ ያሉት የክፍሌ ልጆች ሂክማ ማን ሆንሽ ሂክማ ምን ሆንሽ ሲሉኝ እሰማለሁ፡፡ ዉሀ እምጡ እያሉ ተማሪዉ ሲጮህም እሰማለሁ ትንሽ ትንሽ ..ከዛ ቡሀላ ግን ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም..... ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ.....ሲወስዱኝ ለራሱ አላስታዉስም ....ብቻ ማታ 4 ሰአት ነዉ የነቃሁት ስባንን እኔን ያገኘሁት ኮሪያ ሆስፒታል ነበር እራሴን ስቼ ተኝቼ ከጎኔ እናቴ እና የክፍል ጓደኛቼ ሶስት ልጆች አሉ፡፡

ሂክማ ምን ሁና ነዉ እራሷን የሳተችዉ ...ምን አይታ ነዉ በfb time line ላይ የሀይደር profile pic  ሀኪም ቤት እስከምትገባ ድረስ የሚለዉን ?????
በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን፡

ክፍል 10 ይቀጥላል

Join👇👇

https://www.tg-me.com/mahbubil

Youtube accunt
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC3NmNDSUYHCMWyUKocMaSYw
👍9😢3
አሰላሙ ዐለይኩም ጀመዓው

ውድ የቻናላችን ተከታታዮች የአሏህ ፍቃድ
ሆኖ ተከታታይ አስተማሪ ታሪኮችንን በቆሚነት በፕሮግራማችንን እየለቀቅን ነው አሁን ደሞ የአሏህ ፍቃድ ሆኖ ኢስላማዊ ወዝ ያለቸው ''የህይወት ለውጥ '' የሚል ስያሜ የተሰጠው ስለ ለውጥ የሚያነሳ በራስ መተማመን:መከባበርን:ማንነትን መፈተሻ:ክሎታችንን ማግኛ: ፍልጎታችንን ማወቂያ ....ወዘተ ሀሳቦችን የሚዳስስ ፕሮግራም ለመጀመር አስበናል።

በvote አሳውቁን ሀሳባችሁን

ዋና ማነጀር

ለማግኘት @maganhadra

ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇
@mahbubil

Vote👇👇👇
👍8👎1
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣0⃣



    Face book ላይ profile pic ሳይ ደነገጥኩኝ
የምናገረዉ ጠፋብኝ እክፍል ዉስጥ ወድቂያለሁኝ
......ሀኪም ቤት እራሴን ስቼ ማን እንደወሰደኝ እንኳ የማቀዉ ነገር የለም  ......የወደፊት ባሌ ብየ የሴትነት ክብሬን የወሰደዉ ሀይደር ባለ ትዳር ነዉ፡፡

...,..,fb profile እና time line ብዙ ፎቶዉች አሉ ለሰርጋቸዉ ጊዜ አብረዉ የተነሱት ....ምን ልበል ያዉ የምናገረዉ የለኝም ብቻ በማለቀዉ ድንጋጤ እራሴን ስቼ ሀኪም ቤት ገብቻለሁ፡፡
..... የተኛሁበትም ሆስፒታል እኛ ሰፈር ገርጂ  አቅራቢያ የሚገኘዉ  ኮርያ ሆስፒታል ነዉ፡፡ ሆስፒታል ሁኜ ልረጋጋ አልቻልኩም፡፡

 አባቴም ሸዋሮቢት ከተማ የመንግስት ሰራተኛ አይደል መታመሜን ሲሰማ ጊዜ ሳይፈጅ  መጣ ፡፡ አልናገር ምግብ ለራሱ ብዙም አልበላም ግልኮስ ተተክሎልኛል፡፡ ብቻ በሁለቱም ጉንጬ እንባየ ሲረግፍ ነዉ የሚዉለዉ፡፡ እናቴም በእኔ ሁኔታ ተደናግጣለች የምትዉለዉ የምታድረዉ እኔዉ ጋር ነዉ...እኔ እያለቀስኩ የእናት ሆድ አያስችል አብራ ታለቅስ ነበር፡፡
....እኔስ መናገር ያልቻልኩት የዋጥኩት እሳት ነዉ የሚያስለቅሰኝ.....እናቴ ግን ልጇ ስለሆንኩ መናገር ስለማልችል ሳለቅስ ብቻ ታለቅሳለች፡፡
........ኮርያ ሆስፒታል አምስት ቀን ተኝቼ ህክምና ወስጄ ወደ ቤቴ ተመስኩ፡፡ ግን ምን እንደሆንኩ አላቅም አፌ እንደበፊቱ አቀላጥፎ ማዉራት አልቻለም ፡፡ ምን ሁነሽ ነዉ ??ምንሽን ይሰማሻል ??ይሉኛል... እኔ የሆንኩት ሌላ ለሰዉ የማይነገር ...መልስ የሌለዉ ጥያቄ ነዉ፡፡
......አባቴም የያዛት ጅን ነዉ ተብሎ የሰፈራችን ጀመአዎች አሉ፡፡ ማታ ላይ ሳልሰማ መጥተዉ እስከ 4 ሰአት ቁርአን ቀሩብኝ፡፡ እነሱ የሆንኩትን አያቁም ...ቁርአን ቀርተዉ ምንም የጅን ምልክት ስላላገኙ ....አንዱ ቁርአን ከሚቀሩት አረ ይሄ ጅን አይደለም እናቁም ብለዉ አቁመዉ ሄዱ፡፡
...,.ግን ጅንም ባይሆን ለኔ ቁርአን መቀራቱ ትንሽ ለዉጥ አመጣሁ ማዉራት አፌ መንቀሳቀስ ትንሽ እየከፈተልኝ ነዉ፡፡

አባቴ አላስቻለዉም እኛ ሰፈር ያለዉ ኢብኑ አባስ መስጊድ ዉስጥ ታዋቂ የጂን የሚቀሩት ልጆች አሉ ተብሎ ተነገረዉ፡፡ ማታ ላይ ከመቅሪብ ቡሀላ እቤት ይዟቸዉ መጣ ፡፡ እኔ ሁሉን በሆዴ ይዠዋለሁ ፡፡ መናገር የማልችለዉ ነገር ነዉ፡፡ ከኢብኑ አባስ መስጊድ የመጡ ጀመአዎች ማታ ላይ ሲቀሩብኝ  አመሹ ለዉጥ የለም ያዉ ነዉ፡፡

ግን ቁርአን በተቀራብኝ ቁጥር ልቤ በጭንቀት በሀሳብ አልተረጋጋም ብቻ ግን የተያያዘዉ አፌ  እየተፍታታ ነዉ፡፡
እናቴ ደግሞ ሰፈሩ አሉ የሚባሉት ትላልቅ ሴቶችን ጠርታ ቅዳሜ ቀን በግ ታርዶ ምሳቸዉን አብልታ ከምሳ ሰአት የጀመሩ እስከ መቅሪብ ድረስ ዱአ ሲደረግልኝ ዋለ፡፡ ከእኔ በላይ ቤተሰቦቼን አስቸገሪኩ፡፡

ቤተሰቦችን አስጨነኳቸዉ ለነገሩ አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ ምን ያርጉ አባቴም የመንግስት ስራዉን ከሸዋሮቢት አስፈቅዶ መጥቷል፡፡ እናቴም ጭንቀቷ እኔ ሁኛለሁ ስታየኝ በስስት ሳለቅስ የምታለቅሰዉ ከእኔ በላይ ነዉ፡፡ እኔ ተረብሼ ቤተሰቦቼን እረበሽኩኝ በእኔ ፀባይ  መቀያር እነሱ ተረበሹ በጣም አዘንኩ፡፡

አላህ የዉመል ቂያማ ሲጠይቀኝ መልሴ ምን ይሆን???  የወላጆቻችሁ ሀቅ አደራ
እያለ በቁርአን ነግሮኝ ነብዩ ሙሀመድ ሰ ዐ ወ ጀነት ከእናት እግር ስር ናት ብለዉን ....እኔ ግን ገና ሀይደር ያገባኛል ብየ አምኘዉ እሱ ጋር ወንጀል ሰርቼ ለዛዉም ባለትዳር ሆኖ በራሴ ባለመጠንቀቅ በተጎዳሁ በራሴዉ ጥፋት ቤተሰቦቼን አሰቃይ ይዣለሁ፡፡ አላህ በስንቱ ነዉ የሚቀጣኝ??? አንድ ዚና በመስራቴ ሁለት ወላጆቼን እነሱ በማያቁት ነገር ማስጨነቄ ማስቸገሬ....  ኡፍ እንኳን እንዳትሉ የተባልኩትን ወላጆች በእኔ መረበሽ ማልቀስ ከጀመሩ አንድ ወር ሆናቸዉ ፡፡ ብቻየን እያሰብኩ መኝታ ክፍሌ ገብቼ አለቅሳለሁ፡፡
       አንድ የእናቴ ወንድም አለ ....ደሴ ከተማ የሚኖር ደሴ ትምጣ እዚህ ጥሩ የጂን የሚቀሩ ቁርአን ቀሪዎች አሉ ብሎ ይደዉልላታል፡፡ እናቴም ምንም ይሁን ምንም እኔ አንድ ፍሬ ልጇ ሳለቅስ ስጨነቅ ማየት አልፈለገችም ፡፡ እኔም ሁሉን በሆዴ ደብቄ እነሱ የሚሉኝን እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡

እናቴ ጋር አብረን ከ አዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር ወደ ምትገኘዉ የወሎእምብርት  ደሴ ከተማ ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ጠዋት ተነስተን 8:30 ደሴ ከተማ ገባን፡፡ አጎቴ ተቀብሎን መኖሪያ ቤቱ አረፍ አለን፡፡ ጠዋት ላይ ደሴ ከተማ የሚገኘዉ ተቋም አካባቢ የሚገኘዉ ጦለሀ መስጊድ በብዙ ጀመአ በተሰበሰበበት ቁርአን ቀሩልኝ ከአዲስ አበባ ለየት ያለ አቀራር ነበር፡፡ ግን አብረዉ የሚቀራባቸዉ ጅን የያዛቸዉ ነበሩ የእነሱ ብዙም ሳይቆይ ለቀቀ እኔ ግን ሁሌን በሄዴ ይዤ ቤተሰቦቼን ዘመዶቼን እያስቸገርኩ እያስጨነኩ ነዉ፡፡ በመነገታዉ ማታ ላይ ደግሞ ደሴ ከተማ የሚገኘዉ አሬራ አካባቢ አሬራ መስጊድ ከመቅሪብ ቡሀላ ቁርአን ተቀራልኝ ፡፡ ሁለት ቀን ከተቀራብኝ ቡሀላ አጎቴ ደሴን አሶገበኝኝ አዝናናኝ ፡፡ ደሴ ከተማን አንድ ሳምንት ቆይቼ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩኝ፡፡

አዲስ አበባም እንደተመለስኩኝ ጓደኛቼ የክፍል ተማሪዎችም እየመጡ ይጠይቁኝ አጫዉተዉኝ ይሄዱ ነበር፡፡
ትምህርት ካቆምኩ አንድ ወር ሆነኝ
......አዲስ አበባ የሚኖረዉ አጎቴ አልፎ አልፎ እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር ፡፡
ዛሬ ግን እቤት መጥቶ አንድ መፍትሄ አለኝ ሲል ሰማሁት ለምን አታገባም ??? እኔ እኮ ዳረኝ ብለዉ የጠየቁኝ አሉ ሲል መኝታ ክፍል ሁኜ ሰማሁት...እኔም ደነገጥኩኝ....

#part 1⃣1⃣

ይ............ቀ................
............ጥ..............ላ................ል
ሼር በማድረግ ለሁሉም ያድርሱ

https://www.tg-me.com/mahbubil

የYoutube ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC3NmNDSUYHCMWyUKocMaSYw
👍43
በደንብ አንብበው ያሙሂብ

ሙሂቦች ከሚናገሩት ንግግር በጣም ሚአጅበኝ ነገር ይህ ንግግር ነው።

"አንድም ሰለወት ለማውረድ አትችልም ሰይደል ዉጁድ ሰለላሁ አለይሂ ወአሊሂ ወሰለም የፈቀዱልህ ቢሆን እንጂ"

ይህን ንግግር በደንብ አጥብቀህ ያዝልኝ ከዛም ወደ ሁለተኛው ንግግራቸው እንሂድ፦
"ሁሌ ከምታወርደው ሰለዋት ዊርድ አርገህ ከያዝከው ሰለዋት ትንሽ ከቀነስክ ነፍስህን በጣም ተመራመራት"
እስኪ እንተንትነው፦ምሳሌ በቀን ሺ ሰለዋት ምታወርድ ከሆነ ከዛም ኣንድ ቀን ግን ዘጠኝ መቶ ከሆነብህ መቶውን ካጎደልከው ነፍስህን ተመራመር ምን ወንጀል ሰርተህ ነው? ሰይደል ዉጁድ መቶ ሰለዋቱን እንዳታወርድ የከለከሉህ? ለምን ከለከሉህ?ሁሌም ይሄንን ንግግራቸውን በደንብ አስብበት።

ፋ ያለች ኸሚስ

ከሰይድ Hamid Hamido 🙏💚 Fb የተወሰደ የሩህ ቀለብ

@mahbubil
8👍1
Watch "salatu rabi //madih muhammed amin //#newmenzuma #ya_alemu_shum" on YouTube
https://youtu.be/DKsrhSbg7W0
👍2
Watch "salatu rabi //madih muhammed amin //#newmenzuma #ya_alemu_shum" on YouTube
https://youtu.be/DKsrhSbg7W0
👍2
👆👆👆👆👆
በyoutube ቻናላችን ላይ ተለቋል
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣1⃣

     አጎቴ እቤት መጥቶ አንድ መፍትሄ አለኝ  ለምን አታገባም ??? ሲል መኝታ ክፍል ሁኜ ሰማሁት .......   እኔ እኮ ተማሪ ናት እያልኩ ነዉ እጂ ብዙ ሰወች ጓደኞቼ ለራሱ  ለምን አትድረንም አግብቻት እኔ ጋር ሁና አስተምራታለሁ ያሉኝ አሉ፡፡ ግን እኔ ትምህርቷን ትጨርስ ለእናንተም ማዉራት አይሆንም ትላላችሁ ብየ ዝምታን መርጬ ነዉ ብሎ ለእናቴ ሲናገር ሰማሁት ...

እናቴም እኔንም ብዙ ሰዉ ጠይቆኛል ግን ትምህርቷን ትጨርስ ብየ ነዉ፡፡ እሷም አስራሁለተኛ ክፍል ተፈትና ዉጤትም ቢመጣለት ዩኒቨርስቲ አትገባም ተነጋግረን እሺ ብላኝ ነበር፡፡ አላህ ያለዉ ሆነ እንጂ ይሄዉ ልጄ በሽታዋ ሳይታወቅ ታማለች አሁን ዱአየ አላህ እንዲያሽራት ነዉ፡፡ ጤናዋን ካገኘች ቡሃላ ስለ ሂክማ ትዳር አስብበታለሁ ብላ እናቴ እንባ እየተናነቃት ለወንድሟ ነገረችዉ ፡፡ እኔ እነሱ የሚያወሩትን  ወሬ ስሰማ እዛዉ መኝታ ክፍሌ አለቀስኩ ለምን ለትዳር ብቁ አይደለሁም...ሀይደር አዋቂ መስሎ ሸዉዶኛል የወደፊት የትዳር አጋሬ ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ቢጠይቀኝ ምን መልስ አለኝ????
      ወደ ትምህርት እንዳልመለስ ከወር በላይ አለፈኝ ካቋረጥኩ ፡፡ አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛየ እቤት መጥታ ትምህርቱን ዘንድሮ የማቀጥይ ከሆነ ለምን  ጃክሮስ ሰፈር አካባቢ ጃክሮስ መስጊድ አለ  እዛዉ አካባቢ ሴቶች ተሰባስበዉ ኪታብ የሚቀሩ አሉ እነሱ ጋር ኪታብ አቀሪም??? ብላ አመላከተችኝ፡፡
ከዛም ቅዳሜ ቀን ወስዳ የሚቀሩበትን ቦታ እና አልፎ አልፎም መስጊድ እንደሚቀራ ነገረችኝ፡፡
እዛ ኪታብ መቅራት ጀመርኩ እንደገና ወደ ዲኔ ለመመለስ ወሰንኩኝ ፡፡
   ኪታብ እየቀራሁ አላህን ማረኝ እያልኩ እያለቀስኩኝ ነዉ፡፡ የጀመአ አሚራችን ፊርዶስ ትባላለች እሷ ጋር በጣም ተግባባን ፊርዶስ ጃክሮስ ሰፈር አለፍ ብሎ ያለዉ ጎሮ የሚባለዉ ሰፈር ነዋሪ እንደሆነች ነገረችኝ፡፡
ፊርዶስ ኪታብም ታቀራናለች በጣም ጎበዝ ዲነል ኢስላም ላይ በጣም ጠንካራ ናት ፡፡

 ዲነል ኢስላም ከታዘዝንባቸዉ የዲን ወንድምህን በዘር በብሔር ሳትለይ ሙስሊም ስለሆነ  ዉደድ ሴትም ብትሆን እህትሽ ናት  ተዋደዱ ኢስላም አስተሳስሯችሇል ብሎናል፡፡
ከትምህርት ጓደኞቼ በላይ ፊርዶስን እንደእህቴ ቀረብኳት፡፡  እኔም እህት የለኝም ፊርዶስን እንደ እህቴ ነዉ የማያት ፊርዶስ ሶስት ትልቅ ወንድሞች አሏት ፡፡ ሁለቱ አግብተዋል አንዱ ወንድሟ ግን አላገባም ፡፡
 
     እዛዉ ኪታብ በመቅራት የተዋወቀነው ሲሀም የምትባል ልጅ አለች ሁሌ ኪታብ ቀርተን በተገናኘን  ቁጥር ሂክማ አንድ የኔ ዘመድ  የአንችን ስልክ ቁጥር  ስጭኝ እያለ እያስቸገረኝ ነዉ ፡፡ አብረን ኪታብ እንደምንቀራ አይቶናል .....ቁጥሯን ስጭኝ እኔ አላማየ ቀጥታ ወደ ትዳር ብቻ ነዉ እያለ እያስቸገረኝ ነዉ ሂክማ እኔ ይተዉሻል ብየ ዝም ብለዉ አኔን መቸካቸኩን አላቆመም ያለአንቺ ፍቃድ ደግሞ ቁጥርሽን መስጠት ከበደኝ..ስልክሽን ልስጠዉ አልስጠዉ ?? እስከ ጠዋት አስበሽ ንገሪኝ አለቸኝ፡፡

    ጠዋት ደረሰ ኪታብ የምቀራበት ሄድኩኝ ሲሀምን  አገኘሇት
......ምን አሰብሽ እሱ እንደሆነ በስልክ አላስቀምጠኝ አለ  ልስጠዉ እና  እናንተ አዉሩ አለችኝ
.......እሺ ትንሽ ቆይቼ አሳዉቅሻለሁ ሲሀም አልኳት    
   ፊርዶስ ኪታብ ስጨርስ ለብቻዋ አማከርኳት፡፡ ፊርዶስም አይታወቅም የአላህ ነገር ለኸይር ይሆናል የሀራም መንገድ ሳጀምሩ ስለማንነቱ አጣርተሽ በስልክ በTelegram ሳይረብሽ ቀጥታ ወደ ሀላሉ ሊገባ ከቻለ አላህ የፃፈልሽ እሱ ጋር ሊሆን ስለሚችል ለሲሀም ቁጥርሽን እንድሰጠዉ ፍቀጅላት  አለችኝ ፡፡
    ፊርዶስም ቀጠል አድርጋ  እኔም እኮ በጣም ዲነኛ የሆነ ልጅ በቤተሰብ የመጣ በጣም ጥሩ ስነምግባር ያለዉ ነዉ አይቸዉ ፈትኘዋለሁ ቤተሰቦቼ ጥሩ ባል መርጠዉልኛል እኔም የማመቻቸዉ ነገር ስላለ ነዉ እንጂ   ማግባቴ አይቀርም ...ግን አንቺ ቀድመሽኝ ካገባሽ በጣም ደስተኛ ነኝ ሂኩ አላህ ያሳካዉ ዱአ አትርሺኝ እኔም አረሳሽም አለችኝ እየተሳሳቅን፡፡

ወደ ሲሀም ሂጄ  እሺ ቁጥሬን ስጭዉ አልኳት፡፡
......እሷም ቁጥሬን ሰጠችዉ ...
   ልጁም ደወለልኝ በስነ ስርአት አወራኝ ....በአካል እንደሚያቀኝ ነገረኝ
.....እኔ ግነ አላቅህም አልኩት፡፡ ከአስር ቀን በላይ ሆነን ማዉራት ከጀመርን፡፡ የግድ መገናኘት ስላለብን ተቀጣጥረን ተገናኘን ተያየን ማሻ አላህ ቆንጆ ልጅ ነዉ ፡፡
  ስሙን ከተዋወቅን ቡሀላ እኔ አንቺን ለማጀዘብ ሳይሆን ለትዳር ነዉ የምፈልግሽ አለኝ ፡፡
     ከዛም  እያወራን አንድ ጥያቄ ለመጠየቅ ከብዙ ዝምታ ቡሀላ  የፈራሁት ጥያቄ መጣብኝ
>>>>>>>  ሂክማ ያዉ ለወደፊት የትዳር አጋሬ መርጬሻለሁ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ .አለኝ
....እሺ ጠይቀኝ አልኩት
...... ግን ቢክራ ነሽ አለኝ???
......ምን ብየ ልመልስ ዝም አልኩት,,,,ወንዶች ማግባት የምፈልጉት በቃ ድንግል የሆነች ነዉ??? አልኩት፡፡
......እሱም የሌላዉን አላቅም ግን እኔ በአላህ እምልልሻለሁ እስከ አሁን ተጠብቄ ከሴት ፍትንያ ነፍስያየን አሸንፌያለሁ፡፡  አላማየም ማግባት የምፈልገዉ እንደ እኔዉ የሆነችዉን ክብር ያላትን ነዉ አለኝ፡፡
.....እኔም እሺ  በስልክ አሳዉቅሀለሁ ብየ ተለያየን፡፡ከዛም ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ 

   እቤቴ መኝታ ክፍል ብቻየን ሁኜ.....ሀይደር የኔን ሂወት አበላሽቶብኛል ብቻየን የእንባ ዱብዳ ማጉረፍ ጀመርኩ ......ድንግል ነኝ ብየ ባገባዉ ድንግልናየን ሳያገኝብኝ ቢቀር መፋታቴ ቤተሰቦቼን ማስወቀሴ ነዉየ ......ወይም ሲሰድበኝ ሲያንቋሽሸኝ ወይም የእሱ ሞራሉ እንደተጎዳ ይኖራል፡፡የሴት ልጅ ህይወት ግድ እስከ ክብሯ መገኘቱ ወሳኝ እንደሆነ ተገነዘብኩኝ ፡...ገና ከመጀመሪያዉ የትዳር ፈተና ጀመረኝ፡፡  ስለሆነም ብቻየን መኝታ ክፍሌ አሰብኩኝ ባስበዉ ባስበዉ ምንም መፍትሄ ላገኝ አልቻልኩም  ያረቢ ብየ አለቀስኩ ፡፡ ግን ለእሱ አንድ ዉሸት ዋሸሁት አላህ ይቅር ይበለኝ ሲደዉልልኝ ምን ወሰንሽ???? ብሎ ጠየቀኝ
    እኔም............

#Part 1⃣2⃣

ይ................ቀ...........
.............ጥ............ላ............ል
join👇👇

https://www.tg-me.com/mahbubil

በYoutube ላይ አዲስ የተለቀቀ መንዙማ ግብዣ👇👇👇👇👇
Watch "salatu rabi //madih muhammed amin //#newmenzuma #ya_alemu_shum" on YouTube
https://youtu.be/DKsrhSbg7W0
👍6
ለማንኛውም ሆድ ይፍጀው😭

ታላቁን ዓሊም ጀግናውን መሪ ወቅት አገናዛቢ ምክሮችን በመምከር የሚታወቁትን የታላቁ ሱመያ መስጂድ ዋና ኢማምና ኸጢብ ዑስታዝ ሸይኽ ሰዒድ ሑሰይንን በርካታ ወንድም እህቶች ውዴታቸውን ፣ አድናቆታቸውንና ክብራቸውን ወደ አኺራ በተሸኙበት ወቅት ገልፀዋል🙏

#ሸይኽ #ሰዒድ #ሑሰይን ወንድማችን ሶፋ ኸድር ቤት በተዘጋጀ የዱዓእ እና የሶደቃ ዝግጅት ላይ #ለገነቴዋ ያሳዩት ከፍተኛ መተናነስ በርካቶችን አስለቅሷል😭

ሶደቃው ተበላ ፤ ዱዓውም ተዥጎደጎደ ። የዐሱር ሶላት ወቅት ደረሰ ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ገነቴዋም ዉዱዕ ለማድረግ ተነሱ

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ ሑሰይንም በእኛ ሀገር ትልቅ ሰው ፣ የተከበረ ሰው ዉዱዕ የሚያደርገው እዛው ተቀምጦ የነበረበት ቦታ ነው አሉ🙏

ለገነቴዋም የዉዱዕ ውሃ መጣላቸው ። ገነቴዋ ዉዱዕ ማድረግ ጀመሩና የተከበረው እግራቸው ዘንድ ደረሱ

ታዲያ በዚህን ወቅት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ ሑሰይን እግርዎትን እኔ ነኝ የማጥብሁ አሉ🙏

ገነቴዋም በፊቅሁም ስለማይፈቀድ በፍፁም ሊሆን አይችልም አሉ ። ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ ሑሰይንም በዚህ በዚህ መልኩ ይፈቀዳል ብለው በመረጃ ሞገቱ🙏

ገነቴዋም እንደማይለቋቸው ስላወቁ እየጠሉ እሽታቸውን ሳይወዱ ፈቀዱ😭

እኚህ ታላቅ ዓሊምም የገነቴዋን የተከበረ ቀኝ እግር አዳርሰው አጠቡና ጨረሱ🙏

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ ሑሰይንየተቀረውን የተከበረውን የገነቴዋን ግራ እግር ሊያጥቡ ሲዘጋጁ ገነቴዋ በፍፁም እርስዎ አያጥቡኝም ተፈለገ ሶላቱ ይቀራል በማለት ተቃወሙ

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድም የገነቴዋን ቁርጠኝነት ስለሚያውቁ ማጠቡን ተዉትና "#አሏህ #ሱብሃን #ወተዓላ #ምን #ሰራህ #ብሎ #ቢጠይቀኝ#የዑመርን #እግር #አጥቢያለሁ #እለዋለሁ" ቢሉ እዛ ዱዓእና ሶደቃ ላይ የነበረ ዑለማ ፣ ሙዕሚን ሁላ አለቀሰ🙏

አሁንም ወደ አኺራ ሊሄዱ ሰሞን ስለ ሙፍቲ ገነቴዋ ያሉት አለ ቀኑ ሲደርስ ይገለፃል😭

ዑለሞቻችን እርስ በእርስ ስለሚተዋወቁ ይከባበራሉ ፤ ይዋደዳሉ ፤ እርስ በእርስ ይተናነሳሉ🙏

የዓሊምን ደረጃ የሚያውቀው ዓሊም'ንጂ መች ጃሂልልል ሆነና

የጃሂልልልል አፉ እንደ ምኑ ነው አሉ😳
@mahbubil
🥰3👍1
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣2⃣



   ግን ለእሱ አንድ ዉሸት ዋሸሁት አላህ ይቅር ይበለኝ
ደዉሎ  ምን ወሰንሽ ???ብሎ ጠየቀኝ እኔም
......በዉሸት ወንድሜዋ ከአንተ ከተለያየን ቡሀላ  እናቴን ሚስጥር ስለማልደብቃት ማታ ሁሉንም ነገርኳት...እናቴም እኛ ያዘጋጀነዉ አባትሽ የመረጠልሽ ልጅ አለ አለችኝ ....ወንድም አላህ ከኔ የተሻለ ይስጥህ ከአሁን ቡሀላ መደዋወል እና በtelegram አናወራም ለምን ብትለኝ የወደፊት የትዳር አጋሬ መሆን ስለማንችል ከቤተሰቦቼ ትእዛዝ ዉጭ መፈፀም አልፈልግም አልኩት፡፡
...እሱም መርሀባ ብሎኝ  በዚሁ ተለያየን ክፉም ከአፌ ሳይወጣ እሱም ክፉ ሳይናገረኝ ወደድኩህ ወደድኩሽ የለአንቺ መኖር አልችልም ያለ አንተ መኖር አልችልም ሳንባባል በሀላል መንገድ ጀመርን፡፡ በሰላም ተለያየን አላህ ከእኔ የተሻለ የትዳር አጋር ይስጠዉ፡፡

     ምን ላርግ የጠየቀኝ ጥያቄ ላይ ድንግል አይደለሁም ብለዉ አላህ ወንጀሉን ነዉሩን የሸፈነ እኔ እሸፍንነታለሁ ብሏል እኔ ቶብቻለሁ በወንጀሌ ተፀፅቻለሁ ግን የእሱን ሂወት ዋሽቼ ገብቼ ማበላሸት አልፈለኩም፡፡ እኔ ሀይደር ሸወደኝና ማንኛዉንም ወንድ በክፉ አላይም፡፡ ለምን  አባቴ ወንድ ልጅ ነዉ፡፡ ወንዶች ገደል ይግቡ ካልኩ እኔን ለማሳደግ ለመንከባከብ ከቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ሁኖ የሚኖረዉ አባቴን ተሳደብኩ ማለት ነዉ ፡፡ ይህ ደግሞ የወላጆቼን ሀቅ አልተወጣሁም ማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም ጥሩ ወንዶች አሉ በተዘዋዋሪም ጥሩ ያልሆነ ወንዶች አሉ እነሱንም ከመሳደብ አላህ ልቦና ይስጣቸዉ ግን ይህ ጭካኔ በእህቱ በእናቱ ቢሆን የማይወደዉን በሌላ ሴት ልጅ መጨዋት ግን ያሳፍራል፡፡
      በየሳምንት ከጁምአ ሶላት ቡሀላ የደአዋ ዝግጅት አለ ሴቶች አሚራችን ፊርዶስ ደአዋ ታረግልናለች፡፡ እንደ አጋጣሚ እሷ አሟት ሳትመጣ ቀረች....
     ከዛም አንቺ አድርጊ እያሉ ሌሎች የጀመአ አባላችን ግፊት አርጉብኝ ...እኔም እሺ ብየ  ደአዋ አደረኩኝ፡፡
 የሚገርመኝ የመጀመሪያ ቢሆንም  በጣም የሚያምር ደአዋ አደረኩ የደአዋዉ ርዕስ በወንድ ተኩላዎች እንዳትሸወጅ ነበር፡፡ እኔም የተሰማኝን በደአዋዉ እያለቀስኩኝ ሀይደር የሰራኝ ስራ የሸወደኝ ትዝ እያለኝ እልክ በያዘኝ መልኩ ደአዋ አረኩላቸዉ ...የትምህርቱ ጠቃሚነት ብዙዎቹ አብረዉኝ ያለቅሱ ነበር፡፡ ደአዋዉን ሳረግ ለእህቶቼ ቢጠነቀቁ ብየ በኔ ሂወት የደረሰዉን ጠባሳ  በተለያዩ ዘዴዎች የደአዋ ሲስተም ነገርኳቸዉ  እንዲጠነቀቁ እና የtelegram group ጥቅም እና ጉዳቱን ዘርዝሬ ነገርኳቸዉ ከዛ ደአዋየን ጨርሼ ተቀመኩኝ፡፡

    ከዛ ቡሀላ ጁምአ ሶላት ቡሀላ አሚራችን ፊርዶስ አንቺ አድርጊ ባለፈዉ ሳልመጣ ቀርቼ ያደረግሽዉ ደአዋ በጣም እንደሚያምር ነግረዉኛል ....እንደዚህ የደአዋ ብቃት አለሽ ማለት ነዉ ማሻ አላህ ብያለሁ አለችኝ ፊርዶስ ፡፡
እኔም እኔ ደአዋ አላደርግ አንቺ ስለቀረሽ ነዉ ያረኩት  ብላት
.......እንዴ አላማችን አንቺ አንቺ ልንባባል ሳይሆን ያወቅነዉን ለማሳወቅ ነዉ ሂኩ ፡፡ እኔ ማረግ በምፈልግ ሰአት አረጋለሁ አንቺ አድርጊ አለችኝ...ፊርዶስ አበረታታችኝ ጁምአ ከሶላት ቡሀላ ተሰብስበን ደአዋ አድራጊዉ እኔ ሆንኩ ...

አላህ የሰራሁትን ወንጀል እንዲምረኝ በምሰግድ ሰአት ብቻየን ስሆን ረከአተይን ከሰገድኩ ቡሀላ አላህንም ማረኝ እያልኩ ባገኘሁት አጋጣሚ እያለቀስኩ ነዉ....
     
   እቤት ገብቼ ልተኛ አካባቢ ፊርዶስ አንድ ነገር አማክርሻለሁ ብላ ደወለችልኝ  ከአሱር ቡሀላ ልንገናኝ ተቀጣጠርን፡፡
ከአሱር ቡሀላ ከፊርዶስ ጋር ተገናኝተን አንድ  ያልጠበኩትን ነገር ነገረችኝ፡፡

   ሂክማ ባለፈዉ  የነገርሽኝ ነገር ሲሀም ለትዳር የሚፈልግሽ አለ ብላ እንደነገረችሽ እኔ ሳልነግርሽ አረፈድኩና ግን ዛሬ ልነግርሽ ወስኛለሁ፡፡ ወንድሜ አብረን ስንሄድ አይቶናል አንቺ ጓደኛየ እንደሆንሽ ያቃል ለትዳር እንደሚፈልገኝ ነገረችኝ ፡፡  ሂኩ ወንድሜ  ዲን አለዉ አላህን ፈሪ አንቺን ከጓደኝነት አልፎ ለወንድሜ ዙበይር ብታገቢዉ ደስ ይለኛል ሂኩ ማስተዳደሪያም አልሀምዱሊላህ አላህ እርዚቅ ሰጥቶታል  .... አንቺን እንዲያገባሽ እፈልጋለሁ አለችኝ፡፡ ባለፈዉ የሲሀም ዘመድ ይፈልገኛል ብለሽ ስታማክሪኝ ደነገጥኩ ወንድሜ ዙበይር እሷን ማግባት እፈልጋለሁ እያለ እኔም ወንድሜን እንድታገቢ እየተመኘሁ ያንን ወሬ ስሰማ ለዙበይር ነግሬዉ እንዴት እስከ አሁን ሳነግሪያት ብሎ ተቆጣኝ አለችኝ፡፡
.....እኔም ደነገጥኩኝ እስኪ ቆይ ልሰብበት አልኳት


ከዛም እቤቴ ሂጄ አሰብኩበት ለሚመጣዉ አመት ትምህርት የመማር እቅድ ነበረኝ..... እናቴም ብዙም ትምህርቴን እንድማር አትፈልግም...አባትሽ ተምሮ ለስራ የሚኖረዉ ደብረዘይት, ነዉ፡፡ የእኔን ፍቅር የልጁን ፍቅር ሳይሰጥ ይሄዉ እየኖረ ነዉ፡፡ መማር እንደዚህ ከሆነ ይቅር ትለኝ ነበር፡፡
መኝታ ክፍል ሁኜ ዙበይርስ  ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እያሰብኩ ነዉ፡፡

በጣም ተናደድኩ ሳላስበዉ ሸይጧን ወሰወሰኝ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁመኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ ፡፡ ብዙ ሀይደርን የምጎዳበት ነገሮች መኝታ ክፍሌ ሁኜ የቤታችንን ኮርኒስ  እያየሁ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ቀላል ዘዴ አገኘሁ ...እኛን የቸገረን ኸይር መስራቱ እንጂ ተንኮል መስራቱ መቼ ያቅተናል ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ እስከአሁን ትዝ ሳይለኝ ብየ ተቆጨሁ፡፡ ...የሀይደርን .....

#Part  1⃣3⃣
,,,,,,,,,,ይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,ቀ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ጥ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ላ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ል

ሼር የማታረጉ የቻናል ቤተሰቦቻችን ደህንነታችሁ ሀሳብ ሁኖብናል😉 ለጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ አለን በሉን☺️


https://www.tg-me.com/mahbubil
👍3
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🦋 #Part 1⃣3⃣


    በጣም ተናደድኩ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁ መኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ
    Face book ገብቼ  የሀይደርን የfb ጓደኞች እያየሁኝ ነዉ፡፡ ሚስቱን በprofile ስላየሆት የfb ጓደኛዉ እንደሆነች ብየ መፈለግ ጀመርኩኝ፡፡ ጓደኞችን ስመለከት ብዙዎቹ ጓደኞቼ ሴት ነበሩ ገረመኝ፡፡ Fb ላይ ከ3000 በላይ ጓደኞቼ ነበሩት በስንት ድካም ልፋት ቡሀላ አንድ ፎቶ አየሁ የእሱ እና የእሷ profie የሆነ፡፡ line ገብቼ ስመለከት የእሷ የብቻ ፎቶም አለ ፡፡ ሲጋቡ የተነሱ ፎቶዉ ላይ መብሩክ በሉኝ ብላ ፅፋለች፡፡

     ያሰብኩት ተሳካ አሁን frind አርጌ የእኔን ሂወት እንዳበላሸብኝ የእሱን ላበላሽበት ወሰንኩኝ፡፡ እኔ እያለቀስኩ እሱ ስቆ እንደማይኖር ወሰንኩኝ ...frind request ላኩላት ከአንድ ቀን ቡሀላ ተቀበለችኝ ...በጣም ደስ አለኝ ሀይደር የእኔ ሂወት አበላሽቶታል የእሱንም ሒወት አበላሸዋለሁ እያልኩ ብቻየን እየዛትኩ ነዉ፡፡

  face book ላይ online ቀን ቀን አትጠፋም  ፡፡ ነገሮችን ሁሉ ሳስበዉ እሱ ማታ ማታ በስልኩ ይጀናጀናል እሷም ቀን ላይ ታወራለች ብየ አሰብኩ በትዳር በመሀላቸዉ የሆነ ክፍተት እንዳለ ያስታዉቃል፡፡ እኔም  እያወረሇት ነዉ በሂደት  ተዋወቅን ግን ለክፉም ለደጉም ብየ ትክክለኛ ስሜን አልነገርኳትም ፡፡ ሚስቱ የአዲስ አበባ የመርካቶ ሰፈር ልጅ እንደሆነች ስሟም ኢክራም እንደምትባልና የባሏም ስም ሀይደር እንደሚባል እና የሁለት ልጆች እናት እንደሆነች ..... ቤተሰቦቿ ባለሀብት እንደሆኑ እና ..የባሏ ስም ሀይደር እንደሆነ  በጣም እንደምወደዉና ፡፡ በፊት ሹፌር ነበር ተዋወቅን ተዋደን ተጋባን ....ከዛም አባቴ ሀይደርን ከሹፍርና ስራ አቁም ብሎት አሁን  መርካቶ ሱቅ ከፈተልን ከዛም የቤት መኪናም ዶልፊን አባቴ ገዝቶ እንደሰጠዉ አጫወተችኝ፡፡

      ኢክራም በጣም ግልፅ ልጅ ናት ሁለ ነገሯ ተመቸችኝ ፡፡
አንቺስ ??ብላ ጠየቀችኝ
....እኔ ቂርአት እየቀራሁ እንደሆነ ነገርኳት፡፡ ስለ ሀይደር ምንም አላነሳሁ፡፡ ግን በጣም ገረመኝ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ ለማጥመድ በእጁ አድርጎ የሚፈልገዉን ለመዉሰድ የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም ዉሸታቸዉ ከባድ እንደሆነ ተረዳሁ ፡፡ ጥፋቱ የኔ ነዉ የነገረኝን ማመኔ ብቻ ወደ ጆሮየ የገባዉ ሁሉ እዉነት ይመስለኝ ነበር ፡፡ ሚስጥሩ እያደር ገባኝ ማታ ማታ ስደዉል አይመችም ስልክ ለማንሳት በtelegram እናወራለን የሚለኝ ሚስቱ ኢክራም  ሲያወራ እንዳትሰማዉ እንደሆነ ገባኝ፡፡
     ግን ለምን ?? አረ ለምን?? ኢክራም ፍቅር ያሸንፋል  ከሹፍርና ኑሮ ገላግላዉ በቤተሰቦቿ ጥረት ሱቅ ተከፍቶለት መኪና ተገዝቶለት.... እሷ ባለዉለታዉ ሁና በመኪናዉ ሴት ሲሸወድ እንደ እኔ ያለዉን የተዘነጋ በማዘናጋት እንደዚህ መሆኑ ለኢክራም አዘንኩ፡፡ ወይ ጎራ ሁን ወይ ጎራ ተጠጋ አይደል የሚባለዉ ሀይደር ጎራ ተጠግቶ ይሄዉ በኢክራም ጥረት እና በቤተሰቦቻ ሀብት ለሌላ ለሀራም አላማ እየተጠቀመበት በመሆኑ ያሳፍራል፡፡

ደግሞ ለኔ የዋሸኝ ዉሸት ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ፡፡ ምነዉ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ንገሪያት ንገሪያት የሚል መንፈስ ከጀርባየ አለ፡፡ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ፅፌዉ ልልከዉ ብየ ቆይ ለሁሉም ሰአት አለዉ አልኩና
  ባልሽን ትወጅዋለሽ ???ብየ ጠየኳት
....በጣም እንጂ ሀይደር ሁለ ነገሬ ነዉ በጣም እወደዋለሁ ያለ እሱ መኖር አልችልም በስራም ጎበዝ ነዉ ዉይ ሲወደኝ እኮ ብላ ታወራኝ ይዛለች በfb
......ግን ስለ እሱ መጥፎ ነገር ብሰሚ..ትጠይዋለሽ?? ወይስ አጠይዉም?? ብየ ጠየኳት

.....እሷም እንዴ ሀይደር መጥፎ ነገር የለዉም የሚሰራዉን የሆነዉን ሁሉን ይነግረኛል እኔን ሳያማክር ፈፅሞ አያቅም ፡፡ በህይወቴ እሱ ነዉ የመጀመሪያየ ወንድ በጣም ነዉ የምወደዉ፡፡ ምንም መጥፎ አይሰራም እተማመንበታለሁ አለችኝ፡፡

...እኔም አይ ግን ሰርቶ ብታገኝዉስ?? አልኳት
.......ጭራሽ አያረገዉም ጥያቄዉ መልስ የለዉም ሁሌም ቢሆን በሀይደር የምተማመንበት ጨዋ ልጅ ነዉ፡፡አላህ በስንት ዱአ መሰለሽ የሰጠኝ አለችኝ፡፡

በጣም ደስ የምትል ሚስት አለችዉ ግልፅ ናት እኔም ማንነቴን ደብቄ እናወራ ይዘናል ከመግባባት ብዛት ስልክ ቁጥሯን ተቀበልኳት፡፡  ስልክ ቁጥሯም0911....2372 ብላ በfb text አረገችልኝ ፡፡

 እቤቴ ሁኜ ማሰብ ጀመርኩኝ ሀይደር የእኔን ሂወት እንዳበላሸ ላበላሽበት??? ወይስ እኔን አላህ አለኝ ቶብቻለሁ  ለሚስቱ እና ለሁለት ልጆቹ ሒወት ብየ ልተወዉ?? እያልኩ ተወዛገብኩ፡፡ ያሳለፍኳቸዉ የደብረዘይት ጊዚያቶች እና አሁን ትዳር ሲመጣ የምጨነቃቸዉ ጭንቀቶች ፊቴ ላይ ድቅን ይላሉ፡፡
 ይህን ጉዳይ ለፊርዶስ አላማከርኳትም ...ፊርዶስ ብሰማ ምን ትለኝ ይሆን ?
ስልኬን አንስቼ ቀጥታ ለኢክራም ልደዉል ቁጥሯን አዉጥቼ የሀይደርን ጉድ ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ሀይደር እኔን እንደሸወደ ሚስቱን ሲሸዉድ አይኖርም ...ስልኬን አንስቼ ወደ ሀይደር ሚስት ኢክራም ልደዉል ስልክ ቁጥሯን አወጣሁ....ከዛም

#part 1⃣4⃣

ይ.........ቀ......
........ጥ.............ላ..............ል

https://www.tg-me.com/mahbubil
👍9
ሰላሙን ዐለይኩም

''የህይወት ለውጥ''

part 1

ወዳጆቼ ህይወት እንደምናስበው ከባድ ነው። ጥሩን ፍሬ የምናገኘው ጥሩ ነገር ላይ በለፋነው መጠን ነው ! ሸር ላይ ከለፋን ልክ እንደዛው የህይወታችን ብርሀን በሸር ይሞላል ! ግን ለምን ጥሩን ሰርቶ መደሰት😊እያለ ለመከፋት መቸኮል ! ሁሌም ቢሆን የሚያስፈልገንን ነገር እንወቅ ! ሀይላችንን አውቀን በሀይላችን ላይ እንጎብዝ ያኔ መለወጥ ይመጣል !እድገት ይገኛል ! 🥰

@mahbubil
👍4
ሰላሙን ዐለይኩም

''የህይወት ለውጥ ''

part ''2

መልካምነት ለራስ ነው 🤔 ምን ማለት ነው ? ወዳጆቼ ይህንን ቃል በማህበረሰባችን ዘንድ ስንከፋም ስንደሰትም የምንሰማው ቀላል የሚመስል ነገር የትልቅነትን ዙፋን የያዘ ንግግር ነው !

ሀጂ ሙሳ ራህመቱሏሂ ዐለይሂ እንዲህ ይላሉ !
''መልካምን ነገር ሰርተህ የሰራህለት አካል ባያመሰግንህ ባይደሰትብህም እንኳ መልካምነት ራሷ ትከፍልሀለች !🥰 ሸርን/መጥፎን ነገር ሰርተህ የሰራህበት አካል ባይቆጣህም ባይረግምይም መጥፎ ነገር ራሷ ዋጋ ታስከፍልሀለች''🥺

@mahbubil
#የህይወትለውጥ #የዓለሙሹምሙሀመድﷺ
🥰6
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 1⃣4⃣


     ስልኬን አዉጥቼ ለኢክራም ደዉየ ልነግራት ወስንኩ

ግን ጨነቀኝ የኔ ሂወት አንዴ ተበላሽቷል ግን የሶስት ሰዉ ሒወት ላበላሽ እንደሆነ ተሰማኝ፡፡  ሁለት ልጆቿ እና ኢክራም ..ደግሞ ወደ ፍች ከሄዱ ልጆቹ ካለቤተሰብ ፍቅር ተለያይተዉ ኢክራም ወደ ቤተሰቦቻ ትሄዳለች ሌላም ችግር ፈጠርኩ ማለት ነዉ ..ቤተሰቦች ፀብ ብዙ ነገር  ስልኬን ይዤ ማሰብ ጀመርኩኝ .... ግን ሀይደር የሰራኝ ስራ መልሶ አእምሮየ ጋር ብልጭ ይልብኛል፡፡

ግን ምን ይደረጋል የእኔነ በደል ብሸከም ይሻለኛል የሌላ ሰዉ ሒወት ከማበላሽ....ሁሉንም ነገር ለፈጣሪየ ለአላህ ሰጠሁኝ፡፡  ስልኬን አቅፌ እንደ ወራጅ ወንዝ ማልቀስ ሆነ ያረቢ እርዳኝ ያረቢ እርዳኝ እያልኩ
........የኢክራምን ስልክ ለወደፊት እንደዚህ አይነት ዉሳኔ እንዳልወስን ብየ ከContact ላይ አጠፋሁ፡ Facebook ላልጠቀም ከአሁን ቡሀላ የሀይደርን ሚስት ኢክራምን ላላወራ ብየ ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ በአላህ ተወከልኩ እስከአሁንም የሰራሁትን ስራ አላህ ይማረኝ..ሀይደርን ከነቤተሰቦቹ  ልጎዳዉ ነበር ይቅርብኝ አላህ እሱንም ያስተካክለዉ እኔንም አላህ የተሻለ ይስጠኝ ብየ ዱአየን አርጌ ለመጨረሻ ጊዜ ከሀይደር ለመበቀል ያሰብኩት ሀሳብ ሰረዝኩኝ፡፡
  
   Face book መጠቀም አቆምኩ ግን ሀይደር የሰራኝ ጉድ ለማን ሰዉ እንደምተነፍሰዉ አላቅም ብቻየን ማታ ተኛሁ ብየ  አዳሬን ብቻ ማልቀስ ሁኗል ስራየ ፡፡

   የማይነጋ የለም የወፊት ጫጫታ መንጋቱን አበሰረኝ......ወደ ቂርአት ሄድኩ ፊርዶስን አገኘሇት፡፡
 ዛሬ እናንተ ቤት ሂጄ  እናትሽን መተዋወቅ እፈልጋለሁ አለችኝ
..እኔም ከቂርአት መልስ እቤት ወስጃት ከእናቴ ጋር አስተዋወኳት፡፡ እናቴን ካስተዋወኳት ቡሀላ  ፊርዶስ በረፍት ሰአቷ እኛ ቤት እየመጣች ቤተሰብም ጓደኛም ሆነች አላህ የሰጠኝ የዲን እህቴ ፊርዶስ ነች.....

ፊርዶስ እሁድ እንደምትጋብዘኝ ነገረችኝ .......ሸገር ላይ በሚገኘዉ ታላቁ ወበሪ ሆቴል....ከአሱር ቡሀላ እንሄዳለን አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ ፊርዱ አልኳት፡፡

ቀናቶች በተቆጠሩ ቁጥር እሁድ ደረሰ ፊርዶስ አሱር ሶላት አካባቢ እኛ ቤት መጥታ ሰግደን አብረን ወደ ወበሪ ሆቴል ሔድን፡፡  እዛ ስደርስ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ ወንድም ዙበይር ቀድሞን መጥቶ  ቁጭ ብሎ እየጠበቀን ነዉ፡፡
  ዙበይርን በፊርዶስ ስልክ በፎቶ  አንዴ ስላየሁት እሱ እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ ፊርዶስ ግን ዙበይርም ነዉም አይደለምም አላለችኝም...እሷ ሶስት ወንድሞች ስላሏት ዙበይር  ላይሆን ይችላል ብየ ጠረጠርኩ፡፡ ትኩስ ነገር አዘን አንዳንድ ወሬ እያነሳን ተጨዋዉተን  ተጠቀምን ስንጨርስ እኔን ወደ ቤቴ ሸኝተዉኝ እነሱም ወደ ቤታችን ተመለሱ

ግን ማን ይሆን??? እያልኩ ሳስብ ሳስብ ....ዙበይር ይሆን እንዴ እያልኩ ብቻየን ባዶ ቤት ቁጭ ብየ እኔዉ  ስከራከር.... ዳኛ ከሌለዉ ክርክር ዉስጥ ስልኬ ጮኸ ስልኬም ከክርክሩ ገላገለኝ...ስልኬን ሳየዉ የደወለችዉ ፊርዶስ ነበረች
,,...አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ አለች
......እኔም ወአለይኩም ሰላም ፊርዱ ደህና ነሽ
.......አልሀምዱሊላህ በሰላም እቤት ገባሽ??? አለችኝ
.....እኔም አዎ ገብቻለሁ ፊርዱ
ብዙ ተራ ወሬዎች ካወራን ቡሀላ

....ሂኩየ ቅድም አብሮኝ የመጣዉ ማን እነንደሆነ አዉቀሽዋል ????አለችኝ
.....እኔም መቼም አንቺ ከአጂ ነብይ ጋር እንደማትሄጅ አቃለሁ፡፡ ከሶስት ወንድሞችሽ አንዱ ይሆናል ፊርዱ አልኳት፡፡
.....አዎ አልተሳሳትሽም ዙበይር ነዉ ፡፡ በአካል አገናኚኝ እያለ ረበሸኝ ምን ላድርግ ፡፡ ፊርዱ አንቺ  ለኔ እኮ አይቴ(የወንድሜ ሚስት ለማለት ነዉ) ዙበይርም ወንድሜ ነዉ ፡፡ ዙበይር ናፈቀችኝ ናፈቀችኝ ሲለኝ ነዉ እስከዛሬ በሩቅ ነበር የሚያይሽ ዛሬ ፊት ለፊት እንዲያይሽ ያረኩት አለችኝ ፊርዱ
.....እሷ ባለችኝ ነገር ደርቄ ቀረሁ የምመልሰዉ አጣሁ መልሴ ዝም ሆነ ...

....ፊርዶስም ሄሎ ሄሎ ሄሎ ሂክማ ምነዉ ዝም አልሽ ...አረ በአላህ አጥፍቼ ከሆነ ይቅርታ እንደዚህ ይከፋሻል አላልኩም ሂክማ ..አረ አናግሪኝ አስጨነቅሽኝ .....ሂክማ አረ ሂክማ እያለች እሰማታለሁ ስልኩን አልዘጋሁትም ነበር፡፡

እኔ ምንም የምመልሰዉ መልስ የለም ብቻ እንባየ ቁልቁል ሲወርድ ይታወሰኛል

ፊርዱም ሄሎ ሄሎዉ ማለቷን አላቆመችም በድንጋጤ ..እኔም ስልኩን ዘጋሁት መልሳ ፊርዶ ደወለች እኔም አላነሳሁኝ.....ፊርዶስ በመደወል ትደጋግም ይዛለች.....እኔም በtext ነገ የማወራሽ ነገር አለ ብየ በmessgae ልኬ..ስልኬን አጠፋሁት፡፡ ለፊርዶስ ምን ልበላት እንደባለፈዉ በቤተሰብ የመጣ አለ ብየ ልዋሻት እንዴ  ??? ወይስ እዉነቱን ልንገራት እያልኩ ሁለት ልብ ሆንኩ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በመጨረሻም አንድ ዉሳኔ ወሰንኩ ነገ....ፊርዶስን ሳገኛት.........

ለፊርዶስ በሆዷ ያፈነችዉን ሚስጥር ለሂክማ ትነግራት ይሆን ??? ለሂክማ ነገረች ማለት ዙበይር ሊርቃት ይችላል እናንተ ምን ትላላችሁ ??
በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን፡፡

#Part 1⃣5⃣

ይ.............,......ቀ......
............,ጥ..........,ላ........ል

JOIN👇👇👇

 https://www.tg-me.com/mahbubil
👏4👍3
👆👆👆👆
ታሪኩ ተለቀቀ
👍4
2025/07/08 20:13:29
Back to Top
HTML Embed Code: